Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Photo
የሐጅ ምዝገባ ማስታወቂያ
​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንኳን ለ2019 ዓ.ል. (1448 ዓ.ሒ) የሐጅ ጉዞ በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

​የሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ባካሄደው የአገልግሎት አፈጻጸም ውድድር ጠቅላይ ምክር ቤታችን ባለፈው ዓመት በሰጠው የላቀ አገልግሎት የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል።

​ዘንድሮም የትራንስፖርት፣ የምግብ፣ የማረፊያ ቦታ እና ሌሎች አገልግሎቶቹን ፈጣን፣ ተደራሽና ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ ከጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

የምዝገባ ማዕከላትንም በቴክኖሎጂና በሰለጠኑ ባለሙያዎች በማደራጀት ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል።

​በመሆኑም ለምዝገባ አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችንና ቅድመ ሁኔታዎችን የምታሟሉ አማኞች ከታች በተዘረዘሩት የምዝገባ ማዕከላት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

​ልብ ይበሉ!!!
የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ከታላቁ የረመዳን ወር በፊት ጥር 10 ቀን 2019 ዓ.ም (ሻዕባን 10 ቀን 1448 ዓ.ሒ) ይጠናቀቃል።

​ስለሆነም የሐጅ አዳ እቅድ (ኒያ) ያላችሁ ለሁሉም አገልግሎቶች የተወሰነውን ብር 827,000 (ስምንት መቶ ሀያ ሰባት ሺህ ብር) በክፈል በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ማዕከላት እንድትመዘገቡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የምዝገባ ማዕከላት፡
1. ​በአዲስ አበባ
2. ​በፊንፊኔ
3. ​ሮቤ
4. ​በጊኒር
5. ​በጅማ
6. ​በሀረር
7. ​በነገሌ
8. ​በአዳማ
9. ​በጊምቢ
10. ​በጭሮ
11. ​በፉሪ
12. ​በቡሌ ሆራ
13. ​በሞያሌ
14. ​በሻሸመኔ
15. ​በመቱ
16. ወራቤ
17. ​በሀረር
18. ​በሰመራ
19. ​በደሴ
20. በባህር ዳር
21. በከሚሴ
22. ​በጎንደር
23. ​በጋምቤላ
24. በአሶሳ
25. ​በመቐለ
26. ​በቴፒ
27. ​በሶዶ
28. ​በሐዋሳ
29. ​በጅግ ጅጋ
30. ​በጎዴይ
31. ​በሞያሌ
32. ​በዶሎ አዶ
33. ​በድሬደዋ

​ለበለጠ መረጃ፡
• ​በነጻ የስልክ መስመር፡ 9933
• ​የጠቅላይ ምክር ቤቱ ይፋዊ የትስስር ገጾች
​"የህይወት ዘመን ምኞትዎን እውን ለማድረግ በመመዝገብ ሰበብ ያድርሱ!"
​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
ንያ ያላቸው አማኞች ከወዲሁ በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የሁጃጅ ምዝገባ ማዕከላት በመሄድ እንዲመዘገቡ ዑለማእ ጉባኤው አቀረበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 19/2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
​አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ 2019 ዓ.ል/1448 ዓ.ሒ.የሐጅ ጉዞ ምዝገባን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማእ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሀምዛ የሳውዲ አረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሀጅ ምዝገባው ጥር 10/ 2019 ዓ.ል (ሻዕባን 10/1448 ዓ.ሒ) እንደሚጠናቀቅ አስታውሰው ንያ ያላቸው አማኞች ከወዲሁ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሸይኽ ጁነይድ አክለውም ባለፈው ዓመት በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ሐጅ ለማድረግ ኒያ የነበራቸው ቢሆንም የሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የምዝገባ ቀነ ገደብ መሠረት የሐጅ ምዝገባ ሲስተም (ኑሱክ) በመዝጋቱ ምክንያት ሐጅ ማድረግ አለመቻሉም ብለዋል።

የዑለማእ ጉባዔ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ ዓሊ ሙሀመድ በበኩላቸው ከቀናት በፊት የተጀመረው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተፈቀደለት ኮታ ቀድሞ ከሞላ ምዝገባው ከተያዘለት ቀን ቀድሞ ይጠናቀቃል ብለዋል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል በንባብ ያቀረቡት የዑለማእ ጉባዔው ፀሐፊ ሸይኽ ሙሀመድዘይን ዘኽረዲን ጉባዔው ከነገ ጁምዓ ጀምሮ በሚደረጉ ኹጥባዎችና የዒልም መድረኮች ስለ ሀጅ ኢባዳ እና ስለ ምዝገባው ትምህርትና መረጃ እንዲሰጡ ለዑለማ ጉባዔዎች፣ ለኢማሞችና ለዱዓቶች ጥሪ ቀርቧል።

ሐጅ ለማድረግ ንያና አቅም ያላቸው ሙስሊሞች በተቀመጠው የምዝገባ ሰሌዳ በመመዝገብ የሐጅ አፈጻጸም ትምህርቶችን ከወዲሁ መማር እንደሚገባቸውም ጉባዔው በመግለጫው አሳስቧል።

ሐጅ ታላቅና የተቀደሰ ኢባዳ መሆኑ በመግለጫ የተገለፀ ሲሆን ኢስላማዊ የሚዲያ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የአረህማን እንግዶች የሀጅ ኢባዳቸው ጨርስው ወደ ሀገር ቤት እስኪመለሱ ድረስ በየዕለቱ ተከታታይ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ኢስላማዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም ጉባኤው የአደራ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በመግለጫው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የዑለማእ ጉባኤው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ መሻይሆች እና ዱዓቶች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1