የታላቁ ንጉስ ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በ1ዓመት ከመንፈቅ አንደሚጠናቀቅ የሀገር በቀል ባለሀብቶች ተወካይ ኢንጂነር ዘሀራ አብዱልሀዲ ገለጹ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 22/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አዲስ አበባ |
የነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች አማካኝነት እንዲገነባ በተወሰነው ስምምነት መሠረት ዛሬ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት የክቡር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላለፉት መልዕክት የታላቁ ንጉስ ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ መዘግየት የሁሉም ጥያቄ መሆኑን አንስተው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከ3 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የቁፋሮ የአፈር መንሸራረት መከላከያ (ሾሪንግ) ስራ መስራቱን አስረድተዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ግንባታውን ለሀገር አልሚ ባለሀብቶች ክፍት ባደረገ አጭር ጊዜ ውስጥ ባለሀብቶቹ ግንባታውን እውን ለማድረግ ፈቃደኛ በመሆን ታልቅ ኃላፊነት መውሰድ መቻላቸውንም የጠቀሱት ፕሬዝደነትቱ ግንባታውን በተያዘለት ቀነ ገደብ በማጠናቀቅ ለምረቃት እንዲበቃ ተቋማዊ ኃላፊነት እንደሚወጡን ገልጸዋል።
በግንባታ የማረጀመር መረሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት ሸይኽ ሙሐመድ ሑሴን አል ዓሙዲን የፕሮጀክት ተወካይ ኢንጂነር ዘሀራ አብዱልሀዲ አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልገጠሙ በስተቀር ግንባታውን በ1 ዓመት ከ6 ወር ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ተገንብቶ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ እንደሚያስረክቡ አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጧን አማን የታላቁ ንጉስ ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ለከተማዋ ከፍተኛ እሴት እንደሚሆን ገልጸው በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች መገንባቱ ደግሞ ፋይዳውንም የላቀ ያደርገዋል ብለዋል።
በግንባታ ማስጀመሪያ መረሃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ግንባታውን የሚያከናውኑት ድርጅቶች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት