የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ«ቢላል ሱፐር አፕ» እና የ«ኢ.አር.ፒ ሲስተም» በወቅፍ ተረከበ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 23/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 22/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ«ቢላል ሱፐር አፕ» እና የ«ኢ.አር.ፒ (ERP) ሲስተም» ባለቤትነት መብትን ከአዲስ አበባ አድቫንስድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድርጅት በወቅፉ (ስጦታ) ተረከበ።
ወቅፉን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂ ከአዲስ አበባ አድቫንስድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድርጅት ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሃጂ መሐመድ አደን (አብዲወሌ) ተረክበዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለቴክኖሎጂ ውጤቱ ምንም አይነት ክፍያ ሳይፈጽም ሙሉ ህጋዊ ባለቤትነት የተረከበ ሲሆን አዲስ አበባ አድቫንስድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ባለሙያዎች ነፃ የስልጠና ድጋፍ እንደሚያደርግም ተብራርቷል።
በወቅፍ የተበረከቱት የቴክኖሎጂ ውጤቶች የጠቅላይ ምክር ቤቱንና የክልል መጅሊሶችን አሰራር በማዘመን ህዝበ ሙስሊሙ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ ይሆናል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ውጤት በወቅፍ ላበረከተው ድርጅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዑስታዝ ተምኪን አያይዘው የቴክኖሊጂው ትልቁ አላማ ተቋሙን አሁን ካለንበት የዲጂታል ዘመን ጋር በማዋሃድ ተቋማዊ ልህቀትን ማጎልበት እንደሆነም ገልጸዋል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ፣ የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ጠቅላይ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔውን በነገው ዕለት (27/022019) ማካሄድ ይጀምራል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 26/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 25/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከጥቅምት 27 እስከ 28/2019 በአዲስ አበባ ያካሄዳል።
በጉባኤው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ እና የክቡር አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ይታደማሉ።
ጉባዔው ጠቅላይ ምክር ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት፣ የታዩ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የሚገመግም ሲሆን የ2019 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ እና የበጀት አጠቃቀም ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ሃሳቦችንና የትግበራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።
መደበኛ ጉባዔው ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተጣለበትን ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ኃላፊነት በተሻለ ብቃት በመወጣት የሕዝበ ሙስሊሙን ውክልናና ጥቅም ለማስከበር የሚደረገውን ጉዞ የሚያቀላጥፍ የጋራ መግባባት ላይ ይደርሳልም ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱና ኢብን በጡጣ ፋውንዴሽን በልማትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 26/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 25/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና ኢብን በጡጣ ፋውንዴሽን በማኅበረሰብ ልማት፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ ማበልጸግና በቤተሰብ ግንባታ ዙሪያ በትብብር መሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ እንዲሁም በኢብን በጡጣ ፋውንዴሽን በኩል ደግሞ የፋውንዴሽኑ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢብራሂም ሙነወር ሐሰን የመግባቢያ ስምምነቱን ፈርመዋል።
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት የህዝበ ሙስሊሙን ኑሮ ለማሻሻልና ዘላቂ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የሚያከናውኗቸውን የማትና የማኅበራዊ ዘርፍ ስራዎች ለማጠናከር እንደሚያግዝ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ ተናግረዋል።
ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ የማኅበራዊ ችግሮች የመፍትሔ አካል ለመሆን በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ይህን መሠል የጋር ስምምነቶች የላቀ ጠቀሚታ አለው ብለዋል።
የኢብን በጡጣ ፋውንዴሽን መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢብራሂም ሙነወር በበኩላቸው ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር የተደረገው ስምምነት የፋውንዴሽኑን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ኢብኑ በጡጣ በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራ አገር በቀል የተራድኦ ድርጅት ነው።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••