በጎዴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ::
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 28/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

ጎዴ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ እና በአል ቡኒያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ትብብር በጎዴ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የኢስላም ልሂቃን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ ዓሊ ሙሐመድ ዔባ የሥልጠናውን መጠናቀቅ ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ሰልጣኞች ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ህዝባቸውን በሙሉ አቅማቸው እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ለስድስት ቀናት በተሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከጎዴ ከተማና ከሸበሌ ዞን የተውጣጡ 100 ኢማሞችና ኡስታዞች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማዕ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሀምዛ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
በማጠናቀቂያ መርሀ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዳዕዋ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ አብዱልሽኩር ሸይኽ አብደላ፣ የጎዴ ከተማ እስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ ሸይኽ ኢስማኢል ሙዓሊም እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢው አመራሮች የተገኙ ሲሆን ስልጠናው በሌሎች አካባቢዎች እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት በከፊልና ሙሉ በሙሉ የእይታ ችግር ላጋጠማቸው 1200 ዜጎች ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም/01/2019 ዓ.ል| ረቢዑል አወል 30/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የአል በስር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች ልዑክ ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ኢትዮጵያ ገባ።
ዓለም አቀፉ የጤና ባለሙያዎች ልዑክ ምሽት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ ዶክተር ኢብራሂም አህመድ አቀባበል አድርገውለታል።
በኢትዮጵያ ለአንድ ወር ያህል ቆይታ የሚያደርገው ዓለም አቀፉ የጤና ባለሙያዎች ቡድን በቆይታው 1200 ለሚሆኑ የአይን ሞራ ግርዶች ህሙማን ነጻ የቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አገልግሎቱን መስከረም 4/2019 በአወልያ ጤና ጣቢያ መስጠት ይጀምራል።
በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት በከፊልና ሙሉ በሙሉ የእይታ ችግር ላጋጠማቸው ወገኖች በአወልያ ጤና ጣቢያ መሰጠት የሚጀምረው ነጻ የህክምና አገልግሎት በቀጣይ ቀናትም በጂግጅጋ እና በወራቤ አካባቢዎች የሚቀጥል ይሆናል።