Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.76K photos
76 videos
20 files
999 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ምርመራ እና ህክምና በአወልያ ጤና ጣቢያ ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 4/2019 ዓ.ል| ረቢዕ አል ሳኒ 03/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የሆነው አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ከአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በሳዑዲ ንጉሥ ሰልማን የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የአይን ሞራ ግርዶሽ ነጻ የሕክምና አገልግሎት በአወልያ መሥጠት ጀመረ።

በአወልያ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው የነጻ ህክምና ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጠቅላይ ምክር ቤት የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኸ ሐሚድ ሙሣ የአይን ህክምና አገልግሎት በነጻ እየሰጠ ለሚገኘው የሳዑዲ ዓረብያ የንጉሥ ሰልማን የሰብዓዊ እርዳታ ድረጅት አልበሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን አመስግነዋል።

አወሊያ እርዳታና ልማትድርጅት ከአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለሚሰራው የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ስራ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥም ምክትል ፕሬዝደንቱ አረጋግጠዋል።

የአልበሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጀኔራል ሴክሬታሪ የሆኑት ዶክተር አዲል አብዱልአዚዝ አል ረሹድ ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ ከ26 ዓመታት በላይ የሰበአዊ እና የጤና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ መር ሃ ግብርም በሺዎች ለሚቆጠሩ የአይን ህሙማን የምርመራና የህክምና እንዲሁም ነጻ የመድኃኒትና የመነጽር አቅርቦት ይካሄዳል ብለዋል።

የእንኳን ደህና መጣቹህ መልዕክት ያስተላለፉት የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አሰኪያጅ ሀጂ ሰዒድ እስማረ በበኩላቸው አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት በቀጣይም መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራትን በማጠናከር የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ለማቃለል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በነመርሃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የአል በሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ቦርድ አባልና የፕሮግራም ዳይሬክተር ኢንጂነር ናስር ሙሐመድ አልሱወይዳን፣ የአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በአወልያ ጤና ጣቢያ ለ4 ቀናት የሚቆየው ነጻ የዓይን የህክምና አገልግሎት በጂግጅጋ እና በወራቤ አካባቢዎች አንደሚቀጥል ተገልጿል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eias
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኢማሞችና ዑስታዞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 4 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 3/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ቦንጋ |

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኢማሞችና ዑስታዞች ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና በቦንጋ ከተማ ተጀመረ።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ እና በቡኒያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀው ሲሆን በስልጠናው ላይ ከክልሉ ስድስት ዞኖች የተውጣጡ 100 ኢማሞች፣ ዱዓቶች እና ዑስታዞች ይሳተፋሉ።

​ስልጠናውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሸይኽ አሊ መሐመድ ዔባ በንግግር ያስጀመሩት ሲሆን በንግግራቸውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር እየሰጠ ያለው የኢማሞች፣ የዱዓቶችና የዑስታዞችን የአቅም ግንባታ ስልጠና ውጤታማ እንደቀጠለ ጠቅሰዋል።

የሰልጠኞችን አቅም በማጎልበት ህዝቡ የተሻለ አገልግሎት ከማድረግ አንጻር ስልጠናው ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ሸይኽ አሊ ሙሃመድ አክለው ገልጸዋል።

​የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ያሲን አወል አብዱ በበኩላቸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚያዘጋጃቸው ሥልጠናዎች የዑስታዞችንና የኢማሞችን አቅም ከመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።

​በስልጠና ማስጀመሪያ መድረኩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የክልሉ መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለ1448 ዓ.ሒ የሐጅ ተጓዦች የጤና ምርመራ እና የሕክምና ሰርተፊኬት አገልግሎት የሚሰጡ ብቁ የጤና ተቋማትን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከስር ባሉት ሰነዶች ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሆስፒታሎች ወይም ስፔሻሊስት ክሊኒኮች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

ህጋዊ ተጫራቾች ዛሬን ሳይጨምር በሚቆጠር ሶስት የስራ ቀናት ማሰረጃና እና ሰነዶቻችሁን በ PDF ፎርማት በማዘጋጀት በሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኢ.ሜይል ethiohajj@gmail.com
በመላክ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

መስከረም 07/2019 ዓ.ል
የ1448/2019 የሐጅ ጉዞ ስራዎችን ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ጥራት ያለው ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተገለፀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 8 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 7/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጅግ ጅጋ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የ2018/1447/ የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶ አፈጻጸምን ለመገምገም እና የቀጣይ ስራዎች ላይ ለመምከር የሚያስችል ግምገማዊ ስልጠና በነገው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሸይኽ ኢስሀቅ አደም እንደገለጹት በስልጠናው የጅግጂጋ፣ የጎዴ፣ የድሬዳዋ፣ የሐረር፣ የሐረሪ እና የጭሮ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ሀላፊዎ ፣ የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።

የ2019 የሐጅ ጉዞ አገልግሎቶችን ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ጥራት ያለው ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮች እንደሚዘረጉ የገለጹት ሸይኽ ኢስሀቅ አደም በስልጠናዊ ግምገማው በባለፈው ዓመት የታዩ ጥንካሬ እና ድክመቶችን በጥልቀት በመገምገም የ2019 የሀጅ አገልግሎትና መስተንግዶን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ጠቁመዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1