Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.68K photos
76 videos
20 files
997 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሀጅ አገልግሎት እና መስተንግዶ ግምገማ ማካሄድ ጀመረ::
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 9 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 8/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጅግጂጋ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የ1447/2018 የሐጅ መስተንግዶ አፈጻጸምን ለመገምገም እና በቀጣይ የ1448/2019 በጀት ዓመት የሥራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ያለመ ግምገማ በጂግጂጋ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።

በግምገማው ላይ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እና የምዝገባ ጣቢያ ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን መድረኩን የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ አህመድ መሀመድ መልዕክት በማስተላለፉ አስጀምረውታል።

ሸይኽ አህመድ መሀመድ በመልዕክታቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ በ1447/2018 የሀጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ያስመዘገበው ውጤት የጠቅላይ ምክር ቤቱንና የሀገርን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ በመልካም ያስጠራ መሆኑን አስታውሰዋል።

​ውጤቱ የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ጋር በቅንጅት በመስራት የመጣ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ የ2019 የሐጅ ምዝገባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በላቀ የኃላፊነት ስሜት እንዲሰሩም የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

​የጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሸይኽ ኢስሀቅ አደም በበኩላቸው የ2019 የሐጅ ጉዞ ምዝገባ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር ገልጸው ግምገማዊ ስልጠናው ከምዝገባ ቅድመ ዝግጅቶ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በሁሉም የምዝገባ ማዕከላት ለአገልግሎት ፈላጊዎች የተቀናጀና ጥራት ያለው አገልግሎት በመሰጠት እርካታ ለመፍጠር የምዝገባ ጣቢያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሸይኽ ኢስሀቅ አስረድተዋል።

ባለፈው ዓመት የታዪ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና በቀጣይም የነበሩ ክፍተቶች እንዲታረሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ የስልጠናው ተሳታዎች የገለጹ ሲሆን በዛሬው ዕለት በጂግጂጋ ከተማ የተጀመረው ግምገማዊ ስልጠና በሌሎች ከተሞች እንደሚካሄድም ተመላክቷል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1