Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ሕዝበ ሙስሊሙ በእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሠሰበት ቢላል ኢስላማዊ ፋውንዴሽን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 14 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ሕዝበ ሙስሊሙ በእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደመውን
ቢላል ኢስላሚክ ፋውንዴሽን ቁጥር 2 የኡለሞች እና የዱዓቶች ማፍሪያ ኮሌጅ ዳግም ለመገንባት እንዲረባረብና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ጥሪ አቀረበ።

በቢላል ኢስላሚክ ፋውንዴሽን የተቋቋመው የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤተ የስብሰባ አዳራሽ በእሳት አደጋው ምክንያት ስለወደመው ቢላል ቁጥር 2 የዑለማዎች እና የዱዓቶች ማፍሪያ ማዕከል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሸይኽ መሀመድዘይን ዘህረዲን በዚሁ ዕለት እንደገለጹት በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ የሚገኘው ታዋቂው ኢስላማዊ የትምህርት ማዕከል መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ል በደረሰበት ከፍተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አስታውሰዋል።

​የኮሚቴ ፀሐፊ ዑስታዝ ሰዒድ ዓሊ በንባብ ባቀረቡት መግለጫ በእሳት አደጋው ምክንያት በርካታ ቁርአን፣ የኪታቦች ስብስቦች እና ታሪካዊ ቅርሶች ሙሉ ለሙሉ መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ከአካባቢው መጅሊስ የስራ ኅላፊዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከመንግስት የተውጣጣ ኮሚቴ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን የገለጸው መግለጫው በርካታ የኢስላም ሊቃውንትን እና ዱዓቶችን ማፍራት የቻለው የዕውቀት ማዕከሉ ዳግም ተገንብቶ ወደ ቀድሞ ስራው እንዲመለስ ህዝበ ሙስሊሙ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግም በመግለጫው ጥሪ ቀርቧል።

ህዝበ ሙስሊሙ ድጋፍ ማድረግ እንዲያመቸውም በኮሚቴው እውቅና በተለያዩ ባንኮች አዳዲስ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ተከፍተው እርዳታ ማሰባሰብ ስለመጀመሩ ተመላክቷል። የቢላል ቁርጥ 2 የኡለሞች እና የዱዓቶች ማፍሪያ ኮሌጅ መልሶ ማቋቋሚያ ሀብት ማሰባሰቢያ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000798973731
ዳሽን ባንክ፡ 2906011241111
አዋሽ ባንክ፡ 014381541058500
​አቢሲኒያ ባንክ፡ 268676872
ዘምዘም ባንክ፡ 0099178310301
ሂጅራ ባንክ፡ 1006506710003
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
አራተኛው አህጉር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ማጣሪያ በኦንላይን መካሄድ ጀመረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 15/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 14/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
​
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ከሞሮኮው ንጉሥ ሙሐመድ 6ኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው 4ኛው አህጉር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ማጣሪያ በኦን ላይን ተጀመረ።

ኢትዮጵያን ወክለው እየተወዳደሩ የሚገኙት ቃሩእዎች ሚያዚያ 2018 ዓ.ል በአዲስ አበባ በተደረገው ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ አሸናፊ የነበሩ ሲሆኑ በሶስት የአቀራር ዘርፎች ከ48 ሀገራት ተወካዮች ጋር ይወዳደራሉ።

በ30 ጁዝ ሂፍዝ በሃፍስ ርዋያ ውድድር ራቢያ ኢስማኢል ሀሰን፣ በ30 ጁዝ በዋርሽ ርዋያ ሂፍዝ አቀራር ሙሀመድ አሚን አብደላ እንዲሁም በአምስት ጁዝ ቁርኣንን አሳምሮ በመቅራት (ቲላዋ) ነጃሺ በሺር አባ ሙካ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።

​የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማእ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኅላፊ እንዲሁም የስልጠናና የውድድር ተጠሪ ዶክተር ማህሙድ ሁሴን አብደላ እንደገለጹት ውድድሩ የቁርኣንን ታላቅነት ከፍ ከማድረጉም በላይ የዑለማዎችን ድርሻ ለማጎልበት እና የወጣቶችን አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

በዑለማእ ጉባዔ የፈትዋ አባልና የትምህርትና ካሪኩለም ዘርፍ ኅላፊ እንዲሁም የውድድሩ አስተባባሪ ዶክተር አብደላ ኸደር በበኩላቸው ውድድሩ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ ውድድር የዳኝነት ሥራው በዓለም አቀፍ ዳኞች ይከናወናል ብለዋል።

በዚህ የማጣሪያ ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በሞሮኮ በሚዘጋጀው የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ሽልማት የሚቀበሉ ይሆናል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1