Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.66K photos
76 videos
20 files
995 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የ1447/2018 የሐጅ አፈጻጸም ግምገማ እና የ1448/2019 የሐጅ መስተንግዶ ስልጠናዊ ግምገማ ተጀመረ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 17/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 16/1448 ዓ.ሒ

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
​
ሶስተኛው ዙር የ1447/2018 የሐጅ አፈፃፀም ግምገማ እና የ1448/2019 የሐጅ መስተንግዶ ለክልል ሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎችና የምዝገባ ጣቢያ ሙያተኞች የተዘጋጀ ስልጠናዊ ግምገማ መካሄድ ጀመረ።

በስልጠናዊ ግምገማው የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ዑስታዝ ፈይሰል ዑመር ፤ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከተጣለበት የሰላምና የልማት ስራዎች ጎን ለጎን የሐጅና ዑምራ ጉዞን በበላይነት በማስተዳደር ለሕዝበ ሙስሊሙ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም በ1447/2018 የሐጅ ወቅት በሳውዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር በተዘጋጀው የ"ለበይቱም አዋርድ" ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን የሕዝባችንንና የሀገራችንን ስም በበጎ ማስጠራት መቻሉን አውስተዋል።

ወርቃማ ውጤቱ ከምዝገባ ማስተባበሪያ ጣቢያ ሰራተኞች ጀምሮ የዑለሞች፣ የክልል መጅሊሶችና የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን በመጠቆም፣ በዘንድሮው ዓመትም ይህንን ስኬት ለማስጠበቅ በትጋት እንዲሰራ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

​የተቋማትና ማህበራት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ሐጅ ሽኩር ቃሲም በበኩላቸው፤ ሁጃጆችን ማገልገል፣ መንከባከብና ማስተናገድ እጅግ ከፍተኛ ምንዳ (አጅር) የሚያስገኝ ታላቅ የዒባዳ ዘርፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።
​የጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሼይኽ ኢስሀቅ አደም በበኩላቸው ፤ አገልግሎቱን በሰው ኃይልና በግብአት በማዘመናችን ለአል ራህማን እንግዶች የሚሰጠው አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል ተችሏል ብለዋል።
በ1447/2018 የሐጅ መስተንግዶ ወቅት የታዩ ውስንነቶችን በማረም በዘንድሮው ዓመት የተሻለ አገልግሎት ለሁጃጁ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ መደረጉን ኅላፊው ገልጸዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የለበይቱም እውቅናና ሽልማት ለ2019/1448 ዓ.ሂ. የሐጅ አገልግሎት ቅድመ ዝግጅት መሠረት ሆኖ ቀጥሏል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 18/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 17/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ በ2018 ዓ.ል /1447 ዓ.ሂ. ባስመዘገበው የላቀ የአፈጻጸም ብቃት ያገኘው የ«ለበይቱም» ሽልማት ለ2019/1448 ዓ.ሂ. የሐጅ አገልግሎት ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል የሚያግዝ የእውቅና መርሐ ግብር በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተካሄደ።

​በመርሐ ግብሩ ላይ በሳዑዲ ዓረቢያና ኦማን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ኸድር፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሷሊህ፣ የኤምባሲውና የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ አባላት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች ተገኝተዋል።

​አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ኸድር እና ዶክተር መሀመድ ሷሊህ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የ«ለበይቱም» ሽልማት የጽሕፈት ቤቱ ብቻ ሳይሆን የተባባሪ ተቋማትና የመላው ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

ሽልማቱ የስኬት መደምደሚያ ሳይሆን በቀጣይ ስራዎች ለሑጃጆች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያነሳሳ ምርጥ ተሞክሮ መሆኑንም አክለዋል።

​የ1448 ዓ.ሂ. የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ዝግጅትን ውጤታማ ለማድረግ ከቀድሞ ልምዶች በመማር በቅድመ ዝግጅት፣ በተቋማት ቅንጅት፣ በዲጂታል ሥርዓቶችና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በምዝገባ ማዕከላት አቅም ግንባታ እና ከአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በሚደረግ ትብብር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራም በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል።

መርሐ ግብሩ የባለፈውን ዓመት ጥንካሬዎች በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመፍታት ለ1448 ዓ.ሂ. የሐጅ ተጓዦዥ የተቀናጀና የላቀ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል የጋራ አቋም በመያዝ ተጠናቋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1