Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.66K photos
76 videos
20 files
995 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 100 ኢማሞች እና ኡስታዞች የተሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 19/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

​ወላይታ ሶዶ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ከቡንያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 50 ኢማሞች እና 50 ኡስታዞች ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስተባባሪነት በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው በዚህ የስልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ የመጅሊስ ኃላፊዎች፣ ዑለሞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የስልጠናና የውድድር ተጠሪ ዶክተር ማህሙድ ሁሴን አብደላ እንደተናገሩት፣ ሰልጣኞቹ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ማህበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በቀጣይም ስልጠናው ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ጥናትን መሠረት ያደረጉ ተመሳሳይ የአቅም ማጎልበቻ ፕሮግራሞች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

​ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጅ ያሲን ከድር በበኩላቸው ስልጠናውን የሰጡ ተባባሪ አካላትን አመሥግነው በቀጣይም በሚደረጉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ላይ የክልሉ መጅሊስ ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ዑለሞች ፣ የመጅሊስ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ ስልጠናው ለኡስታዞችና ለኢማሞች የነበራቸውን እውቀት ለማሳደግና የማህበረሰብ አገልግሎታቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተመልክቷል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1