በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 100 ኢማሞች እና ኡስታዞች የተሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 19/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ወላይታ ሶዶ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ከቡንያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 50 ኢማሞች እና 50 ኡስታዞች ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስተባባሪነት በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው በዚህ የስልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ የመጅሊስ ኃላፊዎች፣ ዑለሞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የስልጠናና የውድድር ተጠሪ ዶክተር ማህሙድ ሁሴን አብደላ እንደተናገሩት፣ ሰልጣኞቹ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ማህበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በቀጣይም ስልጠናው ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ጥናትን መሠረት ያደረጉ ተመሳሳይ የአቅም ማጎልበቻ ፕሮግራሞች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጅ ያሲን ከድር በበኩላቸው ስልጠናውን የሰጡ ተባባሪ አካላትን አመሥግነው በቀጣይም በሚደረጉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ላይ የክልሉ መጅሊስ ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ዑለሞች ፣ የመጅሊስ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ ስልጠናው ለኡስታዞችና ለኢማሞች የነበራቸውን እውቀት ለማሳደግና የማህበረሰብ አገልግሎታቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተመልክቷል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ ምክክር አውደ ጥናት በአዳማ ተጀምሯል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 19/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዳማ |
አውደ ጥናቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የፌደራል፣ የክልልና የከተማ የዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የጤና ሚኒስቴር እና የኮራህ (CORHA) የሥራ ኅላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኸድር ባደረጉት ንግግር ፣ ፈትዋ በኢስላም ህግ እና አስተምህሮ ውስጥ ከፍተኛ እና አስፈላጊ ቦታ ያለው ሃይማኖታዊ ውሳኔ ወይም ብያኔ የሚሠጥበት ሂደት መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ ለተከሰቱ ወይም ግልጽ ያልሆኑ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ግላዊ ጉዳዮች ከቁርኣን እና ከሐዲሥ በመነሳት የሚሰጠው ህጋዊ ማብራሪያ ወይም ውሳኔ በቀጣይ አለማዊ ህግ ሆነው ሊያገልገል እንደሚችሉም ተናግረዋል።
በዚህ አወደ ጥናትላይ የሚቀርቡ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች በዑለሞቹ ታይተው ፈተዋ ( ሃይማኖታዊ) ብያኔ እንደሚሰጥባቸውም ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ የሕዝብ ፈንድ (UNFPA) ተወካይ ሚስተር ቶ ታይዎ ኦሉዮሚ፣ በበኩላቸው የምክክር መድረኩ ከዑለሞቹ ጋር የበለጠ መግባባትን በመፍጠር፣ እምነትን በማጠናክር፣ የቤተሰቦችና የማህበረሰቦች ደህንነትና የአናቶችና የህጻናት ጤና ላይ የሚሰጠውን ሃይማኖታዊ ብያኔ መሠረት በማድረግ መመሪያን ለማዘጋጀት እድል ይፈጥራል ብለዋል።
የኮራህ ተወካይ ወ/ሮ ቤተልሄም በዛብህ በኢስላም አስተምህሮ መሠረት በዑለሞች የሚሠጠውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን ብያኔ መሠረት አድርገው በቀጣይ በትብብር ለመሥራት ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ዛሬ በአዳማ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ፈትዋ ለማዘጋጀት ግብኣት ለማሰባሰብ እንዲቻል ምክክር አውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።