Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የአል-ባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የህክምና ሉዑክ የምስጋናና የሽኝት መርሃ-ግብር ተካሄደ

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 20/2019 ዓ.ል| ረቢዕ አል ሳኒ 19/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ l

​የአል-ባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ ከሆነው ከአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሲሰጥ ለነበረው የህክምና ቡድን የእውቅና፣ የምስጋና እና የሽኝት መርሃ-ግብር አካሄደ።

​በሽኝት መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ እና የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ተጠሪ ዶክተር ኢብራሂም አህመድ፤ ለአል-ባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን፣ ለኪንግ ሳልማን የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት፣ ለህክምና ቡድኑ አባላት፣ ለበጎ ፈቃደኞች እና ለስራው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አጋሮች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ዶክተር ኢብራሂም አያይዘውም፦ "ያከናወናችሁት ተግባር ለሰው ልጅ ደህንነት በሚደረገው አለም አቀፋዊ ጥረት ውስጥ የምህረትና የልግስና ማሳያ ከመሆኑ ባሻገር፣ ሰብአዊ አገልግሎትን የሚያበረታታና የሚያነሳሳ ነው" ብለዋል።

​የአወሊያ ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልአዚዝ ጀማል በበኩላቸው፤ የህክምና ቡድኑ በአዲስ አበባ፣ በጂጂጋ እና በወራቤ ከተሞች ባካሄደው የህክምና ዘመቻ የብርሃን ማጣት ችግር የነበረባቸውን 6,702 ዜጎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በዘመቻውም ነፃ የምርመራ፣ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና፣ የመነፅር እና የመድኃኒት ድጋፍ አገልግሎቶች መሰጠታቸውን በሪፖርታቸው አብራርተዋል።

​የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጂ ሰዒድ እስማረ፤ የአል-ባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የህክምና ልዑካን የተጣለባቸውን ሃላፊነት በውጤታማነት በማጠናቀቃቸው አመስግነዋል። ለአገልግሎቱ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የህክምና ቡድኑ አባላትም የክብር የምስክር ወረቀትና ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል።

​የአል-ባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ሜዲካል ዳይሬክተር እና የልዑኩ መሪ ፈክሩዲን ደካን ላደረገላቸው አቀባበልና ትብብር ምስጋና አቅርበው፤ ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን መሰል ነፃ የህክምና አገልግሎትና የአይን ጤና ሽፋን የማስፋፋት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

​በዚሁ የምስጋናና የሽኝት መርሃ-ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚዎች፣ የአወሊያ አመራሮች፣ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ለ1448/2019 ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦች አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ድርጅቶች ተለዩ ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 20/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 19/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

​ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለ1448/2019 የሐጅ ወቅት በሳዑዲ ዓረቢያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦች አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዎችን ለይቷል።

​የሐጅ ወቅት ቅድመ ዝግጅት አካል የሆነው ይህ ጨረታ፣ ጠቅላይ ምክር ቤቱ መስከረም 7/2019 ዓ.ል (ረቢዑል ሳኒ 6/1448 ዓ.ሒ) በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው የግልጽ ጨረታ ጥሪ መሠረት የተከናወነ ነው።

በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅ ና ዑምራ ዘርፍ ኅላፊ ዶክተር ሙሐመድ ሷሊህ እንደገለጹት፣ በጥሪው መሠረት በዘርፉ የተሰማሩ በርካታ የሳዑዲ ዓረቢያ ኩባንያዎች በጨረታው ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።

​የውድድሩ ሂደት ግልጽነትና ፍትሃዊነትን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የጠቆሙት ዶክተር ሙሐመድ ሷሊህ፣ የአሸናፊ ድርጅቶች መለየት ለምዕመናን ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ጥራት ያለው የመስተንግዶ፣ የትራንስፖርት፣ የኬቴሪንግና የማረፊያ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አመላክተዋል ።
​ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዘንድሮውን የሐጅ ጉዞ ዝግጅት በጊዜ በመጀመር በሳዑዲ ዓረቢያ ለኢትዮጵያውያን ሑጃጆች የሚሰጠውን አገልግሎት ደረጃ ለማሻሻልና ያጋጥሙ የነበሩ እክሎችን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ኅላፊው ተናግረዋል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ለ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቀቀ ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 21/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 20/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አዳማ |

ለ ሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ የምክክር አውደ ጥናት ተጠናቋል።

አውደ ጥናቱ ፈትዋ ለማዘጋጀት የሚረዱ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችና ተሞክሮዎች ለፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀርቧል።

በአውደ ጥናቱ የብሔራዊ የቤተሰብ እቅድ፣ እናቶችና ህፃናት ጤና አፈፃፀም እና ዋና ዋና ማስረጃዎች (እ .አ. 2024/25 የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብ እና ጤና ዳሰሳ /EDHS/ በአቶ ሙባረክ ሐሚድ ከጤና ሚኒስቴር ፣በቤተሰብ ዕቅድ እና በእናትና ሕፃናት ጤና ላይ ያለው ክልላዊ እይታ አቶ አብዲራህማን ፡ ከሱማሌ ክልል ጤና ቢሮ በቀረቡት ሰነዶች ላይ ከወቅታዊነትኒ ከግልፀኝነት አኳያ በሊቃውንቱ የተለያዩ የማብራሪያ ጥያቄዎች ቀርበውበታል።

ሌላው የቤተሰብ ምጣኔ (FP) ፈትዋ ለማዘጋጀት በሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ላይ የተደረገ ውይይት፡ ዋና ዋና ግኝቶች፣ ችግሮች እና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች በ አቶ አድነው ሁሴን፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና (RH) አማካሪ ፣በአቶ ሱልጣን አህመድ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ አቅራቢነት ከሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች ጋር በቤተሰብ ዕቅድ፣ በእናትና ሕፃናት ጤና፣ በጾታዊ ጥቃትና መቀንጨርን በመከላከል ዙሪያ የኢንዶኔዢያ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ስልታዊ እቅድ ሰነድ ሊቃውንቱ በሰፊው ውይይት አድርገውበታል።

ፈተዋ መስጠት የነብያችን ሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) ሃይማኖታዊ መመሪያን የማድረስ ሚናን የሚተካና ከፍተኛ ኃላፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ፤ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህና የኡሱል አል-ፊቅህ እውቀት ባላቸው ሙፍቲዎች ፈትዋ ለመስጠት እንዲቻል የአዲስ አበባ ፣ የሶማሌና የአፋር የፈተዋ ቋሚ ሰብሳቢዎች በአውደ ጥናቱ ላይ በተለያየ ምክንያት ባለመገኘታቸው ምክንያት የጥናቱ ሰነድ ቅጂ ተልኮላቸው በቀጣይ ብያኔያቸው ለፌደራል ፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ እንዲልኩ ፤ የፌደራሉም የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ም የቀረቡ ሰነዶቹን መርምሮ በቀጣይ ፈተዋ ለመስጠት ወስኗል።

በአውደ ጥናቱ ላይ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጥናትና ምርምር ዘርፍ በዶክተር ኢብራሂም ሀሰን አቅራቢነት የቀረበው ሰነድ ፣ የሸሪዓ ዓላማዎችን፣ የጋብቻና የልጆችን ደረጃ፣ እንዲሁም የቤተሰብ ምጣኔና ወሊድን መቆጣጠርን በሸሪዓ እይታ ቀርቦ በፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ በሆኑት በዶክተር ሙሀመድ ሀሚዲን አወያይነት በሊቃውንቱ የማዳበሪያ ሃሳብ ተሰጥቶበት ሰነዱ በኮሚቴው ፀድቋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc