የፌዴራል የክልልናከተማ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 24/ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 23/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማ ጉባኤ በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምሯል።
በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ ባደረጉት ንግግር፣ የሕዝበ ሙስሊሙ የመልካም አስተዳደር የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው አዲሱ የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1428/2018 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።
አዲሱ አዋጅ ላለፉት 25 ዓመታት አገልግሎት ላይ የቆየውን አዋጅ ቁጥር 188/1992 ሙሉ በሙሉ የሚተካ መሆኑንም አብራርተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም ዳኝነት (ቃዷእ) በኢስላም ውስጥ ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን፣ የሰዎችን መብት ለማስከበር እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው በመሆኑ፣ ሰልጣኞች ለትምህርቱ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ አገልግሎታቸው ላይ ሊተግብሩት እንደሚገባም የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ መከተ ሙሄ በበኩላቸው፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁ የሆነ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል።
በዚሁ መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የተቋሙን አደረጃጀት የሚያጠናክሩና የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ የአሰራር ስርዓቶችን ከመዘርጋት ጎን ለጎን፣ የባለሙያዎችን ብቃት የሚያሳድጉ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በቀጣይነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
ለተከታታይ 10 ቀናት በሚቆየው በዚህ የስልጠና መርሃ ግብር ላይ የፌዴራል እና የክልል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች (ቃዲዎች) በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ለ1448 ዓ.ሂ. ሐጅ ከሳዑዲው መሻሪቅ አልማሲያ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 24/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 23/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ለ2019 (1448 ዓ.ሂ) ኢትዮጵያዊ ሑጃጆች ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ከሳዑዲ ዓረቢያው ግዙፍ የአገልግሎት አቅራቢ ተቋም መሻሪቅ አልማሲያ ሸሪካ ጋር ተፈራረመ።
በመካ ከተማ የተከናወነውን የውል ስምምነት የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሷሊህ ጀማል እና የመሻሪቅ አልማሲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በንደር ቢን አብዱረህማን አልደመንሁሪ ሰነዱን ተፈራርመዋል።
የውል ስምምነቱ በ2019 (1448 ዓ.ሂ) የሐጅ ጉዞ ለሚሳተፉ 8,000 ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ደህንነታቸው የተረጋገጠ እና ተጠያቂነት የሰፈነባቸው ለማድረግ ያለመ ነው።
ሁለቱ ወገኖች በሐጅ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የሁጃጆችን ምቾት፣ ደህንነትና እርካታ እንዲረጋገጥ ለማስቻል በትኩረት እንደሚሰሩ የተመላከተ ሲሆን የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሃመድ ሷሊህ የ2019 (1448 ዓ.ሂ) የሐጅ ዝግጅት በዘመናዊ አሰራር ተደራጅቶ በአግባቡ እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ከመሻሪቅ አልማሲያ ጋር የተደረሰው ስምምነት የቅድመ ዝግጅት ስራው አካል መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ሀጅና ዑምራ ዘርፉ በቀጣይም ከሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የሁጃጆችን የትራንስፖርት አገልግሎት ምቾትና ደህንነት የሚያረጋግጥ የውል ስምምነት ተፈረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 26/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 25/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከሳዑዲ ዓረቢያው የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ሰማያ የትራንስፖርት ኩባንያ ጋር የትራንስፖርት አገልግሎት ውል ስምምነት ተፈራረመ።
የውል ስምምነቱ ለ2019 (1448) ሁጃጆች ደህንነቱ የተረጋገጠ፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ እና በሰማያ የትራንስፖርት ኩባንያ መካከል የተፈረመው የውል ስምምነት በጥብቅ መስፈርቶችና የአሠራር መርሆዎች መሰረት ተፈጻሚ እንደሚደረግም ተመላክቷል።
የሁጃጆች የጉዞ መርሃ ግብር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ብቻ እንዲከናወን የሚያስችለው ይህ የውል ስምምነት በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች በቅንጅትና በፍጥነት ለመፍታት ትልቅ አቅም ከመፍጠሩ ባሻገር የትራንስፖርት አገልግሎቱ የሁጃጆችን አጠቃላይ የጉዞ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የሚያካትትም ይሆናል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ የ2019 (1448 ዓ.ሂ.) የሐጅ አገልግሎት ቅድመ ዝግጅቱን በተቀናጀ መንገድ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከሰማያ የትራንስፖርት ኩባንያ ጋር የተደረገው ስምምነትም የዚሁ አካል እንደሆነ የጽህፈት ቤቱ የስራ ኃላፊዎች በውልል ስምምነቱ ወቅት አብራርተዋል።
ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ለኢትዮጵያዊ ሁጃጆች የተሟላና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ7 ኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ የሰጠውን ውሳኔ ተከተሎ በትላንትናው ዕለት የኢፌዴሪ መንግስት በመመስረቱ የተሰማውን ደስታ ይገልፃል።
ለተከበሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ለክልል እና ለከተማ አስተዳድር ፕሬዝደንቶችና ከንቲባዎች በሙሉ ከህዝብ የተጣለባችሁን አደራ እና ኃላፊነት በአግባቡ እንድትወጡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲያግዛችሁ እንማጸነዋለን።
የመረጣችሁ ህዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋቸውን ሰላም፣ ልማት እና እድገት ለማምጣት በምታደርጉት ጥረት ሁሉ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ለመግለጽ እንወዳለን።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሀገራችን ወንድማማችነት፣ የህግ የበላይነት እና እኩልነት እንዲሰፍን ከመንግስት እና ከህዝባችን ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ እየገለጽን ዘመናትን ያስቆጠረው የሀገራችንን የመቻቻል፣ የመከባበር እና የአብሮነት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህዝበ ሙስሊሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ አዎንታዊ ሚናውን እንዲወጣ አደራ እንላለን።
በመጨረሻም አዲሱ መንግስት የተጣለበትን ሀገራዊ አደራ እና የህዝብ ፍላጎት በትክክል ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እንዲሰራ እየጠየቅን ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን እንመኛለን።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
26/01/209