በኢትዮጵያና በሞሮኮ የእስልምና ተቋማት መካከል ያለውን ሃይማኖታዊና ተቋማዊ ግንኙነት ያጠናክራል የተባለለት ሀገር አቀፍ የሐዲስ ውድድር ተጀመረ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 28/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 27/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲሰ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ እና በሞሮኮው ንጉሥ ሙሐመድ 6ኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን ትብብር የተዘጋጀው 3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሐዲስ ውድድር ተጀመረ።
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን ለዳኞች፣ ለተወዳዳሪዎች እና ለክብር እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሸይኽ አብዱልከሪም በዚህ መልዕክታቸው በዛሬው ዕለት የተጀመረው የሀዲስ ውድድር በኢትዮጵያና በሞሮኮ የእስልምና ተቋማት መካከል ያለውን ሃይማኖታዊና ተቋማዊ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንቱ አክለውም የንጉሥ ሙሐመድ 6ኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን በየዓመቱ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጃቸው ሃይማኖታዊ ውድድሮች እና ሥልጠናዎች በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የጸና ትብብር የሚያሳዩ መሆናቸውን ጠቁመው ለተወዳዳሪዎች መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል።
የኢትዮጵያ ዑለማ ጉባዔ ምክትል ኃላፊ እና የውድድሩ ዳኛ ሸይኽ መሐመድ ሀሰን በበኩላቸው ውድድሩ የነቢዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ለመከተል፣ የሐዲስ እውቀትን ለማስፋትና አስተምህሯቸውን ለወጣቶች ለማሳወቅ ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው ገልጸዋል።
ውድድሩ ወጣቶች በኢስላማዊ እውቀት እንዲታነጹ ከማድረግ ባለፈ በዑለማዎች መካከል ያለውን ትስስር እንደሚያጠናክርም ሸይኽ መሐመድ ሀሰን አክለዋል።
የሞሮኮ ንጉሥ ሙሐመድ 6ኛ የአፍሪካ ዑለማዎች ፋውንዴሽን የቡድን መሪና የፋይናንስ ኃላፊ ዶክተር ዑስማን ሰቀሊ ሁሰኒ የውድድሩን ዓላማና አስፈላጊነት ያብራሩ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ ዩሱፍ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን፣ የዑለማ ጉባዔ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት