በሦስት ዘርፍ የተካሄደው ሀገር አቀፍ ነቢያዊ የሐዲስ ውድድር ተጠናቀቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 28፣ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 27 1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ እና በሞሮኮ ንጉሥ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ትብብር የተዘጋጀው 3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የነቢያዊ ሐዲስ የማጣሪያ ውድድር አሸናፊዎች ተለዩ።
በሶስት ደረጃ ተከፍሎ በተደረገው ውድድር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባልና የመስጂድ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የውድድሩ የደኝነት ኮሜቴ አባል ሸይህ እንድሪስ ዓሊ ውድድሩን ያዘጋጁትንና ያስተባበሩትን አካላት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የስልጠናና የውድድር ዘርፍ ተጠሪ እና የውድድሩ ዳኛ ዶክተር ሸይኽ መሐመድ ከማል በበኩላቸው ዑለማ ጉባኤው ከሞሮኮ ንጉሥ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ጋር ያለውን ግንኙነት ከውድድር እና ከአቅም ግንባታ ስልጠና ባሻገር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
የማጣሪያ ውድድሩ አሸናፊዎች በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባኤ የትምህርት ካሪኩለም ዘርፍ ኃላፊና የውድድሩ ዋና አስተባባሪ ዶክተር አብደላ ኸድር ይፋ የተደረገ ሲሆን በሦስቱም የውድድር ዘርፎች አንደኛ የወጡት ሦስት አሸናፊዎች በሞሮኮ በሚካሄደውና 48 ሀገራት በሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉም ገልጸዋል።
የማጣሪያ ውድድሩ አሸናፊዎች፡-
40 ሐዲስ በመሀፈዝ
1ኛ፡ አብዱልጀሊል አሊ ( ከአፋር)
2ኛ፡ አብዱራህማን ናስር (ከኦሮሚያ)
3ኛ፡ አብድልበር ድሉ (ከአዲስ አበባ)
30 ሐዲስ ከነማብራሪያው በመሀፈዝ
1ኛ፡ መሐመድ ኸደር (ከአዲስ አበባ)
2ኛ፡ ቃሲም ሸምሰዲን (ከአዲስ አበባ)
3ኛ፡ ሙስጠፋ መሐመድ (ከኦሮሚያ)
30 ሐዲስ በከነ ህግጋቱ መሀፈዝ
(ሙስጠላሐል ሐዲስ)
1ኛ፡ አይመን ጀማል (ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ)
2ኛ፡ ኢብራሂምዓሊ (ከአፋር)
3ኛ፡ ኢብራሂም መሐመድ (ከአዲስ አበባ)
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት