በክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ይፋዊ የስራ ልዑክ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ጎበኘ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 21/2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 20/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ልዑክ በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በተከናወኑ የለውጥ፣ የአገልግሎት ማሻሻያ እና የልማት ስራዎችን ጎበኘ።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሱልጧን አማን ኤባ እና የስራ ኅላፊዎች ከፍተኛ ምክር ቤቱ የተከናወናቸውን የአደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ እና ጅምር የልማት ስራዎችን አስመልከተው ለልዑኩ ገለጻ አድርገዋል።
የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ መጅሊስ ተቋማዊ አሰራርን በማዘመን ማህበረሰቡን ለማገልገል እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ መጅሊስ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉት የለውጥ እና የልማት ስራዎች ለሌሎች የክልል እና የከተማ አስተዳደር መጅሊሶች አርአያ ሊሆን የሚችል እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ መጅሊስ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሱልጧን አማን ኤባ
በበኩላቸው ልዑኩ ላደረገው ጉብኝትና ወንድማዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ከፍተኛ መወክር ቤቱ የጀመራቸውን የለውጥና የልማት ስራዎች በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአዲስ አበባ መጅሊስ አሰራሩን በማዘመን ለሕዝበ ሙስሊሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማቀላጠፍ የዘረጋቸው አሰራሮች በልዑኩ የተጎበኙ ሲሆን መጅሊሱ ሁለንታዊ አቅሙን ለማጠናከር የያዛቸውን ዕቅዶች በተመለከተ ለልዑኩ ገለፃ ተደርጓል።
በይፋዊ የስራ ጉብኝቱ ላይ የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ፣ የልማትና ማሕበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና ሌሎች የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ዑለማዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት