Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.54K photos
76 videos
20 files
991 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ«ቢላል ሱፐር አፕ» እና የ«ኢ.አር.ፒ ሲስተም» በወቅፍ ተረከበ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 23/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 22/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
​አዲስ አበባ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ«ቢላል ሱፐር አፕ» እና የ«ኢ.አር.ፒ (ERP) ሲስተም» ባለቤትነት መብትን ከአዲስ አበባ አድቫንስድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድርጅት በወቅፉ (ስጦታ) ተረከበ።

​ወቅፉን የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂ ከአዲስ አበባ አድቫንስድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድርጅት ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሃጂ መሐመድ አደን (አብዲወሌ) ተረክበዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለቴክኖሎጂ ውጤቱ ምንም አይነት ክፍያ ሳይፈጽም ሙሉ ህጋዊ ባለቤትነት የተረከበ ሲሆን አዲስ አበባ አድቫንስድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ባለሙያዎች ነፃ የስልጠና ድጋፍ እንደሚያደርግም ተብራርቷል።

በወቅፍ የተበረከቱት የቴክኖሎጂ ውጤቶች የጠቅላይ ምክር ቤቱንና የክልል መጅሊሶችን አሰራር በማዘመን ህዝበ ሙስሊሙ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ ይሆናል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ውጤት በወቅፍ ላበረከተው ድርጅት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዑስታዝ ተምኪን አያይዘው የቴክኖሊጂው ትልቁ አላማ ተቋሙን አሁን ካለንበት የዲጂታል ዘመን ጋር በማዋሃድ ተቋማዊ ልህቀትን ማጎልበት እንደሆነም ገልጸዋል።

​በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሣ፣ የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ጠቅላይ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔውን በነገው ዕለት (27/022019) ማካሄድ ይጀምራል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥቅምት 26/ 2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 25/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
​አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከጥቅምት 27 እስከ 28/2019 በአዲስ አበባ ያካሄዳል።

በጉባኤው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ እና የክቡር አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ይታደማሉ።

​ጉባዔው ጠቅላይ ምክር ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት፣ የታዩ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የሚገመግም ሲሆን የ2019 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ እና የበጀት አጠቃቀም ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ሃሳቦችንና የትግበራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።

መደበኛ ጉባዔው ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተጣለበትን ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ኃላፊነት በተሻለ ብቃት በመወጣት የሕዝበ ሙስሊሙን ውክልናና ጥቅም ለማስከበር የሚደረገውን ጉዞ የሚያቀላጥፍ የጋራ መግባባት ላይ ይደርሳልም ተብሎ ይጠበቃል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1