Civil Engineering
1.36K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
674 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
#አዲስ_ምዝገባ፣#አጭር_ምዝገባ እንዲሁም #የዕድሳት አገልግሎት ለማግኘት ወደቢሮው የምዝገባ ፍቃድና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የሚመጡ ተገልጋዮች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመሁኔታዎች፡፡
Why is curing important?
Civil Engineering
Why is curing important?
Curing helps in the following ways:
- reduces the loss of water
-required for cement hydration process, thus will help in gaining the required strength for the concrete
-improves durability of concrete by reducing permeability and porosity
- improves microstructure of concrete
What is Joggle system ?

This is called a joggle in technical term.
The bent is provided to overlap the column reinforcement and to keep in alignment in its dimension (column size )….. if we don’t bend the reinforcement at overlapping then the size of the column will increase when we go up.

So the point is TO MINIMIZE LOAD IN THE TOP AND TO REDUCE THE SIZE OF COLUMN ON THE WAY
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

▶️TODAY GREAT TIP @engineer03
:
👉ዛሬ ደሞ አንድ First year engineering ተማሪዎች የተመረጡ የ engineering mechanics እና የengineering profession lecture notes ፖስት አረገናል
፡
🅾አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
👉ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/
--------- --------------- ----
▶️በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
.
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-
-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡
-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
-በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡
*በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡
*በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
*አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡
▶️በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡
.
http://t.me/engineer03
👉በኮንስትራክሽን ውል አማራጭ የሙግት መፍቻ
@engineer03
====================
መግቢያ
----------------
▶️የኮንስትራክሽን ውሎች በባህሪያቸው ብዙ እና ውስብስብ ቴክኒካል ዶክመንቶችን የውሉ አካል አድርገው የሚያካትቱ ናቸው፡፡ከነዚህም ውስጥ ጀኔራል ኮንዲሽኖች፣ስፔሻል ኮንዲሽን፣ቢል ኦፍ ኳንቲቲ፣ስፔስፊኬሽን፣ዲዛይኖች፣የውል ማስከበሪያ፣የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሰነድ ጨምሮ ሌሎችንም የውል አካል ተደርገው የሚካተቱ ዶክመንቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ በአንድ የኮንስትራክሽን ውል ውስጥ ይሄን ያህል ልዩ ልዩ አይነት ሰነድ መኖሩ በይዘት እርስ በእርሱ የሚጋጭበትን እና በይዘቱ አለመግባባትን የመፍጠር እድሉ ስለሚኖር የውሉ አካል በሚሆኑት መካከል ግጭት የመፈጠሩ አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡
*በኮንስትራክሽን ውሎች ተሳታፊ የሚሆኑ አካላት ብዙ መሆናቸውም ግጭት የመፈጠር እድሉን ሰፊ ያደርገዋል፡፡ይሄውም በኮንስትራክሽን ውል አፈጻጸም ዙሪያ አሰሪ፣ተቋራጭ፣ንኡስ ተቋራጭ፣ዲዛይነር፣አማካሪ መሀንዲስ፣እቃ አቅራቢ፣የዋስትና ሰጭ ባንክና ኢንሹራንስ ተሳታፊዎች መሆናቸው ከተለያየ አቅጣጫ ግጭትና አለመግባባት ሊፈጠር የሚችልበትን አጋጣሚና ሁኔታ ሰፊ ያደርገዋል፡፡
*የኮንስትራክሽን ውል ጋር የተየያዙ ግጭቶች ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ቴክኒካዊ ውስብስብነት የሚኖራቸውና የህግ ሙያ ብቻ ባለው ሰው በቀላሉ እልባት ሊያገኙ የሚችሉ አይደሉም፡፡በኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ የኮንስትራክሽን ውል ጋር የተያያዙ ግጭቶች በአብዛኛው በቀጥታ በፍርድ ቤት በኩል እልባት የሚያገኙበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ይህ ሁኔታም በብዙ መልኩ ሲመዘን ትክክል ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡
*ስለዚሁም በአብዛኛው አለም ሀገራት ጥቅም ላይ የሚውሉ እና በኛም ሀገር በተወሰነ ደረጃ እንደ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ባሉ ተቋማት ጥቅም ላይ የሚውሉና እየዳበሩ የመጡ በጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ የተካተቱ አማራጭ የግጭ መፍቻ መንገዶችን በዚህ ጽሁፍ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
*የኮንስትራክሽን ዘርፉ ግዙፍ ሀብት የሚንቀሳቀስበት እንደመሆኑ መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ የግጭት መፍቻ መንገዶችን አሳሪ የህግ ማእቀፍ በማስተካከል፣የአሰራር ስርአት በመዘርጋት እና አለማቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን የግጭት መፍቻ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ፈጣን ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል፡፡
፡
▶️ከ 1999 በፊት የነበሩ FIDIC ጀኔራል ኮንዲሽኖች በዋናነት ለመሀንዲሱ የውሳኔ ሰጭነት ስልጣን የሚሰጡ ናቸው፡፡ መሀንዲሱም ገለልተኛ እና ነጻ ሆኖ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይገመት ነበር፡፡
*በእርግጥ በአብዛኛው መሀንዲሱ ዲዛይኑን የሚሰራበት ሁኔታ በመኖሩ እና ዲዛይን አዘግይቶ ለተቋራጭ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ስለሚኖር እና ለመሀንዲሱ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍለው አሰሪው በመሆኑ እና መሀንዲሱ ለወደፊት ከአሰሪው ስራ ለማግኘት ሊያስብ ይችላል የሚለው በመኖሩ የመሀንዲሱ ገለልተኛነት ጉዳይ በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የግጭት መነሻ እየሆነ በመምጣቱ ሌሎች ተራማጅ አማራጮችን ማየት አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል፡፡
:
▶️FIDIC 1999 general condition of contract for civil engineering works...
*ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን አዲስ የግጭት አፈታት መንገድ ይዞ ብቅ ያለ ነው፡፡ Dispute Adjudication Board(DAB) በዚህ ቨርሽን የመጣ አዲስ ሀሳብ ነው፡፡
*ይህ ቦርድ ግጭት በተከሰተ ጊዜ በአሰሪና ተቋራጭ የሚመረጥ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ውሉ ሲደረግ ስማቸው የተዘረዘረ ገላጋዮችን የያዘ ዝርዝር የውሉ አካል ተደርጐ እስከውሉ መጨረሻ ድረስ የሚከሰቱ ግጭቶችን በገላጋይነት የሚፈቱበት ሁኔታም ይኖራል፡፡
*እንግዲህ ቦርዱ(DAB) በሰጠው ውሳኔ ላይ ደስተኛ ያልሆነ ወገን ደስተኛ ያለመሆኑን በ28 ቀን ውስጥ ማስታዎቅ ይኖርበታል፡፡ (notice of dissatisfaction) በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የቦርዱ ውሳኔ ላይ ደስተኛ ያለመሆንን ማስታዎቅ ያልተከናወነ እንደሆነ የቦርዱ ውሳኔ አስገዳጅና የመጨረሻ ይሆናል፡፡
*ቀጥሎ የሚመጣው ለ56 ቀን የሚቆይ በሰላም ለመፍታት የመሞከር ሂደት(amicable settlement) ነው፡፡ይህን ሂደት ሳይሞክሩ ማለፍ አይቻልም፡፡ ይህ ሂደት ካልተሳካ የመጨረሻው ሂደት አርቢትሬሽን ይሆናል፡፡
* እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ቦርዱ(DAB) አርቢትሬተር አይደለም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጽያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀን 04/04/2012ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በፓርላማ እንዲጸድቅ ያስተላለፈው የ1958 የኒውዮርክ ኮንቨየንሽን በቦርዱ(DAB) ውሳኔ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ በዚህ አጋጣሚ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኒውዮርክ ኮንቨየንሽንን ለማጽደቅ የመምራቱ ጉዳይ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትንም የመሳብ እድል ይኖረዋል፡፡
:
*ስለ Dispute Adjudication Board(DAB) ዝርዝር ሁኔታወች በተለይ ገላጋዮች ስለሚመረጡበት ሁኔታ እና ስለስነስርአት ድንጋጌዎች በጥልቀት በጀኔራል ኮንዲሽኑ ክሎስ 20 ላይ ተቀምጧል፡፡
:
▶️The new 2017 edition of FIDIC...
ይህ አዲሱ የፊዲክ ቨርሽን ደግሞ dispute avoidance/adjudication board(DAAB) የሚል ቦርድ ያካተተ ነው፡፡ ይሄውም ከ1999 ፊዲክ ጋር በአብዛኛው ጉዳይ ተመሳሳይ ቢሆንም ግጭት ማስወገድ/ avoidance/ የሚለውን አዲስ ሀሳብ ያካተተ ነው፡፡ በዚህም ቦርዱ አሰሪና ተቋራጮች የማያግባባቸው ነገር በሚከሰት ጊዜ ተቀራርበው ተነጋግረው የማያግባባቸውን ነገር እንዲፈቱ የማገዝና ወደ ግጭት እንዳያመራ የማገዝ ስራን የጨመረ ነው፡፡
*ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር ለማወቅ ክሎስ 21 መመልከት ይቻላል፡፡
.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Con'd......


▶️በመጨረሻም.... @engineer03
.
*መንግስት ጊዜ መፍጀት ሳያስፈልገው የፍትሀብሄር ስነስርአት ህጉ አንቀጽ 315 ድንጋጌን በማስተካከል የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በግልግል እንደማይታዩ የሚደነግገውን እንዲያሻሽለው ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡
*በሀገራችን 80 በመቶ የሚሆነው ግንባታ በመንግስት አሰሪነት የሚከናወን እንደመሆኑ እና አለማቀፉን የአርቢትሬሽን ውሳኔ ማስፈጸሚያ ኮንቨየንሽን ለማጽደቅ እየተንቀሳቀስን ባለንበት ሁኔታ የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በአማራጭ የግጭት መፍቻ መንገድ እንደማይፈቱ የሚደነግገውን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315 ባለበት ማስቀጠል አስፈላጊ አይደለም፡፡
*ከዚህ ጋር በተያያዘ በጣና ውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ድሬዳዋ አስተዳደር ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን መካከል በሰ/መ/ቁ 127459 በቀን መስከረም 23/2010ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔም መታየት አለበት፡፡ይዘቱም የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለ ው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም አርቢትሬተር ነው ይላል፡፡አርቢትሬተር የአስተዳደር ውሎችን እንዳይዳኝ በህግ ክልከላ ከተደረገበት አላማ አንጻር አጁዲኬተርም ሊፈቀድለት አይገባም ምክንያቱም የሁለቱም ውሳኔአቸው አስገዳጅነት ያለው ስለሆነ እና ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጭ አለመግባባት የሚፈታባቸው ናቸው ይላል፡፡ስለዚህ በዚህ ውሳኔ መሰረት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውል ጉዳይ በግልግል ዳኝነት አይታይም ማለት ነው፡፡ይህ ውሳኔ ተራማጅ የሆነውን አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ በአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች ጉዳይ ተፈጻሚ እንዳይሆን በማድረግ ምእራፉን የዘጋ ነው፡፡
*ስለሆነም ምእራፉ የተዘጋው አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ ተፈጻሚነት ዳግም እንዲነሳ እና ከአለማቀፉ እድገትና ዝማኔ ጋር መራመድ እንችል ዘንድ መንግስት የኒውዮርክ ኮንቨየንሽንን ለማጽደቅ በጀመረው አግባብ ጎን በጎን የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 315(2) እና በሰ/መ/ቁ 127459 በቀን መስከረም 23/2010ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ(ህግ ስለሆነ) የህግ ማእቀፉን ሊያስተካክለው ይገባል፡፡
.
http://t.me/engineer03