Civil Engineering
1.36K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
673 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
- የፍሳሽ ትቦዎች ሲሰሩ ቁፏሮውን፣ ግንባታውን፣ back fill ኡንም ጭምር quality ማሳነስ ... ክፍያ ላይ ግን quantity አጋኖ ማቅረብ
- መንገዱን አቋርጠው የሚሄዱ ትቦዎች ( cross drainage ወይም culvert) በሚሰሩበት ጊዜ ቁፏሮ፣ backfill ፣ ግንባታውን ወዘተ quality ማሳነስና እንደነገሩ መስራት ... ክፍያ ላይ ያው የተዋዋልነው ተሰርቷል ማለት
- የድንጋይ ስራዎች stone pitching፣ masonry ፣ riprap ወዘተ ስራዎችን ማጋነን
- ለድልድይና ለትቦዎች ደህንነት የሚሰሩ ግንባታዎችን ማጋነን

#Series 4000: Earthworks and Material Stabilisation

- Road bed (( ወይም የመንገዱ የመጀመሪያው ንጣፍ ማለት ይቻላል)) ሲሰራ መጀመሪያ የነበረው ጥሩ ያልሆነ አፈር (unsuitable material) ተነስቶ ሌላ ተተክቷል ይባላል ((እውነት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል)) ለዚህም ክፍያ አለው ... ቀጥሎም Road bed ለተሰራበት ይከፈላል ... የተሰራው መጠንና ካሊቲውን ፈጣሪ ያውቃል

- ሌላው የመንገዱ ትልቁና ዋናው ወጪ Cut እና Fill ነው ።
- Cut section ሲኖር የተቆረጠውን volume አጋኖ ሪፖርት ማድረግ በተጨማሪም በቀላሉ የሚቆረጥ ወይም soft excavation ሆኖ ሳለ Hard Excavation ነው ብሎ ማስገባት ... ብሩ ይጨምራላ

- Fill section ሲሆን ደሞ ያው በጥራትም ይሁን በ volume ብዙ መብላት ይቻላል። በተጨማሪ ደሞ fill ሲደረግ በ Layer ነው የሚሞላው ለምሳሌ በ25 ሳንቲም thickness ትሞላለህ ከዛ ኮምፖክት ታደርጋለህ ከዛ ክፍያ ይሰጥሃል ... ሳይት ላይ ምን ሊደረግ ይችላል መሠለህ?? ... 1 ሜትር ለመሙላት ኮንትራቱ ላይ በ25 እየተሞላ ይጠቅጠቅ ካለ 4 Layer ይኖራል ማለት ነው። 4x25 cm = 1 ሜትር ...ሳይት ላይ ግን በ2 layer ብቻ ሊሞላ ይችላል። በ50 cm ውፍረት ማለት ነው። ኮንትራክተሩ አራቴ ሰርቶ ሊያገኝ የሚገባውን በሁለት ስራ ያገኛል ማለት ነው። በዛ ላይ ከሙሉ ወጪው በግማሽ ይድናል። ለ50 ብር ስራውም 100 ይከፈለዋል።

- Borrow area ለማግኘትም የተወሰኑ ንግግሮች ይኖራሉ በመሬቱ ባለ ይዞታዎችና በመንገዱ ባለቤት መሀል

#Series 5000 : Sub Base, Road Base and Gravel Wearing Course

- እዚህም እንደላይኛው volume በማምታታት ወይም layer በመቀሸብ ... Layer ቅሸባ ከሚገመተው በላይ አዋጭ ነው

#Series 6000 - Bituminous Surfacings and Road Base

- እዚህም እንደሌሎቹ volume ና layer ቅሸባ ነው።

#Series 8000 - Structure

እዚህ ስር ያሉት masonry work , bridges, box and slab culvert, cofferdam, timber structures, structural steelwork ወዘተ ናቸው። እንደሚታወቀው እነዚህን ለመስራት የሚያስፈልጉት ማቴሪያሎች ፌሮ ፣ ሲሚንቶ ፣ aggregate ፣formwork ያስፈልጋል። excavation እና backfill ስራዎች ይኖራሉ .... በሌባ አእምሮ do the maths!

#Series 9000 - Ancillary Work

በእዚህ ስር ያሉት gabion, mattresses, kilometer የሚያመላክቱ ኮንክሪቶች ( Kilometer Post), አስፖልቱ ላይ የሚቀቡ ቀለሞች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ guardrail ፣ ከግንባታ በኋላ አካባቢውንና borrow areaውን ወደ ተፈጥሯዊው ሁኔታ ለመመለስ የሚሰሩ ማስተካከያዎችና የእፅዋት ተከላዎች ፣ አጥሮች ፣ የእግረኛ መንገዶች ፣ ለሴፍቲ ተብለው የሚሰሩ የኮንክሪትና masonry ግድግዳዎች ወዘተ ናቸው።

..........
መንገድ ስራ ላይ ማጭበርበርና ውሸት እንደ hobby ወይም ዝንባሌ ነው። ጥዋት ተነስተህ እስፖርት እንደምትሰራው ምናምን በቃ የመንገድ ስራ ሰራተኞች ወደዛ ያዘነብላሉ። በተለይም ከአዲስ አበባ የራቀ ቦታ ላይ ከሆነ ሌቦቹ እንደፈለጉ ይፈነጩብሃል። መንግስት የለም ወይ የሚያስብለኝ ከህዝቦች መሞት ይልቅ መንገድ ስራ ላይ የሚሠራውን ሳይ ነው። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩ እንደአለቃ ይሆንብሃል። ተቆጣጣሪ ሆነህ ኮንትራክተሩን ብታማ እንዳንተው ተቆጣጣሪ ተብሎ የተሾመው አለቃህ ይገላምጥሀል ፣ ይነዘንዝሃል። ለምን ካልክ ብዙ ሴራዎችን እየሠሩ መሮህ እንድትሄድ ያደርጉሀል። ይሄንን ፅሁፍ የፃፍኩት ስርቆቱ በግልፅ እንዲታወቅና መፍትሄ እንዲሰጠው ነው። ነገሮቹ መዘርዘራቸውም ለእያንዳንዱ ችግር የራሳችሁን መፍትሄ እንድታስቡ ነው። የተሻለ መፍትሄ ካላችሁ ወዲህ በሉ ....
...........

#መፍትሔው ምንድነው??

1. የመንገድ ባለቤቶች የራሳቸውንም ሰራተኛ፣ ኮንሰልታንቱንም ይሁን ኮንትራክተሮችን ማመን የለባቸውም። ከዚህ ሰርክል ወጣ እያሉ ስራዎችን ቼክ ማድረግ።
2. የተለያዩ ምርምሮችን በማሰራት አዳዲስ የአሰራርና የቁጥጥር መንገዶችን መፍጠር
3. የሚያጋልጡ ግለሰቦችን ማበረታታት
4. መንገድ ስራ ላይ በአብዛኛው በሰርተፍኬት/ዲፕሎማ ነው የሚሰሩት። እነዚህም ሰዎች ስራ እናጣለን በሚል ስጋት የተባሉትን አሜን ብለው ነው የሚሰሩት። የተማረውን ማስገባት የተሻለ ነው።
5. የመንገዶች ባለቤቶች የተቆጣጣሪውንና የራሳቸውን ሰራተኞች ደሞዝ ቢጨምሩ ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ይቀንሰዋል።

.
.
ሀሳብ መስጠት ይቻላል!
🏗Plinth beam

👉በመሬት ደረጃ እና በመሬቱ ወለል መካከል ያለው የግድግዳ ክፍል ነው፡፡
*plinth ብዙውን ጊዜ የድንጋይ ንጣፍ ስራ ነው።
*መሠረቱም በእንጨት ላይ ከሆነ ፣ከወለል ወለል በላይ ግድግዳውን ለመደገፍ አንድ ክፈፍ ጣውላ ይጣላል።
*በፕሌይ አናት ላይ እርጥብ ማረጋገጫ ኮርስ ይሰጣል፡፡
*እሱ ብዙውን ጊዜ ከ 75 ሚ.ሜ ውፍረት ያለው የኮንክሪት ኮርስ ነው ፡፡


https://t.me/engineer03
የታላቁ ህዳሴ ግድብ እውነታዎች......

👉 ግድቡ 5,150 ሜ.ዋ ሀይል የማመንጨት አቅም አለው

👉 13 የሀይል ማመንጫ ዩኒቶች (ተርባይኖች) የተገጠሙለት ነው

👉 እያንዳንዱ ተርባይን 375 ሜ.ዋ በላይ የማመንጨት አቅም አለው

👉 ግድቡ 145 ሜትር ወደ ላይ ይረዝማል፤ ወደ ጎን ደግሞ 1.8 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሆኖ ነው የተገነባው

👉 ከዋናው ግድቡ ሞልቶ የሚወጣው ውሃ ሳድል ግድብ (ኮርቻ ግድብ) ውስጥ ይከማቻል

👉 ኮርቻ ግድብ 50 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ወደ ጎን 5.2 ኪ.ሜ የሚሸፍን ነው

👉 በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ግድብ ነው።

👉 አጠቃላይ እስካሁን ባለው መረጃ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 16.2 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል

👉 ግድቡ አሁን ያለበት ደረጃ 1ኛ እና 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቋል

👉 በነገው እለት አንዱ ተርባይን ሀይል የሚያመነጭ ይሆናል

👉 አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 83.9% ተጠናቋል

👉 ግድቡ ለቱሪዝም፣ ለአሳ ሀብት ለኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ጠቀሜታዎች አሉት

👉 ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ 246 ኪ.ሜ የሚሸፍን አርቴፊሻል ሀይቅ ይፈጠራል።
🇪🇹እንኳን ደስ ያለን🇪🇹

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዛሬው እለት በ375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ጀምሯል‼️
❤️🇪🇹

https://t.me/engineer03
BeGet Engineering Solutions PLC. is inviting you to a scheduled Zoom meeting.

Topic:

1. Structural Design Concepts & Office Application


2. Briefing on the major Eurocode chapters

Time:
Mar 13, 2022 02:00 PM Nairobi
Or
ሚያዝያ 4/2014, ቀን 8:00 ሰዓት

Join Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/88912349371?pwd=aDZuWjQrREpVUkd5WDd2eExCN1Z6QT09

Meeting ID: 889 1234 9371
Passcode: 099808
One tap mobile
+16699009128,,88912349371#,,,,*099808# US (San Jose)
+12532158782,,88912349371#,,,,*099808# US (Tacoma)

Dial by your location
+1 669 900 9128 US (San Jose)
+1 253 215 8782 US (Tacoma)
+1 301 715 8592 US (Washington DC)
+1 312 626 6799 US (Chicago)
+1 346 248 7799 US (Houston)
+1 646 558 8656 US (New York)
Meeting ID: 889 1234 9371
Passcode: 099808
Find your local number: https://us02web.zoom.us/u/kcaDQ0FB6f
👍1
Add your Engineer family on a discussion group
Culvert details
Why spacers are provided 🤔