Civil Engineering
1.36K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
674 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
👆👆👆👆Civil engineering huge machinery 👆👆👆👆
👉FACTORS AFFECTING CONCRETE STRENGTH
.
▶️Concrete strength is effected by many factors, such as quality of raw materials, water/cement ratio, coarse/fine aggregate ratio, age of concrete, compaction of concrete,
temperature, relative humidity and curing of concrete.
1. Quality of Raw Materials:
*Cement: Provided the cement conforms with the appropriate standard and it has been stored correctly (i.e. in dry conditions), it should be suitable for use in concrete.
*Aggregates: Quality of aggregates, its size, shape, texture,
strength etc determines the strength of concrete. The
presence of salts (chlorides and sulphates), silt and clay also
reduces the strength of concrete.
*Water: frequently the quality of the water is covered by a
clause stating “..the water should be fit for drinking..”. This
criterion though is not absolute and reference should be
made to respective codes for testing of water construction
purpose.
2. Water / Cement Ratio:
The relation between water cement ratio and strength of
concrete is shown in the plot as shown below:
The higher the water/cement ratio, the greater the initial spacing between the cement grains and the greater the
volume of residual voids not filled by hydration products.
There is one thing missing on the graph. For a given cement
content, the workability of the concrete is reduced if the
water/cement ratio is reduced. A lower water cement ratio
means less water, or more cement and lower workability.
However if the workability becomes too low the concrete
becomes difficult to compact and the strength reduces. For a
given set of materials and environment conditions, the
strength at any age depends only on the water-cement ratio,
providing full compaction can be achieved.
3. Coarse / fine aggregate ratio:
Following points should be noted for coarse/fine aggregate
ratio: If the proportion of fines is increased in relation to
the coarse aggregate, the overall aggregate surface
area will increase.
If the surface area of the aggregate has increased, the water demand will also increase.
*Assuming the water demand has increased, the
water cement ratio will increase Since the water cement ratio has increased, the compressive strength will decrease.
4. Aggregate / Cement Ratio:
*Following points must be noted for aggregate cement ratio:
If the volume remains the same and the proportion of cement in relation to that of sand is increased the surface area of the solid will increase.
*If the surface area of the solids has increased, the
water demand will stay the same for the constant
workability.
*Assuming an increase in cement content for no
increase in water demand, the water cement ratio will
decrease.
*If the water cement ratio reduces, the strength of
the concrete will increase.
*The influence of cement content on workability and strength
is an important one to remember and can be summarized as
follows:
1. For a given workability an increase in the proportion of
cement in a mix has little effect on the water demand and results in a reduction in the water/cement ratio.
2. The reduction in water/cement ratio leads to an increase
in strength of concrete.
3. Therefore, for a given workability an increase in the
cement content results in an increase in strength of concrete.
5. Age of concrete: The degree of hydration is synonymous with the age of concrete provided the concrete has not been allowed to dry out or the temperature is too low.
*In theory, provided the concrete is not allowed to dry out,
then it wil always be increasing albeit at an ever reducing
rate. For convenience and for most practical applications, it
is generally accepted that the majority of the strength has been achieved by 28 days.
6. Compaction of concrete: Any entrapped air resulting from inadequate compaction of the plastic concrete will lead to a reduction in strength.
If there was 10% trapped air in the concrete, the strength will fall down in the range of 30 to 40%. CONT'D 👇👇👇
7. Temperature: The rate of hydration reaction is temperature dependent.
*If the temperature increases the reaction also increases. This
means that the concrete kept at hi gher temperature will gain
strength more quickly than a similar concrete kept at a lower
temperature. However, the final strength of the concrete kept at the higher temperature will be lower. This is because the physical form of the hardened cement paste is less well structured and more porous when hydration proceeds at faster rate.
*This is an important point to remember because temperature
has a similar but more pronounced detrimental effect on
permeability of the concrete.
8. Relative humidity: If the concrete is allowed to dry out, the hydration reaction will stop.
*The hydration reaction cannot proceed without
moisture. The three curves shows the strength development
of similar concretes exposed to different conditions.
9. Curing: It should be clear from what has been said above that the detrimental effects of storage of concrete in a dry
environment can be reduced if the concrete is adequately
cured to prevent excessive moisture loss.

.
▶️FOR MORE UPDATES ሼር
http://t.me/engineer03
▶️የ አዲስአበባ ቀላል ባቡር
፡
👉ሸገር አዱ ገነት❤️
፡
🙏ወብ ምሽት ተመኘን😍
👉በኮንስትራክሽን ውል የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/
---------------
▶️በጉባዔ አሰፋ(ጠበቃና የህግ አማካሪ)
====================
*በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው፡፡
*ተቋራጩ የውሉን የግናባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡
*በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው? አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡
*በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣የሳይት ርክክብ/site handover/፣ የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ መዘግየት ቅጣት/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡
*በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡
*እንግዲህ ከዚሁ በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቸ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡
*እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/part work completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡
*ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል፡፡ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡
*ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/time extension/ ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡
*የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡
*በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ መዘግየት ቅጣት/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡
*የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡
*ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡
*በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ20% መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡
*በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡በኮመን ሎው ሊኩዴትድ ዳሜጅ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ አመሰግናለሁ!

http://t.me/engineer03
👉አሁን እስቲ ስለ Pile foundation ትንሽ እንበል...
.
▶️Pile foundations are the part of a structure used to carry and transfer the load of the structure to the bearing ground located at some depth below ground surface.
*The main components of the foundation are the pile cap and the piles.
*Piles are relatively long and slender members used to transmit foundation loads through soil strata of low bearing capacity to deeper soil or rock having a higher bearing capacity
፡
❇️The purpose of apile foundation
💠to transmit a foundation load to a solid ground
💠to resist vertical ,lateral and uplift load
💠to reduce excessive settlement
፡
✅ When pile foundation is used ??
➡️The soil near the surface does not have sufficient bearing capacity to support the structural loads
➡️The estimate settlement of the soil exceed tolerable limits
➡️Differential settlement due to soil variability is happen
➡️The structural loads consist of lateral loads ,moments & uplift force singly or in combination
፡
✳️pile capacity
🔴The ultimate bearing capacity of a pile is the maximum load which it can carry without failure or excessive settlement of the ground
🔴The allowable load on a pile is the load which can be imposed upon it with an adequate margin of safety ,it may be the ultimate load divided by a suitable factor of safety,or the load at which the settlement reaches the allowable value
:
🅾The bearing capacity of apile depends on:-
👉The method of installation
👉pile c-xes such as pile length ,cross section ,and shape
👉soil configuration and short and long-term soil properties.
: http://t.me/engineer03
👉FOR MORE
Which one is correct ? Why? Use discussion group

👇
@engineersWorks
Busan South Korea 🇰🇷

ውብ ምሽት ተመኘን
Reinforced_concrete_design_to_eurocode_2_ed_2007.pdf
56.1 MB
👉Reinforced concrete design to eurocode 2
AASHTO LRFD Bridge Design Specifications 8th Ed. 2017.pdf
105.7 MB
👉For those of you who are taking Bridge design course! #Request
Columns are designed for minimum eccentricity

A. 10mm
B. 20mm
C. 40mm
D. All

Use discussion group and we justify the reason
👇🏼👇🏼👇🏼
@engineersWorks
Shanghai 🇨🇳

ውብ ምሽት ተመኘን
Civil Engineering pinned «Columns are designed for minimum eccentricity A. 10mm B. 20mm C. 40mm D. All Use discussion group and we justify the reason 👇🏼👇🏼👇🏼 @engineersWorks»
👉ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/
©By: Gubaie A.(ጠበቃና የህግ አማካሪ)
------------- --------------- --------
▶️በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?
*በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
.
*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-
-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡
-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
-በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡
*በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡
*በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
*አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡
*በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡ አመሰግናለሁ
.

@engineer03
@engineer03
👉ቅደመ ክፍያ @engineer03
▶ADVANCE PAYMENT
.
➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል
1) ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
2)በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
3) ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።
Forwarded from መሠረተ ግእዝ
👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

👆 Join ያድርጉና የግእዝ ቋንቋን ይማሩ!!!!
✅ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!!
👉 የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat
with Drop or Solid Slab
.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::
Join us👇
@engineer03
@engineer03
@engineer03

Add your engineer's friends from discussion group
👇@engineersWorks
✉️የ ዛሬ ጥያቅያችን ...
.
👉According to Ethiopian building construction code, minimum reinforcement bar size for elevation column is?
A: dia 8
B; dia 10
C: dia 12
D dia 14
.
▶️GIVE ANSWER ON DISSCUSSON OR @engineersWorks
Add your all engineers friend in the group, then we will send the quation 📄

You must add 20 of your friends 👫, then we will send the selective quations & books inbox as a message for you .
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

@engineersWorks
@engineersWorks
@engineersWorks