Civil Engineering
1.36K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
674 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
Reinforced_concrete_design_to_eurocode_2_ed_2007.pdf
56.1 MB
👉Reinforced concrete design to eurocode 2
AASHTO LRFD Bridge Design Specifications 8th Ed. 2017.pdf
105.7 MB
👉For those of you who are taking Bridge design course! #Request
Columns are designed for minimum eccentricity

A. 10mm
B. 20mm
C. 40mm
D. All

Use discussion group and we justify the reason
👇🏼👇🏼👇🏼
@engineersWorks
Shanghai 🇨🇳

ውብ ምሽት ተመኘን
Civil Engineering pinned «Columns are designed for minimum eccentricity A. 10mm B. 20mm C. 40mm D. All Use discussion group and we justify the reason 👇🏼👇🏼👇🏼 @engineersWorks»
👉ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/
©By: Gubaie A.(ጠበቃና የህግ አማካሪ)
------------- --------------- --------
▶️በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?
*በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
.
*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው፡፡ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-
-በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡
-ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
-በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡
*በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡
*በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት፡፡ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
*አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡
*በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡ አመሰግናለሁ
.

@engineer03
@engineer03
👉ቅደመ ክፍያ @engineer03
▶ADVANCE PAYMENT
.
➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል
1) ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
2)በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
3) ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።
Forwarded from መሠረተ ግእዝ
👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

👆 Join ያድርጉና የግእዝ ቋንቋን ይማሩ!!!!
✅ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!!
👉 የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat
with Drop or Solid Slab
.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::
Join us👇
@engineer03
@engineer03
@engineer03

Add your engineer's friends from discussion group
👇@engineersWorks
✉️የ ዛሬ ጥያቅያችን ...
.
👉According to Ethiopian building construction code, minimum reinforcement bar size for elevation column is?
A: dia 8
B; dia 10
C: dia 12
D dia 14
.
▶️GIVE ANSWER ON DISSCUSSON OR @engineersWorks
Add your all engineers friend in the group, then we will send the quation 📄

You must add 20 of your friends 👫, then we will send the selective quations & books inbox as a message for you .
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼

@engineersWorks
@engineersWorks
@engineersWorks
Civil Engineering pinned «Add your all engineers friend in the group, then we will send the quation 📄 You must add 20 of your friends 👫, then we will send the selective quations & books inbox as a message for you . 👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼 @engineersWorks @engineersWorks @engineersWorks»
Shanghai World Financial Center

👆🏻✌🏽
Top 10 construction companies in the world
......continued.....
#8. China State Construction Engineering Corp. Ltd.
👉Location: Beijing, China
👉Employees: 270,000
👉Revenue: $28.49 billion
👉Founded: 1957
Notable Projects: Shanghai World Financial Center
Akashi Kaikyo Suspension Bridge (World’s LongestBridge-1991m)
Adama Wind Farm, Ethiopia 🇪🇹
👉የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/
፡
▶️የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡አንድ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡
*ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡
*ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡
*ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤትስ?(Announcing the successful bidder)
*ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡፡ የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን(Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የውል ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡


http://t.me/engineer03
👉የ ዕለቱ ግላዊ ዕይታ ... የናንተ ዕይታም @engineersWorks ፃፉልን
.
▶️በሀገራችን የግንባታ ስራዎች ጥራት ማጣት ችግር ወነኛ ተጠያቂ አማካሪዉ ነዉ። ችግሩ በዋነኛነት የሚነሳዉ ከዲዛይኑ በጥራት አለመሰራት ነዉ። የዲዛይን ችግር ብዙ ችግሮች ያስከትላል።
.
1ኛ) ዲዛይኑ ራሱ ትክክል ላይሆንና ተገንብቶ አልቆ የማይሰራ ወይም ወድያዉ የሚበላሽ ሊሆን ይችላል። ባደጉት ሀገሮች እንድህ አይነት ፕሮጄክቶችን ''White Elephant'' ይሉታል። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂ አማካሪዉ ነዉ። ኮንትራክተሩስ ብትሉ በርግጥ አንዳነድ ብቃትና ልምድ ያላቸዉ ገና የጨረታ ዶክመንቱን ሲያዩ ዲዛይኑ ትክክል እንዳልሆነ የሚገባቸዉ አሉ። ብዙዎቹ ዲዛይኑ እንዲስተካከል ይጠይቃሉ ግን መልስ ስለማያገኙ ትተዉ ዋጋ ይሞላሉ ወይንም መወዳደሩን ይተዋሉ። ስግብግቦቹ ተወዳድረዉ ካሸነፉ ወደ ስራ ገብተዉ በየቀኑ የስራ ትእዛዝ አየወሰዱ መረጃና ማስረጃ በጥንቃቄ እየያዙ የሰሩትን ሰርተዉ ገነዘባቸዉን ተቀብለዉ ይሄዳሉ ስለዉጤቱ ግድ አይላቸዉም የኔ ችግር አይደለም የዲዛይኑ ነዉ ይላሉ። ተጠያቂነቱን የአማካሪዉ ያደርጋሉ ማለት ነዉ።
.
2ኛ) የዲዛይን ጥራት ችግር BOQ በጥራት እንዳይዘጋጅ ያደርጋል። በየአይተሙ የኳንቲቲ መብዛት ወይም ማነስ፣ ወይም ጭራሽ BOQ ዉስጥ አለመካተት ያስከትላል። ይህ ደግሞ ስራ ዉስጥ ከተገባ ቡሃላ Variation, price qoutation, additional work order..... ምናምን የሚባሉ ችግሮች ያስከትልና በየግዜዉ በዉሳኔ መዘግየት ስራ እየቆመ አየተሰራ ረጅም ግዜ፣ ከታሰበዉ በላይ ወጪ ና አንዳንዴም አስከመቋረጥ የሚደርስ ችግር ያስከትላል። ይህም በዋነኛነት አማካሪዉ ያመጣዉ ችግር ነዉ።
.
3ኛ) መጀመሪያ የዲዛይን ስህተት ቢኖረዉም ወደ ስራ ሲገባ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ ዲዛይኑን On ground ቼክ አያደረገ(እዚህ ጋ ኮንትራክተሩም ቼክ የማድረግ ሀላፊነት አለበት) ማስተካከያ እየሰጠ ግንባታዉን ዉጤታማ ማድረግ ያለበት በበላይነት አማካሪዉ ነዉ። ስለዚህ በግንባታ ወቅት ይህ ባለመደረጉ በወነኛነት አሁንም አማካሪዉ ተጠያቂ ይሆናል።
.
4ኛ) ሁሉም ቅድመ ግንባታ ስራዎች Perfect ሆነዉ በግንባታ ወቀት ኮንትራክተሩ ስግብግብ ሆኖ በ poor workmanship, poor quality material, other act of corruption ግንባታዉ ቢበላሽ ይህንን እላዩ ላይ ቆሞ በሀላፊነት በየደቂቃዉ እየተቆጣጠረ እንዳይፈጠሩ ማድረግ በዋነኛነት የአማካሪዉ duty ስለሆነ ከዚህ ጋር በተያያዘ ግንባታዉ ቢበላሽ አሁንም ተጠያቂዉ አማካሪዉ ነዉ።
.
ስለዚህ ለሀገራችን የግንባታ ችግሮች ግንባር ቀደም እና ዋነኛ ተጠያቂ አማካሪዉ/Consultant/ ነዉ።
.
የናንተ ዕይታም DISCUSSION ወይም @engineersWorks ፃፉልን
.
.

http://t.me/engineer03
👉መሰረት /ፋውንዴሽን/ @engineer03
▶Foundation
1) ቁፋሮ እና አፈር ሙሌት
*መሰረት ሁልጊዜ የተረጋጋ መሬት ላይ ሊቀመጥ ይገባል።
ጥሩ አፈር ካልሆነ በተመረጠ እና ከሌላ ቦታ በመጣ አፈር በሚገባ
ተጠቅጥቆ እና ተደልድሎ ሊቀመጥ ይገባል።
*የተመረጠው አፈር ንብርብር/layer/ በየ 25 ሴ᎐ሜ በሚገባ
ሊጠቀጠቅ ወይም ሊደለደል/compact/ ሊደረግ ይገባል።
*በሚደለደልበት ወቅት በተወሰነ ረገድ እያንዳንዱን ንብርብር
ለተሻለ ጥቅጠቃ እንዲያመች እርጥበት እነዲያገኝ ውሀ
ማርከፍከፍ ያስፈልጋል
2) አርማታ ሙሌት እና የብረት ስራ
*ቀጭን አርማታ/lean Concrete/ ከተመረጠው አፈር ሙሌት በላይ ሊደረግ ይገባል። እንደአስፈላጊነቱም እርጥበተ መከላከያ/water proof/ ሊደረግ ይችላል።
*አርማታ ሙሌት ለመሰረት፣ ቢም፣ ኮለን እና ወለል ስራ የአርማታ ጥንካሬ በትንሹ C25 ሊኖረው ይገባል። (እንደ ስትራክቸራል ዲዛይኑ ሊለያይ ይችላል)
*የቢም ብረት የላይኛው ብረት መሀል ላይ የታችኛው ደግሞ
ኮለን ድጋፍ/support/ ላይ ሊሆን ይገባል። (ማት ፋውንዴሽን ላይ
የዚህ ተቃራኒ ይሆናል)
*ብረት 4D የብረቱን ውፍረት በአራት በማባዛት የሚሰጠንን
ርዝመት በመደረብ መተላለፍ ይተበቅበታል።
*ዲዛይን ላይ በተቆራረጠ መስመር /hidden line/የሚቀመጡ ብረቶች ሁልጊዜ የታች ብረት ሆነው ይቀመጣሉ።
*የአርማታ ሽፋን/concrete cover/አብዛኛውን ግዜ 5ሴ᎐ሜ
ይሆናል ከመሬት በላይ ግን በ 2᎐5ሴ.ሜ ይሰራል።
*በአርማታ ወይም በብረት የሚሰራ ክፍተት መስጫ/spacer/ ልንጠቀም ይገባል።
.
⚡ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።