Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association
5.36K subscribers
443 photos
12 videos
231 files
156 links
Tefera Gebeyehu Werku
General Manager, EPHEIA
Institutional email: info@ephetveta.com




Website : https://ephetveta.com
Download Telegram
በዳግም ምዝገባ የ 6 የጊዜ ገደብ የተሰጣችሁ ተቋማት ይመለከታል።
👍4❤3
#ExitExam update

የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም ይሰጣል።
የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ከየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ትናንት ጥር 19/2018 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው መረጃ ገልጿል።
የፈተና መርሐግብሩን ትክክለኛነትና ለዩኒቨርሲቲዎች መድረሱን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።
በመሆኑም የ2018 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ዕጩ ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳውን አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ተብሏል።

#ExitExam2018 #MoE
Via @tikvahuniversity
❤13🙏2
Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association
#ExitExam update የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም ይሰጣል። የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ከየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ትናንት ጥር 19/2018 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው መረጃ ገልጿል። የፈተና መርሐግብሩን ትክክለኛነትና ለዩኒቨርሲቲዎች መድረሱን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ…
⚠️የመረጃ ማስተካከያ
==================
የ2018ዓ/ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና መስጫ ከየካቲት 16-27/2018ዓ/ም እንደሚሰጥ መረጃ አጋርተን እንደነበር ይታወቃል።

ነገር ግን ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ እንደተቻለው ጉዳዩ ገና በወይይት ሂደት ላይ ያለ እንደሆነና ትክክለኛ የፈተና ቀናት በውል ያልተለዩ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

ስለሆነም በሚመለከታቸው አካላት የሚገለፁ ትክክለኛና የተረጋገጡ የ 2018ዓ/ም አጋማሽ የፈተና ቀናት የምናጋራ መሆኑን እየገለፅን ለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ እንጠይቃለን።
🤔45😱28❤22👍21
Call for Papers St.Mary's University
❤6
Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association pinned «⚠️የመረጃ ማስተካከያ ================== የ2018ዓ/ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና መስጫ ከየካቲት 16-27/2018ዓ/ም እንደሚሰጥ መረጃ አጋርተን እንደነበር ይታወቃል። ነገር ግን ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ እንደተቻለው ጉዳዩ ገና በወይይት ሂደት ላይ ያለ እንደሆነና ትክክለኛ የፈተና ቀናት በውል ያልተለዩ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ስለሆነም በሚመለከታቸው አካላት የሚገለፁ ትክክለኛና…»
#የመውጫ _ፈተና‼️
==================
የ2018ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜና ፕሮግራም #በነገው_ዕለት በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በኩል ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ እየገለፅን ዝርዝር መረጃውን ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።
👍43❤16🤔8
Time Table, HR and Candidate Distribution by Each Round.xlsx
115.9 KB
Update: #የመውጫ ፈተና

እንደሚታወቀው በከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ዙርያ በሚመለከታቸው አካላት በትናንትናው ዕለት ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፀን የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ይፋዊ የፈተና መርሐ-ግብር ሳይገለፅ ቀርቷል።

ሆኖም ከላይ የተያያዘው የፈተና መርሐ-ግብር  ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መላኩን እና ዩኒቨርሲቲዎቹም ዝግጅታቸውን እያከናወኑ እንዳሉ ለማረጋገጥ ችለናል።

የግል ከፍተኛ ተቋማትም ቅድመ-ዝግጅታቸውን በዚሁ አግባብ እንዲያከናውኑ እያሳሰብን አዲስ መረጃ የሚኖር ከሆነም የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
❤8
#Exit_Exam_Protocols
=========================================
የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከ የካቲት 17 - የካቲት 27/ 2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር መመሪያዎች፦

➡️ተፈታኝ ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የሞባይል ስልክ፣ ሚሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር፣ የራስ ያልሆነ መታወቂያ እንዲሁም ማንኛውም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው መገኘት አይችሉም፡፡
➡️ ተፈታኝ ተማሪዎች ከ3ዐ ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት ክፍል መገኘት አለባቸው፡፡
➡️ተፈታኝ ተማሪዎች ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል፡፡
➡️ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አስፈጻሚን ትዕዛዝ ማክበር ይጠበቅባቸዋል።
➡️ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ራሳቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
➡️ በሌላ ሰው ስም፣ መለያ ቁጥር (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) መፈተን አይቻልም፡፡
❤18👍12👏1
Exit Exam ለመጀመሪያ ጊዜ ለምትወስዱ ተፈታኞች የተላለፈ ወሳኝ መልዕክት 👇
=====================
# የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ቲኬት  ይዞ መቅረብ ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ ከታች በተቀመጠው ናሙና መሠረት ካሁኑኑ በወረቀት መያዝ እንዳለባችሁ እናሳስባለን።
#የመግቢያ ትኬቱን ለማገኘት username እና የይለፍ ቃል (password)  በማስገባት የምታገኙ መሆኑን እየገለፅን፣ የመግቢያ ትኬቱን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለዉን ማስፈንጠሪያ እንዲጠቀሙ በትህትና እንገልፃለን፡፡
URL: https://verify.ethernet.edu.et
❤15👍1
⚠️አስቸኳይ ማስታወቂያ!

የ2018ዓ.ም የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች በሙሉ!
የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የካቲት 17/2018 ዓ/ም መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ባልታሰበ የኃይል መቆራረጥ ችግር በዳታ ማዕከል ላይ በማጋጠሙ ችግሩን በመፍታት እንደገና ለማስጀመር ጥረት የተደረገ ቢሆንም የፕሮግራም መዛባትን በማስከተሉ የፈተናውን ሙሉ ፕሮግራም በአንድ ቀን ማሸጋሸግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ስለሆነም ሁሉም ፕሮግራሞች የዛሬን ጨምሮ ባሉበት ክፍለ ጊዜ ላይ ሆነው በተዋረድ በአንድ ቀን የተሸጋሸጉ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም ተፈታኞች መረጃው እንዲደርሳቸው እንዲደረግ እያሳሰብን ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

#ማስታወሻ፡- ዛሬ ፈተና ጀምረው የነበሩ ተፈታኞች እንደሙከራ ፈተና (Moc Exam) በመውሰድ ነገ በተመሳሳይ ሰዓት እንደገና የሚፈተኑ ይሆናል።
👍13❤3
⚠️Updated_NOTICE_#EXIT_EXAM

አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ሙሉ ቀን በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።

አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት የሚሰጠው ፈተና ከጁምዓ ሶላት ስግደት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ቅዳሜ በሚሰጡ ፈተናዎች ላይ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በኩል ቅሬታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስተካከያ ማድረጉ ታውቋል።

በዚህም አርብ በሁለተኛ ክፍለ-ጊዜ (ከ5:00-7:30) ፈተናዎች ላይ ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ፈተናው የማይሰጥ ይሆናል።
❤12