SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
🚧Subsidence is the downward movement of the ground underneath a building due to the withdrawal of moisture. This leads to the sinking of the foundation, which compromises the stability of the structure.

https://t.me/ethioengineers1
👏3👍2🙏1
SMH General Construction
🚧ይናገራል ፎቶ 👉ለአካል ጉዳተኞች መደረግ የሚገባቸው ዝግጅቶች እና የሰው ማመላለሻ አሳነሰር /Lift የሀገራችን ህግ ምን ይላል? . ▶የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር በመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፮፻፺፩//፪ሺ፫ አንቀጽ 5 እና በኢትዮጵያ ሕንጻ አዋጅ ቁጥር 6፻፳4/፪ሺ፫ ባወጣው አዋጅ መሰረት የህናንፃ ግንባታ ላይ ለሚተከሉ የሰው…
🚧የህንጻ ግንባታ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች ተገልጋይነት ታሳቢ ማድረግ ይኖርበታል.

▶️በኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ አንቀጽ 36 ላይ "ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንጻ ውስጥ በተሸከርካሪ ወንበር ለመንቀሳቀስ የሚገደዱትን እና መራመድ የሚችሉ ሆኖ ደረጃ መውጣት የሚሳናቸውን ጨምሮ የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመች መዳረሻ መዘጋጀት አለበት" በሚል በግልጽ ተደንግጓል፡፡

▶️ድንጋጌው በአስገዳጅ/obligatory/ ሁኔታ የተቀመጠ ነው፡፡

▶️በተጨማሪም በህንጻ ግንባታ ወቅት የሚሰሩ መጸዳጃ ቤቶች የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች የሚመቹ እና ሊደርሱባቸው የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚሁ መጸዳጃ ቤቶችም በበቂ መጠን/ቁጥር መኖር ይገባቸዋል፡፡

▶️ሌላው ከመሬት ወለል በላይ/above the ground floor/ ከ20(ሀያ) ሜትር
በላይ ከፍታ የሚኖራቸው የህንጻ ግንባታዎች ልዩ ግዴታ አለባቸው፡፡

▶️ይሄውም ህንጻው አሳንሰር ወይንም ተመሳሳይ አገልግሎት ሊኖረው እንደሚገባ እና አሳንሰሩም ያለማቋረጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው የህንጻ አዋጁ አንቀጽ 33(4) እና(5) ይደነግጋል፡፡
▶️ስለዚህ አሳንሰር ከግራውንድ ፍሎር ጀምሮ ወደላይ ከሀያ ሜትር በላይ ከፍታ ላላቸው ህንጻዎች የቅንጦት ሳይሆን በህግ የተቀመጠ ግዴታ ነው ማለት ነው፡፡

▶️ይህን የህንጻ ግንባታ ህግ መጣስ ደግሞ ከህንጻ አዋጁ አንቀጽ 47 ጀምሮ በተደነገገው አግባብ የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡

▶️ስለሆነም የህንጻ አዋጁ በሚያስቀምጠው አግባብ የህንጻ ግንባታዎችን እንዲከናወኑ ማድረግ ከተጠያቂነት የሚያድን ከመሆኑም ባሻገር የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች በህግ የተሰጣቸውን መብት እንዲገለገሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠርም መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለሁ፡፡

ጉባኤ አሰፋ
@ethioengineers1
👍16🙏1
Installation_Procedure_For_Etabs_20_3,_Safe_20_3_&_Sap_24_1.avi
212.7 MB
🔶 Here is installation procedure for the newly released Etabs 20.3, Safe 20.3 & Sap 24.1.
🔶 Students Registerd for Advanced Structural Design Package Starting on December 18/2022 Please make sure you have them all.
🔶Setups are posted below
👇

https://t.me/BeGetEngineering
👍32❤3🔥1🙏1
ድብቁ የሲሚንቶ ንግድ ሰንሰለት
***
ኢቢሲ በአዲስ አበባ መገናኛ እንዲሁም ጀሞ አካባቢ የሚካሄደውን ድብቁን የሲሚንቶ ንግድ ቅኝት አድርጓል፡፡

በድብቅ የሚካሄደውን የሲሚንቶ ንግድ ሰንሰለት ኢቢሲ የዘርፉ ተዋናዮች ጭምር በማናገር የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡

https://youtu.be/O56wdqB_8D0
👍8🤔3
🚧Cantilever Slab

A cantilever is a rigid structural element that extends horizontally and is supported at only one end. Typically it extends from a flat vertical surface such as a wall, to which it must be firmly attached. Like other structural elements, a cantilever can be formed as a beam, plate, truss, or slab.

https://t.me/ethioengineers1
👍11😍1
#NewsAlert

" ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲሸጥ ተወሰነ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገለፀ።

መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር ገልጾ በዚህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር አሳውቋል።

በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው ተብሏል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ተገልጿል።

#መንግስት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም መንግስት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ሚኒስቴሩ አሳውቋቃ።

በግብይቱ ውስጥም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን የተጠቆመ ሲሆን እያንዳንዱ ፋብሪካ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም አከፋፋዩን የመምረጥ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

Credit :
#ኤፍቢሲ

https://t.me/ethioengineers1
👍7❤6🙏1
SMH General Construction
#NewsAlert " ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲሸጥ ተወሰነ። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገለፀ። መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር ገልጾ…
#ሲሚንቶ

🚧ፋብሪካዎች ያቀረቡት የመሸጫ ዋጋና የተወሰነው መሸጫ ዋጋ !

👉 ዳንጎቴ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 549.49
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 811.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤795.93

👉 ደርባ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.59
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 779.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 761.55

👉 ሙገር

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 643.95
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 802.73
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 755.70

👉 ናሽናል

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል➤ 561.00
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 779.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 756.50

👉 ሀበሻ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 683.44
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 947.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 754.48

👉 PIONEER

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 510.04
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1783.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 753.95

👉 ኢትዮ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 595.66
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 973.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 753.60

👉 INCHINI

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 0
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1298.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤750.21

👉 KUYU

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 628.10
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤1019.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 752.50

👉 ኢስት

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 506.99
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1064.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤753.82

👉 ካፒታል

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 633.38
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 905.00
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤751.34

#አማካይ

- በስራ ላይ ያለ የመሸጫ ዋጋ በኩ/ል ➤ 590.3
- አሁን ያስገቡት መሸጫ ዋጋ ➤ 1014.6
- የተወሰነው የመሸጫ ዋጋ ➤ 758.1


https://t.me/ethioengineers1
👍21👏1
🏗ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማረችሁ ባለሙያዎች ያለን ጥቆማ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር ያዘጋጀነውን online package ተጠቃሚ በመሆን❗️

🏗በአካል መምጣት እና መማር ለምትችሉ
👉Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614

📞0911890392/ 0944186744

Join 🔸 @BeGetEngineering
👍15
#ኮንስትራክሽን ክሌም
         
#የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው።
#የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል።
#DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yelow Book ለDB መጠቀም ይቻላል።
#የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም።ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
#ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት።
#ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል።
#ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል።

        
#አመሰግናለሁ
ጉባዔ አሰፋ(0910217422)

https://t.me/ethioengineers1
👍20🔥1🤔1
🚧ለመቆጣጠር በሚል በኬላዎች ሲሚንቶን መያዝ ‹‹በጥብቅ›› ተከለከለ

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ጸድቆና ተግባራዊ ተደርጎ ሲሠራበት የነበረው የሲሚንቶ አቅርቦትና ሥርጭት መመርያ ተቀይሮ፣ ሲሚንቶን ለቁጥጥርና ለክትትል በሚል በየኬላዎችና ሌሎች ሥፍራዎች መያዝና መውረስ በጥብቅ ተከለከለ፡፡

ከባለፈው ሐሙስ ታኅሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ መመርያ፣ በተቀየረው መመርያ ላይ ይከናወኑ የነበሩ ሲሚንቶን በየኬላው በቁጥጥር ምክንያት መያዝ፣ እንዲሁም አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን ለፋብሪካዎች መምረጥ የመሰሉ ዓይነት ተግባራት፣ በማንኛውም የመንግሥት አካላት እንዳይከናወኑ ተከለከሉ፡፡ በአዲሱ መመርያ ‹‹በጥብቅ ለተከለከሉ ጉዳዮች›› መካከልም ሲሚንቶን ካለ ደረሰኝ መሸጥና ተሽከርካሪዎች ከፋብሪካ ሲወጡ ካለ መዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደማይችሉም ይገኙበታል፡፡

መመርያውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ እንደገለጹት፣ ከዚሁ መመርያ በኋላ መኪኖች ክትትልና ቁጥጥር እየተባለ ‹‹የሚታደኑበት ምክንያት የለም›› ብለዋል፡፡ ለዚህም ተቆጣጣሪ አካላት ተሰጥቷቸው የነበረው ኃላፊነት ከዚህ መመርያ በኋላ መነሳቱን ተናግረዋል፡፡

‹‹በጣም የሚያሳዝነው የባለፈው መመርያ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ በቁጥጥር ስም የሲሚንቶ አዳኙ ብዙ ነው ሆነው፤›› ሲሉ አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡ እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ ከዚህ በኋላ ቁጥጥር የሚኖረው መንገድ ላይ የሲሚንቶ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ሳይሆን በደረሰኝና በዋጋው እየተሸጠ መሆን አለመሆኑን በመሸጫ መጋዘን ውስጥ መቆጣጠር ብቻ ነው፡፡ ‹‹ይህ ምርት ከዚህ በኋላ በነፃ ይንቀሳቀሳል›› ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡

የክልልና የከተማ መስተዳደሮች ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉና የሚቸረችሩ የመንግሥትና የማኅበር ድርጅቶችን ከዚህ በፊት ይመርጡ የነበረ ሲሆን፣ እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ ይህ ተግባር ከዚህ መመርያ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ አምራች ፋብሪካዎች በራሳቸው አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን መምረጥ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ሲሚንቶን ‹‹ነፃነቱ የተጠበቀ ሸቀጥ›› ሆኗል በማለት በነፃነት ከማምረቻው እስከ ፋብሪካዎች መሄድ እንደሚችል አቶ በልሁ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሚያሳልጥና ቀልጣፋ ይሆንልናል ያሉትን ነገሮች ፋብሪካዎች ይመርጣሉ›› በማለት አክለዋል፡፡

በተጨማሪም ከተከለከሉ ተግባራት ውስጥ የሲሚንቶ ተሽከርካሪዎችን ከፋብሪካ ያለ መዳረሻ ሰነድ ማስወጣት ሲሆን፣ መዳረሻቸውን የሚያሳውቅ ሰነድ አዘጋጅተው ፋብሪካዎች መሸኘት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዙሪያም ከፋብሪካዎች ጋር በመነጋገር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡

በሲሚንቶ ሥርጭትና ግብይት ላይ የመንግሥት ድርሻ ሰፊ እንደበረና ከዚህ በኋላ ግን፣ ‹‹በረባ ባልረባ ውስጥ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ይቆማል›› ሲሉ አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የመንግሥት ድርሻ ሊሆን የሚችለው የሲሚንቶ ሽያጩ በደረሰኝ መሆን አለመሆኑን መቆጣጠር፣ እንዲሁም አጠቃላይ የበላይ ክትትልና ቁጥጥር ብቻ ይሆናል፡፡

ሆኖም ግን መንግሥት የሲሚንቶ የፋብሪካ ዋጋን አሁንም ‹‹ለተወሰነ ጊዜ›› በየስድስት ወር እያወጣ የሚቀጥል ሲሆን፣ ባለፈው መስከረም ወር አውጥቶት የነበረውን ዋጋ አሁን በድጋሚ ከልሶታል፡፡ ይህም ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆየውና እንዳዲስ የተከለሰው ዋጋ ፋብሪካዎች ሲሸጡበት ከነበረው የተወሰነ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

ለ11 ፋብሪካዎች ከተደረገው ጭማሪ በአማካይ በፊት ከነበረበት በኩንታል ከ590 ብር ወደ 758 ብር ከፍ ብሏል፡፡ ባለፈው አምስት ወራት ከተመረተው 18.7 ሚሊዮን ኩንታል ሲሚንቶ ውስጥ 10.2 ሚሊዮኑን ያመረተው ዳንጎቴ ሲሚንቶ፣ ከመስከረም ወር ጀምሮ ሲሸጥበት ከነበረው በኩንታል 549.49 ብር አሁን በኩንታል 795.93 ብር እንዲሸጥ ተወስኖለታል፡፡ ፋብሪካው ግን የጠየቀው በኩንታል 811 ብር እንዲሸጥ ነበር፡፡ ሌሎችም አብዛኞቹ ፋብሪካዎች ለመሸጥ ከጠየቁበት ዋጋ አነስ ባለ ነው መንግሥት ለቀጣይ ስድስት ወራት እንዲሸጡ የፈቀደላቸው፡፡(ሪፖርተር)

https://t.me/ethioengineers1
👍21🔥1🙏1
🏗በአንድ ወቅት የነበረን የተገነባ የመንገድ ደረጃ መነሻ(መሠረት ) በማድረግ በመንገዱ ግራ ቀኝ አዋሳኝ በሆነ ይዞታ ላይ ተገቢዉን ርቀት በመጠበቅ ንብረትን ያፈራ ሰው በሌላ ጊዜ የመንገድ ደረጀ ከፍ እንዲል በመደረጉ የተነሣ በአዋሳኝ ይዞታው ላይ ግለሰቡ ያፈራቸው ንብረቶች ላይ ጉደት የደረሰ እንደሆነ ጉደት ያደረሰው ወገን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት (የሚኖርበት )ስለመሆኑ ሰበር አዋጅ ቁ.65/1936 አንቀጽ 2(ሀ) አዋጅ ቁ.66/1936 አንቀጽ 1(ለ) አዋጅ ቁ.455/1997 ,የኤ.ፌዲረ ህገ መንግሥት አንቀጽ 40(8) በመጥቀስ በቅፅ 14 ሰ/መ/ቁ 75343 ትርጉም ተሰጥቷል
👍15
How to select steel for building construction?

1-check Diameter & grade of steel-
So first of all you have to check the diameter of the steel and also the grade of steel we have different grades of steel 40,60, and 75 .so must check the diameter and grade of the steel before buying.

2. Check the weight of the steel-
Here is an example to check the weight of steel. if we have an 8 mm diameter steel bar and a length is 12 meters so the weight of the steel-
FORMULA TO CALCULATE WEIGHT OF STEEL = D²L/162
given data

D = 8 mm, L = 12 meter

So the weight of steel = ( 8 x 8 x 12)/162

weight of steel  = 4.74 kg
3. Check for rust and loose Coating-
if you wanna purchase you have to check for rust and lose coating .it should not be rust and it should not be loose if there is loose coating in steel don't for building construction.

4. Check for cracks-
If we bend the steel 180 degrees so the surface the of steel is the top surface of the steel should not be white and it should not be developed any cracks. it's very important so don't you this steel

5. Never store steel on the ground-
sometimes we placed steel on the ground that steel should rust and rusted steel should not be used in building construction otherwise it will make more problems and rust can weaken the strength of the steel remember these points. if you wanna store steel on the ground so it should be up from the ground mini 4 inches .
So these are some important tips before purchasing steel.
👍27❤1
የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል ተባለ

የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎት እንዲጣጣም ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት እንደሚገባቸው ተገለጸ::

የሲሚንቶ አምራቾች ማህበርና የሲሚንቶ አምራቾች ባለቤቶች ማህበር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷በተለያዩ የፀጥታ ችግሮችና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ምርት ያቆሙና በሙሉ አቅማቸው የማያመርቱ ፋብሪካዎች መኖራቸውን ገልጸዋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታም መፋጠን እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ምርት አቁሞ የነበረው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ በመግለጫው ተነስቷል::

ፋብሪካው በቅርቡ ስራ እንዲጀምር ለማድረግም አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንደሚላኩ ተመላክቷል፡፡

የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት ማቆሙ ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነው የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት እንዲቀንስ አድርጎት እንደነበረም ነው የተገለጸው ።

ቸርቻሪዎችም የሚሸጡበትን የሲሚንቶ ዋጋ የመለጠፍ ግዴታ እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው::


(FBC)
https://t.me/ethioengineers1
👍5
🏗ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማረችሁ ባለሙያዎች ያለን ጥቆማ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር ያዘጋጀነውን online package ተጠቃሚ በመሆን❗️

🏗በአካል መምጣት እና መማር ለምትችሉ
👉Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614

📞0911890392/ 0944186744

Join 🔸 @BeGetEngineering
❤7👍6
👉የአርማታ ብረት ላይ የሚታዩ ችግሮች /ILLNESS IN REINFORCEMENT CONCRETE/

➡️1. ዝገት/Corrosion in reinforcement bar/

When the rebar is exposed to outer environment other than concrete it will rust /corrode As you guys know know reinforcement counters tension as a result of corrosion the tension member fails it’s causes tension failure

*⃣የፌሮ መዛግ - ፎሮ ከ አርማታ እቅፍ በወጣ ጊዜ ዝገት ያስከትላል ለምሳሌ አፈር ላይ ረዥም ጊዜ ከተኛ ይዝጋል ወይም ደግሞ ለረዥም ግዜ coloride ያለበት ወይም ጨዋማ ውሀ ከነካው ይሄም tension failure /ውጥረትን መቋቋም የማይችል ባለፌሮ አርማታ መዋቅር(RC structure)  ይሆናል።


➡️2.  Carbonation of concrete
 
Is the chemical reaction between carbon dioxide in the air and calcium hydroxide and hydrated calcium silicate in the concrete to give mainly carbonates. This slowly changes the PH of concrete.

*⃣Carbonation - አርማታችን  በከባቢያችን(አየር)  ካሉ “ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ” ፣ “ካልሲየም ሀይድሮ ኦክሳይድ” እና “ሀይድሬትድ ካልሲየም ሲልኬት” ጋር በመዋሀድ ወደ ካርቦኔት ይቀይረዋል ይኼም PH value alter እንዲያረግ ያረጋል፡፡


➡️3. Sanding

Unreasonable sand grading, high mud content too fine soil and sand will also cause the ground sand, affecting the early hydration of cement and concrete condensation. construction vibration is too large: this will aggravate the concrete surface bleeding, thereby reducing the surface strength of concrete. 

*⃣አርማታችን - ከተፈለገው በላይ ነጭ የመሆን(“አመዳም”) የመሆን ነገር ይሄም የሚሆነው   አርማታ በሚቦካበት ጊዜ ያልተፈለጉ ብናኞች ሲዋሀዱ ነው፤ በ አርማታ ውህደት ጊዜ በውሀ እና በሲሚንቶ መሀል ያለው ውህደት temperature ከፍ እንዲል ያደርጋል ይሄም hydration ይባላል ወይም ደግሞ (concrete maturity) ብዙ ብናኞች በገቡ ጊዜ  አርማታችን ቶሎ ይረጋል ከወትሮ ቀደም ብሎ ይሄም የ አርማታው ጥንካሬ (compressive strength) ላይ በ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

➡️4.  Cracks in concrete

the deformation of concrete it might be due to ratio or quality of Material

*⃣የ አርማታ መሰንጠቅ - ይሄም የሚሆነው አርማታ ስናቦካ የምንፈልገውን compressive strength(fck) ለማግኘት በratio ነው ወይም በመስፈር በዚን ጊዜ የ አሰፋፈር ችግር ካለ in the long run ስንጥቃት ይኖራል ሌላው ደግሞ የ ግብዓት ጥራት ለምሳሌ ደለላማ አሸዋ ከተጠቀምን ስንጥቃት ይበዛዋል ፡፡


➡️5. Concrete segregation

one of the defects of concrete it’s the separation of cement paste and aggregates of concrete from each other during handling and placement.

Via zion

https://t.me/ethioengineers1
👍21
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!
https://t.me/BeGetEngineering
🙏6👍1