https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍19❤4
1. የፕሮጀክት እቅድ ማውጣት፡ MS ፕሮጀክት የግንባታ ፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ዝርዝር የፕሮጀክት እቅዶችን ከተግባራት፣ ከችግሮች እና ከጥገኛዎች ጋር እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።
ይህም የእንቅስቃሴዎችን ቅደም ተከተል በመለየት እና ሀብቶችን በአግባቡ ለመመደብ ይረዳል.
2. መርሐግብር ማውጣት፡- የግንባታ ፕሮጀክቶች በተወሰነ ቅደም ተከተል መጠናቀቅ ያለባቸውን በርካታ ሥራዎችን ያካትታሉ።
MS ፕሮጄክት ዝርዝር መርሃ ግብር ለመፍጠር ፣ ለተግባራት ቀናትን ለመመደብ እና ሁሉም ነገር በጊዜው መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ይረዳል።
3. የሀብት አስተዳደር፡- የግንባታ ፕሮጀክቶች የተለያዩ ግብዓቶችን ማለትም ቁሳቁስ፣መሳሪያ እና ጉልበት ይፈልጋሉ። ኤምኤስ ፕሮጄክት የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ሃብቶችን ለተግባራት እንዲመድቡ፣ መኖራቸውን እንዲከታተሉ እና ከመጠን በላይ ወይም ከጥቅም ውጪ እንዳይሆኑ ያስችላቸዋል።
4. የሂደት ክትትል፡ MS Project የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች የፕሮጀክቱን ሂደት በቅጽበት እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።
ይህ የተጠናቀቁ ተግባራትን መከታተል, መዘግየቶችን መለየት እና የጊዜ ሰሌዳውን እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከልን ያካትታል.
5. ትብብር፡ MS ፕሮጀክት የፕሮጀክት ቡድኖች ሰነዶችን በመጋራት፣ ተግባራትን በማዘመን እና በእውነተኛ ጊዜ በመገናኘት በፕሮጀክት እቅድ እና መርሃ ግብር ላይ እንዲተባበሩ ያስችላቸዋል።
በአጠቃላይ የኤምኤስ ፕሮጄክት ሶፍትዌር የፕሮጀክት አስተዳደር ሂደቶችን በማሳለጥ፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና የግንባታ ፕሮጀክቶችን በወቅቱ እና በበጀት ውስጥ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍24❤2
ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ ፈጣን የሆነ የህዝብ ቁጥር ዕድገት በሚታይባቸው ሀገራት ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ወይም አፓርትመንት እጥረት እየተከሰተ ነው፡፡
የሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት ለኑሮ አመቺ በሆነ ቦታ እና ተገቢ በሆነ ወጪ ማግኘት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡
ይህንን እጥረት እና ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስችሉ የግንባታ ዘዴዎች ውስጥ ቀደም ብለው በተለያዩ ሳይቶች የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት የወለል ምንጣፎች፣ ግርግዳዎች እና ቋሚ ማዕዘኖች "ፕሪካስት ኮንክሪቶች" ትኩረት ከሚሹ የግንባታ ዘዴዎች መካል በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡
በፕሪካስት ቴክኖሎጂ በፋብሪካ ውስጥ እየተመረቱ በሰለጠነ መንገድ የሚገጣጠሙ የሕንፃ ቁሳቁሶች፣ የመኖሪያ ቤትን ዕጥረትን በፍጥነት ለመቅረፍ ከሚያስገኙት ተጨማሪ ጠቀሜታዎች እና የአመራረት ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
ለሕንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ ተገጣጣሚ ኮንክሪቶች የሚዘጋጁት ለቁጥጥር አመቺ በሆኑ ገላጣ ቦታዎችና መጠኑ ባልተዛባ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ውኃ በመሳሰሉ የግንባታ ቁሳቁሶች በመሆኑ አላስፈላጊ ብክነት ወይም ዕጥረትን በማስወገድ ወጪን ይቀንሳሉ፡፡
ኮንክሪቶቹ የሚዘጋጁት ከሰው ፍላጎት እና ተጽዕኖ በጸዳ፣ በፕሮግራም በሚታዘዝ (አውቶማቲክ) የማምረት ዘዴ በመሆኑ የተፈለገውን ምርት በተፈለገው ፍጥነት በማምረት የጊዜ ብክነትን ያስወግዳሉ፡፡
በተለመደው የሕንፃ ግንባታ ዘዴ በግንባታ ሳይት ላይ የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ዲዛይኖችን ለመስራት የሚያስፈልጉ ውስብስብ የእንጨት እና የብረት ድጋፎችን በማስወገድ ለሚፈለገው ቅርፅ ሞልድ (ቅርፅ) ማውጫ በማዘጋጀት የተፈለገውን ዲዛይን በፍጥነት ለማምረት የባለሙያን ወጪን ይቀንሳል፡፡
አንድ የፕሪካስት ማምረቻ ድርጅት ወደ ማምረት ሂደት የሚገባው አንድ አስገንቢ ድርጅት ለሚሠራው ሕንፃ የሚያስፈልገውን የተገጣጠመ ኮንክሪት መጠን እና ዲዛይን መነሻ በማድረግ ቀደም ያለ የውል ስምምነት በመፈረም ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ አምራች ድርጅቱ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የማያቋርጥ አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርለት ያደርጋል፡፡
በፕሪካስት የሚገነቡ ሕንፃዎች ትርፍ የሆነ ሙቀትን በማመቅ በዝግታ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ እንዲወገድ በማድረግ፣ በሕንፃ ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ክብደት ወይም ጭነት በማስወገድ፣ በተለመደው መንገድ ሳይት ላይ ከሚገነቡ ሕንፃዎች ከ50 በመቶ የበለጠ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳሉ፡፡
ይህን ብቃት እንዲላበሱ ከሚያደርጋቸው ውስጥ ለምሳሌ፣ የተለያዩ ፎቅ ባላቸው ሕንፃዎች ለወለል የሚዘጋጁ ውስጣቸው ክፍት በሆነ ብሎኬት እና ኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት ምንጣፎች ከተለመደው ግንባታ ከ50 እስከ 60 በመቶ ክብደታቸው የቀነሰ ከመሆኑም በላይ ጥራታቸው በተጠበቀ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት እና የመሳሰሉት የግንባታ ቁሶች የሚዘጋጁ ናቸው፡፡
ከዚሁ በተጨማሪ፣ እንደየአስፈላነቱ ግንባታው በሚካሄድበት ቦታ ያለውን የከባቢ አየር ድምጽ መስተጋባት፣ የመሬት ርደት ወዘተን መነሻ አድርገው ስለሚመረቱ አላስፈላጊ የሆነ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን በመቀነስ የበለጠ ዕድሜ እና ጥንካሬን እንዲኖራቸው የሚያደርግ ብቃት የተላበሱ ያደርጋቸዋል፡፡
በፕሪካስት ኮንክሪት የሚገነቡ ሕንፃዎች ከሚያስፈልጋቸው ቁሳቁሶች ውስጥ በብረት እና በኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ ወለሎች፣ በአራት መዐዘን እና በተፈለገው ቅርጽ የሚዘጋጁ ጠፍጣፋ የኮንክሪት ወለሎች ተገጣጣሚ ግድግዳዎች፣ የቋሚ እና የአግድም መዐዘን የኮንክሪት ፍሬሞች ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ ተገጣጣሚ የግንባታ ቁሳቁሶች የሚዘጋጁት በተወሰነ ሳይት ላይ ሆኖ፣ በቀላሉ ሊገጣጠሙ በሚችሉ እና ለማጓጓዝ አመቺ በሆነ መጠን እና ዲዛይን ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ሳይት ላይ ጥሬ ቁሶችን በማቅረብ እና በተለመደው መንገድ ለመገንባት የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ ማጓጓዣ፣ በኮንክሪት ሙሌት የሚወጣ የጉልበት እና የመሳሪያ አቅርቦት ወጪን ይቀንሳሉ፡፡ ክፍት የሆኑት የኮንክሪት ምንጣፎች እስከ 20 ሜትር የሚረዝም ቁመና የተላበሱ በመሆናቸው በተለመደው መንገድ ከ6 እስከ 10 ሜትር ብቻ በሚረዝም ፓሌት (የብረት ማዕዘን) እየተገጣጠመ የሚሞላ የኮንክሪት መዐዘን ለማዘጋጀት የሚያስፈልግ የጉልበትና የግንባታን ወጪን በመቀነስ ግንባታው በፍጥነት እንዲከናወን በማድረግ ያላቸውን ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍21❤5🔥1
#በአዲስ_አበባ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ‼️
በመዲናይቱ አዲስ አበባ፣ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12፣ ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለው ቦታ የመኖሪያ ህንጻ ተደርምሶ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።
የመንግስት መገናኛ ብዙሃ የወረዳውን ስራ አስፈፃሚ አይዳ አወልን ጠቅሶ እንደዘገበው አደጋው የተከሰተው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው፡፡ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 5 ሰአት ላይ ነው።
ዜናው ስለ ተጎጂዎች፣ ስለ አደጋው መንስኤ እና ሌሎች ጉዳቶች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭22👍10❤5
ይባስ ብላ ለአቶ ታረቀኝ የሸጠችውን ይዞታ በስሟ ካርታና ፕላን አሰርታ ከይዞታዋ ጋር ትቀላቅለዋለች፡፡ ይሄን ጊዜ አቶ ታረቀኝ ይዞታውን የገዛሁበትን ብር 500 ሺ እና መኖሪያ ቤቱን ለማሰራት ያወጣሁትን ወጪ ብር 700 ሺ #በድምሩ ብር አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ ብር ወ/ሮ ህሊና እንድትከፍለኝ በማለት ክሳቸውን ለፍ/ቤት አቅርበዋል፡፡
❗ #ጥያቄ
አቶ ታረቀኝ ይዞታውን የገዙበት ብር 500 ሺ እና ለመኖሪያ ቤቱ ግንባታ ያወጡትን ወጪ ብር 700 ሺ ፤ እንድትከፍል ፍ/ቤቱ ወ/ሮ ህሊናን ያስገድድ ይሆን❓
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍35🤔11❤5
SMH General Construction
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 /3/ መሰረት ‹‹የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነዉ፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው በማለት ደንግጓታል፡፡ ይህን ድንጋጌ ተግባራዊ ለማድረግ ከወጡት ዝርዝር ሕጎች መካከል የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝን እንደገና ለመደንገግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 272/1994 እና ይህን አዋጅ የሻረ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡ እነዚህ እና ሌሎች ዝርዝር ሕጎችን ማየት እንደሚቻለዉ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት በሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት ተከትሎ ስልጣን ያለዉን አካል ጠይቆ ከማግኘት ዉጭ በሽያጭ ገዝቶ መያዝ እንደማይቻል ያስገነዝባሉ፡፡ የከተማ ቦታ በሽያጭ ዉል ተሽጦ ከሆነ ዉሉ ሕገ መንግስቱንም ሆነ ዝርዝር ሕጎቹን የሚጥስ ስለሆነ ሕገ ወጥና ፈራሽ ዉል ነዉ፡፡
በዚህ መሰረት አቶ ታረቀኝ ባዶ ቦታ ከወ/ሮ ህሊና በውል ገዝቶ ቤት የሰራ መሆኑ ይህ ዉል ሕገ ወጥ እና ፈረሽ ዉል ነዉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ግራ ቀኛቸዉ ወደ ነበሩበት ሊመለሱ ይገባል፡፡ በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1815 ማየት ይቻላል፡፡ ግራ ቀኛቸዉ ወደ ነበሩበት ሊመለሱ ይገባል ሲባል ግን የባለይዞታነት መብት ያለዉን ሰዉ/አካል ላይ እዳ በመጫን መሬቱን ሊያጣዉ የሚችል የገንዘብ ክፍያ ሊጣልበት አይገባም፡፡
በመሆኑም ይህ ዉል ሕገ ወጥ በመሆኑ እስከፈረሰ ድረስ ወ/ሮ ህሊና ለአቶ ታረቀኝ ልትከፍለዉ የሚገባት ብር 500 ሺ ብቻ ነው፡፡ አቶ ታረቀኝ በሕገ ወጥ ዉል በያዘዉ ቦታ ላይ የሰራዉን ቤት ለማሰራት ያወጣዉን ወጪ ወ/ሮ ህሊና የምትከፍልበት የሕግ አግባብ የለም፡፡ ስለሆነም አቶ ታረቀኝ በወ/ሮ ህሊና ቦታ ላይ የሰራዉን ቤት በራሱ ወጪ በማፍረስ ቦታዉን ለወ/ሮ ህሊና ለማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
በአጭሩ አቶ ታረቀኝ በራሱ ወጪ ቤቱን ከወ/ሮ ህሊና ቦታ ላይ አፍርሶ በማንሳት ቦታዉን ለወ/ሮ ህሊና ሊለቅ ይገባል፡፡ አቶ ታረቀኝ ቤቱን ለመስራት ያወጣዉን ወጪ ወ/ሮ ህሊና ለመክፈል አትገደድም ፡፡
ይህ ኬዝ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው:: ሙሉ የታሪኩን ይዘት ለመረዳት የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መስከረም 26 ቀን 2010 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 128650 (ቅፅ 22) የሰጠውን የሕግ ትርጉም ይመልከቱ፡፡
ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍25❤13😭4😍1
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፥ በከተማው በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ዘንድሮ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነተ ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?
- “ ከተማው ውስጥ ብዙ የግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ። በተለይ አሁን ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት በኮንክትራክሽን / በግንባታ ዘርፉ ያሉ የቀን ሠራተኞች ናቸው። ”
- “ የቀን ሠራተኞች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ብዙ ጊዜ ጉልበታቸውን ነው ይዘው የሚገቡት፤ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ቴክኒካል እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የላቸውም። እንዴት የሥራ ላይ አደጋን መከላከል እንደሚችሉ ስለጠና እንኳ አይሰጥም። ”
- “ ' #የቀን_ሠራተኞች_እንፈልጋለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችን የኮንስትራክሽን ሳይቶች ላይ እናያለን። በዚያው ሥራ ያጣ መንገደኛ ይገባል ግን ሥራውን ለመከናውን ምን ሊያጋጥም ይችላል ? ብሎ አስቀድሞ የመገመት እውቀት አይኖርም። ”
- “ ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች ላይ ትልቁ ኃላፊነት ይወድቃል። እነርሱ ደግሞ በሚፈለገው ደረጃ ለዘርፉ ትኩረት እየሰጡ አይደለም። አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ #ቦታው_ላይ_አይገኙም። ”
- “ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የደህንነት መርሆዎችን ያለመከተል ሁኔታ አለ። ”
Q. መፍትሄውን ምንድነው ?
- “ መፍትሄውማ ፈቃድ ሰጪው አካልም ፈቃድ ከሰጠ በኋላ በየጊዜው ጠብቅ ቁጥጥር በማድረግ ለአደጋ የተጋለጡ አሰራሮችን እየለዩ በህንጻ አዋጁ መሠረት እርምጃዎችን ቶሎ ቶሎ መውሰድ ያስፈልጋል። ”
ሰሞኑን የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የድንጋይ እና አፈር ናዳ አደጋ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች ላይ ባለመድረሱ ለየት ያለ ቢሆንም ይህንኑ አደጋ ጨምሮ በ2016 ዓ/ም እስካሁን 12 ሰዎች በተለያዩ ጊዜዎችና አደጋዎች ሞተዋል።
የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጨምሯል።
TikvahEthiopiaFamilyAA
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍36❤1
ይህ ሆቴል ከአለማችን ሠማይ ጠቀስ ሆቴሎችም በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ይሁን እንጂ፣ ከዚህ ረጅም ሕንፃ ውስጥ 39 ከመቶ የሚሆነው የሕንፃው አናት ክፍል ጥቅም አልባ (non occupied) ሲሆን፣ ሕንፃውን ለመገንባት 7.6 ቢሊየን ዳላር ወጪ ተደርጓል።
ቡርጂ አል አረብ፣ ያረፈው በሰው ሰራሽ ደሴት ላይ ከመሆኑም በላይ፣ ሕንፃው ከመሬት ጋር የሚገናኘው በድልድይ ነው።
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍19❤1😍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏗ወስን ተጠግቶ ለሚገነባ ግንባታ አዋሳኙ ባለመብት በአዋሰኝ በኩል ያለዉን የህንፃ ገፅ ለመስራት የመከልከል መብት አለው ወይስ የለዉም ?
#መልሱን_ቀጠይ_እመለስበታለሁ ❗️
🏗 ሳይት ላይ ያጋጠማችሁን ማገራት ለምትፈልጉ @Ethiocon143bot
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤20👍5👏2
SMH General Construction
💥ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/ 1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate) • ከ 20% እስከ 30% ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሥራ ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ • ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡ • አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤…
✨በውል ላይ ካልተቀመጠ advance መከፈል ግዴታ አይደለም
ነገር ግን FIDIC አንቀጽ 14.2 ላይ Advance ለስራ ተቋራጭ የሚከፈል ከወለድ ነፃ የሆነ ብድር መሆኑን ይገልፃል::
ይህም ማለት ተቋራጭ advance ካልተከፈለው በራሱ ገንዘብ ስርቶ payment ሲጠይቅ ግን ወለዱን የመጠየቅ መብት ይኖረዋል::
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍15❤9
1- Rebars must cross like the fingers of a hand.
2- Put an additional rebar around the outer corner.
3- Extend hooked bars from the inside to the outside.
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍21
በዚህ ዘመን ኮንስትራክሽን ማለት ይበልጡኑ ቴክኖሎጂ እና ማሽነሪ ነው። ከዚያም አመራርም አለ። በመሆኑም፣ ጥራት ያለው ግንባታን በተያዘለት ጊዜና በጀት ጨርሶ ለማስረከብ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ወሳኝ ናቸው።
ከታች በፎቶ የተቀመጠው የእግረኛ መንገዶችና የሕዝብ መሰብሰቢያ ግልጽ ቦታዎች ላይ ግንባታ ለማከናወን ጠቃሚነቱ ወደር የለውም።
ይህ ማሽን ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ባለሀብት ቢጠፋ እንኳ፣ ማሽኑን መንግሥት ቢያስመጣው በተለይ ለኮሪደር ልማትና ተያያዥ የፕሮጀክቶች ሥራዎችን በፍጥነት ለመጨረስ ተኪ የሚገኝለት አይደለም።
https://t.me/ethioengineers1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍33❤2😍2