SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ
የሃይድሮሊክስ/ሲቪል ኢንጅንየር ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ
ነጥቦች @civil_Cotm_eng
.
1 የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING
MATERIALS)
አንድ ጥሩ ኢንጂንየር በሳይት ላይ የሚሰሩ የግንባታ እቃዎችን
ለመፈተሽ የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ
ይጠበቅበታል። ከታች የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች
ተጠቅሰዋል
የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test): Slump test,
compression test(cubic or cylindrical test),
split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test): Core cutter test,
compaction
test,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test: Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ
አንማር ይሆናል ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ
ለመቅረብ የግድ መማር ማወቅ አለብን ዩቲዩብ
( YouTube.com ) ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉ ቁም
ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማዬ ነው )
.
2 የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና ርጉእነት (settlement and stability )
የምንገነባው አካል ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን። እንደ
ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ በሳይት ላይ
የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው ። አሪፍ
ኢንጂንየር ለመባል
3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ
(USES OF SURVEYING
INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል
ስቴሽን እና ቴዎዶላይት አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅንየር የግድ
ማወቅ አለበት። የግድ !
4 4. የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD
CODES USED IN
CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካምድራቸው የአየር
የንፋስ የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር
የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ (Construction codes)
አላቸው። አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን
ስታንዳርድ ኮድ የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው
ቁስ ሃገሪቱ ባላት ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና
እንዳይወድም። እነዚህን ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል
የሚገነባ የትኛውም ግንባታ የመፍረስ አቅሙ በእጥፍ የጨመረ
ነው።
5 BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት
(በተለይ ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት
ሬንፎርስድ የሆነው የግንባታ አካል ማለትም ቢም ኮለን ስላብ
ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን
ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና ምን ያክል ተመሳሳይ
እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል ውስጥ እንደሚኖሩ
በግልፅ ይነግረናል ። ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም
እና የስትራክቸሩን ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ
ይጠቅመናል
6 የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND
DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጂንየር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ዲዛይን እና ንድፎችን
በትክክል ማንበብ እና መተርጎም ከቻለ ለሳይት ኢንጂንየርነት
የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል ማለት ነው። ስለዚህ
በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው
7 ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው። (እንዴት መገመት
እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)
8 የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)
ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው። ጥራቱን
የጠበቀ ግንባታ ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን
ነው። አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩ ኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ
የግንባታ መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት
ጉዳቶች እንዳደረሰ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። አንድ ሳይት
ኢንጂንየር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት የማወቅ ግዴታ
አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን አደጋ
ለመከላከል።
9 የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD
MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣
ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች
ማወቅ ግዴታችን ነው
10 ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION WITH
LABOR)
የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ እና ያልተማሩ
ሰራተኞችን እንዴት ማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ ሊኖረን
ይገባል። ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ወርዶ መስራትም
ይጠበቅብናል። ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር
መስራት ወሳኝ እና ወሳኝ ነገር ነው።
.
.
አንድ ጥሩ የሚባል እንጅነር ማወቅ ስለሚገባው ነገሮች በቂ
የሆነ እውቀት እንደሰጠኋቹ ተስፋ አረጋለው። እንኳን ወደ ቻናላችን መጡ አሪፍ ትምህርት እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነን ሼር በማድረግ ይተባበሩን @civil_Cotm_eng
👍2
ድፍርስ ውሃን እንዴት በባህላዊ መንገድ ማጣራት እንችላለን ? @civil_Cotm_eng
.
የንፁ ውሃ አቅርቦት በሃገር ደራጃ 20% እንኳ በቅጡ ያልሞላን ፤ ከፊታችን ትልቅ የቤት ስራ የሚጠብቀን ፤ አሁን ከምንኖርበት በ20Km ራዲየስ ውስጥ ዛሬም እንኳን ሰው ከብት ሊጠጣው የማይገባውን ውሃ አገልግሎት ላይ የሚውል ... በቂ የከርሰ ምድርም ሆነ የላእላይ ምድር ውሃ ባለቤት ሆነን ግና የውሃ ፍላጎታችን ማሟላት ያልቻልን ምስኪን ህዝቦች ነን ።
.
ይህን ተንተርሰን መንግስት ላይም ሆነ የሚመለከተው አካል ላይ እጃችንን መቀሰር የፖለቲከኞች ስራ እንጂ የኛ ኢንጅነሮች ስራ አይደለም። እኛ ያለንን ሃብት እንዴት መጠቀም እንደምንችል መላዎችን መፍጠር እና በሌሎች ሃገራት ያሉ ቀላል ተሞክሮዎችን ወደ ሃገር ማምጣት ነው።
.
በዚህ ፅሁፍ በሜክሲኮ ገጠራማ አካባቢዎች የቁልቋል (Cactus ) ተክልን ተጠቅመው ድፍርስ ውሃን እንዴት እንደሚያጠሩ እናያለን። ይህ ዘዴ የደፈረሰን ውሃ እስከ 95% እንዲሁም ውሃው በባክቴርያ የተበከለ ከሆነ ባክቴርያውን እስከ 89% የማጥራት አቅም እንዳለው ተረጋግጧል።
.
- መጀመርያ የቁልቋል ተክልን እንቆርጥ እና ላዩ ላይ የሚገኙ እሾ ነገሮችን እናራግፍና በውሃ እናጥበዋለን

- ቁልቋሉን ለሁለት ሰንጥቀን በፀሐይ እንዲደርቅ እናሰጣዋለን

- የተሰጣው ቁልቋል በቂ ፀሐይ አጊኝቶ እንደደረቀ በመቆጫ ወይም በሌላ መፍጫ እንፈጨዋለን

- የተፈጨውን ቁልቋል ባጠራቀምነው የደፈረሰ ውሃ እንጨምራለን (ማጠራቀሚያው ባልዲ ቢሆን ይመረጣል )
- ለ አስራምስት ደቂቃ ያክል እናማስላለን
ከተማሰለ በኋላ እንዲሰክን ከ30 እስከ 45 ደቂቃ እንተወዋለን።

- ውሃው ከሰከነ በኋላ ከላይ እያጠለሉ መጠጣት ወይም ከላይ አጥልሎ ንፁሁን ውሃ በሌላ ማስቀመጫ መገልበጥ እና ለአገልግሎት መጠቀም ።
. @civil_Cotm_eng
የውሃ ችግር ባለባቸው አከባቢዎች የምትገኙ ይህን ዘዴ እንድታስተዋውቁ እንመክራለን ።
👍1
የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir) @civil_Cotm_eng
.
የውሃ ጋኖች #ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ 
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።

ትምህርት እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነን ሼር በማድረግ ይተባበሩን @civil_Cotm_eng
Weir( የዊር) ዋና አገልግሎት ውሀውን @civil_Cotm_eng
በምንፈልገው ጥልቀት በመገደብ በላይኛው ተፋሰስ
(Upstream side) ውሀው እንዲከማች ማድረግ ነው፡፡
ቀሪውም ውሀ በዊሩ አናት ላይ ወይም በር/ Gate በማዘጋጀት
እንዲፈስ እናደርገዋለን፡፡
# የዊር ጥቅም
1. Flood Control - የምንፈልገውን ያህል ጥልቀት ውሃውን
ስለምንገድበው በታችኛው ተፋሰስ/ Downstream ጎርፍ
ይቀንሳል፡፡
2. Flow Measurement - የዊሩ ዳይሜንሽን ስለሚታወቅ
የወንዙን Discharge በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡፡ ((( Q=
CLH^n )))
3. የተጠራቀመውን ውሀ divert በማድረግ ለእርሻና ለተለያዩ
አገልግሎቶች መጠቀም እንችላለን፡፡
4. ወንዙ ለውሃ ላይ ትራንስፖርት አመቺ እንዲሆን ያደርጋል ፣
የተለያዩ የሚሰደዱ የአሳ ዝርያዎችን እንዳያልፉ ይገድባል
ወዘተ..
# የዊር ጉዳት
1. የወንዙን ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ይቀይረዋል
2. Siltation
3. አሳዎቹ የመንቀሳቀስ መብታቸውን ይገድባል ... Fish
Ladder ሊያስፈልግ ይችላል፡፡
4. ዊሩ አካባቢ ውሃው የተረጋጋ ቢመስልም ለዋና/
ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ቦታ ነው ሀይድሮሊክ ጃምፕም ይኖራል
#የዊር አይነቶች
Polynomial, V - notch, Broad Crested, Compound,
Gated/ Ungated, etc.
Polynomial - የዊሩ ቅርፅ በፓሊኖሚያል equation
ስለሚሠራ ነው
V- notch : ዊሩ መሀሉ በ V ቅርፅ ተቆርጦ ወጥቷል፡፡ ይህ
በመሆኑም በኖርማል ፍሰት ጊዜ ውሃው በዛ ይፈሳል:: በቅርፁም
ምክ/ት discharge ለማግኘት ይቀለናል፡፡ Broad Crested - ጠፍጣፋ የሆነ አናት
ወይም flat crest አለው፡፡
Compound : የተለያዩ የዊር አይነቶችን አንድ

እንኳን ወደ ቻናላችን መጡ አሪፍ ትምህርት እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነን ሼር በማድረግ ይተባበሩን @civil_Cotm_eng
❤1
👉CONSTRUCTION ENGINEERING TIPS @civil_Cotm_eng
.
*ASTM Abbrevation : American Society for Testing Materials
*Grade of Concrete is denoted as Cement: Sand: Aggregate (Ex C-20 Grade : 1:2:3)
*C/C means Center to Center Distance
*DL means Development Length
*Lapping of bars not allowed if the dia of bar is more than 36mm.
*For circular column minimum of 6 longitudinal bars are used and 4 for Rectangular.
*The minimum thickness of slab is 0.125m
*Water pH value less than 6 should not be used for construction purpose.
*The concrete Should not be thrown from a height more than 1.5m.
*The Compressive strength of Bricks is 3.5 N /mm
*The initial setting time shall not be less than 30 minutes and the final setting time of cement is 10hours.
*Dead Load means Self weight of Structure
*Sand having moisture content more than 5% should not be used for Concrete mix.
*DPC means Damp Proof Course. The thickness of DPC should not be less than 2.5cm.
*Cube test is carried out for each 30m usage of concrete.
*RMC : Ready Mix concrete, The concrete is made at factory and transported to the site, This type of concrete is used where there is a lack of space for mixing the concrete and used where a huge amount of concrete is required for construction.
*The height of floor is usually 3m or 10ft (If a person asks you whats the height of 12 storied building?
Ans: 3m x 12floors = 36m)
*A head mason can work 25-30m in a day.
*In construction, the rate analysis for the work of workers is calculated in Man Hours. (Ex: 10 Birr for 1 Man hour)
*Cantilever Beam has One fixed support and the other end is free.
*Simple supported beam has a minimum of two supports. @civil_Cotm_eng
*PCC (Plain Cement Concrete) this type of concrete is used on members only when the tensile forces are not acting on it.
*The weight of first class clay brick should be 3.85 Kg. and it has a crushing
strength of 10.5MN/m
*Adding more water in the concrete mix to increase setting time leads to form
the Cracks or honeycomb in hardened concrete.
*Vibration in freshly made concrete is done to remove the air bubbles in concrete mix.
*Impermeability of concrete: The concrete which resists the the entry of water or moisture into it.
*The concrete can be lifted to a maximum height of 50m using Concrete
Pumps.
*The curing Period of RCC is 28days .
*The minimum sill level height should be
44 inches.
*The transverse reinforcement provided in columns are called Ties .
*The transverse reinforcement provided in
Beams is called as Stirrups .
*Stirrups in Beams and Ties in Column are provided to handle the shear force and to keep longitudinal bars in position.
*The Prime reason for using steel as reinforcement is due to thermal expansion.
The thermal expansion
coefficient of concrete and steel is (approximately) same having value
*C-25 grade of concrete is generally used in the construction of slab.
*Weight of Bar is calculated using formula D /162 (D = Dia of bar in mm)
*The No. of HCB required for 1 metr square of masonary wall are 13 HCB blocks.
*Specific gravity of Cement is 3.16g/ cm ; Bricks is 2g/cm ; Sand is 2.65g/cm ,
*Standard Size of Brick is 19cm x 9cm x 4 cm or 19cm or 9cm x 9 cm
*Floor area occupied by 50kg of Cement bag is 0.3m and height of 0.18m.
*As per EBCS Maximum dia of bar used in the slab should not exceed 1/8th of the total thickness of the slab.
*The slope or Pitch of the stair should be in between 25 degrees to 40 degrees.
*The rise in stairs is in between 150mm to 200mm.
*Tread in staircase is in between 250mm to 300mm.
*Hook length should not be less than 9D (Dia of Bar)
*Unit weight of PCC is 24KN/m , RCC is 25 KN/m , Steel is 7850Kg/m
*The volume of 50kg cement bag is
1.3CFT.
*Theodolite least count is 20Secs whereas Compass Least count is 30mins .
*TMT bars : TMT means Thermo Mechanically treated bars
*Cement more than 3 months old cannot be used for construction
*The length of each bar from factory is 12m.
.
👉ለተጨማሪ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች 🚩 እዚህ ይጫኑ
👇👇👇👇👇
@civil_Cotm_eng
😍1