SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያፈራውና አስደማሚ የግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ቪዲዮዎችን የሚሠራው ‘THE B1M’ የዩቲዩብ ገጽ እ.ኤ.አ በ2020 ከሚጠናቀቁ ግንባታዎች መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ከመጀመሪያዎቹ 20 ግዙፍ ግንባታዎች አንዱ እንደሆነ የሚያሳይ ዘገባ ሠርቷል!

Via:- Ethio construction

ሊንክ: https://www.youtube.com/watch?v=LZQsMSaeLO8&feature=youtu.be
👉ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት

.
⏩የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት ሲሆን የኮንክሪትን የመስራት አቅም (Workability) እና ፅኑእነት (Consistency) ለመለካት ይጠቅማል
.
➡ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት
ስራውስጥ መተግበር አለበት ። ስላምፕ ቴስት በትንሽ ወጪ
ምንተገብረው የኮንክሪትን Workability ምንመዝንበት ተመራጭ መፈተሻ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።
.
➡የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ነገሮች
(Factors which influence the concrete slump test)
.
1- ለ ኮንክሪቱ እንደግብአት የተጠቀምናቸው እቃዎች
ባህርይ...ለምሳሌ ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ
መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣
እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም.
.
2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠን አይነት መስተጋብር...
.
3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም
.
4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ
.
5- የኮንክሪቱ temperature
.
6- በኮንክሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውሃ መጠን
.
7- ኮንክሪቱ ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ
.
➡Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች
.
Slump ለመስራት የሚያገለግል መሃሉ ክፍት የሆነ ኮን (cone) መሰል ቅርፅ ማውጫ ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm ርዝመት 20 cm የታችኛው ዲያሜትር 10cm የላይኛው ዲያሜትር ያለው ነው (mold) መለኪያ ማስመሪያ
ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው መጠቅጠቂያ ብረት ያስፈልጉናል።
.
➡ስላምፕ ቴስትን የመከወኛ ቅደም ተከተል
.
*step-1 መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ
መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት
.
*step-2 ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር
ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን ላይ አቁመው
.
*Step 3- የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት ሙሉት
.
*Step 4- እያንዳንዱን የኮንክሪት ላየር 25 ግዜ
በመጠቅጠቂያ ብረት ምቱት (ጠቅጥቁት) የአጠቃጠቅ
ጉልበታችሁ እኩል መሆን አለበት
.
*Step 5- ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ዲያ ባለው
ጫፍ ላይ ያል ትርፍ ኮንክሪትን አስወግዱት ጫፉንም ለስኑት
.
*Step 6- ቅስ በማለት የኮንክሪት ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ከኮንክሪቱ አለያዩት
.
*Step 7- ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold)
ያለውን የርዝመት ልዩነት ለኩት
.
.
Note - እዚጋ ማሳሰብ ምፈልገው ነገር ይህን ቴስት ስታደርጉ ቦታው ከእርግብግቢት (Vibration) የፀዳ መሆን አለበት ያልተረጋጋ ቦታ ላይ ማድረግ የቴስቱን ውጤት
ያበላሸዋል...ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን
መከወን አለብን
.
.
➡ከኮንክሪት ስላምፕ ቴስት የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች
.
*True Slump - ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ብቸኛው ልኬት
ነው ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ
ቁመት ከቅርፅ ማውጫው በንፃሬ የምናገኘው ልዩነት (ምስሉን
ይመልከቱ)
.
*Zero Slump - ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃ-
ሲሚንቶ ratio ያለው መሆኑን ያሳያል ዜሮ ስላምፕ ያለው ኮንክሪት ለመንገድ ግንባታ አገልግቶት ላይ ይውላል...
.
*Collapsed Slump - ይህ ደግሞ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃ ሲሚንቶ ውህድ Ratio ትልቅ መሆን ያሳያል
ይህ ማለት የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠን ከፍተኛ መሆኑን እና
High workability mix ያሳየናል።
.
*Shear Slump- ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤት ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።


https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
❤1
👉በኮንስትራክሽን ውል ጉዳይ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate ምን ይላል?

፡✅✅✅✅✅✅✅✅✅
▶️የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ በአሰሪው በሚመደብ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና በተቋራጩ ተረጋግጦና ተማምነውበት የሚፈረም ሲሆን ለተቋራጩ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠንም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
*የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪ አባሪ ተደርጐ ይያያዛል፡፡
*ቴክ ኦፍ ሽት የአሰሪው አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና የተቋራጩ መሀንዲስ በግንባታ ቦታ በአካል የሳይት ቪዚት በማካሄድ የተሰራውን ስራ መጠን እና አይነት ከለቀሙ በኋላ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ከተመለከተው የእያንዳንዱ ስራ አይተም ዩኒት ሬት/ነጠላ ዋጋ አንጻር በዝርዝር በተናጠል በዋጋ የሚያስቀምጡበት የተሰራውን ስራ መጠን እና የገንዘብ መጠን ገላጭ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡
*ግራንድ ሳመሪ ደግሞ በዋናነት የግንባታወችን ዝርዝር/ብሎክ በማስቀመጥ የውሉን ዋጋ፣አስቀድሞ የተከናወነ ስራ መጠን፣አሁን የተከናወነ ስራ መጠን እና አጠቃላይ በተቋራጩ የተሰራውን የግንባታ ስራ መጠን ይጠቅሳል፡፡
*የክፍያ ሰርተፍኬት በአብዛኛው በአንድ ገጽ ተጠቃሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በይዘት ደረጃ ግን ብዙ መረጃወችን አምቆ የያዘ ሰነድ ነው፡፡
*የክፍያ ሰርተፍኬት በተለይ ክፍያው የመጀመሪያ ዙር፣ሁለተኛ ዙር እያለ በሚታወቅበት መንገድ የሚዘጋጅ ሲሆን የመጨረሻ ዙር ክፍያ የሚባልም አለው፡፡
*የመጀመሪያ ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በአብዛኛው ከቅድሚያ ክፍያ በኋላ ሲሆን ክፍያውም ለተሰራ ስራ የሚፈጸም ነው፡፡
*የመጨረሻ ዙር ክፍያ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ጊዜአዊ ርክክብ/provisional acceptance/ ከተከናወነ በኋላ በህግ ከተቀመጡ ተቀናሾች በስተቀር ቀሪውን የስራ ክፍያ ጠቅልሎ አካቶ ወዲያውኑ በግንባታ ውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡
*የክፍያ ሰርተፍኬት የፕሮጀክቱን ስም፣ቦታ፣አሰሪውን፣ተቋራጩን፣አማካሪውን ይጠቅሳል፡፡ ዋናውን የውል ገንዘብ መጠን፣ተቀጽላ ስራዎችን፣ቫሬሽንን እና የተከናወነውን የስራ መጠን ያመለክታል፡፡ውሉ የተደረገበትን ጊዜ እና ኮመንስመንት ዴት ይጠቁማል፡፡በተጨማሪም የቅድሚያ ክፍያ መጠን እና አድቫንስ ሪፔይ ያመለክታል፡፡በዚህም አስቀድሞ የነበሩ የክፍያ ቁጥሮችን ጭምር ይጠቁማል፡፡ እንደዚሁም የሪቴንሽን መጠን እና የቅጣት መረጃንም የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ መረጃ በያዘ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ አሰሪው/ተቆጣጣሪው/አማካሪው እና ተቋራጩ የሚፈራረሙበት ይሆናል፡፡
*ስለዚህ የክፍያ ሰርተፍኬት ጸደቀ ማለት በሰርተፍኬቱ ላይ የተመለከተው ስራ ስለመሰራቱ እና ዋጋውንም ጭምር አሰሪውና ተቋራጩ አምነውበታል ማለት ነው፡፡
*እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የአሰሪው ዋና ግዴታ ለተቋራጩ በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ነው፡፡
*የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ክሎስ 28.5 ላይ ስለኮንስትራክሽን ስራዎች ክፍያ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ይዘረዝራል፡፡
*በዚህ ረገድ በተለይ ክሎስ 28.5(a) ላይ የተቀመጠው እንደሚያስገነዝበው በኮንስትራክሽን ስራዎች ጉዳይ ክፍያ የሚፈጸመው በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠና የጸደቀ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ እንዲቀርብ በማድረግ መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
*እንግዲህ የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብ በመጀመሪያ ተቋራጩ እንደመሆኑ አማካሪው/ተቆጣጣሪው መሀንዲስ የሳይት ቪዚት በማካሄድ የክፍያ ጥያቄውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ የክፍያ ሰርተፍኬቱን፣ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪውን ጨምሮ የሚያጸድቅና አረጋግጦ የሚፈርምበት እና በማህተምም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
*አማካሪው/ቶጣጣሪው በተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማረጋገጡን ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባው በዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(d) ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡
*እንደዚሁም አሰሪው ደግሞ በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያውን መፈጸም እንደሚገባው በአስገዳጅ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡
*እንግዲህ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በእጁ ይዞ እያለ እና አሰሪውም ደርሶት እያለ ሳይከፍለው ያዘገየበት እንደሆነ በግንባታ ውሉ እና የውል አካል በሚያደርጉት ጀኔራል ኮንዲሽን በተመለከተው አግባብ ተቋራጩ ኪሳራ ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል ዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(g) በግልጽ እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
*ፒፒኤ 2011 ክሎስ 59 እንደዚሁ የኮንስትራክሽን ጉዳይ የስራ ክፍያ የሚፈጸመው በክፍያ ሰርተፍኬት አማካይነት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡
*በአጠቃላይ ከላይ የተመለከተው የክፍያ ሰርተፍኬት ባህሪ እና የፒፒኤ ድንጋጌ የሚያስገነዝበው ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በአማካሪው/ተቆጣጣሪው እስከጸደቀለት ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ክፍያ ሊፈጸምለት እንደሚገባ ነው፡፡ አመሰግናለሁ::

⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
🔖ማሳሰብያ ለውድ Ethio construction ቤተሰቦች

🚧ለሁላቹሁም በ ጠቅላላ የ ኮንስራክሽን ዘርፍ ላይ ጆርናል ና መፅሄት እትሞች፣በ ራድዮ እና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች፣በ ዲዛይን አውደ ርእይ እና ውድድሮች በማዘጋጀት የተሰማራቹ እንዲሁም በ ኮንስትራክሽን ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ የ ስራ ሃላፊነት ድርሻ ላይ የ ምትገኙ በ ሙሉ @ethioengineers1 የ ቴሌግራም ቻናል ከናንተ በትብብር መስራት ስለሚፈልግ ከኛ ጋር አብራቹ መስራት ለምትፈልጉ @Ethiocon143bot ላይ በ ውስጥ መስመር እንድታገኙን በትህትና እንጠይቃለን።

➡️ኢትዮጵያ ሀገራችንን በበጎ ስራ እናገልግል የምህንድስና ሙያን ወደ ከፍታው እንመልስ!!
፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!🙏
📌▪️Difference between working stress approach and limit state approach

🔸Working Stress Approach -

🚧The service loads are used in the whole design and the strength of material is not utilized in the full extent. In this method of design, stresses acting on
structural members are calculated based on elastic method and they are designed not to exceed certain allowable values. In fact, the whole structure during the lifespan may only experience loading stresses far below the ultimate state and that is the reason why this method is called working stress approach. Under such scenario, the most economical
design can hardly be obtained by using working stress approach which is now commonly used in the design of temporary works.



🔸Limit State Approach -

🚧 For each material and load, a partial safety factor is assigned
individually depending on the material properties and load properties. Therefore, each
element of load and material properties is accurately assessed resulting in a more refined and accurate analysis of the structure. In this connection, the material strength can be utilized to its maximum value during its lifespan and loads can be assessed with reasonable
probability of occurrence. Limit state approach is commonly used for the majority of
reinforced concrete design because it ensures the utilization of material strength with the lowest construction cost input.

https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
በቢም webinar ላይ ተሳታፊዎች ብዛት ያላችሁ ነበራችሁ። በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ስለ ቢም (Building Information Modeling) ትንሽ ግንዛቤ ያገኛችሁ ይመስለኛል።

በዕለቱ Waiting Room ላቆይኋችሁ ይቅርታ እየጠየኩ ወደፊት ግን ምንም ሳትጠብቁ ቀጥታ እንድትገቡ ይደረጋል።

ይላችሁን አስተያየትም ማንኛውንም ጥያቄ በውስጥ መስመር ብትልኩልን።

በምሽት ፕሮግራም ላይ ያልተገኛችሁ ወይም በድጋሚ ማየት ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማየት ይቻላል።
https://youtu.be/i27WQLANMcE

ሐሙስ 3rd Sept. 2020 (ነሐሴ 28 ቀን 2012 ዓም) በተመሳሳይ ሰዓት ይቀጥላል።

እናመሰግናለን
ስለሺ ተሰማ
በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/
======******=======
# በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም
ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final
acceptance) የሚያካትት ነው፡፡
# በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን
የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ
ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ
2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡
** ** **
🚧 ግዚያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance/
# ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች
ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ
ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር
ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን
ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ
በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ
የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም
የሚያረጋግጥ ነው፡፡
# ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/
በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ
ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ
ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡
# እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ
እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ
እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡
# በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን
የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት
ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ
ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ
ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው
በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት
ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ
ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ
ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87
ያስቀምጣል፡፡
# ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ
በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት
እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ
ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡
ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው
ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው
ይቆጠራል ነው፡፡
# እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period)
መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡
** ** **
# የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)
# የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ
መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ
ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው
ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277
ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ
እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7
ያስቀምጣል፡፡
# ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው
በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ
3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን
ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡
# በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን
እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ
እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ
ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3
ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡
** ** **
# ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/
-በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም
አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the
work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ
ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ
ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ
ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
** ** **
🚧የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/
# የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ
በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው
ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively
appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
# የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት
በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም
ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ
መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ
አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ
ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡
# በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ
በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ
ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ
ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡
ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም
እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ
የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
# የመጨረሻ ርክክብ መደረጉ የተቋራጩን መሰረታዊ ግዴታ የሚያወርድለት
ሲሆን ቀሪ ክፍያ ካለው እንዲከፈለው እና ዋስትና እንዲወርድለትና የዋስትና
መያዣ ገንዘብ ካለም እንዲለቀቅለት ለተቋራጩ መብት የመስጠት ውጤት
እንደሚኖረው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3281 ይደነግጋል፡፡
# ፒፒኤ ክሎስ 89 በተመሳሳይ ስለመጨረሻ ርክክብ የደነገገ ሲሆን የመጨረሻ
ርክክብ ሰርተፍኬትም በመሀንዲሱ ለአሰሪውና ለተቋራጩ እንደሚሰጥ
ያስቀምጣል፡፡
👌ጉባኤ
አሰፋ
👍1
Reinforcement steel current price in Addis Ababa

Made: Turkey with vat
8=×185
10=×285
12=×415
16=×740
20=×1250
24=×1800


Via:- construction resource

https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
👉ስለ ብሎኬት
.
⏩Hollow Concret Block (HCB) ወይም የግድግዳ ብሎኬት/Wall HCB/ በመባል ይታወቃል።
*የብሎኬት ምርት ሲደረግ ጠቀሜታው ለሁለት ጉዳይ ነው
1. ሸክም መቌቌም የሚችል/Load Bearing/
2. ሸክም መቌቌም የማይችል /Non-Load Bearing/
*ይሄንን መሰረት ያደረገም የደረጃ ክፍፍል/Class/ ይኖራቸዋል።
*ሸክም መቌቌም የሚችሉት ብሎኬቶች "ክላስ ኤ እና ቢ" /
Class A and B/ በመባል ሲመደቡ ሸክም መቌቌም
የማይችሉት የብሎኬቶች ደግሞ "ክላስ ሲ" /Class C/ በመባል
ይመደባሉ።
➡ብሎኬት በተለምዶ በመጠናቸው ባለ10፣ ባለ15 እና ባለ 20 በመባል ይለያሉ::
ርዝመት x ስፋት x ቁመት/ Length x width x depth/
ማለትም Standard Dimenssion
*40x20x20cm
*40x20x15cm
*40x20x10cm
➡እያንዳንዱ ብሎኬት ሸክም የመቌቌም አቅማቸው
በሜጋ ፓስካል(Mpa) ይለካል
*Note:
1 kilogram per square centimetre = 0.0981 mega pascal

*Class A=3.8mpa
*Class B=3.2mpa
*Class C=1.8mpa .


https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
👉Rahel Shawl, the Ethiopian Star Architect gave an interview to the daily "Addis Zemen" Enjoy it.
@ethioengineers1

➡️‹‹ሕንፃዎችን ለመቶ ዓመት እንጂ ለአስርና ሃያ ዓመት ብለህ አትገነባም››- አርክቴክት ራሔል ሻውል አርክቴክት ራሔል ሻውል የተወለዱትና ያደጉት አዲስ አበባ ፒያሳ ነው። የአራዳ ልጅ ናቸው። ይሄ ትርጉም አለው ከሕብረተሰቡ ጋር ተግባብተህ ብዙ ነገር አውቀህ ታድጋለህ ከሕይወቴ አንዱ የምወደው አስተዳደጌን ነው ይላሉ በንጉሡ ጊዜ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት የጀነራል ሻውል ዘለቀ ልጅ ናቸው ደርግ አባታቸውን 8 ዓመት በእስር ቤት አቆይቷቸዋል አባታቸው በመታሰራቸው ምክንያት አምስቱንም ልጆች ያሳደጉት እናታቸው ናቸው የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ናዝሬት ስኩል ነው የተከታተሉት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕንፃ ኮሌጅ በመግባት በአርክቴክቸርና የከተማ ፕላኒንግ (አርበን ፕላኒንግ) ተመርቀዋል። በአርክቴክትነት( ኪነ ሕንፃ) የሥራ ዓለም ብዙ አሳልፈዋል የተለያዩ ዓለም አቀፍ አዋርዶች (ሽልማቶች) ተሸላሚም ናቸው በአርክቴክት ሙያ ለዓለም አቀፍ ሽልማት ሲቀርቡ አፍሪካን ወክለው የተመረጡ ሀገርን ያኮሩ ባለሙያ ናቸው።

ድሮ ኢትዮጵያ ብዙ ሴት አርክቴክቶች አልነበሯትም ትምህርት ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በነበሩበት ጊዜ ከ20 ወንዶች የአርክቴክት ተማሪዎች ሴት እሳቸው ብቻ ነበሩ ዛሬ ግን ብዙ የሴት አርክቴክቶች አሉን። በሀገራችን ስማቸው ጎልቶ የሚነሳ ታዋቂና ቀደምት የሴት አርክቴክት ናቸው በኢትዮጵያ አርክቴክት (ስነሕንፃ)፤ በሠሯቸው ሥራዎችና በዚህ ሙያ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ፤ ከሙያው ጋር በተያያዘ ስላሉት ችግሮችና መፍትሔዎች ከአዲስ ዘመን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለዛሬ ይዘን ቀርበናል።

አዲስ ዘመን፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ የመጀመሪያ ሥራዎትን የት ጀመሩ?

አርክቴክት ራሔል፡- የመጀመሪያ ሥራዬን ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች ኤንድ ቲዎሎጂ ኮሌጅ የሚባል የመጀመሪያ ፕሮጀክት ቢሮ ነበረ ወደአፍሪካ ሕብረት ሳር ቤት አካባቢ ያለ ነው ለሁለት ዓመት ተኩል እዚያ ነው የሠራሁት።

አዲስ ዘመን፡- ምን ምን ሥራዎችን ሠራችሁ ?

አርክቴክት ራሔል፡- ኮንሰፕት ዲዛይኑን (መነሻ ንድፉን) የቤተክርስትያኑንና ኮሌጁን የሠራው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያለን አስተማሪያችን ነበር ዲዛይን ዴቨሎፕመንት የሚባል አለ ድሮዊንጎችን እዚያው ደግሞ ፕሮጀክት ቢሮ ስለሆነ ዲዛይኑ እየተሠራ ግንባታውን ትቆጣጠራለህ ማለት ነው ሁለት ዓመት ተኩል እዚያ ላይ ስለ ሠራሁ ራሱን ያቻለ ትልቅ ትምህርት ሆነኝ በእኛ ጊዜ ትልቅ ፕሮጀክት ስለሆነ ዲዛይኑ በአዲስ አበባ ስታይል አርክቴክቸር በሚባል ነው የተሠራው የሕንፃው ዝርዝሩ፤ ውስጡ፤ ውጪው መሬቱን ዙሪያ አቀማመጡን አጥሩን ግንባታውን ሁሉንም ዲዛይን ሦስት ሆነን ነው የሠራነው አርክቴክቱ ማልከም ማግሬገር ይባላል ስኮትሽ ነው ቤተክርስትያኑ ቀጥሮን ከእሱ ጋር ነው የሠራ ነው ለእኔ ቀጥታ ከትምህርት ቤት ወጥቼ እዚያ መሥራቴ ትልቅ ዕድል ነበር ሙሉ በሙሉ ከዲዛይንና ኮንስትራክሽን ዝርዝር ከእዚያም ሱፕርቪዥን (ቁጥጥር) የሚለውን ነገር በጣም ነው የተማርኩበት።

አዲስ ዘመን፡- ቀጥለው በአርክቴክትነት የት ሠሩ ?

አርክቴክት ራሔል፡- ከዚህ ሥራ በኋላ የራሳችንን ቢሮ ከፈትን።

አዲስ ዘመን፤- ድርጅቱ ማን ይባላል ?

አርክቴክት ራሔል፡- ሦስት ሆነን ነበር የጀመርነው ከመጀመሪያው በኋላ ከመቀጠር ለምን የራሳችንን ሥራ አንሠራም ብለን ወሰንን እኔ ፣ ዮሴፍ በረደድና ሊያ ኤፍሬም ነበርን ትንሽ ቢሮ ይዘን ቪላዎች፤ ኤክስፓንሽኖች (ማስፋፋቶች)፤በዚህ ሥራዎችን ጀመርን የድርጅቱ ስም አባ አርክቴክት ይባላል 8 ዓመት ሠራን በ2014 (እኤአ) መስከረም ላይ ተለያየን ከዚያም የራሴን ቢሮ ራስ አርክቴክት በሚል ከፈትኩ ቢሮው ከተከፈተ መጪው መስከረም 16 ዓመት ይሆነዋል።

አዲስ ዘመን፡- ራስ አርክቴክት መጀመሪያ የት ሠራ?

አርክቴክት ራሔል፡- ከትንሹ ጀምረን 8 ዓመት አብረን ስንሠራ ብዙ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እየሠራን መጣን መጨረሻ ሽግግሩ ላይ ኔዘርላንድስ የሚባለው ፕሮጀክት ትልቅ ሥራ ስለነበር እኔ በኢትዮጵያ በኩል የፕሮጀክቱ ሊድ አርክቴክት(መሪ አርክቴክት) ነበርኩ ዳቾች ናቸው ዲዛይኑን የሠሩት በትብብር ነው የተሠራው።
አርክቴክቶች ገና ከውጭ ሲመጡ አባ አርክቴክት ሆኜ እተዋወቃቸዋለሁ ከዚያ በፊት ትላልቅ ፊስቱላ ሆስፒታሎችን በሙሉ እኛ ነን የሠራነው አዲስ አበባ አጉስታ ጋ ያለውን እሱ ፕሮጀክት ላይ ብዙ ዓመት ከዮሴፍ በረደድ ጋር አባ አርክቴክት ሆንን አብረን ሠርተናል ሦስተኛዋ ሊያ ኤፍሬም ሁለት ዓመት ብቻ ሠርታ አሜሪካ ገባች እኔና ዮሴፍ ነን የቀጠልነው።
በሕይወትህ ውስጥ የማእዘን ድንጋይ ተደርገው የሚወሰዱ ለውጦች ዕርምጃዎች አሉ በሙያህ የምታድግበት የመጀመሪያ የሠራነው ቤተክርስትያኑን ነው ከዚያ ፊስቱላ ሆስፒታሎቹን ሆስፒታሉ ፈንድ እየሰበሰበ ስለሆነ የምንሠራው እኛም በሙያው ብዙ አድገንብታል በክፍል በክፍል እየተደረገ ነው የተሠራው መካነ እየሱስ፤ቢንግሀም አካዳሚ ብዙ ሥራዎች ሠርተናል ከዮሴፍ በረደድ ጋር ከተለያየን በኋላ እኔም አንድ ሁለት ፕሮጀክቶች (አውት ሪቾች) ሀረር፤ መቀሌ ይሠራ ነበር እኔ ብቻዬን የሠራሁት መቱ ላይ ያለውን ነው ስንለያይ ቢሮ ስላለ እሱ ቀጠለ።

አዲስ ዘመን፡- ራስ አርክቴክት የሠራቸውን ሥራዎች ቢገልጹልን ?

አርክቴክት ራሔል፡- ራስ አርክቴክትን ከ16 ዓመት በፊት ስከፍት ምንድነው የሆነው ኔዘርላንድ ኤምባሲ የነበረውን ሥራ እኔ ነበርኩ የምመራው አብረህ ስትሠራ ፕሮጀክት እየተከፋፈልክ ስለሆነ እኔ እሱን ነበር የምቆጣጠረው ፕሮጀክቱ የአምስት ስድስት ዓመት ነበር ከዲዛይን ጀምሮ መሰረት ሲወጣ ግንባታ ሲጀመር ሁለት ዓመት ፈጀ በእኔ ሱፐር ቪዥን 2004 ላይ ግንባታው ተጠናቋል።
ከዚያ ወደ ራስ አርክቴክት ስገባ የሚቀሩ ሥራዎች ነበሩ ያው ፕሮጀክት አያልቅም እኔ ስወጣ ትንንሽ ሥራዎች ተሠርተው ተመርቀዋል እሱን ይዤ ነው ቤቴ እሠራ የነበረው በዚህ ሰዓት ላይ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ ወጣ ገባ እያልኩ ነው የሠራሁት እንደ ሴትም ብትወስደው በጣም ትልቅ ፕሮጀክት ነው የመጀመሪያ ሥራ ራስ አርክቴክትን እንደጀመርኩ ትንሿ ልጄ ተወለደች በእጄ ላይ አንዳንድ ሥራዎች ስለነበሩ ቀጣይነትም ስለነበረው የግዴታ ላይሰንስ (የሥራ ፈቃድ) አስፈለገኝ፤ አወጣሁ በዚያ ነው የራሴ ድርጅት ራስ አርክቴክት የተጀመረው በራስ አርክቴክት ድርጅት ውስጥ የሠራነው ትልቁ ፕሮጀከት የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ነው።

አዲስ ዘመን፡- የኤምባሲውን ሕንፃ ዲዛይን አርስዎ ነዎት የሠሩት?

አርክቴክት ራሔል፡- ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲን ከሠራሁ በኋላ ብዙ ኤምባሲዎችን ሠርቼአለሁ የኤምባሲው ሥራ የኮላበሬሽን ሥራ ነው ኤምባሲው የግንባታ ሥራ ሲያስብ የሀገራቸው አርክቴክቶች መጥተው የሀገር ውስጥ አርክቴክቶችን ያወዳድራሉ ኔዘርላንድ ኤምባሲ ላይ ጥሩ የሥራ ውጤት ስለነበረኝ ወዲያውኑ ሰጡኝ።
ደቡብ አፍሪካዊ አርክቴክት ነበር ከእሱ ጋር ሆኜ ከዲዛይን ዴቨሎፕመንት ጀምሬ እየተመላለስኩ ሠራሁ እነሱም እየመጡ እዚህ ያለውን ዲዛይን ወደ አስር ኢንጂነሮች ነበሩ አብረን ሠራን በእነሱና በእኛ ግንባታው ሁለት ዓመት ፈጅቶ ተጠናቀቀ።

via:- addis zemen
https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
👍1
I salute Arch. Rahel Shawel.
We need more women Engineers in the construction sector. Women engineers and architects should group themselves and start discussing how women can get more involved in Engineering.
DIGITALIZATION IN THE CONSTRUCTION INDUSTRY HAS BEEN A GROWING TREND FOR MANY YEARS: HOWEVER, NOW ITS SPEED IS ACCELERATING

The Construction Industry is reshaping itself, albeit slowly but certainly faster than previously. Pressure for change is coming from several complementary directions:

Evolving client expectations
Clients, influenced by other rapidly changing markets, now expect also the same from their homes, offices, commercial buildings and infrastructures to make their “connected lives” even more a reality. Constructions need to be more and more individualized, modular, connected to the Internet of Things (IoT) and allow for specific performance tracking, optimization of energy and improved security and health parameters for instance. Client demands are quickly rising and become more and more complex with expectations increasingly on the “usage” more than on the product itself.

New technological capabilities
Sensors and various hardware as well as software have seen cost drop and efficiency rise over the past few years opening the path to new possibilities. Technologies available on the market are more numerous than ever before (such as virtual and augmented reality, drones, robotics and additive printing) making it urgent to separate the more valuable ones from mere novelties.

New generation of craftsmen and professionals
Tech savviness is spreading in the construction industry, which traditionally has been, resistant to change, accelerating the adoption of digital tools. Innovative university curricula are training the younger generations for emerging tech-related jobs. Many new jobs, not yet known, will be created in the years to come with the adoption of new tools and processes.

Booming start-up environment
Start-ups have taken advantage of the market opportunities induced by some of these trends to fill newly created added-value gaps. Oliver Wyman has identified nearly 1,200 startups worldwide since 2010 in real estate and construction. These startups have received around US$19.4 billion in funding over the period, half of it in 2017.

Supportive legal frameworks
Governments, particularly in the Nordic countries and the UK, are increasing their CO2 and energy efficiency regulations and raising their targets. Digitalization provides a great opportunity to reduce the environmental impact of construction projects. There will also be heightened requirements on data usage and cyber security in buildings and infrastructures going forward that will need to be carefully analyzed (General Data Protection Regulation). Importantly, labels and groups are also more and more launched to help the market move in one common direction and support innovation.

Launch of large infrastructure projects
Market needs are tremendous in terms of new infrastructure networks between cities (such as the Grand Paris Express with 200km of new automated metro lines in France, the High Speed 2 (HS2) in the UK or the Rastatt tunnel in Germany) as well as in terms of upgrading partly old existing structures.

All players in the industry, whether they are promoters, engineering companies, builders, suppliers of equipment, materials, or distributors will be impacted by digital pressures. Each one will experience this differently, of course, but there is no doubt that significant change is coming. The outlined trends put pressure on incumbents (both equipment and traditional construction and service players) by producing a more complex and dynamic competitive landscape and the progressive disruption of traditional channels in the battle for customer access and control.

Click on the link below to read more. https://www.mmc.com/content/dam/mmc-web/Files/OliverWyman_Digitalization_in_the_construction_industry_web_final.pdf

#DigitalTransformation
#BIM

@BIMDigital
@ethioengineers1

በአዳማ (ናዝሬት) ከተማ ቦኩ ሸነን ቀበሌ አዳማ ቆርቆሮ አጠገብ ግንባታው ተጠናቅቆ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የአስፓልት መንገድ ከፊል ገጽታ።

(ከዚህ በመቀጠል የትራፊክ አደጋ ሪፖርት ጠዋት ጠዋት ይቀርባል
)

https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
HOW AEC FIRMS CAN PREPARE FOR BIM

Making the move
Talking about BIM, talked how it can be successfully adopted, there’s no one right way. The following can be taken as common steps in adopting BIM that help to both accelerate the process and reduce the disruption that can accompany change.

Step One.
Get to know BIM
Designate one or two people to learn more about how BIM will affect the way your team works. For instance, in the 2D world, many firms leave the details to the later stages of the design process. With BIM, many design details need to be worked out much earlier.

Step Two.
Communicate the change to your people.
High-level leaders should take a leading role in letting people know the firm is definitely moving to BIM. The message is “we are moving to BIM because it’s critical to our future,” not “we’re trying BIM.”

Step Three.
Account for software and hardware needs.
BIM isn’t just software; it’s a collaborative process that relies on intelligent 3D models. But you’ll need software to create those models. Take the time to explore available software, and consider whether your current hardware has sufficient processing power.

Step Four:
Develop a change management plan.
This plan should document at a high level how your team anticipates BIM changing established workflows, who needs training and when they’ll get it, and how you’ll support people when they have questions and issues. Support is probably the most important item; organizational change happens faster and more successfully when you help people adopt new ways of working.

Step Five:
Start a pilot program, and train the pilot team.
For most firms, it makes sense to run a BIM pilot. If you do dozens of small projects each year, consider completing one pilot and capturing lessons learned before running several more pilot projects.

To be continued….

#BIM
#DigitalTransformation

@BIMDigital
@ethioengineers1
Types of Columns in Building Construction
Columns are classified based on the several conditions which include:

Based on Types of Reinforcement
Based on Types of Loading
Based on Slenderness Ratio
Based on Shape
Based on Construction Material
Based on Types of Reinforcement

We'll post 14 different types of columns in the following posts.

via:- construction world

https://t.me/joinchat/AAAAAEo_NBVYFBTZCKpA4w
1. Tied Column
This type of column is commonly construction from reinforced concrete. Longitudinal reinforcement are confined within closely spaced tie reinforcement. It is estimated that 95% of all columns in buildings are tied.

@ethioengineers1
2. Spiral Column
Spiral column is also construction from reinforced concrete. In this type of column, longitudinal bars are confined within closely spaced and continuously wound spiral reinforcement.
Spiral reinforcement provide lateral restrains (Poisson’s effect) and delays axial load failure (ductile).


@ethioengineers1
3. Composite column
When the longitudinal reinforcement is in the form of structural steel section or pipe with or without longitudinal bars, it is called as a composite column.

This type of column have high strength with fairly small cross section, in addition to exhibit good fire performance.


@ethioengineers1