SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
#How do we consider Earthquake as a load ?

➡️Earthquake) የመሬት መንቀጥቀጥ እንዴት እንደ LOAD consider እንደሚደረግ እንመልከት።

The SI unit of LOAD is NEWTON(N). And Load is a type force.
የ Load SI unit ኒውተን ነው። እናም the second law of Newton አንድ እውቅ formula አስተዋውቆናል። እሱም

F=m x ā
Where F= force ( load in our case )
m= mass
ā= acceleration

ስለዚህ

👉🏿‘m’ mass= የህንፃው ክብደት (self weight)

👉🏿 ‘ā’ acceleration = wave from epicenter የመሬቱ እርግብግቢት


https://t.me/ethioengineers1
👆ካለይ ባለው
የመንገድ ዲዛይን ውስጥ በትንሹ ከዚህ በታች ያሉት የትምህርት መስኮች
ይሳተፉበታል። Structural, Geotechnical, Hydraulic, Highway
Engineering, Surveying and Geologic disciplines.
ስለዚህ በየትኛው ምክንያት ይህን ቅርጽ እንደያዘ ዝርዝር ጥናት ይፈልጋል
የቢሆን ምክንያቶች(If scenarios)
1.
#Topography - #መንገዱ_ሜዳ_አይደለም ። ብዙው ሰው ይህን
ፎቶ ተመልክቶ(ምናልባትም አንተም) የሚወቅሰን ቦታው ሜዳ ሆኖ
መሃንዲሱ ያጠማዘዘው ይመስለዋል። ግን አይደለም።
በፎቶው ላይ እንደሚታየው ከመንገዱ በግራ በኩል (ለመንገዱ) ወንዝ
አለ። ወንዝ ካለ ደግሞ Elevation difference አለ ማለት ነው(ውኃው
እንዲፈስ)። በተጨማሪም የተራራ ጥላዎች፣ የመኪኖቹ ጥላዎችና
positions እና Natural contours ስለሚታዩ with high probablity
(99%) በፎቶው ላይ የሚታየው መንገድ ሜዳ ላይ የተገነባ ሳይሆን ዳገት
(ከ1 ወደ 6) ወይም ቁልቁለት(ከ6 ወደ 1) ላይ የተገነባ መንገድ ነው።
እናም መንገዱ steep slope ያለውን ተራራ እየተጠማዘዘ ለመውጣት
(ለመውረድ) የተሠራ መንገድ ነው። የፎቶው perspective view ሜዳ
ስለሚመስል ነው። ስለዚህ ቀጥታ መሥራት አይቻልም። በእኛ ሀገር
standard maximum road slope እስከ 12% ነው። This is for both
the safety of the vehicle and the road structure itself. So,
it shouldn't be constructed as per the sketch shown with Red
arrows.
2
#Economy:
ከላይ ያልኩት በልዩ ሁኔታ(1%) ባይሆን እና ብዙው ሰው እንደሚረዳው
ቦታው ሜዳ ሆኖ እንዲህ ማጠማዘዝ ቢገባ በፎቶው ላይ እንደሚታየው
እኔ በጻፍኳቸው 6 ቁጥሮች መካከል gorge (ሸለቆ) ይታያል። በ6ቱ
ሸለቆች መካከል 5 ወይም 4 ወይም 3 ድልድይ ከመሥራት መንገዱን
በዚህ መልክ መሥራት economical ሊሆን ይችላል።
3.
#Safety
ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ያልኩት በልዩ ሁኔታ ባይሆን እና ቦታው ሜዳ
ወይም መለስተኛ ተዳፋት (slope) ቢሆን:
3.1. ለመንገዱ ደኅንነት ሲባል በጻፍኳቸው ቁጥሮች መካከል ያለው ቦታ
ለመንገድ ደኅንነት(safety) ምቹ ያልሆነ ከሆነ route selection
criteria ያላሟላ weak soil(rock) stratum. ሆኖ ሊሆን ይችላል
3.2 ለተሽከርካሪ(አሽከርካሪ) ደኅንነት ሲባል ምንም ያክል ሜዳ መንገድ
ቢሆን ከ 5 ኪሎ ሜትር በላይ ቀጥ ያለ(without horizontal or
vertical curve) መንገድ መገንባት አይመከርም። The driver may
lose his consciousness due to the straightness of the road.
So, intentionally a horizontal curve will be provided. በርግጥ
በፎቶው ላይ ሲታይ ለዚህ የሚያበቃ አይመስልም።


https://t.me/ethioengineers1
Here you have a brief presentation on Design of structures for earthquake resistance according to EBCS-EN.👇
@CENGGsoftwaresolution
👉ስለ ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
⚡ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን
ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
*ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው።
ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ።
የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength)
ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች
አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት
ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
(compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ
ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ
ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
*ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
*አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ
መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15
የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15
የሚለውን ይጠቀማሉ (ከታች በምስሉ እንደተጠቀሰው) ....በ
«C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።

@ethioengineers1
👍1
Hello Dear Members.
Here you have real estate compound with its
Topo data & Site plan layout.
we prepared new package which is helpful especially for proffessionals who want to practice both
Structural & Highway designs. The structural design is done using ETABS & road network design is done using CIVIL 3D Both are done using most recent versions of the softwares.
@CENGGsoftwaresolution
#የኮንስትራክሽን_ውል_የተደረገበት_ቀን/ #contract_signing_date/ እና #በኮንስትራክሽን_ውል_የስራ_መጀመሪያ_ቀን/#Commencement_date/

⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡

-------///-------///-----

#በኮንስትራክሽን_ውል_የስራ_መጀመሪያ_ቀን/#Commencement_date /

✍️በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/ ካልተፈጸመለት ስራ መጀመር አይችልም፡፡ስለዚህ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታውን ጊዜ መቁጠር ተገቢነት የለውም፡፡እንደዚሁም ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡

✍️በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡ይሄ ተገቢ አሰራር አይደለም፡፡

✍️በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡

FIDIC RED BOOK 1999

✍️በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡ እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡

✍️ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ 8 ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል፡፡

FIDIC 1987

✍️በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡

✍️እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡

MoWUD 1994

✍️ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994/ በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡

PPA 2011

✍️በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡

የፍትሀብሄር ህግ

✍️የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610-2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡

የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

✍️የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡

✍️ይሄውም በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የግንባታ ስራዎቹ በሙሉ የሚከናወኑበት ጠቅላላው ጊዜ ብቻ ተጠቅሶ እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት/client/ የግንባታ ስራው የሚጀመርበትን ጊዜ/ Commencement date/ ዘርዝሮ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3253(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ ---------///---------///----------
#የኮንስትራክሽን_ውል_የተደረገበት_ቀን/ #contract_signing_date/


https://t.me/ethioengineers1
🔹Important concept -

#Plastic bitumen is generally used for Crack filling.

👉🏿The waste plastic is shredded & coated over aggregate & mixed with hot bitumen and resulted mix is used for pavement construction. This will not only strengthen the pavement and also increases its durability.


https://t.me/ethioengineers1
The maximum value of centrifugal ratio on roads and railway respectively are taken as 1/4 and 1/8

#Centrifugal force is defined as P, however, this 'overturning force' is counteracted by the mass (W) of the vehicle, and may be expressed as P/W, termed the centrifugal ratio.


https://t.me/ethioengineers1
ConMIS
Here you have locally developed best database program which is very important for both Contractors & Consultants;
It uses quantities as an input & helps in;
👉Creating a database for construction activities & resource data
👉Cost estimation (bidding) & planning
👉Quantity surveying & payment
👉Work progress & tracking
👉Project resource quantities & cost tracking (material, labor, equipment & overhead)
👉Stock controlling
👉Equipment’s fuel, oil, lubricant quantity & cost controlling
👉Equipment maintenance log & cost
👉Resources usage quantities & cost for tasks & evaluation & monitoring of unit rates
👉Working along with Excel & Ms project
(Commonly it helps to prepare
Take off sheet,Bar schedule,Bill of quantities,Payments certificates,Resource requirements & usage on material,labour,equipment)
@CENGGsoftwaresolution
🚧በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ
ኢንጅነርዎች ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ ነጥቦች...
.
1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING
MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ
አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል
የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ
አንማር ይሆናል
ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር
ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም
ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::
:
2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና
ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን።
እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።
:
3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት
አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !
:
4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካ ምድራቸው
የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር
የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ
(Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።
፡
5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ
አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች
የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና
ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ።
ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል
፡
6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።
ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ
ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል
ማለት ነው።
ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው::
፡
7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው።
(እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)
፡
8 የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)
ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።
ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ
ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።
አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ
መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት
የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን
አደጋ ለመከላከል።
፡
9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣
ለጥንቃቄ
የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን
ነው
:
10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION
WITHLABOR) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ
እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ
ሊኖረን ይገባል።
ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።
ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና
ወሳኝ ነገር ነው።
.
.
አንድ ጥሩ የሚባል CONSTRUCTION እንጅነር ማወቅ
ስለሚገባው ነገሮች ትንሽም ቢሆን እውቀት እንደሰጠናቹ ተስፋ
እናረጋለን::

@ethioengineers1
👍1
ConMIS Introduction.mp4
75.5 MB
Here you have a brief introduction on ConMIS with an example done on it.
@CENGGsoftwaresolution
Why is the bending?

This is called a #joggle in technical term.
👉🏿The bent is provided to overlap the column reinforcement and to keep in alignment in its dimension (column size )..... if we don’t bend the reinforcement at overlapping then the size of the column will increase when we go up.
👉🏿So the point is TO MINIMIZE LOAD IN THE TOP AND TO REDUCE THE SIZE OF COLUMN ON THE WAY
.
⚡አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።

https://t.me/ethioengineers1