🏗መንግስት የህንጻ ነዳፊዎችንና የአማካሪዎችን የሙያ ዋጋ (Professional fee) ሊወስን ነው።
👉ጥራት ላይ ማተኮር ሲገባው ዝቅተኛውን ዋጋ አቅራቢ እያበረታታ የንድፍና የሙያ ጥራት እንዲያሽቆለቁል ያደረገው የዋጋ ሰበራ ልምድን ያስቀራል ተብሎ ይጠበቃል። በሌሎች አገሮች እንደተለመደው ሁሉ የንድፍ ማማከር ስራ ከግንባታው ወጪ ጋር በመቶኛ ተያይዞ የሚቀርብ ሲሆን ከዚህ መቶኛ ያነሰ ዋጋ የሚያቀርብ ነዳፊ ወይም አማካሪ ስራውን በብቃት ይሰራዋል ተብሎ አይወሰድም።
ዝርዝሩን ከማስፈንጠርያው ላይ ይመልከቱ
https://addisfortune.news/government-to-decide-threshold-fees-for-architects-consultants/
https://t.me/ethioengineers1

addisfortune.news
Government to Decide Threshold Fees for Architects, Consultants
The state will soon determine fees in the construction industry for design and supervision works, ending a competitive m...
🏗አዲስ አበባ ቅርሷን ማበላሸት አላቆመችም።
👉ይህ አንኳር ባለሙያዎችና የከተማው ነዋሪዎች የተቹት በዘመናዊው የግንባታ ዘመን (60s modernist buildings) የአዲስአበባ ህንጻዎችን ሰማያዊና ነጭ የማልበስ ሂደት ፋታ ሳያገኝ ቀጥሏል። ሌላ ቀለም ማልበስ ሌላ ማንነትን ከመፍጠር አይተናነስም። ስነከተማዊ አካባቢ ነፍስ እንዳለውና ትዝታ እንደሚኖረው ጉዳይ ይቆጠራል። ነጩን ህንጻ ቀይ ወይም ቢጫ ስናደርግ እንዳለ የስነከተማ ትውስታን (urban memory) ነው የምንደመስሰው።
ቢጮህም አንድ ሰሞን ነው በሚል ይመስላል ያለ ፋታ የዘመናዊ ኪነህንጻዎቻችንን ማንነት እያጣን እንገኛለን።
ምስል ምንጭ ብሩክ ክፍሌ EAU

🏗ሀይባይ ያጣው ኖህ ሪልስቴት #NOHA
በሪልስቴት ዘርፍ የተሰማራው ኖህ ሪልስቴት 22 አካባቢ በቀድሞው ዘሪውን ህንጻ ቦታ ላይ እያከናወነ በሚገኘው የህንጻ ግንባታ ቦታ ላይ የሚጠቀምበትን ክሬን በድልድይ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ በመዝጋት ለበርካታ ቀናት ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ እያስቀመጠ ይገኛል።
ከተማችን ላይ ትንንሽ ምክንያቶችን እያሳደዱ ለመቅጣት የሚጣደፉ አካሎች የተበራከቱትን ያህል እንዲህ አይነት ግልፅ አስጊ ድርጊት ፈፃሚዎችን አይተው እንዳላዮ የሚያልፉት ለምን ይሆን?
በቂ የቅድመ ደህንነት ምልክቶች ባልተሟሉበት በምሽት እንዲታይ አስፈላጊ አንፀባራቂ ምልክቶች ባልተቀመጡበት ሁኔታ እንደነገሩ ለይምሰል ጣል በተደረገች ጃኬት አደጋን መከላከል ይቻል ይሆን?
👉መቼ ይሆን ከልብ ስለ ሴፍቲ ተጨንቀን መስራት የምንችለው❓
Source :-housing in Addis fb
#ethioconstruction

👍1
👌ግሩም ቻናል እናስተዋዉቆ
CENGG SOFTWARE SOLUTION
ምህንድስና ላይ የሶፍትዌር ዕውቀት በቀላሉ እና በአማርኛ ስልኮን ብቻ ተጠቅመው ያግኙ፤
👇👇👇
https://t.me/joinchat/RA4wSoF-CtPwOig4
👆👆👆
👍በአካል ለምትችሉ አድራሻችን:
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ ቢሮ ቁ 625.
📞 0911890392
👉ከ አዲስ አበባ ውጪ ያላቹ ወይም በስራ ምክኒያት መጥታቹ ሶፍትዌር ስልጠና መውሰድ ያልቻላቹ በአማርኛ የቪዲዮ ትምህርት አዘጋጅተናል፡፡
😳YouTube ላይም አለን
👉https://youtube.com/channel/UCqOrxoDFgaOX3fwI0bqPGuQ

🏗የአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት ቁስምስልና ንድፍ (model & drawings)
በ1955 አም አካባቢ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤቱን ንድፍ አካባቢው ጋር ካለ የገጸምድና የስነከተማ ንድፍ ጋር የሚያሳይ ቁስምስል እና የወረቀት ንድፍ። ይህ ዘመናዊ የስነከተማ ንድፍ እንደታሰበው ቢሰራ ኖሮ አዲስአበባ በታሪኳ ትልቁ ዘመናዊ በንድፍ የተሰራ የስነከተማ አካባቢ (urban design) ይኖራት ነበር።
ምንጭ። በብርሀነስላሴ ጌታቸው ተክሉ አማካኝነት HPFTHOA, ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች።
ethiopianarchitectureandurbanism
(በዳዊት በንቲ)
#ethioconstruction
https://t.me/ethioengineers1
በ1955 አም አካባቢ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤቱን ንድፍ አካባቢው ጋር ካለ የገጸምድና የስነከተማ ንድፍ ጋር የሚያሳይ ቁስምስል እና የወረቀት ንድፍ። ይህ ዘመናዊ የስነከተማ ንድፍ እንደታሰበው ቢሰራ ኖሮ አዲስአበባ በታሪኳ ትልቁ ዘመናዊ በንድፍ የተሰራ የስነከተማ አካባቢ (urban design) ይኖራት ነበር።
ምንጭ። በብርሀነስላሴ ጌታቸው ተክሉ አማካኝነት HPFTHOA, ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች።
ethiopianarchitectureandurbanism
(በዳዊት በንቲ)
#ethioconstruction
https://t.me/ethioengineers1
👍2
🏗Why do we use steel and not any other metal in concrete
🔸We use steel in concrete as the co-efficient of thermal expansion of concrete and steel is almost same and steel has very good strength to withstand with the tensile loads.
https://t.me/ethioengineers1
🔸We use steel in concrete as the co-efficient of thermal expansion of concrete and steel is almost same and steel has very good strength to withstand with the tensile loads.
https://t.me/ethioengineers1
በ ግንባታ ላይ ከነበረ ህንፃ 14 ኛ ፎቅ የወደቀ የጉልበት ሰራተኛ ህይወቱ አለፈ።
**
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጋዜቦ አደባባይ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ወረድ ብሎ ባለ እና ቀድሞ 34 ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንፃ 14 ኛ ወለል ላይ የወደቀ የጉልበት ሰራተኛ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።
Source:-ShegerTimesMedia
#ethioconstruction
https://t.me/ethioengineers1
**
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጋዜቦ አደባባይ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ወረድ ብሎ ባለ እና ቀድሞ 34 ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንፃ 14 ኛ ወለል ላይ የወደቀ የጉልበት ሰራተኛ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።
Source:-ShegerTimesMedia
#ethioconstruction
https://t.me/ethioengineers1
🏗ሸበሌ ፊት ለፊት ከሚክሲኮ ወደ ቄራ የሚወስደው መንገድ ለምን ባለ አንድ አቅጣጫ ተደረገ?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ሸበሌ ፊት ለፊት ከሚክሲኮ ወደ ቄራ የሚወስደው መንገድ ባለ አንድ አቅጣጫ የተደረገው በአካባቢው እየተገነባ ባለው ህንጻ ምክንያት ለእግረኞች እና ተሽከርካሪዎች ደህንነት ሲባል ነው ሲል ገልጿል።
ኤጀንሲው በአካባቢው ላይ ባለ 35 ፎቅን በማስገንባት ሂደት ላይ የሚገኘው ተቋም ግንባታውን የሚያከናውነው የውጭ ሀገር ተቋራጭ መሰረቱን ለመገንባት ከ20 ሜትር በላይ በጥልቀት የተቆፈረ በመሆኑ ኮንትራክተሮቹ የደህንነት ስጋታቸውን በደብዳቤ መግለጻቸውን አስታውቋል።
አካባቢው ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች የሚያልፉበት እንዲሁም የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መንገድ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም ህንፃውን የሚያስገነባው ተቋም ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት አስፈላጊውን ፈቃድ ካገኘ በኃላ መሠረቱ እስኪጠናቀቅና የደህንነት ስጋቱ እስኪቀረፍ መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ እንዲያደርግ በመጠየቁ መንገዱ ላይ ጊዜያዊ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።
እየተገነባ የሚገኘው ህንፃ ፕሮጀክት በአካባቢው የሚስተዋለውን የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ችግርን በዘላቂነት የሚቀርፍ አድርጎ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
ህንፃውን እየገነባ የሚገኘው ተቋረጭ እና እያስገነባ ያለው ተቋም የህንጻውን የመሰረት ግንባታ በአጭር ጊዜ አጠናቀው ለጊዜው ባለ አንድ አቅጣጫ የተደረገው መንገድ ለትራፊክ ፍሰት ክፍት እንደሚደረግ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡ (TMA)
Source:-tikvahethmagazine

🏗ይህ ከላይ የምትመለከቱት Seismic dampers በመባል ይጠራል ይህም በህንፃዎች ፣ድልድዮች እና በሌሎች ግንባታዎች ውስጥ ለሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያገለግል ነው::
There are many types of dampers for buildings, and damping through friction tends to be one of the most efficient methods of dissipating seismic energy. The friction damper operates by dissipating kinetic energy through friction.
The Dampers allow the building to move elastically and dissipate the energy of the earthquake. This, in turn, produces substantial savings as structural elements can be optimized for cost savings.

🏗በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ/Variation/
🔸ቫሬሽን/variation/ ምን አይነት ትርጉም ሊሰጠው ይችላል?
*በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ(variation) የሚባለው በዋናነት የግንባታ ስራ ጥራትን፣መጠን፣ዲዛይን፣የግንባታ ቁሳቁስ፣የስራ ጊዜ፣የግንባታ ማከናወኛ ቦታ መጠን የመሳሰሉትን የማሻሻል፣የመጨመር ወይም የመቀነስን የሚመለከት የኮንስትራክሽን ውል መሰረታዊ ነጥብ ነው፡፡
*ስለዚህ ቫሬሽን የዋናውን የኮንስትራክሽን ውል ይዘት/object of the contract/ በመጠኑ የመለወጥ ባህሪ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
*PPA 2011 ክሎስ 15.1 ይሄንኑ አረዳድ በሚያጠናክር ሁኔታ ለቫሬሽን ትርጉም ይሰጠዋል፡፡
🔸ቫሬሽን ኦርደር/variation order/ የሚባለውስ ምንድን ነው? ማነው ኦርደር ሰጭው? በቃል ኦርደር መስጠት ይቻላል? በምን አይነት መልኩ ነው ትእዛዝ የሚሰጥ? በዚህ ረገድ ህጉ ምን ይላል?
*ቫሬሽን ኦርደር ከመሀንዲሱ ለተቋራጩ በጽሁፍ የሚሰጥ የስራ ለውጥ ትእዛዝ ነው፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ ለግንባታ ስራው መልካም አፈጻጸም ሲባል የስራ ለውጥ ትእዛዝ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ትእዛዝ መስጠት ይችላል፡፡
*በመጀመሪያ ግን በአማካሪ መሀንዲሱ አማካይነት ለተቋራጩ ስለለውጥ ስራው ባህሪና ምንነት ማሳወቂያ/ኖቲስ/ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ኖቲስ እንደደረሰው ተቋራጩ የለውጥ ስራውን አስመልክቶ ትሮፖዛል ያቀርባል፡፡ፕሮፖዛሉም የጊዜ ማራዘሚያ/ስኬጁል፣የዋጋ ሁኔታን የሚያካትት ይሆናል፡፡(PPA 15.3)
*የስራ ለውጥ ትእዛዝ በጽሁፍ ነው መደረግ እንዳለበት PPA 2011 ክሎስ 15.2 ያስቀምጣል፡፡አንዳንዴ ግን አማካሪ መሀንዲሱ በቃል የቫሬሽን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል PPA 2011 ክሎስ 15.2(a) ላይ ፈቃጅ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን በቶሎ የለውጥ ስራ ትእዛዙ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡
እዚህ ጋር አብሮ የሚታየው ነገር የአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች በጽሁፍ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ይሄውም ስለውሎች በጠቅላላው በሚመለከተው የውል ህግ አንቀጽ 1724 ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*አንድ ውል የሚሻሻለው ደግሞ ከመጀመሪያው ውል ጋር ተመሳሳይ በሆነ ፎርም ነው፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1722 ላይ "ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ(ፎርም) መሰራት አለበት፡፡" በሚል የተደነገገው የሚያስገነዝበውም ቫሬሽን ዋናውን ውል በከፊል የመለወጥ ሁኔታ ስለሚኖረው ከዋናው የኮንስትራክሽን ውል ጋር በተመሳሳይ የአጻጻፍ ፎርም በጽሁፍ መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለዚህ ነው በመርህ ደረጃ ቫሬሽን በጽሁፍ መደረግ አለበት የሚባለው፡፡
🔸የስራ ለውጥ ውል/change agreement/ ምን ማለት ነው? ከህግ አንጻር በዚህ ረገድ ምን ነጥቦች ሊነሱ ይችላሉ?
*PPA 2011 ክሎስ 15.9 ላይ እንደተቀመጠው በየስራ ለውጥ ውል የሚባለው ከቫሬሽን ኦርደር በኋላ አሰሪው/ተወካይ መሀንዲሱ እና ተቋራጩ በጽሁፍ የሚስማሙበት የማሻሻያ ውል ነው፡፡ ሆኖም በዚህ የፒፒኤ ትርጉም ጸሀፊው አይስማማም፡፡ምክንያቱም አማካሪው ስራ ለመቆጣጠር እንጅ ውል ለመዋዋል በአማካሪነት ውሉ ላይ ብዙ ጊዜ ስልጣን አይኖረውም፡፡በተቋራጭና አሰሪ መካከል የተደረገ የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ በሚደረግ ስምምነት/ውል ሊሻሻል ከሚችል በስተቀር አማካሪ መሀንዲሱን ውል እንዲዋዋል እስከመፍቀድ የሚደርስ ትርጓሜ መሰጠቱ ተገቢነት የለውም፡፡
*የስራ ለውጥ ውሎች ቀን፣ቁጥርና ቅደምተከተል ይሰጣቸዋል፡፡(ፒፒኤ15.10)
*ሌላው የስራ ለውጥ ውል ወደኋላ ሄዶ እንደማይሰራና ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ብቻ አስገዳጅ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.10 ላይ ተቀምጧል፡፡
🔸በቫሬሽን የተሰሩ ስራዎች የዋጋ አወሳሰን/Valuation of variation/ በምን ሁኔታ ይከናወናል?
*የተሰራው ተጨማሪ ስራ ከሆነ እና በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ ዋጋ ተተክሎለት ካለ በዚያው የዋጋ ሬት የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(a) ላይ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የሚሰራው ስራ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ያልተካተተ አዲስ የስራ አይተም ከሆነ በመሀንዲሱና ተቋራጩ በስምምነት በወቅታዊ ዋጋ የሚሰላ እንደሚሆን PPA 2011 ክሎስ 15.5(b) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*በቫሬሽን የተካተተው የስራ አይተም ዋጋው በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ላይ የተካተተ ቢሆን እንኳ የተጋነነ ከሆነ በመሀንዲሱ ሊስተካከል እንደሚችል ደግሞ PPA 2011 ክሎስ 15.5(c) ይገልጻል፡፡
*ቫሬሽኑ የተከሰተው በተቋራጩ ጥፋት ከሆነ ደግሞ በአሰሪው ለተቋራጩ ዋጋ አይከፈልበትም በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.5(d) በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
🔸ቫሬሽን እስከስንት ፐርሰንት ይፈቀዳል? በፍርድ ቤቶች አካባቢ ያለው የህጉ አረዳድስ ምን ይመስላል?
*የቫሬሽኑ መጠን ከ25% በላይ በሆነ ጊዜና ከተቋራጩ ጥፋት ባልሆነ ሁኔታ የተከሰተ ከሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ስለብልጫው መጠንና ስለዋጋው ከአሰሪው መስሪያ ቤት ጋር በመመካከር ይወስናል በሚል PPA 2011 ክሎስ 15.7 ላይ ተቀምጧል፡፡
የቫሬሽን መጠን ከመጀመሪያው ዋጋ ከ30% በላይ መብለጥ እንደሌለበት በአስገዳጅ ሁኔታ PPA 2011 ክሎስ 15.8 ላይ ተቀምጧል፡፡
*በዚህ በጀኔራል ኮንዲሽን ከተቀመጠው ተርሰንት/ከገደቡ በላይ በቫሬሽን ስራ ተሰርቶ ቢገኝስ ምን ይሆናል? እንግዲህ በዚህ ረገድ ጀኔራል ኮንዲሽኑም ሆነ አግባብነት ያለው የግዥ አዋጅና መመሪያ ግልጽ ምላሽ አያስቀምጥም፡፡ ሆኖም ግን ተቋራጩ ስራውን እስከሰራው ድረስ አሰሪው አላግባብ በተቋራጩ ድካምና ገንዘብ በልጽጐ እንዲቀር ፈቃጅ ህግ ሊኖር አይችልም፡፡ፍትሀዊም አይሆንም፡፡
*ስለዚህ በዚህ ረገድ በአማካሪ መሀንዲሱ እውቅና እና ትእዛዝ በቫሬሽን ለተሰሩ ስራዎች ከገደቡ በላይ ያለፈ ቢሆንም እንኳ አሰሪው ለተቋራጩ ሊከፍለው እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ5ዳኞች እንደህግ በሚቆጠር ሁኔታ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ይሄውም አስገዳጅ ውሳኔ በሰ/መ/ቁ 71972 ቅጽ 14 ገጽ 25 ላይ ይገኛል፡፡
🔸ቫሬሽን ከሙስና ጋር ምን ያገናኘዋል?
*በዚህ ረገድ የኢፌዴሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የኪራይ ሰብሳቢነት መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በሚል በመስከረም 2010ዓ.ም ባዘጋጀው የውይይት ሰነድ ላይ ቫሬሽን ለሙስና አንዱ ምንጭ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
*ይሄውም ለምሳሌ ያህል የማይጣጣሙ ዲዛይኖችና የስራ ዝርዝር መኖር አንዱ ነው፡፡
*ሌላኛው ደግሞ ሆነ ብሎ የስራ ዝርዝር መዝለል/omission of work item/ ነው፡፡
🔸በአይነቱ አዲስ የሆነ ተጨማሪ ስራ/unrelated and new item of additional work/ ሲያጋጥምስ በየትኛው ህግ የሚታይ ይሆናል?
*በመርህ ደረጃ አሰሪው መስሪያ ቤት በውል ውስጥ የሌሉትን ስራዎች በአዲስ ዋጋ እንዲሰራቸው ስራ ተቋራጩን ለማዘዝ እንደሚችል በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3284(1) ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
#constructionlaw

Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍2