ደረጃ፣ በረንዳ እና የተለያየ ክፍተት ያላቸው ቤቶች ውስጥ የምትኖሩ ወላጆች!
እንደ ኮንዶሚኒየም ያሉ ደረጃ፣ በረንዳ እና ክፍተት ያላቸው ቤቶች ውስጥ የምትኖሩ ወላጆች ልጆቻችሁ ላይ የመውደቅ አደጋ እንዳይደርስ ከፍ ያለ ጥንቃቄ አይለያችሁ።
ዛሬ ቦሌ አራብሳ አካባቢ አንድ ህፃን ከስድስተኛ ፎቅ በመስኮት ወድቆ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፣ ከዚህ ቀደምም እዚሁ ቦታ ተመሳሳይ አደጋ ደርሷል። ከአፓርትመንት ላይ በመውደቅ የሞት አደጋ ያጋጠመው ህፃን ታሪክን ከጥቂት ወራት ሰምቻለሁ።
ስለዚህ መስኮቶች፣ የበረንዳ ድጋፎች እና መወጣጫዎች ህፃናትን በማያሳልፍ/በማያሾልክ መልኩ መከላከያ እንዳላቸው አረጋግጡ። መንግስትም የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለህብረተሰቡ ከማስረከቡ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ቢያደርግ እላለው። ነዋሪዎችም በህብረት እንዲህ አይነት የማጠናከርያ ስራዎችን መስራት ይኖርባቸዋል።
ካለፈ በሗላ ከመፀፀት አሁኑኑ ማስተካከያ ማድረግ ይሻላል።
Source : eliasmeseret
#እትዮ_ኮንስትራክሽን😭😭
https://t.me/ethioengineers1

#የአገር ውስጥ ጦርነት እና የኮንስትራክሽን እቃወች የዋጋ ንረት ከኮንስትራክሽን ውሎች አንጻር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ሊባል ይችላል? By:Gubaie Assefa(Construction Lawyer,0910217422)
👉ሀገር ውሰጥ ጦርነት በባህሪው ግጭት በለባቸው አካባቢወች የኮንስትራክሽን ስራወችን የማስቆም እና የተጀመሩ ግንባታወችን እስከመውደም እና የግንባታ ቁሳቁስ መጥፋትን ሊያስከትል እንደሚችል ይታመናል፡፡የአገር ውስጥ ጦርነት ባለበት አገር ውስጥ ሆኖ በቀጥታ ግጭት የሚካሄድበት ቦታ ባይሆን እንኳ በጦርነቱ ምክንያት በኮንስትራክሽን ስራወች ላይ የተለያ ጫና መፈጠሩ አይቀርም፡፡
#በዚህም ምክንያት የውል ህግ፣የግዥ ህግ፣ፊዲክ እና አገራችን ለኮንስትራክሽን ውሎች የምትጠቀምባቸው ጀኔራል ኮንዲሽኖች የሀገር ወስጥ ጦረነትን በተመለከተ ድንጋጌወችን አካተው ይገኛሉ፡፡ይህን የህግና የውል ሁኔታ በአግባቡ ተገንዝቦ መፍትሄ መስጠት ውልን ከሚያስተዳድሩ አካላት የሚጠበቅ በመሆኑ እና በጉዳዩ ላይ ለበለጠና ለዳበረ ውይይት መነሻ ግንዛቤ መፍጠር ደግሞ ከዘርፉ ባለሙያወች የሚጠበቅ በመሆኑ ይህ ጸሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡
****
#በውል ህግ በተለይ በፍትሐብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1791(1) ላይ ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛው እንደውሉ ያልፈጸመ እንደሆነ ጥፋት ባያደርግ እንኳ ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን የጉዳት ኪሳራ የመክፈል ሀላፊነት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡
#በዚሁ አንቀጽ 1791(2) ላይ ደግሞ እንደውሉ ያልፈጸመው ወገን ግዴታውን ያልፈጸመበትን በቂ ምክንያት ማቅረብ የቻለ እንደሆነ እና ይሄውም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መሆኑ የተረጋገጠለት እንደሆነ የውሉ አለመፈጸም ከሚያመጣው ሀላፊነት ሊድን እንደሚችል ያስገነዝባል፡፡
#ስለዚህ ከአቅም በላይ የሆነ ሀይል(Force majeure) ሲባል ምን ማለት ነው?የሀገር ውስጥ ጦርነትስ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል ወይ የሚለውን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
****
#ከአቅም በላይ የሆነ ሀይል ተከስቷል የሚባለው ተቋራጩ ሊያስበው የማይችል እና ግዴታውን ከመወጣት ፍጹም በሆነ ሁኔታ የሚከለክለው ነገረ ሲከሰት ስለመሆኑ የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ አንቀጽ 49 ያስቀምጣል፡፡
#በዚሁ በፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ላይ አለማቀፍ ወይም የሀገር ውስጥ ጦርነት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርገው እንደሚቆጠሩ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
#ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ለሚለው በክሎስ 19 ላይ ትርጉም አስቀምጦለታል፡፡በዚህም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ልዩ ሁኔታ ሲሆን ከተዋዋዮች ቁጥጥር ውጭ የሆነ፣ተዋዋዮች ውል ውል ከመግባታቸው በፊት ሊያውቁትና ሊያስቡት የማይችሉት፣ከተከሰተ ተዋዋዮች ሊያስወግዱት የማይችሉት እና ክስተቱ በአንደኛው ወገን ችግር ያልመጣ መሆን ይገባዋል፡፡
#ይሄው ፊዲክ ሬድ ቡክ ጦርነት፣የሀገር ውስጥ ጦርነት እና ሽብር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርገው እንደሚወሰዱ ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡
#በተጨማሪም ፒፒኤ 2011 ክሎስ 18 ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያትን በሚመለከት አስቀምጧል፡፡በዚህም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት ከተቋራጩ ቁጥጥር ውጭ የሆነ እና የውል ግዴታውን ለመወጣት የማያስችለው ፍጹማዊ ሁኔታ ነው፡፡
#ፒፒኤ 2011 የሀገር ውስጥ ጦርነትን ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አድርጐ ያስቀምጠዋል፡፡
****
#ስለዚህ የሀገር ውስጥ ጦርነት ከኮንስትረክሸን ውሎች ጋር በተየያያዘ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ ይወሰዳል ከተባለ ሂደቱና ውጤቱ ምን ይመስላል የሚለውን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
#ሂደቱን በተመለከተ ጀኔራል ኮንዲሽኖችም ሆነ የህትሀብሄር ህጉ በተለይ የውል ግዴታየን ለመፈጸም የማያስችል ከአቅም በላይ የሆነ ሀይል ገጥሞኛል የሚለው ተዋዋይ ወገን
ሁኔታውን ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን ማሳወቅ ወይም ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፣
ሁኔታውን ተቋቁሞ የውል ግዴታውን ለመወጣት ጥረት ማድረግ ይኖርበታል
ከአቅም በላይ የሆነው ሁኔታ የሚያስከትለውን ጉዳት መጠን በሚችለው መቀነስ ይጠበቅበታል፡፡
#ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መከሰቱ ከተረጋገጠ ተዋዋዩ ወገን ግዴታውን አልፈጸመም በሚል ለሌላኛው ተዋዋይ ወገን ኪሳራ ለመክፈል የሚገደድበት አግባብ አይኖርም፡፡እንደውም ተቋራጩ እንደውሉ ሁነኔታ በገጠመው ከአቅም በላይ የሆነ መክንያት የደረሰበትን ተጨማሪ ወጭ እንደ ሰራተኛ ዲሞቢላይዜሽን ያሉ ወጭወችን ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፡፡በተጨማሪም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ለመስጠት በቂ ምክንያት ይሆናል፡፡እንደውሉ ልዩ ሁኔታ ውል ለማቋረጥም ምክንያት ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡
****
#ሌላው የኮንስትራክሽን እቃወች የዋጋ ጭማሪ/መናር በተለይ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ እንደሚቆጠር በግልጽ ካልጠቀሱ በስተቀር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ እንደማይቆጠር የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ አንቀጽ 49 ይደነግጋል፡፡ፒፒኤ 2011 ደግሞ የዋጋ መናር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ አይወሰድም በሚል ያስቀምጣል፡፡
#በመሰረቱ የግንባታ እቃወች ዋጋ ንረት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ተደርጐ የማይወሰድበት መነሻው በኮንስትራክሽን ውሎች የዋጋ ንረት ማካካሻ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ምክንያታዊ ግምት አለ፡፡ነገር ግን በአንዳንድ ክልሎች የኮንስትራክሽን እቃወች ዋጋ ንረት ማካካሻ የማይተገበርበት ሁኔታ በመኖሩ ተቋራጮችን ለከፍተኛ ኪሳራ ይዳርጋል፡፡
#ስለዚህ ተቋራጮችም ሆነ አሰሪዎች በሀገራችን በቅርብ ጊዜያት የተከሰቱት የሀገር ውስጥ ጦርነትና የኮንስትራክሽን እቃወች የዋጋ ንረት የሚኖራቸውን የውልና የህግ ውጤት በመረዳት የተጀመሩ የመሰረተልማት ግንባታወች እንዲጠናቀቁ ለማስቻል በሚያመች መንገድ ህጋዊና ሚዛናዊ የውል አስተዳደር ስራወችን በብስለት መፈጸም አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡
አመሰግናለሁ!!
https://t.me/ethioengineers1 Un

Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍2
Wuhalek with Architect Rahel Shawel and Dawit Benti 28-05-14
<unknown>
#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_የውሃልክ_አድማጮቻችን…
የኢትየጵያውያን በሆነው ቤተ-ሬዲዮ "ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8" የዓየር ሞገድ ላይ በዛሬው ዕለት ጥር 28/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ፪ እስከ ፫ በተደመጠው "ውሃልክ" የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ፤ በዛሬው ዕለት አንድ ውድ አርኪቴክት ተዋውቀናል። በቅድሚያ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መ/ር የሆኑትን አርኪቴክት ዳዊት በንቲ ኢረናን ከልብ አመስግኑልን፤ እናመሠግናለንም።
በመ/ር እና አርኪቴክት ዳዊት በንቲ ግብዣ በቀጥታው ስርጭት የተገኘችው የዛሬዋ እንግዳችን በአህጉራችን ብሎም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስመጥር እና ታዋቂ የሆችው አርኪቴክት ራሄል ሻውል ናት።
የሥነ-ሕንፃ ባለሞያዋ ራሔል... በሀገር አና አህጉር ያልተገደበ እምቅ የሞያ አቅም ያላት!፤ በተግባር ተፈተኖ የዳበረ ጠንካራ የሥራ ተነሳሽነት እና ተሞክርዎን የታደለች፤ ፈፅሞ ከማያጥጥ፣ ከማያባራ እና ጥልቅ ከሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት የተጋመደች፤ ደማቅ ፈገግታ የማይለያት "የአራዳ ልጅ" ስትሆን ተጨልፎ እና ተዝቆ ከማያልቀው፣ በውብ ገጠመኞች ከተኳለው እና ፈፅሞ ከማይዘነጋው የት/ቤት፣ የቤተሠብ እና የሞያ ጓዶቿ ድምር ወግ የፈቀደችውን ተውሳ እስክንደነቅ አጨዋውታናለች። ለዚህም ክብረት ይስጥልን አልን።
#ውድ_አድማጮች...
ስለ ውይይቱ ፍሬ-ነገር ብዙ ከምንላችሁ እናንተው ተገባብዛችሁ እንድታደምጡት እነሆ ብለናል።
#ሁሌም_ቢሆን_የማድመጥ_ሚናችሁ_አይለየን።
#ውሃልክ_ሚዲያ_እና_ኮሚዩኒኬሽን።

❤1
የበጎ ፍቃደኝነት ጥሪ
CALL FOR VOLUNTEER
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር በአገራችን በተከሰተው ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በተሻለ ሁኔታ ዳግም እንዲገነቡ የሞያዊ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከዚህም አንዱ አካል የሆነው የትምህርት ቤቶች እድሳት (3000 ት/ቤት) እና ዳግም ግንባታ(1100 ት/ቤት) ለማከናወን ከትምህርት ሚኒስትር ጋር በመስራት ላይ ይገኛል።
ስለዚህም ከማህበሩ ጋር በበጎ ፍቃደኝነት መስራት የምትፈልጉ የማህበሩ አባላት፣ ድርጅቶች እና የአላማው ደጋፊዎች ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የፍላጎት መግለጫውን በመሙላት እንድትመዘገቡ ማህበሩ ጥሪ ያሰተላልፋል።
ማህበሩ የለያቸው ስራዎች
👉የቅድመ ጥናት ስራዎች ( Assessment/ site Reconnaissance, feasibility study, Geotechnical investigation…)
👉ዲዛይን ስራዎች (Structural design, Sanitary and other engineering designs)
👉በጥናቶች መሰረት የግንባታ መፍትሄ ማዘጋጀት(Remedial Measures and construction methodologies… )
👉የሰነድ ዝግጅቶች (Preparation of Bill of quantities, Cost Estimation detailed specification, cost estimation and contract documents)
👉የክትትል እና ጥራት ቁጥጥር (The supervision & quality assurance)
👉ፕሮጀክት ማኔጀመንት (project management)
👉ሌሎች ድጋፎች____
በተጨማሪ ሁሉም ተመዝጋቢ የሚከተሉትን መረጃዎች በኢሜል eacetraining@gmail.com subject label “Volunteer” በሚል እስከ የካቲት 07 2014 መላክ አለባቹሁ። ሁሉም ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ባለሞያ/ድርጅት የሚያሳትፍ ስለሆነ ማህበሩ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ ያስተላልፋል።
መመዝገቢያ ማስፈንጠሪያ፡ https://forms.gle/QdVqejok6QoGNfdHA
ግለስብ
መታውቂያ (አባል ላልሆኑ)፣ የስራ ልምድ (ለሁሉም ፣ካለ) እና የትምህርት መስረጃ (አባል ላልሆኑ)
በድርጅት
ንግድ ፍቃድ፣ ቲን፣ የስራ ልምድ (ካለ) እና ብቃት ማረጋገጫ (ለአማካሪ እና ኮንትራክተር)
ለተጨማሪ መረጃ
eacecivil@gmail.com or 0115521248 መጠየቅ ይችላሉ። www.eacecivil.org

Google Docs
የበጎ ፍቃደኝነት ጥሪ CALL FOR VOLUNTEER
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር በአገራችን በተከሰተው ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በተሻለ ሁኔታ ዳግም እንዲገነቡ የሞያዊ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከዚህም አንዱ አካል የሆነው የትምህርት ቤቶች እድሳት (3000 ት/ቤት) እና ዳግም ግንባታ(1100 ት/ቤት) ለማከናወን ከትምህርት ሚኒስትር ጋር በመስራት ላይ ይገኛል።
Individual Member Form
Individual Member Form
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
የአዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ መኪና ማቆሚያ ፦
ነገ እንደሚመረቅ የሚጠበቀው አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ከምድር በታች 4 ወለል የመኪና ማቆሚያ እንዳለው እና እስከ 1500 መኪና ማቆም እንደሚችል ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ባንኩ እንደገለፀው ፥ በሁለተኛው ምድር ቤት የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ በዓይነቱ ለየት ያለና ዘመናዊ ሜካኒካል መኪና ማቆሚያ ነው።
ይህም በአንድ ጊዜ 541 መካከለኛ መኪኖችን ደራርቦ ማቆም እና በካርድ መኪኖችን መጥራት የሚያስችል መሳሪያ የተገጠመለት መሆኑ ተብራርቷል።
አውቶማቲክ መሳሪያው ብልሽት ሲኖር የሚጠቁም እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጠገን የሚያስችል ሲስተም እንዳለውም ተገልጿል።
የታዋቂው የቻይናው " ዳያንግ ፓርኪንግ " ስሪት የሆነ መሳሪያ እንደተገጠመለት የተገለፀው ይህ መካኒካል መኪና ማቆሚያ በጥቂት ቦታ ብዙ መኪኖችን ማቆም የሚያስችል የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ባንኩ ይፋ ያደረገው መረጃ ያሳያል።
Source:- tikvahethiopia

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ አመነጨ ። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከተሳካ የኤሌክትሪክ ሀይል ሙከራ ቡኋላ ወደ ሙሉ በመሉ የኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ተሸጋግሯል። ግድቡ በዘንድሮው አመት ያመነጨዋል ከተባለው 300 ሜጋዋት ውስጥ 180 ሜጋውቱ አምንጭቶ ከጣና በለስ ቅርጫፍ መስመር ጋር እየሰራ ሲሆን። ከዋናው የአዲስ አበባ ቅርጫ ጋር ተገናቶ መሉ መሉ በስራ መሆኑን አረጋግጫለሁ።
እንኳን ደስ ያላችሁ ውድ የethio construction ቤተሰቦቻችን !
ሱሌማን አብደላ
https://t.me/ethioengineers1
እንኳን ደስ ያላችሁ ውድ የethio construction ቤተሰቦቻችን !
ሱሌማን አብደላ
https://t.me/ethioengineers1
🏗በግንባት እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ምንድነው ?
በግንባታ ግብዓቶች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ነጋዴዎች እየገለጹ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
በተለይ በቤት ክዳን ቆርቆሮ እና በሚስማር ምርቶች ላይ በ2 ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።
ለጋዜጣው ቃል የሰጡ ነጋዴዎች ፥ በቆርቆሮ ምርት ላይ ከ150 ብር በላይ ጭማሪ መታየቱን ገልፀዋል በአንድ ሳምንት ውስጥ ከነበረበት 250 ብር ወደ 400 ብር ከፍ ማለቱን አስረድተዋል።
ከዚህ በፊት 500 ብር የነበረው ጋልቫናይዝድ የቤት ክዳን ቆርቆሮ በአሁኑ ወቅት ከ1,000 ብር በላይ እየተሸጠ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
በሚስማር ዋጋ ላይ በካርቶን እስከ ከ200 ብር በላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። 4 መቶ ብር የነበረው የአንድ ካርቶን ሚስማር ዋጋ በ2 ሳምንታት ውስጥ 6 መቶ ብር መድረሱን ይገልጻል፡፡ በየቀኑም የዋጋ ጭማሪ እያሳየ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
እንደ ቱቦላሬ እና አርማታ ብረት ያሉ የግንባታ ምርቶች ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየታቸውን ተገልጿል።
ከፍተኛ እጥረት እንዳለበት የሚታይበት የሲሚንቶ ምርትም በየጊዜው ጭማሪ እያሳየ ነው፡፡
ቃላቸውን ለጋዜጣው የሰጡ ነጋዴዎች የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ እስከ 720 ብር መድረሱንና በአንድ ወር ውስጥም ከ40 በመቶ በላይ ጭማሪ ማሳየቱን ገልፀዋል።
በምርቶቹ ላይ ያለው ዋጋ እንደ ሌሎች መጠነኛ ጭማሪ እየታየ የመጣ ቢሆንም፣ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ ያለው የዋጋ ጭማሪ ግን ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የጭማሪው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ እንዳልቻሉ ነጋዴዎቹ ለጋዜጣው ተናግረዋል።
#ሪፖርተር
Source:-tikvahethiopia
#ethioconstruction

#AlebelDestaCAE
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ለሚገነባው መታሰቢያ ሀውልትና ፖርክ የንድፍ ውድድር ኢትዮጵያዊው አለበል ደስታ አማካሪ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ተገልጸል።
በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ ለሚሰራው ይሄው የመታሰቢያ ሀውልትና ፖርክ በ4 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ የታሰበ ሲሆን የማስታወሻ፣ የአረንጓዴ ቦታና የውጪ መሰብሰቢያ ስፍራ ያካተተ ነው። ድርጅቱ ውድድሩን በማሸነፉ የ10,000 ዶላር ሽልማት አግኝቷል።
📸 Alebel Desta CAE
Source:-tikvahethmagazine