SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
As engineer, we have heard the terms "one way slab" and "two way slab". The major difference between them is the placement of steel and encountered bending forces. In one way slab, main reinforcement is provided on one side only because bending moment occurs on one direction only i.e., shorter direction, whereas in two way slab main reinforcement is provided in both sides because moment is generated on both sides.
Apart from that, if Longer to shorter side value is greater than 2, it will be one way slab. If value is less than 2 it will be two way slab.

In two way slab, main bars are cranked which are also called as cranked bars. These bars are cranked at an angle of 45 degrees. And these are placed alternatively in the slab. Moreover, to counter the shear forces at corners or supports, extra bars are provided.

Attached picture is a two way slab and reinforcement details are illustrated as well.


https://t.me/ethioengineers1
BeGet Engineering Plc.

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች:
በ CENGG Software Solution የሚሰጡትን ስልጠናዎች በሙሉ የአድራሻ ለውጥ በማድረግ በ BeGet Engineering Plc. ስር በተደራጀ, በጥራትና በምቾት መገናኛ ቅርንጫፍ እየሰጠን እንገኛለን።
ቀድሞ ስልጠና ላይ ትኩረት ሰጥተንበት የነበረውን አሁን ወደ Consulting ሰላሳደግነው የበለጠ ተጠቃሚ ያረጋችሁዋል።

https://t.me/BeGetEngineering
በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/
======**=======
#በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡
#በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡
**
#ግዚያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance/
#ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
#ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡
#እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡
#በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡
#ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡
#እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡
**
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡
#ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡
#በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡
**
#ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/
-በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
**
#የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/
#የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
#የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡
#በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
#henoktayelawoffice

https://t.me/ethioengineers1
👍3❤1
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የምህንድስና ባለሙያዎች ስልጠና ላይ በአዳማ ከተማ:

1. 2in1 Package [ Civil 3D, Revit ]
2. 4in1 Package [ AutoCAD ,Sap, Etabs, Safe]


https://t.me/BeGetEngineering
BeGet Engineering Plc.

● መጋቢት 14/2014 የሚጀምር አዲስ ፕሮግራም
● New schedule starting March 23/2022
( Registration is active)

📌 መገናኛ ማራቶን ህንፃ ቢሮ ቁ. 614
📲 ስልክ፦ 0911890392 / 0944186744


https://t.me/BeGetEngineering
በኮንስትራክሽን ውል አሰሪው የተቋራጩን ክፍያ አዘግይቶ መክፈል ጉዳይ/Delay payment/

# የኮንስትራክሽ ውል መሰረታዊ ባህሪው ሲታይ በዋናነት አሰሪና ተቋራጭን በተዋዋይነት የሚይዝ ሲሆን ጉልህ የሆነው ግዴታቸው ሲታይ ደግሞ ተቋራጩ በውሉና ዲዛይኑ/ስፔስፊኬሽኑ መሰረት ግንባታውን የማከናወን ሀላፊነት የሚኖርበት ሲሆን ክፍያ የመክፈል ጉዳይ ደግሞ ለአሰሪው ዋናውና ትልቁ ግዴታው ነው፡፡የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610፣3019እና 3020 እንዲሁም 3244 ተገናዝቦ ሲታይ ይሄን ሁኔታ ያስገነዝባል፡፡
# የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ "ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም" በሚል የተደነገገው በኮንስትራክሽን ውል ለተቋራጩ የሚከፈለው ክፍያ ጉዳይ የውሉ መሰረታዊ ነጥብ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ስለክፍያ አይነቶች የህጉን ጉዳይ ወደፊት በሌላ ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡
# አሰሪው ለተቋራጩ ክፍያ የመክፈሉን ሁኔታ ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት አይችልም፡፡
# አማካሪ መሀንዲሱ በተለይ ከተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ የማረጋገጥና የማጽደቁን ስራ በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(d)
# አሰሪው መስሪያ ቤት ደግሞ በአማካሪ መሀንዲሱ የጸደቀ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(e)
# አማካሪ መሀንዲሱ በተቋራጩ የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሰባት ቀናት ውስጥ የማረጋገጥና የማጽደቅ ስራ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*በዚህ ረገድ የመመሪያው አንቀጽ አንቀጽ 28.5(f) ግልጽ ምላሽ አስቀምጧል፡፡
*ይሄውም ተቋራጩ በዚህ ምክንያት ከአሰሪው ላይ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ የጠየቀ እንደሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ይህን ተጨማሪ ክፍያ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
*ሆኖም ግን አማካሪ መሀንዲሱ ለሚሰጠው አገልግሎት ከሚከፈለው ክፍያ በላይ የሆነ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነት አይኖርበትም፡፡
*በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636 የአማካሪ መሀንዲሱን የእውቀት ስራ ውል ግዴታ ይደነግጋል፡፡ይሄውም አማካሪው "የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሰሪው በኩል ስራ ተቋራጩን ሀላፊነት አይነካውም" በሚል ተቀምጧል፡፡(2636(2)) እንደዚሁም አማካሪው ሳይሰራ ከመቅረቱ የተነሳ ወይም በአሰሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ስራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል እንደሚችል የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636(3) ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ አማካሪው ክፍያ የማረጋገጥ እና የማጽደቅ ስራውን በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባለማከናወኑ አሰሪው ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል በተቋራጩ የተጠየቀ እንደሆነ አማካሪው አጥፊ ነው ሊባል ያስችለዋል ማለት ነው፡፡
#አሰሪው በአማካሪው የጸደቀው የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14 ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*አሰሪው ያለበቂ ምክንያት ክፍያ ያዘገየ እንደሆነ ለተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ ለመክፈል ሀላፊነት እንደሚኖርበት የፌዴራል የግዥ መመሪያ/Federal public procurement directive/ አንቀጽ 28.5(g) ይደነግጋል፡፡
*ተጨማሪ ክፍያ ሲባልስ ምንን ያጠቃልላል? የሚለው ሲታይ በዋናነት ወለድ የመክፈል ሀላፊነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3268 ተቋራጩ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብት ይሰጠዋል፡፡የወለዱ መጠንም በውል ያልተወሰነ የሆነ እንደሆነ በአንቀጽ 1751 መሰረት ህጋዊ ወለድ በአመት 9(ዘጠኝ) በመቶ ሆኖ የሚሰላ ይሆናል፡፡
*ሌላው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ክፍያን ማዘግየት የሚኖረውን ውጤት አስመልክቶ የቅጣት ስምምነት/penality clause/ ያካተቱ ከሆነ የፍትሀብሄር ህጉ አንቀጽ 1889 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ እውቅና ስለሚሰጠው እና በአንቀጽ 1731 መሰረት ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ስለሚቆጠር ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
*አንዳንድ ክልሎችም በዚህ ረገድ በግዥ መመሪያቸው ላይ ዝርዝር ውጤቱን ያስቀምጣሉ፡፡
*አሰሪው ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ከወለድ ባለፈ ሌላም ጉዳት የደረሰበት ተቋራጭስ ከጉዳቱ ጋር እኩል የሆነ ኪሳራ ሊከፈለው አይገባም ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡ምክንያቱም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2091 እና 1790(2) ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ መሆኑ በህግ የታወቀ ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሳ ሀላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት በሚል በግልጽ ይደነግጋል፡፡
#በአጠቃላይ አሰሪው በማናቸውም ምክንያት የተቋራጩን ክፍያ በሚያዘገይበት ጊዜ ተቋራጩን ለውድቀት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ምክንያቱም በሀገራችን አብዛኛው ተቋራጭ ድርጅት የፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስርአት የለውም፡፡ተቋራጮቻችን የገንዘብ አቅማቸውም ደካማ ነው፡፡አብዛኛው ተቋራጭ ለአንዱ ፕሮጀክት የሚወስደውን የቅድሚያ ክፍያ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ይጠቀምበታል፡፡በዚህ ምክንያት አንድ ተቋራጭ ሲከስር ብዙ ሰራተኛ እንደሚበተን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ በአሰሪዎች በኩል ተቋራጮች የሰሩበትን ክፍያ በወቅቱ እና በተሰራው ስራ ልክ አንዲከፈላቸው ለማድረግ እና በህጉ የተቀመጠው የክፍያ የጊዜ ገደብ እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም ወስዶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

By:Gubaie Assefa(Construction Lawyer

https://t.me/ethioengineers1
👍1
🏗የሲቪል ምህንድስና መሰረታዊ እውቀት ሲቪል መሐንዲሶች እንደ የመንገድ ፣ የአውሮፕላን ማረፊያ ፣ ዋሻዎች ፣ ግድቦች እና ድልድዮች ያሉ ወሳኝ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ዲዛይን ያደርጋሉ። እንዲሁም የፕሮጀክት ግንባታ እና ጥገናን ይቆጣጠራሉ። ከወጪ ሂሳብ እስከ ጂኦሎጂ ድረስ አጠቃላይ የክህሎት ስብስብ ሊኖራቸው ይገባል።
ብዙ የሲቪል መሐንዲሶች በግንባታ ውስጥ በጣም የተግባር ሚና የሚጠይቁ ሥራዎች አሏቸው ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለተቆጣጣሪ እና ለአስተዳደር ችሎታዎች የበለጠ ክብደት ያላቸው ቦታዎች ሊኖራቸው ይችላል። ስለዚህ የሲቪል መሐንዲሶች የሲቪል ምህንድስና መሰረታዊ ነገሮችን ማወቅ አለባቸው።
ሲቪል መሐንዲሶች ብዙውን ጊዜ በጣም የተወሳሰቡ ፕሮጄክቶችን ማስተዳደር አለባቸው ፣ ይህም ብዙዎች ከበርካታ አካባቢዎች በአንዱ ውስጥ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። ስኬታማ የሲቪል መሐንዲስ ለመሆን ሁሉንም መረጃ እና አስፈላጊ ክህሎቶችን እና ጥራቶችን እና የሲቪል ምህንድስና መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ።
* * *
የሲቪል ኢንጂነሪንግ መሰረታዊ ቴክኒካዊ ችሎታዎች
አንድ ጥሩ ሲቪል መሐንዲስ የምህንድስና ችግሮችን የሚለይ እና የሚፈታ የሂሳብ እና የፊዚክስ ደረጃ ሊኖረው ይገባል።
ሲቪል መሐንዲሶችም በዲዛይን ቴክኒኮች የተካኑ እና ከካርታዎች ፣ ስዕሎች ፣ ሞዴሎች እና ከ CAD ሶፍትዌሮች ጋር መሥራት አለባቸው። ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን መተንበይ እና ለእነሱ መፍትሄ መፈለግ መቻል አለባቸው።

እያንዳንዱ የሲቪል መሐንዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ከፍተኛ የቴክኒክ ክህሎት ሊኖረው ይገባል።
የሚከተሉት ሊያውቋቸው የሚገቡ አንዳንድ ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች ናቸው።

👉የሂሳብ ችሎታዎች
ሲቪል መሐንዲሶች በሂሳብ ውስጥ የካልኩለስ ፣ ትሪጎኖሜትሪ እና ሌሎች የላቁ ርዕሶችን ለሥራ ትንተና ፣ ዲዛይን እና መላ መፈለግ መርሆዎችን ይጠቀማሉ።

👉የግንባታ ቁሳቁሶች ሙከራዎች( Building material test)
ጤናማ የሲቪል መሐንዲስ ስለ የግንባታ ዕቃዎች የተለያዩ ፈተናዎች ትክክለኛ ዕውቀት ሊኖረው ይገባል። አንዳንድ ትክክለኛ ሙከራዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
Concrete Test: Slump test, compression test, split tensile test, soundness, etc.
Soil Test: Core cutter test, compaction test, sand replacement test, triaxial test, consolidation test, etc.
Bitumen Test: Ductility test, softening point test, gravity test, penetration test, etc.

👉የአፈር ምርመራ(Soil Investigation)
ግንባታ ከመጀመሩ በፊት የአፈርን ሰፈራ እና መረጋጋት(settlement and stability) ለመወሰን የተለያዩ የአፈር ምርመራዎች ይካሄዳሉ። ስለዚህ እንደ ሲቪል መሐንዲስ በቦታው የተከናወኑትን የእነዚህ ምርመራዎች በቂ እውቀት ሊኖርዎት ይገባል።

👉የዳሰሳ ጥናት መሣሪያዎች አጠቃቀም(surveying Instrument)

እንደ አጠቃላይ ጣቢያ(Total Station) ፣ ቴዎዶላይት ፣ ወዘተ የመሳሰሉት የቅየሳ መሣሪያዎች አጠቃቀምም ለእያንዳንዱ የሲቪል መሐንዲስ ግዴታ ነው። እነዚህ መሣሪያዎች ምልክት ለማድረግ እና ለመለካት ያገለግላሉ።

👉በግንባታ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መደበኛ ኮዶች( Building codes and standards)
እያንዳንዱ አገር ከግንባታ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት መመዘኛዎች አለው። በመደበኛ ኮዶች ውስጥ የተጠቀሱትን ሁሉንም ህጎች እና ሂደቶች በመከተል ሁሉም አዲስ ግንባታ መደረግ አለበት። ያለበለዚያ የአንድ መዋቅር ውድቀት ዕድሉ ሁል ጊዜ ከፍ ያለ ይሆናል።

👉bar bending schedule ለሲቪል መሐንዲሶች እና ለሲቪል ምህንድስና መሠረታዊ ነገሮች አስፈላጊ ሰንጠረዥ ነው። እንደ የመቁረጥ ፣ ማጠፍ ፣ የመታጠፍ መጠን ፣ ወዘተ የመሳሰሉትን የ RC structure የማጠናከሪያ ስሌት ይሰጣል።
ስዕል እና ዲዛይን( drawing and design
ቀጣይነት ላለው ፕሮጀክት drawing and design ዋና ቁልፎች ናቸው። ለዚያ ፕሮጀክት የሚያስፈልጉትን ሁሉንም መመዘኛዎች ይሰጣል። እያንዳንዱ የጣቢያ መሐንዲስ የእንደዚህ ዓይነቶቹ ስዕሎች እና ንድፎች የመተንተን ኃይል ሊኖረው ይገባል።

👉ግምት እና ሂሳቦች( estimations and bills)
በግንባታ ፕሮጀክት ውስጥ በሲቪል መሐንዲስ ግምት እና ሂሳቦች መዘጋጀት አለባቸው።

👉የጥራት ቁጥጥር( quality control)
የጥራት ቁጥጥር ተጨማሪ ወጪዎችን በመቀነስ የፕሮጀክቱን ትርፍ ያረጋግጣል። ስለዚህ የጥራት ቁጥጥር መሰረታዊ ዕውቀት ሊኖርዎት ይገባል።

👉በመስክ ላይ አስተዳደር( On site management)
የቅፅ ሥራ ፣ የማጠናከሪያ ፣ የደህንነት እርምጃዎች ፣ ወዘተ ዕውቀት እንዲሁ አስፈላጊ ገጽታ ነው።
ይቀጥላል...

https://t.me/ethioengineers1
👍1
Forwarded from Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700 (ምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ)
Wuhalek_about_Mechanical_Engineering_with_Engineer_Mekonen_Getachew.MP3
54.6 MB
#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_የውሃልክ_አድማጮቻችን...

#ቀደም_ባሉት_ጊዜያት "ወደ ተግባረ-ዕድ ወይም ወደ ሞያ ማበልፀጊያ ተቋማት የሚቀላቀሉት በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እንደሆኑ" ይነገራል።

#በዛሬው_ዘመንስ?

በውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ... ስለ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ እያነሣሣን እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር የተጨዋወትንበትን የዛሬውን ፕሮግራም እነሆ ዳግም ታደምጡልን ዘንድ ስንጋብዛችሁ እንደሁልጊዜው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

#ውድ_አድማጮች...
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን_እንገንባ!
#ውሃልክ_ሚዲያ_እና_ኮሚዩኒኬሽን።
🏗የዓለማችን አምስቱ ውብ
ከተሞች


👉በአሁኑ ወቀት በበርካታ የአለማችን በከተሞች ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

👉እነዚህ ተግባራትም ከተሞችን ከብክለትና መሰል ችግሮች በመታደግ አረንጓዴ እና ጤናማ የሆኑ ከተሞችን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ዋነኛ አላማ ያደረገ ነው፡፡

👉እኛም በአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ ውጤታማ ስራ የሰሩና ለሌሎች የአለማችን ከተሞች ተሞክሮ መሆን የቻሉ 5 ከተሞችን በደረጃ ልናስተዋውቃችሁ ወደናል::

🔸በአለማችን የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ውጤታማ ስራ ከሰሩ ከተሞች መካከል በ5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው በአሜሪካን ሀገር የምትገኘው ሳንፍራንሲስኮ ከተማ ናት ከተማዋ በዘርፉ ከሰራቻቸው ስራዎች መካከልም በሀገሪቱ ከሚገኙ ከተሞች በፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በኤሌትሪክ ሀይል የሚሰሩ የሀይል አማራጮችን በመጠቀም ተጠቃሽ ናቸው ይህም ጠንካራ ህግ ተፈፃሚ ከማድረግ ባሻገር ህብረተሰቡ ይህን ለመተግበር በአመለካከት የተለወጠ መሆኑ ነው ባጠቃላይ በከተማዋ 40 በመቶ የሚሆነው ክፍልም በአረንጓዴ ስፍራ የተሸፈነ ነው::

🔸በአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ በ4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ በእስያ አህጉር የምትገኘው ሲንጋፖር ከተማ ናት ይህች ከተማ ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል መልኩ መሰረታዊ የከተማ ልማት ጥያቄዎችን መፍታት የቻለች ከተማ ናት በከተሞቻቸው የሚሰሩ ስራዎች ለመጠበቅ ጠንካራ ህግ ከማርቀቅ ጎን ለጎን በአረንጓዴ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ በተለይ ደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻን መልሶ አገልግሎት ላይ እንዲውል በማድረግ ረገድ ለሌሎች ከተሞች ተምሳሌት ሆነዋል፡፡
*በከተማዋ ወደ ሰላሳ የሚጠጉት አረንጓዴ የህዝብ ፓርኮችም ከተማዋ ለአረንጓዴ ልማት የሰጠችውን ትኩረት ማሳያዎች ሲሆኑ በከተማዋ ሰፋፊ ጥብቅ ደኖችም ይገኛሉ፡፡
*በቅርቡም ከተማዋ ተግባራዊ እድርጋ ውጤት ባስመዘገበችባቸው ስራዎች በዩኒስኮ የአለም ከተሞች ተምሳሌት በመሆን ያገኘችው ሽልማት ተጠቃሽ ነው፡፡

🔸በ3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ የብራዚሏ ኩሪቲባ ከተማ ናት ይህች ከተማ ከአለማችን ከተሞች መካከል በአረንጓዴነቷ የሶስተኛ ደረጃን ይዛለች በከተማው ከሚወጣው ቆሻሻም 70 በሞቶውን ለመልሶ አገልግሎት ማዋል ችለዋል፡፡ *በርካታ ጥብቅ ደኖች በከተማዋ መኖራቸው እና ዘመናዊና ቀላል የአውቶብስ የትራንስፖርት ተግባራዊ ማድረጋቸው ከስኬቶቻቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

🔸በ2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ ደግሞ የፊንላዷ ሄልሲንኪ ናት ይህች ከተማ በአካባቢ ጥበቃና በ መሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በአግባቡ በመቅረፍ ብሎም ለኪነ ህንፃ እና ሁለንተናዊ ለሆነ የከተማ ውበት ልዩ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ስራ ሰርተዋል በዚህም በአለማችን እጅግ በጣም ማራኪ ከሚባሉ ከተሞች ቀዳሚ ለመሆን ችለዋል ለዚህም እንደማሳያ የከተማዋ አብዛኛው ስፍራ በማራኪ አረንጉዴ ስፍራዎች ከመሸፈኑ ጎን ለጎን ከተማቸውን ማራኪ በሆነ የስነ ህንፃ ዲዛይን ዉብ ማድረግ በመቻላቸው ነው፡፡

🔸በመጨረሻም በዘርፉ በ1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ የዴንማርኳ ኮፐንሀገን ናት ይህች ከተማ ከአለማችን ከተሞች
በቀዳሚነት የካርቦን ልቀት በመቀነስ አረንጓዴ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ ከተማ መቀለስ ችላለች፡፡ *በተጎናጸፉት ስኬትም በከተማ ልማት ዘርፍ አንከን አይወጣላቸውም እየተባሉ ይወደሳሉ፡፡
*ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም ይህች ከተማ በአለማችንም እጅግ በጣም ደስተኛ ዜጎች ከሚኖሩባቸው ከተሞች መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ከተሞች ተርታ ተሰልፋለች፡፡

🌴እኛም ከነዚህ ከተሞች በርካታ ተሞክሮዎች መቅሰም ይኖርብናል እነዚህ ከተሞች ዛሬ የደረሱበት ስኬት ጠንካራ ህጎችን ማርቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ወይም ደግሞ ከተሞቹ በመደቡት የገንዘብ አቅም እንዳይመስሎ በነዋሪዎቻቸው ዘንድ በአውንታዊና ቅን በሆነ አመለካከት የተቃኘ የአስተሳሰብ ልእልና መገንባት በመቻላቸው እንጂ፡፡

☘️በአረንጓዴ እና ዉብ ስፍራዎች የሚኖሩ ዜጎችም ደስተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ የዜጎችን ህይወት መቀየር ይችላሉ፡፡

🇪🇹በሀገራችን ከተሞችም በቅርቡ የተጀመሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች አሁን ባለው ተነሳሽነት ማስቀጠል ከቻልን በአለማችን ተጠቃሽ ከሆኑ አረንጓዴ እና ዉብ ከተሞች መካከል ከተሞቻችንን ለማስጠራት የሚያግደን ነገር አይኖርም።

https://t.me/ethioengineers1
👍1
መቆሚያ ያጣው የሲሚንቶ ዋጋ
.
- ከ450 ብር በታች ከፋብሪካዎች እየወጣ ከአንድ ሺህ ብር በላይ ይሸጣል
- ኮንትራክተሮችና ሸማቾች ዋጋው በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ300 ብር በላይ መጨመሩን
ይናገራሉ
አዲስ አበባ፡- የሲሚንቶ ዋጋ በመወደዱ ለግንባታ መጓተትና ለአላስፈላጊ ወጪ ተዳርገናል ሲሉ ኮንትራክተሮችና ሸማቾች አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራቾች ማኅበር በበኩሉ ሲሚንቶ በአማካይ ከ450 ብር በታች በሆነ ሽያጭ ከፋብሪካዎች ቢወጣም ገበያው ላይ አንድ ሺህ ብር እየተሸጠ መሆኑን ጠቁሞ፤ ችግሩ በዋነኝነት በሕገወጥ ደላሎች የተከሰተ መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያነጋገራቸው ኮንትራክተሮች እንዳረጋገጡት ቸርቻሪዎች ዘንድ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከ950 ብር እስከ 1000 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል። የሲሚንቶ ዋጋ ንረቱ ገሃድ የወጣ ችግር መሆኑን ተዘዋውረን ተመልክተናል።

ኮንትራክተሩ አቶ በቀለ ኡርጋ እንደተናገሩት፤ የሲሚንቶ ዋጋ በመወደዱ ምክንያት መሸጫ ቦታዎች ላይ ስንጠይቅ አናገኝም። በጣም አስቸኳይ ግንባታ ቢኖር እንኳን ሲሚንቶ ብንፈልግ በተዘዋዋሪ ከደላሎች እንጂ ከሱቅ አናገኝም። ከደላሎች ሲገዛም ጠዋት የገዛንበት ከሰዓት ላይ ጨምሮ እናገኘዋለን ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል።በአንድ ሳምንት ውስጥም እስከ 300 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ጠቁመዋል።

ይህም ለግንባታ መጓተትና ለአላስፈላጊ ወጪ ዳርጎናል። የሲሚንቶ ዋጋ መናርና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚታየው የሕገወጥ ደላሎች ገበያውን የመቆጣጠር አባዜ ካልተስተካከለ ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ይበልጥ ከባድ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል።

ዋይቲኤስ በተሰኘው የኮንስትራክሽን ድርጅት የሚሰሩት ኢንጂነር በሱፍቃድ ሰለሞን በበኩላቸው ሲሚንቶ በመወደዱ የተነሳ ከቸርቻሪዎች ዘንድ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። ገንዘብ ይዘን እንኳን ለመግዛት የምንቸገርበት ወቅት አለ። የዋጋ መናሩ ሳያንስ በወቅት አለመገኘቱ ፈተና ሆኖብናል ሲሉ ተናግረዋል።

ኮንትራክተር አቶ ዐብይ አለሙ በበኩላቸው የሲሚንቶ ዋጋ በመናሩ የግንባታ ሥራዎች በወቅቱና በተያዘላቸው በጀት እንዳይጠናቀቁ እክል እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። በየሰዓቱ የሚለዋወጠውን የሲሚንቶ ገበያ ማረጋጋት ካልተቻለ በኮሮና ዘመን የተጎዳው የኮንስትራክሽን ዘርፉ ይበልጥ ይጎዳል ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራቾች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የደርባ ሲሚንቶ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሲሚንቶ ከፋብሪካዎች ሲወጣ በአማካይ ከ450 ብር በታች ነው፤ ገበያው ላይ ግን ከእጥፍ በላይ እየተሸጠ ነው። ለዋጋ ንረቱንም ሕገወጥ ደላሎች የፈጠሩት ችግርና የምርትና አቅርቦት አለመጣጣም ዋነኛ ዋነኛ ምክንያቶች ሆነዋል።

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በግብዓት ዕጥረት ምክንያት ምርታቸውን በእጅጉ መቀነሳቸው በአቅርቦት ላይ የእራሱ የሆነ ጫና አሳድሯል የሚሉት አቶ ኃይሌ፤ በተለይ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከወለጋና ከቤኒሻንጉል እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች የድንጋይ ከሰል ግብዓት ማጓጓዝ አስቸጋሪ በመሆኑ ፋብሪካዎች ውስን ምርት እንዲያቀርቡ አስገድዷል ብለዋል።

በዚህም በርካታ ፋብሪካዎች የምርት ሰዓታቸውን ቀንሰዋል። ለአብነት ደርባ ሲሚንቶን ብንወስድ አሁን ላይ የምሽት ፈረቃ ምርቱን አቁሞ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ብቻ እየሰራ ይገኛል። ሌሎቹ አምራቾች ላይም መጠኑ ይለያይ እንጂ ተመሳሳይ ችግር አለ። ይህም የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን በመፍጠሩ ገበያው ላይ ሲሚንቶ እንዲወደድ አንዱ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የአገር ውስጡ የድንጋይ ከሰል ለማግኘት ችግር በመፈጠሩ ከውጭ የሚመጣውን ለመጠቀም እየሞከርን ነው። ከውጭ የሚመጣው ደግሞ በዩክሬንና በሩሲያ ጦርነት ምክንያት የድንጋይ ከሰል ዋጋው በሶስት እጥፍ ጨምሯል። ከዚህ ባለፈ ግን ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች አንዱ ግብአት የሆነው የከባድ ጥቁር ናፍጣ ዋጋ መጨመሩን አስታውሰዋል።

ይህ ሁሉ እያለ ግን የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መሸጥ ካለባቸው ዋጋ ቀንሰው እያቀረቡ ይገኛል። ምክንያቱም ጦርነቱ ቀጣይነት አይኖረውም ከሚል እሳቤ የተነሳ በፍጥነት የተጋነነ ዋጋ ለመጨመር ፍላጎት የለንም ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም ፋብሪካዎች በአማካይ አንድ ኩንታሉን ሲሚንቶ በቅናሽ እያቀረቡ ቢሆንም ምርቱ ከፋብሪካ ከወጣ በኋላ ተጠቃሚው ጋር እስኪደርስ ቢያንስ አምስት ሕገወጥ ደላሎች እጅ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ኃይሌ ከሆነ፤ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሲሚንቶ ፍላጎት ከ11 ሚሊዮን ቶን በላይ ቢሆንም ፋብሪካዎች ግን ስምንት ሚሊዮን ቶን ነው እያመረቱ የሚገኙት። ደላሎቹ ይህንን የፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን ስለተረዱ የሲሚንቶውን ዋጋ የበለጠ እንዲንር በማድረግ ለግል ጥቅማቸው ያውሉታል።

በጉዳዩ ላይ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ውይይት መደረጉን ያነሱት አቶ ኃይሌ፤ ሚኒስቴሩ ሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም የፋብሪካዎቹ ማኔጅመንት ማጠናከር፤ የሲሚንቶ አምራቾች ማኀበሩም ማጠናከር እና በሌላ በኩልም ከአቅም በታች የሚያመርቱትን አጠናክሮ በአቅማቸው እንዲያመርቱ ማድረግ ይገባል የሚል ሃሳብ ከሚኒስቴሩ መቅረቡን ተናግረዋል።

በአቅም ለማምረት ደግሞ የግብዓት እጥረቱን መፍታት ያስፈልጋል፤ ለዚህም ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል ተቋማት ጋር አስፈላጊውን ማስተካከያ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። መከላከያ ሚኒስቴርም የተካተተበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ግብአቶቹን ያለችግር ማቅረብ የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የድንጋይ ከሰል ፍጆታ ለማቅረብ የሚረዳ ፋብሪካ ግንባታ ከሶስት ሳምንታት በፊት በዳውሮ ዞን መጀመሩ የሚታወስ ነው። የሲሚንቶ ዋጋ ንረቱን በተመለከተና በተለይም ደግሞ ህገወጥ ደላሎችን ለመቆጣጠር ያልተቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ጉዳዩ ወደሚመለከተው ወደ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራዎችን ብናደርግም ጥረታችን አልተሳካም ።

አዲስ ዘመን
👍1
የግንባታ ግብዓት ዋጋ ማሻቀብ እና በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ስር የሰደደው የሌብነት ተግባር የዘርፉ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተመለከተ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የከተማ ልማት፣ኮንስትራክሽንና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮን የስራ እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡

ለኮሚቴው አባላት ማብራሪያ የሰጡት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ከ2 እስከ 3 ወራት ይፈጅ የነበረው የተቋራጭ ክፍያ አሁን ላይ ከ1 ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ እንደሚወስድ ጠቅሰው ከተለያዩ ተቋማት የሚመጡ የዋጋ ተከላ ጥያቄዎችን ቢሮው በወቅቱ አጥንቶ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በየዕለቱ እየተስተዋለ የሚገኘው የግንባታ ግብዓት ዋጋ ማሻቀብ እንዲሁም በዘርፉ ስር የሰደደው የሌብነት ተግባር የኢንዱስትሪው ተግዳሮቶች መሆናቸውን ጠቅሰው እንደቢሮ እነዚህን ፈተናዎች ሁሉ እያለፍን ፕሮጀክቶቻችንን በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ በላይ ደጀን በስራ ግምገማው ወቅት እንዳሉት ቢሮው የፕሮጀክት አፈፃፀም ስኬቱን ለማሳደግ እያደረገ ያለው ዕለታዊ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ የተቋሙን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመገምገም አፋጣኝ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል መልካም ተሞክሮ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ቢሮው አላስፈላጊ የጥቅም ትስስሮችን ለመበጠስ ከማዕከል አስከ ወረዳ የሚገኘውን መዋቅር መፈተሸ አለበት ያሉ ሲሆን ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ፕሮጀክቶች በውለታቸው መሰረት የማጠናቀቅ ኃላፊነቱንም በሚገባ መወጣት እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ቢሮው በባለቤትነት እያስገነባ የሚገኘውን የዳግማዊ ሚኒኪክ የዓይን ህክምና ማዕከል ግንባታ ሂደት እና የዳያሊሲስ ማዕከሉ ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ መጋቢት 19/2014 ዓ/ም

https://t.me/ethioengineers1
👍1