SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
ተመልከቱ ይህን የሀገር ሀብት ሀላፊነት በማይሰማቸው አመራሮች እንደዚህ ባክኖ ይቀራ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ግቢ ገብርኤል አጠገብ ያለ ቀበሌ ውስጥ ያለ ነው!

Via merkebu Haile
📩ለሃሳብ እና ኣስተያየት ይጠቀሙ
👇👇
@Ethiocon143bot

https://t.me/ethioengineers1
የግንባታው “ሳይት” ጉዳይ

አንድ የሕንጻ ግንባታ ስፍራ ምንም እንኳን አጥሩ ታጥሮ፣ ለግንባታ የሚሆነው ቁሳቁስ በሙሉ ተከምሮና በአካባቢው ግንባታውን ለመስራት የተዘጋጁ ሰዎች ቢተራመሱም፣ ግንባታ ተጀምሮና ተጠናቆ ስራ ላይ እስካልዋለ ድረስ ቦታው የግንባታ “ሳይት” ከመሆን ውጪ ሌላ ጥቅም የለውም፡፡

የእኔና የእናንተም ሕይወት እንደዚሁ ነው፡፡ በአእምሯችን፣ በእጃችንም ሆነ በአካባቢያችን ያሉ በርካታ አቅርቦቶች ኖረውን ሳለ እነዚህን አቅርቦቶች እንዲሁ ከማከማቸት ባለፈ ሁኔታ ከዓላማ አንጻር ካልተጠቀምንባቸው አንድ መልክ ያለውን ነገር ለመገንባት አንችልም፡፡ እነዚህን ነገሮች ስንሰበስባቸውና ከዓላማ አንጻር ስንጠቀምባቸውና ስንገነባቸው ብቻ ውጤታማ እንሆናለን፡፡

የሚከተሉትን የክምችት አቅሞቻችሁን አስቧቸው . . .

1. የሰው አቅም፡- በዙሪያችሁ የሚገኙ በግልም ሆነ በሌላው ሰው የምታውቋቸው ሰዎች ለዓላማችሁ ትልቅ መዋጮ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አትዘንጉ፡፡ ምናልባት ማድረግ የሚኖርባችሁ፣ ሃሳባችሁን በመግለጥ ድጋፋቸውን መጠየቅ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

2. የእውቀት አቅም፡- በአእምሯችሁ ውስጥ ያለው እውቀትም ሆነ በእጃችሁ ላይ ያለው ክህሎት ለዓላማችሁ መሳካት ትልቅ ስፍራ አለው፡፡ ባላችሁ እውቀት መንቀሳቀስ ስትጀምሩ ማመን የማትችሉት በር ሲፈትላችሁ ማየት ትጀምራላችሁ፡፡

3. የገንዘብ አቅም፡- በእጃችሁ ላይ ያለው ገንዘብ ትንሽም ሆነ ትልቅ በትክክለኛው መንገድ ከተጠቀማችሁበት ሕልማችሁን እውን የማድረግ አቅም አለው፡፡ ገቢን በመጨመርም ሆነ ወጪን በመቀነስ ያላችሁን የገንዘብ አቅም ከዓላማችሁ አንጻር መቃኘትና መጠቀም ስትጀምሩ የሚያስገርም የገንዘብ መባዛትና የዓላማ ስኬት ማግኘት ትጀምራላችሁ፡፡

በርቱና ከግንባታ “ሳይትነት” ወደ ተገነባ ባለራእይነት ተሸጋገሩ ዶ/ር እዮብ ማሞ🙏
#የኮንስትራክሽን ግብአቶች እንደ ሲሚንቶ እና ብረት ያሉት ዋጋቸው ከፍ እንዳለ ነው።
#መንግስትም ዝምታን መርጧል።
#እስቲ በችግሩ ዋና መንስኤና መፍትሄው ላይ ሀሳብ አስተያየት ስጡበት።

📩ለሃሳብ እና ኣስተያየት ይጠቀሙ
👇
@Ethiocon143bot
የአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ እንዲሆን ተወሰነ
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ‹‹የተዘበራረቀ›› የሕንፃዎች ቀለም ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማውጣት ባደረገው ጥናት፣ ሁሉም ሕንፃዎች ቀለማቸው ግራጫ (ግሬይ) እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔውን አስመልክቶ የሕንፃ ባለቤት ከሆኑ የከተማዋ ባለሀብቶች ጋር ውይይት የጀመረ ሲሆን፣ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ባለ ጊዜ ውስጥ የውሳኔው ማሳያ የሚሆን ሞዴል አካባቢ ለማዘጋጀት አቅዷል፡፡

በከተማው ለሚገኙ ሕንፃዎች ቀለማቸው ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት ላለፈው አንድ ወር ጥናት ሲደረግ መቆየቱን ለሪፖርተር የተናገሩት የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አካለ (ኢንጂነር)፣ በጥናቱ አብዛኞቹ ሕንፃዎች ቀለማቸው ምን ዓይነት እንደሆነ የመለየት ሥራ እንደተከናወነ ገልጸዋል፡፡ እንደ እሳቸው ገለጻ፣ የከተማዋ ሕንፃዎች ተቆጥረው ቀለማቸው የተለየበት ጥናት አብዛኞቹ ሕንፃዎች ግራጫ ቀለም ያላቸው መሆኑን አመላክቷል፡፡ ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ለማሳያነት የጠቀሱት ኃላፊው፣ በቂርቆስ ከ100 ሕንፃዎች ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ሕንፃዎች ቀለም ግራጫ ነው ብለዋል፡፡ ከእዚህ ውጪ ያሉት ቀለሞች አነስተኛ ቁጥር ያላቸውና የተለያዩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

‹‹መሬት ላይ የሌለ አዲስ ቀለም ብናስቀምጥ የተሠሩት ሁሉም ሕንፃዎች እንደ ገና [ቀለም] ሊቀይሩ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዋነኛው የትኛው ቀለም ነው የሚለውን ወስደን ቀሪዎቹ ሕንፃዎችና ወደፊትም የሚሠሩት በተመሳሳይ ግራጫ እንዲሆኑ ወስነናል፤›› ሲሉ ለከተማዋ ሕንፃዎች ግራጫ የተመረጠበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

1/2
2/2

ግራጫ ቀለም ሲወሰን ሁሉም ሕንፃዎች ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ ቀለም ይኖራቸዋል ማለት እንዳልሆነ የሚናገሩት ኃላፊው፣ እስከ 30 የሚደርሱ በኮድ የሚለያዩ የግራጫ ቀለም ዓይነቶች እንዳሉና የሕንፃ ባለቤቶች ከእነዚህ ውስጥ መምረጥ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከግራጫ ቀለም ዓይነቶች ውስጥ የማይካተት ቀለም የተቀቡ ሕንፃዎች በሙሉ፣ ቀለማቸውን በግራጫ ቀለም አማራጮች እንደሚቀይሩ አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው እንደሚናገሩት በከተማ ውስጥ ያሉት ሕንፃዎች ቀለም የተዘበራረቀ፣ እርስ በርስ የሚጋጭና ጎን ለጎን ባሉ ሕንፃዎች መካከል እንኳን ተቀራራቢነት የሌለው ነው፡፡ ከእዚህ በላይ ‹‹ለዓይን ዕይታና ለጤና ጉዳት ያላቸው›› መስታወቶችንና አልሙኒየሞችን የሚገጥሙ ባለ ሕንፃዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ አሠራር መቅረትና ወጥ በሆነ ስታንዳርድ መመራት እንዳለበት የሚገልጹት ስጦታው (ኢንጂነር)፣ አሁን ያለው አሠራር የከተማዋን የአፍሪካ መዲናነትንም ሆነ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ከተማነት የማይመጥን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሕንፃዎቻቸው የቀለም ስታንዳርድ ያበጁ ከተሞች እንዳሉ ጠቅሰው፣ የከተማ አስተዳደሩም ይህንን ልምድ በአዲስ አበባ ለመተግበር ማሰቡን አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ የወጣው የሕንፃ አዋጅም ሆነ የከተማዋ የሕንፃ መመርያ የቀለም ስታንዳርድን ስለማያስቀምጡ፣ የከተማ አስተዳደሩ በ2010 ዓ.ም. የወጣውን የሕንፃ መመርያ ቁጥር 2/2010 በማሻሻል ረቂቁን ለከተማዋ ዓቃቤ ሕግ መላኩን ገልጸዋል፡፡ የሕንፃና የቀለም ስታንዳርድ መመርያው ላይ የተካተቱ አዲስ ሐሳቦች መሆናቸውን የተናገሩት ስጦታው (ኢንጂነር)፣ በየአንቀጾቹ ሌሎች ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ረቂቅ መመርያው ከፀደቀ በኋላ ቢሮው የሕንፃዎችን ቀለም መቆጣጠር ኃላፊነት እንደሚኖርበት፣ አዲስ ሕንፃ ገንቢዎችም ካሉት የግራጫ ቀለም አማራጮች ውስጥ የመረጡት ቀለም በቢሮው ፈቃድ ሳያገኝ መቀባት እንደማይችሉ አብራርተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለሕንፃዎች የወሰነውን የቀለም ስታንዳርድ በተመለከተ ካለፈው ሳምንት አንስቶ ትልልቅ ሕንፃዎች ካሏቸው ባለሀብቶች ጋር ውይይት ማድረግ የጀመረ ሲሆን፣ እስካሁን በቂርቆስና በልደታ ክፍላተ ከተሞች ውይይት ተደርጓል፡፡ እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ በተደረጉት ውይይቶች የሕንፃ ባለቤቶች ውሳኔውን በመደገፍ ለመተግበር ተስማምተዋል፡፡ በየአካባቢው ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ማኅበራት ጋርም ምክክር መጀመሩን፣ የሕንፃዎቹንና የጣርያዎቹን ቀለም ወደ የሚፈለገው ስታንዳርድ ለማምጣት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ ይህ ውይይት በሁሉም ክፍላተ ከተሞችና ወረዳዎች እንደሚቀጥልም አክለዋል፡፡

የከተማዋን ሕንፃዎች ቀለም ወደ ግራጫ ለመቀየር ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ያስረዱት ኃላፊው፣ እስካሁን ድረስ የሕንፃዎችን ቀለም ለመቀየር የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ እናደርጋለን፣ እስከ መቼ ድረስ ሊጨርሱ ይችላሉ የሚለውን አስበንና ጊዜ ሰጥተናቸው እንወስናለን፤›› ብለዋል፡፡

በመጪው ሁለትና ሦስት ወራት ግን በአንድ የተመረጠ አካባቢ የሚገኙ ሕንፃዎችን ቀለም ሙሉ ለሙሉ ወደ ግራጫ በመቀየር ሞዴል አካባቢ የማሳየት ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡ ሞዴል አካባቢው ሌሎች ክፍላተ ከተሞች ጭምር ያምራል አያምርም የሚለውን መጥተው ልምድ የሚወስዱበት፣ ይሳካል አይሳካም የሚለውንም የሚመለከቱበት እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

ይሁንና በከተማው ውስጥ የሚገኙ ስማቸው መለያ (ብራንድ) የሆኑ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ሕንፃቸውን በግራጫ ቀለም ለመቀየር እንደማይገደዱ ስጦታው (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡ የተለየ ቀለም ያለው መስታወት ወይም አልሙኒየም የተገጠመላቸው ሕንፃዎችን በተመለከተ፣ ‹‹እንዴት እናርመው የሚለውን ተወያይተን መፍትሔ እንፈልጋለን፤›› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለከተማዋ ሕንፃዎች የቀለም ስታንዳርድ ተግባራዊ የማድረግን ሐሳብ ከሳምንታት በፊት በተደረገው የከተማ አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ አንስተው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለከተማ ካቢኔ አባላት መመርያ ካስተላለፉባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ስለሆነው የሕንፃዎች ቀለም ጉዳይ ሲናገሩ፣ የከተማዋ ሕንፃዎች ቀለም ወጥነት የሚጎድለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዓብይ (ዶ/ር)፣ ‹‹እያንዳንዱ ሕንፃ በተፈቀደለት የቀለም ዓይነት ነው እንጂ የሚቀባው፣ የእኔ ስለሆነ ቀለም ስላማረኝ ብሎ ሁላችንም የምናየውን ቀለም እንደፈለገ መቀባት አይችልም፤›› ካሉ በኋላ፣ የካቢኔ አባላት ሊመለከቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ተናግረው ነበ
ር፡፡

Reporter
👉ስለግራጫ ቀለም ውሳኔ

ጌታሁን ሄራሞ እንደፃፈው

አዲስ አበባ "ግራጫ ትሁን" ተብሏል። ግራጫ፣ ነጭና ብርማ "ቀለሞች" ከኪነ ሕንፃ ታሪክ አኳያ ሞደርኒዝም ከናኘበት ከዛሬ 60 ዓመታት በፊት በብዙ ሀገራት ተሞክረው ቀለሞቹ በሰው ልጆች ሥነ ልቦናና አካል ላይ ከሚያስከትሉ ተፅዕኖ አንፃር በብቸኝነት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተደረጉ ናቸው። ሲጀመር እነዚህ በዘልማድ በቀለምነት ይፈረጁ እንጂ ቀለም-አልባ ዝሪያዎች(Achromatic) ናቸው።

ከሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖ አንፃር በተለይም ግራጫ ቀለም ሰፊ ቦታ ከተሰጠው ራስን የማጥፋት(Suicide commitment) ውሳኔን የሚያበረታታ "ቀለም" መሆኑ በብዙ ጥናቶች የተረጋገጠ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ግራጫ "ቀለም" ሲያይል ድባቴን(Depression) ፈጥሮ ሰዎች ከራሳቸው ወጣ ብለው እንዳይንሸራሸሩ የሚያደርገውን "Introvert" ሰብዕናን ማበረታቱ ነው። በተለይም በሌሎች የግልና ማህበረሰባዊ ችግሮች ለተወጠሩ ሰዎች(ለምሣሌ ኑሮ ውድነት፣ጦርነት) "Extrovert" እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው አካባቢ ነው መፈጠር ያለበት። ይህም መሠረታዊ የሁባሬን መርሆችን(Harmony principles) የተከተለ የቀለማት አጠቃቃም(Chromatic environment) ይተገበር ዘንድ ግድ ይላል። በተለያዩ ቀውሶች ለተከበበ ማህበረሰብ ድባቴን የሚፈጥሩ "ቀለሞችን" እንካችሁ ማለት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍን እንደመጥራት ይቆጠራል።

በነገራችን ላይ የአንድ ከተማ ቀለም ከመወሰኑ በፊት በከተማው ማስተር ፕላን ውስጥ ዕቅዱ መካተት አለበት። የአዲስአበባ ከተማ ማስተር ፕላን ደግሞ ቀለምን በተመለከተ የሚለው አንዳች የለውም። በማስተር ፕላኑ የሌለውን መርህ ለመተግበር መሞከር በራሱ አጠያያቂ ነው። አንዳንድ የአሜሪካ፣ የካናዳ፣የአውሮፓና የእስያ ከተሞች በማስተር ፕላናቸው ውስጥ "City Color Planning" ዲፓርትመንት አላቸው። በዲፓርትመንቱ ውስጥ የከለር አማካሪዎችና ኢንቫይሮመንታል ሳይኮሎጂስቶች፣ የከተማ ፕላነርስና አርክቴክቶች፣ ሠዓሊዎች፣ ግራፊክ ዲዛይነሮችና የታሪክ ባለሙያዎች ተካትተው በይነዲስፒሊናዊ በሆነ መልኩ የቀለም ፕላንግ ንድፍ ያወጣሉ። አንድ ሕንፃ ከመገንባቱ በፊት ልክ እንደ ግንባታ ፈቃዱ የቀለሙም ፈቃድ በቅድሚያ ዲዛይን ውስጥ ተካትቶ ይጠናና ውሳኔው ይሰጣል። ስለዚህም የትኛውም የከተማ ቀለም ከመወሰኑ በፊት ፕላንጉ በማስተር ፕላኑ መታቀፍ አለበት። ይህ ባልሆነበት የከተማን ቀለም መወሰን እንደ ሕገወጥ ግንባታ መቆጠር አለበት። አቅሙ ካለ ከሁሉም አስቀድሞ ማስተር ፕላኑ ውስጥ የከለር ፕላንግ መካተት አለበት። ይህ በኮሚቴ የሚወሰን ርዕሰ ጉዳይ አይደለም።

አንዳንዶቻችሁ በዚህ ሥራ ተሳታፊ ሆኜ የበኩሌን እንዳበረክት ስትጠይቁኝ ነበር። እስከአሁን ባለው መረጃ በግልፅ ከሚመለከታቸው የከተማ ኃላፊዎች በሥራው እንድሳተፍ የተደረገ ጥሪ የለም፣ በእርግጥ አንድ ወጣት አርክቴክት(በኮሚቴው ሳይኖር አይቀርም) በግል ጠይቆኛል። በእኔ አረዳድ ጥያቄው መቅረብ ያለበት ግን በግለሰቦች ሳይሆን ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች መሆን አለበት ባይ ነኝ። ብዙውን ጊዜ ደግሞ ውሳኔዎች በችኮለ ስለሚሰጡ እንደ እኛ ዓይነት ባለሙያዎች በውሳኔ አሰጣጡ ልናዘገይ ስለምንችል እንደ እንቅፋት ሳንቆጠር አንቀርም። መኪና ማርሽና ነዳጅ መስጫ ብቻ አይደለም ያለው። ፍሬን የሚባል መቆጣጠሪያም አለው። በአብዛኛው በፖለቲከኞች ዘንድ ፕሮፌሽናልስ እንደ "ፍሬን" ብቻ ነው የሚታዩት! ፍሬኑ ተገፍቶ በማርሽና በነዳጅ መስጫ ብቻ ምን እንደሚደርስና የት እንምንደርስ አብረን የምናያው ይሆናል::
📩
ለሃሳብ እና ኣስተያየት ይጠቀሙ
👇👇
@Ethiocon143bot

https://t.me/ethioengineers1
👍2
ለማንኛውም አዲስ አበባን ጨምሮ የኢትዮጵያ ከተሞች መለያቸው የሀገረሰብእ (Indigenous) ቅኝት የሚስተዋልባቸው ቅይጥ (Mixed) ጠባይ ያላቸው ናቸው።

እንደ ሞዛይክ ቅይጥ መልካቸውን በማጥፋት አንድን ከተማ "አንድ ዓይነት" ቀለም ለመቀባት መወሰን ፍጹም ስህተት ነው። ይህንን የመሰለ አስተሳሰብ እና አሠራር ምንጩ ግን ምን ይሆን ?

ሀ) አለማወቅ ?
ለ) አጀንዳ መስጠት ?

#ፕሮፐርቲ ታክስ:::::>ህንፃህን የመረጥከውን ቀለም መቀባት አትችልም(ግራጫ ቀባ)::::::>ቀጣዩን የንብረት መብት እጣፋንታ(ገምቱ)

📩 ይጠቀሙ
👇👇
@Ethiocon143bot

😏Good night 🙏
🗣 #ሲሚንቶ‼️
👉እስኪ ትንሽ ስለቀለሙ የገንዘብ ወጭ!

ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ለ1,000,000 ህንፃዎች ቀለም እንቀይር ብልን
በአማካይ የቀለም ቅብ በካሬ ለአንድ ህንፃ 150m2 ቢሆን በጣም በትንሹ ማለቴ ነው።
ቀለም አሁን ባለው የአ.አ ዋጋ ለካሬ 120ብር ቢሆን
1,000,000x150x120 = 18,000,000,000 ብር ያስወጣል።
በዚህ የቀለም ስራ ተጠቃሚ ማህበረሰብ የለም። ግለሰቦች ይበለፅጉበታል።
ቀለም ቀቢ + የቀለም አምራች + ደላላ
አይይ የዚች ሃገር ነገር።

18 ቢሊዮን ብር አዲስ የቤት ግንባታ ወይም ለስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ቢፈጠርላቸው ወይም የኑኖ ውድነቱን ቢያረጋጉበት አይሻልም።

ቀለም ለድሃ ሆድ አይሞላም።

#እትዮ_ኮንስትራክሽን
⤵️የሙያ ነጻነት ለአርክቴክት ግራጫ ቀለም
***

ግራጫ አካባቢ ነው፡፡ “It is a gray area” ፈረንጆች ነገሩ አልገባ ሲላቸው ወይም ሲያወዛግባቸው የሚጠቀሙት ሃረግ ነው፡፡ ቀለሙና አባባሉ መገጣጠሙ ገርሞኛል፡፡

በኪነ ህንጻ ጥበብ (Architecture) ዋነኛ የህንፃ ቀለማት ዲዛይንና መረጣ የአርክቴክቱ ዋነኛ ኃላፊነት ነው፡፡ የቀለማት ስራ ህንጻውን ከማስዋብ ባሻገር በሰው ላይ ተፈጥሮአዊ ስሜትና ስን ልቦና የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከባድ በመሆኑ በጥንቃቄ የሚታቀድ እና የሚፈጸም ስራ ነው፡፡ የቀለምን ንድፈ ሃሳብ ለማብራራት አስቸጋሪ ቢሆንም ሰዎች በተራዘመ ጉዞ የለዩትን ትርጓሜ ይዞ ማየቱ ስለምንነቱ ለመረዳት ያግዛል፡፡
ቀለማት ድምጽ አልባ የመግባቢያ መሳሪያ ተደርገው ስለሚወሰዱ የብዙሃኑን ቀልብ ይስባል፡፡ ለቀለማት ያለን ምርጫና ዝንባሌም ከሰው ሰው የሚለያይ መሆኑ ደግሞ ሌላው የቀለማት ባህሪ ነው፡፡

በአዲስ አበባ በቂ የሆነ የህዝብ ግንኙነት ስራ አለመሰራቱ ካልሆነ በስተቀር የህንጻ ቀለማት ዓይነት፣ የሚመረጡበት ዘዴና በተጓዳኝ እንደ ህንጻው አጠቃቀም ሊኖረው ስለሚገባው የቀለም ገጽታ ዝቅተኛ መስፈርቶች በቴክኒክ መመሪያ ውስጥ ተመልከተው አሉ፡፡ ባልሳሳት አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ደረጃውን ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መግዛት ይቻላል፡፡

በአንድ አንድ ሀገራት መንደሮች በልዩ ሁኔታ ወጥ የሆነ ቀለም እንዲቀቡ የሚያስገድድ ተፈጥሮአዊ ታሪካዊና መሰል ሁኔታዎች አሉ፡፡ የብዙ ሀገራትን ልምድ እንዳየሁት ከሆነ ከዝቅተኛው መስፈርት በላይ በደምሳሳው የከተማን ቀለም ወጥ አድርጎ መወሰን ግን የተለመደ አይደለም፡፡ ይሁን ቢባል እንኳን ብዙ የሚያነጋግሩ የሙያና ሞራላዊ ጉዳዮች አሉት፡፡

የሆነው ሆኖ ሰሞኑን አዲስ አበባ መስተዳድር የከተማዋን ቀለም ግራጫ እንዲሆን ወሰነ አሉ፡፡ እንግዲህ ውሳኔው የሚያስገኙትን ጥቅሞች እንዳያሳጣን እና ደግሞ ጉዳትም እንዳያስከትል በእውቀት ላይ የተመሰረተ አስተያየት ለመሰንዘር ያስገድደናል፡፡

በአጠቃላይ ባደረኩት ጥናት በሳይንሱ የሚታወቁት ቀለማትን ሀገራት ከራሳቸው ባህላዊና ስነልቦናዊ ሁኔታ በመነሳት የሚሰጡት ትርጓሜ ቢኖርም በአብዛኛው ማለት በሚቻል በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀለማት የሚከተለውን እንደየአግባብነቱ ትርጓሜ እንዲይዙ ስምምነት አለ፡፡
• ቀይ :- ጥልቅ ስሜት፣ ፍቅር፣ ቁጣ
• ብርቱካናማ :- ጉልበት፣ ደስታ፣ ህይወት
• ቢጫ :- ደስታ፣ ተስፋ፣ ማታለል
• አረንጓዴ :- አዲስ ጅምሮ፣ የተትረፈረፈ፣ ተፈጥሮ
• ሰማያዊ :- ረጋ ያለ፣ ሀላፊነት፣ ሀዘን
• ሐምራዊ :- ፈጠራ፣ ንጉሳዊ፣ ሀብት
• ጥቁር :- ምስጢር፣ ውበት፣ ክፋት
• ግራጫ :- ተለዋዋጭ ስሜት፣ ወግ አጥባቂ፣ መደበኛነት
• ነጭ :- ጥሩነት፣ ንጽህና፣ በጎነት
• ቡናማ:- ተፈጥሮ፣ ጤናማነት፣ ጥገኛነት
• ታን ወይም ቤይጅ:- ወግ አጥባቂ፣ ቅድስና፣ ደደብ
• ክሬም ወይም የዝሆን ጥርስ:- የተረጋጋ፣ የሚያምር፣ ንፅህና

ግራጫ ቀለም በዝርዝር
የግራጫ ቀለም አዎንታዊ ጎኖችን ስንመለከት፤ ግራጫ ገለልተኛ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ቀዝቃዛ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ስሜት ቀስቃሽ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ጥበብ ነው፡፡ ግራጫ ተራነት ነው፡፡ ግራጫ ዘመናዊነት ነው፡፡
የግራጫ ቀለምን አሉታዊ ጎኖች ስናይ ደግሞ፤ ግራጫ ተስፋ አስቆራጭ ቀለም ነው፡፡ ግራጫ ወግ አጥባቂነት ነው፡፡ ግራጫ ሃዘን ነው፡፡ ግራጫ ሰውን ከሰው የመነጠል ስሜትም ነው፡፡ ግራጫ መራራቅም ነው፡፡ ግራጫ ያልተለመዱ ኢ-ስነምግባር ድርጊትንም ይወክላል፡፡ ግራጫ አሻሚነት ነው፡፡

እንግዲህ ከእነዚህ እሳቤዎች በመነሳት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የከተማዋ ቀለም አሉታዊውን ጎኖች እንዲወክልለት አስቦ እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡

በእኔ እይታ ግራጫ የህዝብ ቀለም እንዲሆን የታሰበው ምናልባት አዲስ አበባ የሀገሪቱ ርዕሰ መዲና በመሆኗ እና በአሁኑ የሀገራችን ፖለቲካ ውጥንቅጥ ገለልተኛነቷን ለማመላከት ወይስ የፖለቲካ ቅራኔ መጫሪያነቷን ለማብረድ እንድትቀዘቅዝ፤ ወይስ አዲስ አበባ በታላቅነቷ አነቃቂ ስሜት ቀስቃሽ እንድትሆን ተፈልጎ፤ ወይስ አዲስ አበባ የጥበብ ማዕከልነቷን እውቅና ለመስጠት፤ ወይስ ለዘመናዊነቷ ምላሽ ይሆን ዘንድ ታስቦ የተቸረ የቀለም ሽልማት? ይህ ከሆነ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ይህ ነው ብሎ ከተማውን ግራጫ በግራጫ ለመቀባት መወሰን ደግሞ ስህተት ይመስለኛል፡፡ ሌሎች ቀለሞች ከላይ በአጭሩ እንዳስቀመጥኩት ከግራጫ ቀለም ባልተናነሰ የሚነግሩን አለና፡፡

ለማንኛውም በመርህ ደረጃ ህዝባዊ ቀለም ለመምረጥ የተኬደበትን ርቀት እያደነኩና እያከበርኩ ተግባራዊ ይደረግ ቢባል ሊፈጸም የማይችል ቢተገበር እንኳን ሙያዊነትና ስነምግባር የጎደለው መሆኑን ተረድቶ አስተዳደሩ ውሳኔውን እንዲያጤነው እጠቁማለሁ፡፡ ከግራጫ ቀለም ባልተናነሰ ጥቅም ያላቸውን ቀለማት ዋጋ ማሳጣትና የአርክቴክቱን የሙያ ነጻነት የሚጋፋ አደገኛ ውሳኔ እንዳይሆን ከልብ በሆነ ትህትና ጭምር ነው፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ ክትትል እና ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያቤት ከውሳኔው ጀርባ ያለው በቀጥታ የሚመለከተው መ/ቤት እንደመሆኑ መጠን በህንጻ አዋጁ ላይ የተመለከቱትን ዝቅተኛ መስፈርቶች መሟላታችውን ማረጋገጥ እና ማስጠበቅ ሚናውን እንዲወጣ እና የቀለም መረጣው ጉዳይ ደግሞ የአርክቴክቱ ኃላፊነት መሆኑን ተረድቶ ወደ ዋናውደ ስራ ቢገባ የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ የኢትዮጰያ አርኪቴክቶች ማህበርም እንደዚህ ያሉ ግድፈቶችን ለማቀናት መንግስትንና ህዝብን ማገዝ ነውና አንዱ አላማችሁ ጉዳዩን ፈትሻችሁ የደረሳችሁበትን ለትምህርታችን እንዲሆን አሳውቁን፡፡

ሰላም ሁኑ
ኢንጅነር ኃይለመስቀል ተፈራ
👍1
ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ‼️

ዛሬ ለማድረስ የፈለግኩት ጉዳይ ከሳርቤት (ፑሽኪን አደባባይ)ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው መንገድ ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለምዶ ከጎፋማዞሪያ ወደ መብራትኃይል እንዲሁም ከጎፋማዞሪያ ወደ ጨርቆስ እየተሰራ ያለው መንገድም በከፊል እየተጠናቀቀ ይገኛል ነገርግን የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ የመንገዱን እድሜ የሚያሳጥር አካባቢውንም ወደፊት በጎርፍ እንዲጥለቀለቅ የሚያደርግ ስራ እየተከናወነ ነው ይህም የመንገዱን ስራ የሚቆጣጠር ሃላፊ የሌለ በሚመስል መልክ አዲስ የተሰሩ የፍሳሽ መስመሮች (ፖሴቲዎች)ከአፍ እስከ ገደፋቸው ድረስ (ሙሉበሙሉ) በኮረትና በድንጋይ እንደተሞላ ክዳን እየተገጠመላቸው ነው ። በአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ የወረዳ አመራሮች ሳያዩ ቀርተው ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል ባለቤቱ ማነው ባንተ በኩል መድረስ ከቻለ ክረምት ከመግባቱ በፊት እንዲስተካከል ቢደረግ ። እንደለመደብን ጨረስን ብለን በማግስቱ ወደ ቁፋሮ እንዳንገባ በህዝብና በመንግሥት ገንዘብ መቀለድም እንዳይሆን ብዬ ነው ።

#እትዮ_ኮንስትራክሽን
#ሲሚንቶ
* *
ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው

የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

አዲስ ማለዳ
#የኛ ሀሳብ
* ****
#ህዝቡ የሲሚንቶ ገበያ ይረጋጋል ብሎ እየተጠባበቀ ነው።ጉዳዩን በቀላሉ ባታዩት ጥሩ ነው።
#ቸርቻሪስ ወጣ እንበል ዋናወቹ ጅምላ አከፋፋዮችስ(ዋናዎች ችግር ፈጣሪዎች ማለት ነው) ባሉበት ይቀጥላሉ?

#እትዮ_ኮንስትራክሽን
#አዋጁን_አፈር_በላው?

መሬት ሲሰጡ ያውቃሉ ፣ ዲዛይን ሲያጸደቁ አምነውበት ነው ፣ ግንባታውን ሲሰሩ የት እንደሚደርስ ምን እንደሚያጋጥም ሳያውቁት ቀርተው ወይንስ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ነው? ይህ ግንባታ ሰሚት አከባቢ ነው።
ማን ያስፈጽም ማን ይፈጸም? ባላቤት አልባ ህንጻ ሆነኮ! መብራት ሀይልስ እንዴት ዝም አለ?


https://t.me/ethioengineers1
👍1
#ሲሚንቶ ከሰሞኑ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።ፋብሪካ ላይ ግን የዋጋ ለውጥ የለም።
#የትምህርት ቤት፣የጤና ተቋም፣የውሀ፣ መንገድ መሰረተልማት ግንባታ በምን ሲሚንቶ ይከናወን?
#እንዴት ይሄን ችግር መፍታት ያቅታል? በእውነት በጣም ያሳዝናል፣ያበሳጫል።

https://t.me/ethioengineers1
SUMMARY
በቀላሉ ለመምረጥና ማየት እንዲመቻቹ ከስራናቸው ማስተማሪያ አማርኛ ቪዲዮዎች መካከል በተደጋጋሚ ከምንጠየቃቸው ዉስጥ የተወሰኑ የመረጥናቸውን የዩቲዩብ ሊንክ አስቀምጠናል።
1.Gravity Loading Calculations
https://youtu.be/t-WFwP2FWos
2. Ribbed Slab Concept, Analysis , Design & Quantity Calculations
https://youtu.be/3SoW8vdVwKQ
3.ConMIS introduction , A program which helps to work quantity ,planning & payment certeficate
https://youtu.be/1TWavJhnKyk
4. Introduction to Structural Design
https://youtu.be/nXnqz8lW0_4
5. Non Uniform Loading on ETABS & SAP
https://youtu.be/FGqrkc524c0
6. Bar Spacing Conversion
https://youtu.be/53c2u9FAw0M
7. Stair Detailing presentation
https://youtu.be/kXJm0UbeJxI
8. Mat Foundation on SAFE
https://youtu.be/UDEVA0OcvDI
9. Ribbed Slab Analysis & Design Hand Calculation
https://youtu.be/EsEPq2qIof4
10. Highway Design Introduction
https://www.youtube.com/watch?v=TVmEuigLzV8&t=11s

@BeGetEngineering
👍1
👉የLoader ተሽከርካሪ ጎማ ዋጋ በሦስት ወር ውስጥ ከ80 ሺሕ ወደ 150 ሺሕ ብር ከፍ ማለቱን የሎደር አሽከርካሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።

👉የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በእያንዳንዱ ከተማና ዞኖቹ የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል፡፡

ጥሩ ጅምር ነው። ሌላው ክልልም መተግበር ቢችል ይመከራል።

ይህ የተወሰነው ውሳኔ የነበረውን ችግር ምን ያህል ይፈታዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?

https://t.me/ethioengineers1
Did you know?

🏗Number of days required for curing of concrete

➡️Super Sulphate cement : 7 days

➡️Ordinary Portland cement OPC : 10 days

➡️Minerals and Admixture added cement : 14 days


https://t.me/ethioengineers1
🏗የሲሚንቶ ዋጋ ንረትና እጥረትን ለመቆጣጠር የሚያሰችል አሰራር ሊዘረጋ ነው

መንግሥት በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ መጨመርና እጥረትን ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን አሰራር ሊዘረጋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከአንድ ዓመት በላይ በሚባል ደረጃ የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት እንደተከሰተ ገልፀው ይሄም የፋብሪካዎች ከአቅም በታች ማምረትና ሌሎች ችግሮችን እንደ ምክንያትነት አንስተዋል።

ከፋብሪካው የሚመረተው ምርትም በኤጀንቶች፣ በአከፋፋዮችና በነጋዴው ከገበያ እንዲጠፋ ሲደረግ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር መደረጉን አንስተዋል።

👉አሁን የሚወጣ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግ ሲሚንቶ በኤጀንቶች፣ አከፋፋዮችና በችርቻሮ መሸጫ በኩል መሸጥ እንደሚቆም ተናግረዋል።

በአዲሱ አሰራር መሰረት ሲሚንቶ እንደ ፕሮጀክቶች ክብደት ታይቶ እንደሚከፋፈል የተናገሩት ሚኒስትሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ቀጥታ ከፋብሪካው እንዲያወጡና ሌሎች ደግሞ በየክልሉ በሚዘጋጁ የሲሚንቶ ማጠራቀሚያዎች በቅደም ተከተል እንዲስተናገዱ ይደረጋል ብለዋል።

ይህ የአጭር ጊዜ መፍትሄ እንደሆነና በቀጣይ መንግሥት የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲጨምር ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ማስፋፊያ እያደረጉ ያሉ ፋብሪካዎች ቶሎ ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ በማድረግ የሲሚንቶ እጥረቱን እንፈታለን ሲሉም ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

መንግሥት የሲሚንቶ እጥረቱ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ የተለያዩ የመፍትሔ አማራጮችን እንደሚወስድም በመግለጫው ተመልክቷል።

ዋልታ
👍1👏1
#ኢንጂኒየር አይዳኝ ዘለቀ በደረሰባቸው ድንገተኛ የልብ ሕመም በተወለዱ በ53 ዓመታቸው በትላንትናው ዕለት ዜና እረፍታቸው ተሰምቷል።

👉ኢንጂኒየር አይዳኝ ዘለቀ ዜና ረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ዘመድ አዝማዶቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለሞያ አጋሮቻቸው እንዲሁም ለሚያውቋቸው ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን፤

🙏ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነቱ ያኑሩልን።

https://t.me/ethioengineers1