SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
🚧ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) እና ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)

1, ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB)
#በኮንስትራክሽን ጉዳይ በአብዛኛው በሀገራችን የሚሰራበት የፕሮጀክት አይነት ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ መንገድ እንዲዘጋጅ ካደረገ በኃላ ግንባታውን በተቋራጭ እንዲከናወን የሚያደርግበት ነው።ይሄውም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) በመባል ይታወቃል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን/ በሌላ አርክቴክት ድርጅት/ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡በመቀጠልም በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ ወደመምረጥ ሂደት ይገባል፡፡የግንባታው ባለቤት የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነ እንደሆነ ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ የመምረጡ ስራ የሚከናወነው በግዥ ህግ መሰረት ይሆናል፡፡ይሄ አይነቱ ፕሮጀክት በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡


2, ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
#በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ዲዛይኑን እና ግንባታውን በራሱ የሚያከናውንበት የፕሮጀክት አይነትም አለ።ይሄውም ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB) ይባላል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት ተቋራጩ የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት ያከናውናል፡፡የአርክቴክት ስራው የሚያስከትለው ሀላፊነት የተቋራጩ ይሆናል፡፡ከዲዛይን ስራው ጋር የተያያዘ ችግር የሚያስከትለው ሀላፊነት አሰሪውን/የግንባታውን ባለቤት አይነካውም፡፡ሆኖም ተቋራጩ ዲዛይኑን ያሰራው በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት የሆነ እንደሆነ ከአርክቴክቸር ስራው ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ለአሰሪው የሚኖርበት ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አርክቴክቱም ለተቋራጩ በፍትሀብሄር ህጉ ስለእውቀት ስራ ውል በተደነገገው አግባብ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡በዚህ አይነት ፕሮጀክት የግንባታው ባለቤት/አሰሪው ሙሉ በሙሉ የኮንስትራክሽን ስጋቶችን/risks/ ወደ ተቋራጩ ያስተላልፋል፡፡ይህ ማለት አሰሪው ውጤቱን ማለትም ግንባታውን በመጀመሪያ በቀረበለት ዲዛይን አግባብ በጥራት ተከናውኖለት ከመረከብና በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ ዋጋ ከመክፈል ባለፈ ማናቸውም አይነት ሀላፊነት አይኖርበትም ማለት ነው፡፡ለአብነት ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን(ERA) ዲዛይን ቢዩልድ የመንገድ ፕሮጀክት ሲኖረው ተወዳዳሪ ተቋራጮች የሰርቨየይንግና ዲዛይን ስራዎችን በራሳቸው ከሰሩ በኋላ በዋጋ ይወዳደራሉ፡፡ተቋራጮቹ ዲዛይኑን ሲሰሩ አሮጌ ድልድዮች ካሉ እና ተጠግነው በአዲስ ድልድይ የጥራት ደረጃ መድረስ የሚችሉ ከሆነ ተቋራጮች እንደየፍላጐታቸውና ሙያዊ ምርመራቸው/ምክንያታቸው ተጠጋኝ ድልድይ እና በአዲስ የሚገነባ ድልድይ እያሉ በዝርዝር በዲዛይን አካተው የሚያቀርቡ ሲሆን ምንም ሆነ ምን በውጤት ደረጃ አሰሪው በሚፈልገው የጥራት ደረጃ/ስታንዳርድ መገንባቱ እና ይሄውም በአማካሪው መረጋገጡ ግን የግድ ነው፡፡ምናልባት ተጠግኖ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ይደርሳል የተባለው አሮጌ ድልድይ በጥገና ወቅት ቢፈርስ እንኳ አሰሪውን ክፍያ የመጨመር ሀላፊነት አያስከትልበትም፡፡ስለዚህ ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ለአሰሪዎች ሪስክ ፍሪ/ከስጋት ነጻ የሆነ የፕሮጀክት አይነት ነው፡፡

#ሌላው ሁለቱም የፕሮጀክት አይነቶች ለኮንስትራክሽን ውላቸው የሚጠቀሙት ጀኔራል ኮንዲሽን የተለያየ ነው።FIDIC በዚህ ረገድ የግንባታ ውል ዝግጅትን በማቅለል ለአለማችን ትልቅ ስጦታ ነው። አለበለዚያ አሰሪና ተቋራጭ በየአንዳንዱ ውል ዝግጅት ወቅት በሁሉም የውል ሁኔታወች ላይ መደራደርን ይጠይቃቸው ነበር።ዛሬ ላይ ግን ለውሉ ጥቅም ላይ የሚውለውን ጀኔራል ኮንዲሽን አስመልክቶ FIDIC ቨርሽን መረጣ እና በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በሚካተቱ ነጥቦች ላይ ብቻ መወያየት በቂ ነው።
#በተጨማሪም በዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት የኮንስትራክሽን ስጋት/ሪስክ ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋራጩ የሚተላለፍ በመሆኑ ልዩ የዋስትና ሽፋን ያስፈልገዋል፡፡ስለዚሁም ተቋራጩ በግንባታው ዋጋ ልክ All risk insurance እንዲገባ እና ለዲዛይን ስህተት፣ለስራው ብልሽትና በተቋራጩ ባለሙያወች የስራ ስህተት ለሚከሰት ጉዳትና ኪሳራ ደግሞ professional indemenity insurance እንዲገባ FIDIC ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ኮምፖቴብል የሆነው ተርንኪ ጀኔራል ኮንዲሽን ግዴታ ያስቀምጣል።
#በሀገራችን ዲዛይን ቢዩልድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ብዙም የተለመደ አይደለም።ሆኖም በመንገድ ግንባታ ውሎች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ይጠቀምበታል።
#በአጠቃላይ በሀገራችን በኮንሰትራክሽን ዲዛይኒንግ እና የውል አስተዳደር ረገድ ሰፊ የእውቀት ክፍተት ያለ በመሆኑ እና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ የማይጠናቀቁበት ሁኔታ በሰፊው የሚስተዋል እንደመሆኑ ሙሉ የኮንስትራክሽን ሪስክ/ስጋት ወደ ተቋራጩ በማስተላለፍ መንግስታዊ ግንባታዎችን በዲዛይን ቢዩልድ የፕሮጀክት አይነት እንዲከናወኑ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም እወዳለሁ።
👉ጉባኤ አሰፍ

@ethioengineers1
👍6
1,ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማረችሁ ባለሙያዎች ያለን ጥቆማ

የሲቪል ኢንጂነሪንግ፣አርክቴክቸር፣ ኮተምና ኢንቲሪየር ዲዛይን ሶፍትዌርዎችን የትም ሆነው መማር ይችላሉ ከ ሰርተፊኬት ጋር ያዘጋጀነውን online package ተጠቃሚ በመሆን❗️

🏗በአካል መምጣት እና መማር ለምትችሉ
👉Megenagna
Marathon Building , 6th Floor, Office No 614


📞0911890392/ 0944186744
👉@BeGetEngineering

2,በአዲሱ አመት ፣ በሁሉም የግምባታ ባለሙያዎች እጅ መገኘት ያለበትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ !

1. ጃዕፈር መፅሃፍት መሸጫ ( ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያዉ አጠገብ ፣ ተወልደ ህንፃ ስር)
ተጨማሪ የመሸጫ መዳረሻዎች ፤
2. መገናኛ ፣ ዲያስፖራ አደባባይ፣ ኤደን መፅሃፍት ወይንም ማራቶን ህንፃ 6ኛ ፎቅ BeGet ኢንጅነሪንግ
3. አራት ኪሎ ዩኒቨርቲ ፊት ለፊት ፣ ዩኒቨርሳል መፅሃፍት
5. ገርጂ-መብራት ሃይል ፣ፍዉንቴን ሕንፃ ጎን 100ሜ ወረድ ብሎ ፣በለጠ መፅሃፍት
6. ገርጂ-ታክሲ ተራ ፊት ለፊት ፣ዕዉቀትን ፍለጋ መፅሃፍት
7. ባህር ዳር ፣ ፊደል ሆቴል (0583202212)
8. ሀዋሳ፣ፒያሳ ፣ ዳሸን ህንፃ፣2ኛ ፎቅ ፣ ቢ.ቁ. 106 ( ኤምዲሲ ኮንሰልቲንግ)


3,በ ስልክዎ ላይ የሚወጡትን የተረጋገጡ
~ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
~ የግንባታ ጨረታዎች፣
~ የግንባታ ዕቃዎችን ወቅታዊ ዋጋ፣ ~ የባለሙያዎችን አድራሻ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማገኘት ይቀላቀሉ

👇
https://t.me/conlinkcatalogue
👍1
ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ለሚኒስትሩ ባለሙያዎች

● ArcGIS
● WaterGEMS
● SewerGEMS
ላይ የተሳካ ስልጠና ሰጥተናል።

https://t.me/BeGetEngineering
👍1
🚧እየጨመረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል አዲስ የዋጋ ተመን ማውጣቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል ፋብሪካዎች የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ያወጡት ዋጋ እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ነው በዘርፉ ያለውን የምርት ሂደት ጥናት የሚያደርግ ቡድን በማቋቋም አዲስ የዋጋ ተመን ይፋ ያደረገው፡፡

በዚህ መሰረት ሲሚንቶ ከፋብሪካ የሚወጣበት አዲሱ የዋጋ ተመን ዝቅተኛው 510 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 683 ብር ከ44 ሳንቲም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ÷ አሁን ላይ የሲሚንቶ ምርት እጥረት በመኖሩ ለመንግስታዊ ስራዎች ቅድሚያ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም ማረጋገጫ በማምጣት ከፋብሪካዎች በቀጥታ ምርት የሚገዙበት መንገድ ተመቻችቷል ነው ያሉት፡፡

የግል ተጠቃሚዎችን በተመለከተም የሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ፍላጎት ምን ያህል እንደሆነ ስለሚታወቅ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና በተደራጁ ማህበራት በኩል እንደሚያገኙ አስረድተዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ይሁንታ ካገኙ አካላት ውጪ ሲሚንቶ ይዞ የሚገኝና በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ግብይቶች ህገወጥ በመሆናቸው ተቋሙ ማስታወቂያ ካስነገረበት ቀን ጀምሮ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

🏗የፋብሪካዎች የሲሚንቶ አዲስ የመሸጫ ዋጋ

በዚህም መሠረት ደርባ ሲሚንቶ 590᎐59፣ ዳንጎቴ ሲሚንቶ 549.49፣ ኢትዮ ሲሚንቶ 595.66፣ ሙገር ሲሚንቶ 643.95፣ ሐበሻ ሲሚንቶ 683.44፣ ናሽናል ሲሚንቶ 561.39፣ ካፒታል ሲሚንቶ 633.38፣ ኩዩ ሲሚንቶ 628.10፣ ኢስት ሲሚንቶ 595.66 እና ፒዮኒር ሲሚንቶ 510᎐04 ብር እንዲሸጡ ተወስኗል።

-ሪፖርተር


https://t.me/ethioengineers1
❤1👍1
SMH General Construction
🚧እየጨመረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል አዲስ የዋጋ ተመን ማውጣቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ለማስተካከል ፋብሪካዎች የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተጠይቀው ያወጡት ዋጋ እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ነው በዘርፉ ያለውን የምርት ሂደት ጥናት የሚያደርግ ቡድን በማቋቋም አዲስ የዋጋ ተመን ይፋ ያደረገው፡፡ በዚህ መሰረት ሲሚንቶ…
🚧የሲሚንቶ ስርጭትና ዝውውርን ለመወሰን የወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ‼️

1. ማንኛውም የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት   መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት ለተፈቀደላቸው አካላት ብቻ የሲሚንቶ ሽያጭ መፈፀም አለበት፤

2. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በፌደራልም ወይም በክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ በመወሰድ ለየክልልና ከተሞች እንዲያቀርቡ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ ማናቸዉም ሰው የሲሚንቶ ምርት ለግብይት ያዞ መገኘት አይችልም፤

3. ለአንድ ጊዜ ለግል ወይም ለቤተሰብ ፍጆታ የተፈቀደ ከፍተኛው የሲሚንቶ ምርት መጠን 15 ኩንታል ነው፤

4. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሚንቶ እንዲያከፋፍሉ የተፈቀደላቸው አካላት ወይም በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተፈቀደላቸው ተቋራጮች የገዙትን የሲሚንቶ ምርት ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለሽያጭ ማቅረብ፣ ለመሸጥ መሞከር ወይም ከተፈቀደለት መስመር ውጪ በማንኛውም ማጓጓዣ ጭኖ መገኘት፣ ማጓጓዝ፣ በንግድ መደብር ወይም በማናቸውም ቦታ አከማችቶ መገኘት የተከለከለ ነው፤

5. ማንኛውም ሰው ከዚህ በላይ የተገለጸውን የሕዝብ ማስታወቂያ ተላልፎ ከተገኘ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 43 እና አግባብ ባላቸው ሌሎች ህጎች መሠረት በአስተዳደራዊ እና በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፤

6. ይህ የህዝብ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሌላ የህዝብ ማስታወቂያ እስከሚሻር ድረስ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
       
[ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ]


https://t.me/ethioengineers1
❤1
🚧ሃይብሪድ ፋውንዴሽን

Hybrid Foundation:- is used to reduce the amount of settlement in high rise building, which contains both soils supported mat and piles.

https://t.me/ethioengineers1
👍2
🚧what is The circled Number with the letter R in the picture❓

🏗The number "42.5" and the letter "R" together gives information about the strength class of cement.

🏗The strength class of cement classifies its compressive strength at 28 days.


🚧ስለ ኦፒሲ እና ፒፒሲ የ ሲሚንቶ ኣይነቶች ትንሽ እንንገራቹ
.
⏩OPC— Ordinary Portland cement

⏩PPC —Portland pozzollana cement

➡በሀገራችን ኢትዮጲያ በስፋት ህንፃ እና መሰረተ ልማት ግንባታ
ላይ በስፋት እየተጠቀምንባቸው የምንገኝባቸው የሲሚንቶ አይነቶች ናቸው።
የሁለቱንም የሲሚንቶ አይነቶች ጥቅም አንድነት እና ልዩነት ከዚህ በታች አጠር አድርገን እናቀርባለን።

▶ኦፒሲ/OPC/ በምጣነ ስርገት( Permeability) ከ ፒፒሲ/ PPC/ ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ ነው።
ውሃ ዘልነት /Heat of Hydration/ የኦፐሲ ከፍተኛ በመሆኑ ከፒፒሲ በተሻለ መልኩ ቶሎ የሚፈለገውን ጥረንካሬ ቀድሞ ያገኛል። በተቃራኒው ደግሞ ፒፒሲ heat of hydration ቀርፋፋ በመሆኑ ለመርጋት/curing period/ ተጨማሪ ቀናት ይወስዳል
ማለት ነው።

🏗በጥንካሬ ደረጃ /Grade of Strength / ኦፒሲ 42.5R grade cement ሲሆን ፒፒሲ ደግሞ 32.5R Grade Cement ነው።

➡Note: Number represent compressive strength of
cement in MPa.


https://t.me/ethioengineers1
👍8
🚧በሚሰሩት የመንገድም ሆነ የፍሳሽ መስመር ቁፋሮ ላይ ሴፍቲን ወይም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክት ለመትከል ሀላፊነት የማይሰማቸው ግዴለሽ፣ እንዝህላል እና ተጠያቂነት የማያውቁ ተቋማት እስካሉ ድረስ አደጋን መቀነስ እና መከላከል ዘበት ነው!!

ቦሌ ጃፖን አካባቢ!!
#ሰናይ፣ ሄኖክ
source :-Driving in addis
fb page

https://t.me/ethioengineers1
👍2
SMH General Construction
🚧what is The circled Number with the letter R in the picture❓ 🏗The number "42.5" and the letter "R" together gives information about the strength class of cement. 🏗The strength class of cement classifies its compressive strength at 28 days. 🚧ስለ ኦፒሲ እና ፒፒሲ…
......continued

PPC is only produced with
32.5 grade of cement

OPC cement in general has 3 grades
32.5R/32.5N
42.5R/42.5N
52.5R/52.5N

*Main difference between the above numbers is the fineness of cement, finer cement gives more strength due to its more covering capacity and taking part in hydration process by each particle.

32.5 is indicated for application where a high strength is not required.

42.5 are mostly used in the event that required compressive strength of concrete at 28 days must exceed 30N/mm2 and its also suitable for Lower temperature.

52.5 is rare to get but can produce higher stregth concrete easly.

N: represents Normal early strength
like no early strength (28th day)
But
R: means the strength can be achieved earlier (Rapid early strength )

By ጌታሁን አስረስ

https://t.me/ethioengineers1
👍5
የመፅሃፍ ፤ምረቃ ጥሪ !

በግንባታ ዕቅድና ቁጥጥር ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፃፍኩት መፅሃፍ ቅዳሜ ፣ መስከረም 28 ፣ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ፣ በኔክሰስ ሆቴል ይመረቃል ፡፡

በዚህ ፕሮግራም ፣ በዘርፍ ያሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የንግድና የሙያ ማህበራት ፕረዚደንቶች፣ ስራ ተቌራጮች ፣ አማካሪ መሃንዲሶችና የግንባታ ባለሙያዎች ይገኛሉ ፡፡ በተሳታፊዎች መካከል ለሚደረግ የመረጃ ልዉዉጥና የስራ ትስስርም ረዘም ያለ ሰዓት ተይዟል ፡፡
መፅሃፍ ፣ የፕሮጀክት ማኔጅመንት እንደመሆኑ መጠን ፣ የምረቃዉ ዝግጅት የPMBOK ስታንዳርድ፣ የቡድንና የጥምረት ፣ የስራ ሂደት አንቀፅ 9.4፣ የሚከተል ይሆናል ፡፡ ለዚህም፣ ቡድኖች (teams) ተዋቅረዋል ፤ የዕለቱ ኩነት ፣ ዉጤትም ፣ የቡድን ሆኖ ይመዘገባል ፡፡

ይህን ፕሮግራም በአካል ወይንም በኢንተርኔት በመከታተል ፣ ማገዝ ለምትፈልጉ ፣ የተያያዘዉን የጎግል ቅፅ በመሙላት ፍላጎታችሁን እንድትገልፅሉን ፣እንጠይቃለን ፡፡

እንዳወቀ ፈንታ
መስከረም 8፣2015

https://forms.gle/sMye3MxgwYTo9Gsj7
👍5🤔1
SMH General Construction
🚧የሲሚንቶ ስርጭትና ዝውውርን ለመወሰን የወጣ የሕዝብ ማስታወቂያ‼️ 1. ማንኛውም የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት   መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት ለተፈቀደላቸው አካላት ብቻ የሲሚንቶ ሽያጭ መፈፀም አለበት፤ 2. በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 መሠረት በፌደራልም ወይም በክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ በመወሰድ ለየክልልና ከተሞች…
የሲሚንቶ ምርት በተመጣጠነ ዋጋ እየቀረበ ነው ተባለ፡፡ ከ550 ብር ጀምሮ ለሽያጭ ቀረቧል።

*የሚሸጥባቸው ቅርንጫፎች
👉በአብነት፣
👉ጦር ሀይሎች፣
👉በኮልፌ፣
👉በፈረንሳይ እና ጨው በረንዳ በሚገኙ ቅርንጫፍ ሽያጭ እየተደረገ ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍1
🚧አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው። በመሆኑም ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ፦

"The reasons a building collapses can be due to
*poor structural design,
*poor compliance with specifications
*poor quality control
*faulty construction methodology foundation failure
*extraordinary loads and corruption. Natural disaster is also identified as a cause of building collapse.

✍️በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል
☑️ poor structural design
☑️faulty construction
☑️poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።

*አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??

#⃣ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1,በ Fatigue ና
2, Creep ነው

1,Fatigue
*ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡

2,Creep
*አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡


@ethioengineers1
👍9