Continued …….
3. Sanding - unreasonable sand grading, high mud content too fine soil and sand will also cause the ground sand, affecting the early hydration of cement and concrete condensation. construction vibration is too large: this will aggravate the concrete surface bleeding, thereby reducing the surface strength of concrete.
፫. አርማታችን - ከተፈለገው በላይ ነጭ የመሆን(“አመዳም”) የመሆን ነገር ይሄም የሚሆነው አርማታ በሚቦካበት ጊዜ ያልተፈለጉ ብናኞች ሲዋሀዱ ነው፤ በ አርማታ ውህደት ጊዜ በውሀ እና በሲሚንቶ መሀል ያለው ውህደት temperature ከፍ እንዲል ያደርጋል ይሄም hydration ይባላል ወይም ደግሞ (concrete maturity) ብዙ ብናኞች በገቡ ጊዜ አርማታችን ቶሎ ይረጋል ከወትሮ ቀደም ብሎ ይሄም የ አርማታው ጥንካሬ (compressive strength) ላይ በ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል
4. Cracks in concrete- the deformation of concrete it might be due to ratio or quality of material
፬. የ አርማታ መሰንጠቅ - ይሄም የሚሆነው አርማታ ስናቦካ የምንፈልገውን compressive strength(fck) ለማግኘት በratio ነው ወይም በመስፈር በዚን ጊዜ የ አሰፋፈር ችግር ካለ in the long run ስንጥቃት ይኖራል ሌላው ደግሞ የ ግብዓት ጥራት ለምሳሌ ደለላማ አሸዋ ከተጠቀምን ስንጥቃት ይበዛዋል
5. Concrete segregation- one of the defects of concrete it’s the separation of cement paste and aggregates of concrete from each other during handling and placement.
፭. የ አርማታው አይን ማውጣት - ጠጠሩ ከተበጠበጠው ሲሚንቶ(paste) ጋር ሲለያይ እና ጠጠሮች በተሞሉ(cast) በተደረጉ አርማታዎች መታየት ሲጀምሩ
Prepared by :- jordano jomole
https://t.me/ethioengineers1

Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍4
d230a9d7-5091-4324-ae52-7444853ca3fe.pdf
2.3 MB
🚧የኮንስትራክሽን ፍቃድ ማውጣት ለምትፈልጉ
🏗በኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
https://t.me/ethioengineers1
🏗በኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
https://t.me/ethioengineers1
👍4❤2
ዉድ የእትዮ-ኮንስትራክሽን ቤተሰቦቻችን G"NBATA ገበያ ላይ ነው‼️
በምህንድስና ዘርፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ "G'NBATA" የተሰኘ መፅሀፍ ለገበያ ቀርቧል።
መፅሀፉ የግንባታ ቴክኒኮችን፣ የግንባታ ሂደት፣ የዘርፉ ተዋናዮች፣ የግንባታ ደህንነት እንዲሁም ሌሎች የግንባታ ዘርፍ እውነታዎችን በጥልቀት ይዳስሳል።
መፅሀፉ በተለይ ለምህንድስና ተማሪዎች እና በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ደራሲው ኢንጂነር ባስልኤል ተዋበ ገልጸዋል።
በእንግሊዝኛ የተጻፈው መፅሀፉ፤ በ380 ብር ለገበያ ቀርቧል።

👍9
🚧 TRUSS
.
*Truss የምንለው Axial Load (compressive & tensile force) ብቻ የሚሸከሙ መዋቅሮች ናቸው፡፡
የትረስ ሜምበሮች የሚገናኙት በፒን ኮኔክሽን ማለትም (በአብዛኛው በብየዳና በብሎን ) ነው የሚገናኙት፡፡
*ሁለት አይነት ትረሶች አሉ
1,Plain (2D)
2,Space truss (3D
ለምሳሌ የቴሌ ታወሮች )፡፡ *ትረሶችን ለህንፃና ለድልድዮች
ተመራጭ የሆኑበት ምክንያት ጠንካራና ክብደታቸው ቀላል ስለሆነ ነው፡፡ እናም ዛሬ ስለትረስ ልናወራ የቻልንበት ዋነኛ ምክንያት ብዙ ሳይቶች ላይ የግንባታ ግድፈት ስለምናይ አንዳንድ ነገር ለመጠቆም ያህል ነው::
ምንድነው ነገሩ ትረሶች ሲፈጠሩ Axial Load ብቻ እንዲሸከሙ ነው ሺርና ሞመንት መሸከም አይችሉም - Axial ፎርስም የሚሸከሙት የሚመጣውን ሎድ ቀጥታ መገናኛቸው ወይም joint ላይ ሲጫንባቸው ብቻ ነው:: ይህም ከጆይቱ ነው ወደ ሜምበሮች ሄዶ ከዛ ነው ወደ ኮለን ወይም ቢም የሚሄደው - ሳይት ላይ ግን ፐርሊኑን መሃል ሜምበሮቹ ላይ ሲበይዱት ይታያል - joint ላይ ነው መበየድ ወይም መታሰር ያለበት - ሳይት ላይ የሚደረገው ከሳይንስ ውጪ ነው ሃይለኛ ንፋስ ወይም ዝናብ ያለባቸው አካባቢዎች ይህ ነገር አሳሳቢ እና ኣደጋም ሊያደርስ ይችላል፡፡
https://t.me/ethioengineers1
.
*Truss የምንለው Axial Load (compressive & tensile force) ብቻ የሚሸከሙ መዋቅሮች ናቸው፡፡
የትረስ ሜምበሮች የሚገናኙት በፒን ኮኔክሽን ማለትም (በአብዛኛው በብየዳና በብሎን ) ነው የሚገናኙት፡፡
*ሁለት አይነት ትረሶች አሉ
1,Plain (2D)
2,Space truss (3D
ለምሳሌ የቴሌ ታወሮች )፡፡ *ትረሶችን ለህንፃና ለድልድዮች
ተመራጭ የሆኑበት ምክንያት ጠንካራና ክብደታቸው ቀላል ስለሆነ ነው፡፡ እናም ዛሬ ስለትረስ ልናወራ የቻልንበት ዋነኛ ምክንያት ብዙ ሳይቶች ላይ የግንባታ ግድፈት ስለምናይ አንዳንድ ነገር ለመጠቆም ያህል ነው::
ምንድነው ነገሩ ትረሶች ሲፈጠሩ Axial Load ብቻ እንዲሸከሙ ነው ሺርና ሞመንት መሸከም አይችሉም - Axial ፎርስም የሚሸከሙት የሚመጣውን ሎድ ቀጥታ መገናኛቸው ወይም joint ላይ ሲጫንባቸው ብቻ ነው:: ይህም ከጆይቱ ነው ወደ ሜምበሮች ሄዶ ከዛ ነው ወደ ኮለን ወይም ቢም የሚሄደው - ሳይት ላይ ግን ፐርሊኑን መሃል ሜምበሮቹ ላይ ሲበይዱት ይታያል - joint ላይ ነው መበየድ ወይም መታሰር ያለበት - ሳይት ላይ የሚደረገው ከሳይንስ ውጪ ነው ሃይለኛ ንፋስ ወይም ዝናብ ያለባቸው አካባቢዎች ይህ ነገር አሳሳቢ እና ኣደጋም ሊያደርስ ይችላል፡፡
https://t.me/ethioengineers1
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍3🔥1
🚧በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ በተደረመሰው ድልድይ ምክንያት ተጠያቂው ማን ነው? (From technical point of view)
1. የድልድዩ ዲዛይን ችግር ካለበት (standard ያላሟላ ዲዛይን) ከሆነ የድልድዩን ጥናትና ዲዛይን የሠራ አካልና ለተሰራው ጥናትና ዲዛይን እውቅና የሠጠ (authority body) ይሆናል።
2. የድልድዩን ግንባታ ጥራት ይቆጣጠር የነበረ አማካሪ (ኮንሰልቲንግ) ድርጅት የተሰረው ዲዛይን በትክክል ሥራ ላይ እንዳይውል አድርጎ ከሆነ አማካሪው ድርጅት ሀላፊነቱን ይወስዳል።
3. የድልድዩን ግንባታ ሲያካሄድ የነበረው የሥራ ተቋራጭ ውል በገባው መሠረት (specification & drawings) የድልድዩን ግንባታ ካልሰራ ተጠያቂ ይሆናል።
*4. የድልድዩ ዲዛይን ሲሰራ የመሸከም አቅሙ ተገድቦ ከሆነ (load limitations) የመሸከም አቅሙም በግልጽ ተቀምጦ ከሆነ በዛሬው ዕለት ለፈተና የሄዱት ተማሪዎች ከድልድዩ የመሸከም አቅም በላይ እንድጠቀሙ ያደረጉት አካላት ተጠያቂ ይሆናሉ‼️
ከሁሉ በላይ በቴክኖሎጂ (engineering faculty) ግቢ ውስጥ የተሰራው ድልድይ ተደረመሰ የሚል ዜና መስማት ግን በጣም ያሳዝናል።
ከህግ አንፃር ደግሞ የህግ ባለሙያዎች ማብራሪያ ቢሰጡ ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ።
Raji lemasa

👍6
SMH General Construction
🚧በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ በተደረመሰው ድልድይ ምክንያት ተጠያቂው ማን ነው? (From technical point of view) 1. የድልድዩ ዲዛይን ችግር ካለበት (standard ያላሟላ ዲዛይን) ከሆነ የድልድዩን ጥናትና ዲዛይን የሠራ አካልና ለተሰራው ጥናትና ዲዛይን እውቅና የሠጠ (authority body) ይሆናል። 2. የድልድዩን ግንባታ ጥራት ይቆጣጠር የነበረ አማካሪ (ኮንሰልቲንግ) ድርጅት…
ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ ይህን ብለዋል…
አንድ ግንባታ ሲገነባ ቋሚ ክብደት (ዴድ ሎድ) ተንቀሳሽ ከብደት (ላይቭ ሎድ) የሚባል አለ። ለምሳሌ እነዚህ ተንቀሳቃሽ ወይም ድንገት መጥ ክብደቶች ሊመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምተው ዲዛይን ተደርገው ይገነባሉ።
ድንገት የሚመጡ ክብደቶች ለመቆጣጠር አዳጋች የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ አንድ የመሸጋገሪያ ድልድይ በላዩ ማለፍ የሚችለው ክብደት 4ቶን ቢሆን 100ቶን በላዩ ላይ ቢቆም ኮላብስ ሊያደርግ ይችላል።
በእኛ ሀገር ብዙውን ጊዜ የሚገነቡ ህንፃዎች ሥራቸው የሚወሰነው ካለቁ በኋላ በገንቢው ወይም በባለቤቱ ነው።
ለመኖሪያ ቤት የተገነባ ህንጻ በአካባቢው አዳራሽ እንደሌለ የተረዳው ገንቢው የሰርግ ወይም የስብሰባ አዳራሽ ሊያደርገው ይችላል።
ተመልከቱ ለመኖሪያ ቤት ዲዛይን ሲደርግ ተንቀሳቃሽ ክብደቱ ከ 5 - 10 ቤተሰብ ሊሆን ይችላል። ይሄው ቤት ለስብሰባ ወይም ለሰርግ አዳራሻ ቢደርግ 100 ሰው ተሸከም እያልነው ነው። አሥር ሰው እንዲይዝ የተሰራን ቤት 100 ሰዉ መሸከም ለምን አልቻለም አይባልም።
100 ሰው ለሠርግ ገብቶበት ሰዉ እየዘለለ ቢጨፍርበት በዚህ አጋጣሚ ያ! ወለል ኮላብስ ሊያደርግ ይችላል። ለምን ከአቅሙ በላይ ሸክም ስለ መጣባት ነው። በዚህ ጉዳይ ኮንትራክተሩም ይሁን የንድፍ ባለሙያው ሊወቀሱ አይችሉም።
የአዋሳ ዩኒቨርስቲ ሁለቱን ግቢ አገናኝ ድልድይ ምናልባት ዲዘይን የተደረገው በአንዴ ከ10-15 ሰዉ ያልፍበታል ተብሎ ተገምቶ ይሆናል። ነገር ግን 200 ተማሪ ከቆመበት ለምን ፈረስ ሊባል ላይችል ይችላል።
ሁሉም የመያዝ አቅም ይኖረዋል። የዲዛይንና የግንባታ ችግር ፈጽሞ ሊኖር አይችልም እያልኩ አይደለም። ጋዜጠኞች ስትተቹ በቂ መረጃ ኖሯችሁ እንዲሆን ብዬ ነው።

👍8
👆የሥራ ተቋራጭ (Contractor) የሕግ ተጠያቂነት❗
በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክቦች ያሉ ሲሆን እነሱም 👉 ግዚያዊ ርክክብ እና የመጨረሻ ርክክብ በመባል ይታወቃሉ፡፡
1/ ግዚያዊ ርክክብ
ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ነው:: (የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1)):: ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው፡፡ በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
እንግዲህ ስራው ከተመረመረ በኋላ አሰሪው ያላመነበትን ግንባታ ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል:: በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል፡፡
2/ የመጨረሻ ርክክብ
የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት ፣ ለስራው ጥራት መድህን ሆኖም ይቀጥላል፡፡ ስለሆነም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተደረመሰውን ድልድይ የገነባው ሥራ ተቋራጭ ለደረሰው ጉዳት በሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት አግባብ ሊኖር ይችላል:: ይሁን እንጂ በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ የጥራት ጉድለቶች ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡
በአጠቃላይ በደረሰው አደጋ ዙሪያ ሙያዊ ማብራሪያ ለመስጠት ዝርዝር ጥናት ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን በዋናነት ድልድዩ የተደረመሰው መሸከም ከሚችለው ጭነት (Load) በላይ ስለተጫነበት ነው ❓ወይስ ችግሩ ከዲዛይኑ ነው❓ ወይስ በግንባታው ሂደት የማቴሪያል ጥራትና የወርክ ማን ሽፕ ችግር❓ ...መጠናት አለበት። በተለይ የግንባታ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ አስተያየታችሁን ስጡበት::
👇
@Ethiocon143bot
በመጨረሻም የዩኒቨርስቲው ህንፃ አስተዳደር አካል ጥንቃቄ እዲደረግ እና ድልድዩ መቻል የሚችለዉን የጭነት መጠን መግለፅ ነበረበት::
ጉዳቱ ለደረሰባቸው ተማሪዎችና ቤተሠባቸው መረጋጋትንና መፅናናትን እመኛለሁ።🙏
https://t.me/ethioengineers1
በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክቦች ያሉ ሲሆን እነሱም 👉 ግዚያዊ ርክክብ እና የመጨረሻ ርክክብ በመባል ይታወቃሉ፡፡
1/ ግዚያዊ ርክክብ
ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ነው:: (የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1)):: ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው፡፡ በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
እንግዲህ ስራው ከተመረመረ በኋላ አሰሪው ያላመነበትን ግንባታ ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል:: በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል፡፡
2/ የመጨረሻ ርክክብ
የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት ፣ ለስራው ጥራት መድህን ሆኖም ይቀጥላል፡፡ ስለሆነም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተደረመሰውን ድልድይ የገነባው ሥራ ተቋራጭ ለደረሰው ጉዳት በሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት አግባብ ሊኖር ይችላል:: ይሁን እንጂ በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ የጥራት ጉድለቶች ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡
በአጠቃላይ በደረሰው አደጋ ዙሪያ ሙያዊ ማብራሪያ ለመስጠት ዝርዝር ጥናት ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን በዋናነት ድልድዩ የተደረመሰው መሸከም ከሚችለው ጭነት (Load) በላይ ስለተጫነበት ነው ❓ወይስ ችግሩ ከዲዛይኑ ነው❓ ወይስ በግንባታው ሂደት የማቴሪያል ጥራትና የወርክ ማን ሽፕ ችግር❓ ...መጠናት አለበት። በተለይ የግንባታ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ አስተያየታችሁን ስጡበት::
👇
@Ethiocon143bot
በመጨረሻም የዩኒቨርስቲው ህንፃ አስተዳደር አካል ጥንቃቄ እዲደረግ እና ድልድዩ መቻል የሚችለዉን የጭነት መጠን መግለፅ ነበረበት::
ጉዳቱ ለደረሰባቸው ተማሪዎችና ቤተሠባቸው መረጋጋትንና መፅናናትን እመኛለሁ።🙏
https://t.me/ethioengineers1
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍3
#ለአደጋው መከሰት ችግሩ የዲዛይን፣የግንባታ ጥራት መጓደል ወይስ የአጠቃቀም ችግር የሚለው በባለሙያ መረጋገጥ ይኖርበታል።
የስፓኑ ስፋት ግን ይገርማል።ያለምሰሶ ይሄን ያህል ድልድይ መቆሙ ያስገርማል❗️
*ጥራት የሌለው ግንባታ የተጠመደ ፈንጅ ማለት ነው።*
ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ 🙏
https://t.me/ethioengineers1
የስፓኑ ስፋት ግን ይገርማል።ያለምሰሶ ይሄን ያህል ድልድይ መቆሙ ያስገርማል❗️
*ጥራት የሌለው ግንባታ የተጠመደ ፈንጅ ማለት ነው።*
ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ 🙏
https://t.me/ethioengineers1
👍5
🚧ስለ ኮንክሪት እና የኮንክሪት ግሬዶች
.
⚡ኮንክሪት (concrete) ስሙን ያገኘው ከጥንት ሮማኖች ሲሆን
ቃሉም የመጣው ኮንክሪተስ (Concretus) ከሚለው የሮማኖች ቃል ነው የቃል በቃል ትርጉሙ ተያይዞ ማደግ / አንድ ላይ ማደግ የሚለውን ይወክላል።
.
*ኮንክሪት በአለም ላይ በብዛት የምንጠቀመው የግንባታ ቁስ ነው።
ኮንክሪት የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠሮች ውህድ ነው ።
የኮንክሪት የእመቃ ጥንካሬ (compressive strength)
ሚለካው በግሬዱ ነው (Grade)። የተለያዩ የኮንክሪት ግሬዶች
አሉ C-5 ፣ C-15 C-25 C-30 ወዘተ የኮንክሪት ግሬድ ማለት
ኮንክሪቱ ከሃያ ስምንት ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
(compressive strength ) ማለት ነው ለምሳላ C-25 የሆነ
ኮንክሪት ግሬድ ከ28 ቀን በኋላ የሚኖረው የእመቃ ጥንካሬ
25N/mm^2 ይሆናል ማለት ነው የC-30 ግሬድ ደግሞ
ጥንካሬው 30N/mm^2 ነው
.
*ለውሃ ስራዎች ብዙን ግዜ ተመራጩ የኮንክሪት ግሬድ ከ C-30 በላይ ነው
.
*አንዳንድ ግዜ የኮንክሪት ግሬዶች በተለያዩ መፅሃፎች በተለያየ
መልክ ይጠቀሳሉ ለምሳሌ አንዳንድ መፅሃፎች C-30 C-15
የሚለውን አጠቃቀስ ሲጠቀሙ አንዳንዶቹ ደግሞ M-30 M-15
የሚለውን ይጠቀማሉ .
«C»የሚጠቀሱ የኮንክሪት ግሬዶች በC መጠቀሳቸው የእመቃ ጥንካሬያቸው የተለካው በሲሊንደሪካል ፍተሻ (CYLINDRICAL test ) ስለሆነ ነው በM የሚጠቀሱት ደግሞ ፍተሻው (test) የተደረገው በኪውቢክ ፍተሻ (cubic test) ስለሆነ ነው። በሁለቱ የፍተሻ አይነቶች የሚደረጉ የኮንክሪት ግሬዶች የእመቃ ጥንካሬአቸው ይለያያል። ሲሊንደሪካል ፍተሻ በአንፃራዊነት የኮንክሪትን ትክክለኛ እምቅ ጥንካሬ ይገልፃል ስለዚህ ከኪውቢክ ፍተሻው የተሻለ ነው ማለት ነው።
@ethioengineers1

👍21
🚧ስለንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract)
-ንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract) በፍትሀብሄር ህጉ አገላለጽ ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ ይባላል፡፡ ይሄውም ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በከፊል ለማስፈጸም ከአንድ ሶስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(2))
-ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ደግሞ ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(1))
-ስለዚህ ንኡስ ተቋራጭነት የግንባታ ስራ ተቋራጮች ከአሰሪው ጋር ሊገነቡት ግዴታ የገቡበትን የግንባታ ስራ በከፊል ለሌላ ተቋራጭ በውል በሚያሰሩበት ጊዜ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ውሎችን ለሌላ መልቀቅ የሚባለውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡
-ንኡስ ተቋራጭነት ሁለት አይነት ነው፡፡በአሰሪው የሚታወቅ(Nominated sub-contracting) እና በአሰሪው የማይታወቅ(Non nominated sub-contracting)::ከውጤት አንጻር ተመሳሳይ ቢሆኑም ንኡስ ተቋራጭነቱን አሰሪው የፈቀደውና ያወቀው የሆነ እንደሆነ ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ከመዘግየት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3206)
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩበት ክፍያ ከማን መጠየቅ ይችላሉ?
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩት ስራ በውላቸው መሰረት ከዋናው ተቋራጭ ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 1755፣1756) ምክንያቱም ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ1731)
-በተጨማሪም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3040 በአንድ የህንጻ ስራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ወይም ሰራተኞች የሰሩበትን ስራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሰሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን ለመጠየቅ መብት አላቸው በሚል ይደነግጋል፡፡ስለዚህ ከዋናው አሰሪ ላይም በቀጥታ ክፍያ ለመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡
https://t.me/ethioengineers1
-ንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract) በፍትሀብሄር ህጉ አገላለጽ ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ ይባላል፡፡ ይሄውም ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በከፊል ለማስፈጸም ከአንድ ሶስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(2))
-ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ደግሞ ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(1))
-ስለዚህ ንኡስ ተቋራጭነት የግንባታ ስራ ተቋራጮች ከአሰሪው ጋር ሊገነቡት ግዴታ የገቡበትን የግንባታ ስራ በከፊል ለሌላ ተቋራጭ በውል በሚያሰሩበት ጊዜ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ውሎችን ለሌላ መልቀቅ የሚባለውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡
-ንኡስ ተቋራጭነት ሁለት አይነት ነው፡፡በአሰሪው የሚታወቅ(Nominated sub-contracting) እና በአሰሪው የማይታወቅ(Non nominated sub-contracting)::ከውጤት አንጻር ተመሳሳይ ቢሆኑም ንኡስ ተቋራጭነቱን አሰሪው የፈቀደውና ያወቀው የሆነ እንደሆነ ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ከመዘግየት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3206)
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩበት ክፍያ ከማን መጠየቅ ይችላሉ?
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩት ስራ በውላቸው መሰረት ከዋናው ተቋራጭ ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 1755፣1756) ምክንያቱም ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ1731)
-በተጨማሪም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3040 በአንድ የህንጻ ስራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ወይም ሰራተኞች የሰሩበትን ስራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሰሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን ለመጠየቅ መብት አላቸው በሚል ይደነግጋል፡፡ስለዚህ ከዋናው አሰሪ ላይም በቀጥታ ክፍያ ለመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡
https://t.me/ethioengineers1
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍22🙏2
🏗በህንፃዎች ላይ በእርጥበት ምክንያት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮች እንደሚከተለው ሊጠቃለሉ ይችላሉ ።
1. efflorescence ሊያስከትል ይችላል, ይህም በመጨረሻ ወደ ድንጋይ, ጡቦች እና ጡቦች መፈራረስ ሊያመራ ይችላል.
2. የልስን መሰነጣጠቅ ( መሰባበር) ሊያስከትል ይችላል.
3. It can cause bleaching and flaking of paint, leading to the appearance of coloured patches.
4. የእንጨት መበስበስ ,መሰነጠቅ ሊያስከትል ይችላል
(This can lead to deformation, warping and rotting of wood)
5. የብረታ ብረት መዛግ,መሰበር ሊያስከትል ይችላል.
6. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች መበላሸት ሊያስከትል ይችላል(It could cause the deterioration of electrical fittings)
7. ምስጦችን እንድበዙ ይረዳል(It aids in the growth of termites)
8. *ለነዋሪዎች ደህንነቱ ያልተጠበቀ የኑሮ ሁኔታን ያስከትላል(It causes unsafe living conditions for residents)

👍15
#የኮንስትራክሽን_ውል_የተደረገበት_ቀን (contract_signing_date) እና
#በኮንስትራክሽን_ውል_የስራ_መጀመሪያ_ቀን/(Commencement_date)
በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡
1,በኮንስትራክሽን_ውል_የስራ_መጀመሪያ_ቀን (Commencement_date )
👉በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/ ካልተፈጸመለት ስራ መጀመር አይችልም፡፡ስለዚህ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታውን ጊዜ መቁጠር ተገቢነት የለውም፡፡እንደዚሁም ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡
👉በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡ይሄ ተገቢ አሰራር አይደለም፡፡
👉በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡
FIDIC RED BOOK 1999
👉በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡ እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡
👉ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ 8 ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል፡፡
FIDIC 1987
👉በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡
👉እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡
MoWUD 1994
👉ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994/ በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡
PPA 2011
👉በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡
የፍትሀብሄር ህግ
👉የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610-2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡
የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡
👉የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡
👉ይሄውም በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የግንባታ ስራዎቹ በሙሉ የሚከናወኑበት ጠቅላላው ጊዜ ብቻ ተጠቅሶ እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት/client/ የግንባታ ስራው የሚጀመርበትን ጊዜ/ Commencement date/ ዘርዝሮ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3253(2) ላይ ተደንግጓል፡፡

👍39
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
● Short presentation for Bridge Design with Midas Civil software Starting on November 5/2022
👇👇👇
https://youtu.be/H7tjYQU-eBA
👇👇👇
https://youtu.be/H7tjYQU-eBA
❤8👍5
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
Contents of Bridge Design with Midas Civil Software
I) General introduction ( 1 hr)
II) Major Drainage Structures (Bridges)
● Superstructure design
● Slab Bridge Design (10 hrs)
● T-Girder Bridge Design (15 hrs)
● Box Girder Bridge Design (10 hrs)
● Substructure Design
● Abutment Design (5 hrs)
● Pier Design (10 hrs)
III) Minor Drainage Structures (Culverts)
● Box Culvert Design (10 hrs)
● Slab Culvert Design (5 hrs)
● Retaining Wall Design
● Bridge and Culverts Drawing Preparation ,and Detailing (5hrs)
IV) Bill of Quantity Preparation (BOQ) (5hrs)
● Manuals:
- AASHTO LRFD BRIDGE DESIGN SPECIFICATIONS
- ERA MANUAL 2013
● Softwares
- AutoCAD
- Microsoft Excel
- Midas Civil
https://t.me/BeGetEngineering
📌 Megenagna, Marathon Bldg, Office No. 614
📲 ፦ 0911890392 / 0920933016

የማምረት ተግባራቸው ተስተጓጉሎ የነበሩ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ማምረት ጀመሩ!
በጸጥታ ችግር ምክንያት የማምረት ተግባራቸውን የተስተጓጎለው የታጠቅ እና የሙገር ሲምንቶ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት መመለሳቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡
https://t.me/ethioengineers1
በጸጥታ ችግር ምክንያት የማምረት ተግባራቸውን የተስተጓጎለው የታጠቅ እና የሙገር ሲምንቶ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት መመለሳቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡
https://t.me/ethioengineers1
👍12
Forwarded from BeGet Engineering Plc [CENGG]
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bridge with Midas Civil Software
Class on Progress📲 0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍7
🚧8ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ሳምንት እና 6ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ኮንፈረንስ ሊከበር ነው።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ መሀንዲሶች የሚካፈሉበት ይህ ፕሮግራም፣ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ፕሮግራሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንደገለፁት፣ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ20 በላይ የተለያዩ የጥናት ፅሁፎች ከሀገራችን እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተውጣጡ ባለሙያዎች ይቀርባሉ።
ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው ይህ ዝግጅት፣ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን መክፈቻውንም በሳይንስ ሙዚየም ያደርጋል ነው ያሉት።
ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓለም ኢንጂነሪንግ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የኮንፍረንሱ ፕሬዝዳንት የተገኙ ሲሆን "ሁሌም ለአፍሪካ የሌላ ሀገር መሀንዲሶች መንገዱን ፣ ህንፃውን መስራት የለባቸውም፤ይህ ቀጣይነት የለውም፣በእኛው በራሳችን መስራት አለብን፤ እንችላለንም " ሲሉ ገልጸዋል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት የሪል ስቴት አልሚ ተቋማት ፣ የሊዝ አገልግሎት ሰጪዎች ፣ የሀገራት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስቴሮች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘርፉ መምህራን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
መሪ ቃሉም “የአፍሪካን የመሠረተ ልማት ዕድገት በጋራ እናፋጥን” የሚል መሆኑንም ለማወቅ ችለናል።
source :Ethio Fm
https://t.me/ethioengineers1
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ መሀንዲሶች የሚካፈሉበት ይህ ፕሮግራም፣ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ፕሮግራሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንደገለፁት፣ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ20 በላይ የተለያዩ የጥናት ፅሁፎች ከሀገራችን እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተውጣጡ ባለሙያዎች ይቀርባሉ።
ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው ይህ ዝግጅት፣ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን መክፈቻውንም በሳይንስ ሙዚየም ያደርጋል ነው ያሉት።
ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓለም ኢንጂነሪንግ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የኮንፍረንሱ ፕሬዝዳንት የተገኙ ሲሆን "ሁሌም ለአፍሪካ የሌላ ሀገር መሀንዲሶች መንገዱን ፣ ህንፃውን መስራት የለባቸውም፤ይህ ቀጣይነት የለውም፣በእኛው በራሳችን መስራት አለብን፤ እንችላለንም " ሲሉ ገልጸዋል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት የሪል ስቴት አልሚ ተቋማት ፣ የሊዝ አገልግሎት ሰጪዎች ፣ የሀገራት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስቴሮች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘርፉ መምህራን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
መሪ ቃሉም “የአፍሪካን የመሠረተ ልማት ዕድገት በጋራ እናፋጥን” የሚል መሆኑንም ለማወቅ ችለናል።
source :Ethio Fm
https://t.me/ethioengineers1
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍10❤5
🚧ይህ የሂሳባዊ ጂኦሜትሪ ፅንሰ ሀሳብ "issoseles triangle inscribed in a circle"
ስንቶቻችን ነን በኮንስትራክሽን ሳይት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የምናውቀው?
ይህ የምትመለከቱት ሂሳባዊ ጂኦሜትሪ በተለየ መልኩ በኮንስትራክሽን ሳይት በበሮች፣በመስኮቶችና በበረንዳ ኮለኖች መካከል የምንሰራቸው( ከግማሽ) ሰርክል ውጪ የሆኑ በሌላ አገላለፅ የአርኩ ዲያሜትር ከላይ ከጠቀስኳቸው ከበሮች፣ከመስኮቶችና ከኮለኖች ውጪ ሲሆን አርኮችን ለመስራት የምንጠቀምበት ጂኦሜትሪ ነው።
እንዴት አድርገን ሳይት ውስጥ እንደምንጠቀምበት ቀጥለን እንመልከት 👇

👍10❤4🤔1