SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
🏗በህንፃዎች ላይ በእርጥበት ምክንያት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮች እንደሚከተለው ሊጠቃለሉ ይችላሉ ።

1. efflorescence ሊያስከትል ይችላል, ይህም በመጨረሻ ወደ ድንጋይ, ጡቦች እና ጡቦች መፈራረስ ሊያመራ ይችላል.

2. የልስን መሰነጣጠቅ ( መሰባበር) ሊያስከትል ይችላል.

3. It can cause bleaching and flaking of paint, leading to the appearance of coloured patches.

4. የእንጨት መበስበስ ,መሰነጠቅ ሊያስከትል ይችላል
(This can lead to deformation, warping and rotting of wood)

5. የብረታ ብረት መዛግ,መሰበር ሊያስከትል ይችላል.

6. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች መበላሸት ሊያስከትል ይችላል(It could cause the deterioration of electrical fittings)

7. ምስጦችን እንድበዙ ይረዳል(It aids in the growth of termites)

8. *ለነዋሪዎች ደህንነቱ ያልተጠበቀ የኑሮ ሁኔታን ያስከትላል(It causes unsafe living conditions for residents)


https://t.me/ethioengineers1
👍15
#የኮንስትራክሽን_ውል_የተደረገበት_ቀን (contract_signing_date) እና
#በኮንስትራክሽን_ውል_የስራ_መጀመሪያ_ቀን/(Commencement_date)


በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡

1,በኮንስትራክሽን_ውል_የስራ_መጀመሪያ_ቀን (Commencement_date )

👉በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/ ካልተፈጸመለት ስራ መጀመር አይችልም፡፡ስለዚህ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታውን ጊዜ መቁጠር ተገቢነት የለውም፡፡እንደዚሁም ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡

👉በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡ይሄ ተገቢ አሰራር አይደለም፡፡

👉በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡

FIDIC RED BOOK 1999

👉በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡ እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡

👉ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ 8 ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል፡፡

FIDIC 1987

👉በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡

👉እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡

MoWUD 1994

👉ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994/ በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡

PPA 2011

👉በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡

የፍትሀብሄር ህግ

👉የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610-2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡

የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

👉የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡

👉ይሄውም በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የግንባታ ስራዎቹ በሙሉ የሚከናወኑበት ጠቅላላው ጊዜ ብቻ ተጠቅሶ እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት/client/ የግንባታ ስራው የሚጀመርበትን ጊዜ/ Commencement date/ ዘርዝሮ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3253(2) ላይ ተደንግጓል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍39
● Short presentation for Bridge Design with Midas Civil software Starting on November 5/2022
👇👇👇
https://youtu.be/H7tjYQU-eBA
❤8👍5
🚧የስራ ቦታ የደህንነት ጉዳይ ይታሰብበት !!

https://t.me/ethioengineers1
👍13❤2🤔1
Contents of Bridge Design with Midas Civil Software       
I) General introduction   ( 1 hr)   
II) Major Drainage Structures (Bridges)     
● Superstructure design    
      ● Slab Bridge Design   (10 hrs)
      ● T-Girder Bridge Design   (15 hrs)
      ● Box Girder Bridge Design   (10 hrs)
  ● Substructure Design    
        ● Abutment Design   (5 hrs)
        ● Pier Design   (10 hrs)
III)  Minor Drainage Structures (Culverts)     
       ● Box Culvert Design    (10 hrs)
       ● Slab Culvert Design    (5 hrs)
       ● Retaining Wall Design     
● Bridge and Culverts Drawing Preparation ,and Detailing     (5hrs)
IV) Bill of Quantity Preparation (BOQ)     (5hrs)
      
       ● Manuals:     
   - AASHTO LRFD BRIDGE DESIGN SPECIFICATIONS    
   - ERA MANUAL 2013    
        ● Softwares     
   - AutoCAD    
   - Microsoft Excel    
   - Midas Civil

https://t.me/BeGetEngineering
📌 Megenagna, Marathon Bldg, Office No. 614
📲 ፦ 0911890392 / 0920933016
👍15
የማምረት ተግባራቸው ተስተጓጉሎ የነበሩ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ማምረት ጀመሩ!

በጸጥታ ችግር ምክንያት የማምረት ተግባራቸውን የተስተጓጎለው የታጠቅ እና የሙገር ሲምንቶ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት መመለሳቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

https://t.me/ethioengineers1
👍12
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bridge with Midas Civil Software
Class on Progress


📲 0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍7
🚧8ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ሳምንት እና 6ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ኮንፈረንስ ሊከበር ነው።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ120 በላይ መሀንዲሶች የሚካፈሉበት ይህ ፕሮግራም፣ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ፕሮግራሙን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንደገለፁት፣ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ20 በላይ የተለያዩ የጥናት ፅሁፎች ከሀገራችን እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በተውጣጡ ባለሙያዎች ይቀርባሉ።

ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው ይህ ዝግጅት፣ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን መክፈቻውንም በሳይንስ ሙዚየም ያደርጋል ነው ያሉት።

ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓለም ኢንጂነሪንግ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የኮንፍረንሱ ፕሬዝዳንት የተገኙ ሲሆን "ሁሌም ለአፍሪካ የሌላ ሀገር መሀንዲሶች መንገዱን ፣ ህንፃውን መስራት የለባቸውም፤ይህ ቀጣይነት የለውም፣በእኛው በራሳችን መስራት አለብን፤ እንችላለንም " ሲሉ ገልጸዋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት የሪል ስቴት አልሚ ተቋማት ፣ የሊዝ አገልግሎት ሰጪዎች ፣ የሀገራት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስቴሮች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘርፉ መምህራን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
መሪ ቃሉም “የአፍሪካን የመሠረተ ልማት ዕድገት በጋራ እናፋጥን” የሚል መሆኑንም ለማወቅ ችለናል።

source :Ethio Fm
https://t.me/ethioengineers1
👍10❤5
🚧ይህ የሂሳባዊ ጂኦሜትሪ ፅንሰ ሀሳብ "issoseles triangle inscribed in a circle"
ስንቶቻችን ነን በኮንስትራክሽን ሳይት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የምናውቀው?
ይህ የምትመለከቱት ሂሳባዊ ጂኦሜትሪ በተለየ መልኩ በኮንስትራክሽን ሳይት በበሮች፣በመስኮቶችና በበረንዳ ኮለኖች መካከል የምንሰራቸው( ከግማሽ) ሰርክል ውጪ የሆኑ በሌላ አገላለፅ የአርኩ ዲያሜትር ከላይ ከጠቀስኳቸው ከበሮች፣ከመስኮቶችና ከኮለኖች ውጪ ሲሆን አርኮችን  ለመስራት የምንጠቀምበት ጂኦሜትሪ ነው።
እንዴት አድርገን ሳይት ውስጥ እንደምንጠቀምበት ቀጥለን እንመልከት 👇


https://t.me/ethioengineers1
👍10❤4🤔1
Answer

Info.
Floor to floor  height= 310cm
Slab thickness =15cm
Verticall RC wall drop down from Rc slab=10cm
CD=70cm 👉see the previous image
Spacing of veranda column =300cm 👉it's face to face length.
እኛ ሳይት መሀንዲስ ሆነን ተመድበን ሳይት ውስጥ ነን እንዴት አድርገን እንስራው ነው?
ሀሳቡ ግልፅ እንዲሆንላችሁ ራዲየስ እንዴት እናግኝ ነው።
በተለምዶ የምንሰራው አርክ Radis=width/2 አድርገን ነው እንደዛ ብንሰራው አንችልም ወይ? ትሉ ይሆናል ነገር ግን Width/2  የሚሰራው በጣም ለተቀራረቡ ኮለኖች በሮችና መስኮቶች ነው።
የኮለኖች፣ የበሮችና የመስኮቶች width በጨመረ ቁጥር  width/2=radius አድርገን ብንሰራ የአርክ መነሻ point ወደታች እየወረደ ስለሚመጣ እንደዛ ብንሰራ እጅግ የሚያስጠላ ዲዛይን ይሆናል።
ይሄንንም በኋላ በቁጥር አስደግፌ አቀርባለሁ።
ወደ ሀሳቡ እንመለስና
Let say
FTH) 👉floor to floor height =310cm
(FCH)👉 floor to ceiling height=295cm
FCH ማለት FTH-slab thickness ነው።
                   310cm-15cm=295cm
አርክ ቶፕ ከማድረጋችን በፊት 10 cm hanging vertically Rc wall አለን
አርኩ central top ድሮፕ የሚያደርገው ከslab bottom 10cm ወርዶ ነው 
Arch starting point =295cm-10cm-70cm=215cm
የአርክ ጫማ የሚነሳው ከመሬት በላይ 215cm ላይ ነው ማለት ነው image ከላይ አስደግፌያለሁ።


https://t.me/ethioengineers1
👍9❤6
ከዚህ በመቀጠል ግን ይህንን የምትመለከቱት figure በመያዝ የተወሰነ የgeometric calculation ሰርተን እንዴት ሬዲየስ እናገኛለን እንየው።

እንደምትመለከቱት isosles triangle ይታያል በዚህ መሠረት
AB=300cm
AD=AB/2=150cm
CD=70cm
AC=?
Phytagorian formula በመጠቀም AC እናግኝ
AC=√(AD²+CD²)=√(150²+70²)=165.53
AC=165.53cm
Find <DAC=DbBC?
tan‐¹(70÷150)=25°
Using sine low
👉165.52/sinA=300/sinC=165.52/sinB
=2R

2R=165.5/sin25°=2R=391.43cm
R=391.43cm/2=195.72cm✅
አሁን ይሄንን 195.72cm ራዲየስ ከሁለቱ ኮለኖች መሀል ባለው አናት ስላብ ወደ ታች ለክቶ በምስሉ እንደሚታየው ወርዶ በሚስማር ማርክ አድርጎ በሲባጎ አርኩን አርኩን ማርክ መመድረግና formwork ማሰራት ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍9❤6
ይህ መጨረሻ ላይ ብረት ሰርተን ኮንክሪት ሞልተን formwork ስናነሳ የምናገኘው structural member ነው።
እንግዲህ ለማንኛውም ከhalf አርክ ውጪ የሆነ የarch structure ለመስራት ያገለግላል ማለት ነው።
ከበሮች ከመስኮቶችና ከኮለኖች መሀል ላይ ከሚገኙ አርኮች በተጨማሪ የስላብ ጠርዞች የexternal structures design በሙሉ ለመሥራት መጠቀም ይቻላል🙏

https://t.me/ethioengineers1
👍7❤4
Finally

Source:- ethiopian construction work professional
prepared by :-asnake negash

https://t.me/ethioengineers1
❤6👍2🙏2
🚧ቻይና

በ19 ቀናት ይህን የሚያክል ግዙፍ ህንፃ መገንባት ከምርም ታምር ነው።

Broad sustainable building የተባለው የቻይና ድርጅት ነው ይህን ህንፃ የገነባው። በቀን ሶስት ፎቆችን እየገነባ ነው እንግዲህ 57 ፎቅ ያለውን ህንፃ ገጭ ያደረገው።

ይህ ህንፃ በውስጡ 800 አፓርትመንት ክፍሎች እና ለቢሮ የሚሆኑ አመች ቦታወች 4000 ያህልም የያዘው።

ይህም ህንፃ በሰው ልጅ የክነህንፃ ግንባታ ፈጠራ ፍጥነት አዲስ ታሪክንም ይዞዋል ነው የተባለው።


https://t.me/ethioengineers1
👍33