SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ ተማሪዎቻችን።
እናንተ የ BeGet አንባሳደሮች ናቹ።
ተጋግዘን የተሻለውን ሁሉ ለሀገራችንና ለራሳችንም እንሰራለን።

@BeGetEngineering
👍9❤8
🚧በስራ ቦታ ሁልጊዜም መገንባት ያለበት ግንኙነት

1. ከሰዎች ጋር ለመስራት ስትፈልግ ሶስት ነገሮቻቸውን ተመልከት፦ ብልህነት (intelligence)፣ ጉልበት (energy) እና ታማኝነት (integrity)፡፡ እና የመጨረሻው ከሌላቸው ስለ መጀመሪያዎቹ ሁለት ስብእናዎች አትጨነቅ!
☞ ምክንያቱም በእውነት (truth)፣ በሐቀኝነት (honesty) እና በስነ-ምግባር (ethics) ልኬቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ማንም ባይመለከታቸው እንኳ ልባቸውን ያዳምጣሉ፣ ትክክለኛውን ነገርም ያደርጋሉ ፡፡

2. ስኬታማ በሆኑና ያልተሳካላቸው ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ስኬታማ ሰዎች በማያስፈልጉ ነገሮች ላይ 'ምንጊዜም 'አይሆንም' (no) ስለሚሉ ነው።
☞ በየቀኑ ወደ እኛ አቅጣጫ ለሚመጡ አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ደግመን ደጋግመን 'አይሆንም' (no) ማለት እና አስፈላጊ ለሆኑ ጥቂት ነገሮች ትኩረት በመስጠት 'እሽ' ማለት አለብን።
ይህን መርህ በየትኛውም ነባራዊ ሁኔታ፣ በዕለት ተዕለት የውሳኔ አሰጣጥ መንታ መንገድ ላይ ስትደርስ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ይህን ካደረክ ህይወትህን ማቅለል ትችላለህ።

3. ከአንተ የተሻሉ ሰዎች ጋር ጊዜህን አሳልፍ!
☞ በባህሪያቸው ከአንተ የተሻሉ ጓደኞችን መምረጥ ከቻልክና ከእነሱ ጋር ጊዜህን ካሳለፍክ አንተም ወደዚያ አቅጣጫ መጓዝ ትችላለህ፡፡
ዕድሜህም ሆነ ያለህበት ደረጃ ምንም ይሁን ምን እንደ መሪ፣ የንግድ ሰው ፣ ሠራተኛ እና ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ የሚያደርግህን ጥበብ ፣ ልምድ እና ባህርይ የበለጠ ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች መማር አስፈላጊ ነው፡፡
.
4. ሀብታም ብትሆን ወይም የገንዘብ ነጻነት ቢኖርህ ልትሰራው የምትችለውን ስራ ለመስራት ወስን!
☞ ይህን ስታደርግ የምትወደውን እና የምትጓጓለትን ነገር መፈለግና ያንን የህይወትህ ዋና ተግባር እንድታደርገው ይረዳሃል።
ይህ ማለት በየቀኑ ልትሰራው የምትጓጓለት ስራ ስላለህ ከአልጋህ ዘለህ ትነሳለህ፣ ምንጊዜም አንድ ነገር ትማራለህ ይህም ደስታን ይሰጥሃል።

5. ዝናን ለመገንባት 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል ይህን ለማበላሸት ግን አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል ፡፡ ይህን ማስብ ከቻልክ ነገሮችን በተለየ መንገድ ማድረግ ትችላለህ።
☞ የማንኛውም ሰው ዝና ወይም እውቅና በአሸዋ እንደተገነባ ቤት በፍጥነት ሊወድቅ ይችላል። ስለሆነም በህይወት ጉዞህ የምትመራበትን ታማኝነት (integrity) በውስጣዊ የጂፒኤስ ስርዓትህ ውስጥ ሳትገነባ ከቀረህ መውደቅህ የማይቀር ነገር ነው፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍25❤4
Skill enhancement training under the title
"Role of Quantity Surveying in the overall building design and construction phases"

with Melbana Seifu

@The Urban Center
on Saturday, May 13, 2023,
from  9:00am - 12:30pm

Door opens at 8:30am

Registration is Mandatory!

Registration Link :
https://cutt.ly/I5NSWzi

The Urban Center
For better urbanity in Ethiopia
👍11
📌ትብብርን ስለመጠየቅ ይመለከታል

✋ጤና ይስጥልኝ ፤ ፉአድ ረሺድ እባላለው የ ኮንስትራክሽን ባለሙያ ነኝ በአሁን ወቅት በ Leadership and Management " ማስተርሴን ለማጠናቀቅ የመመረቂያ ጥናት በመስራት ላይ እገኛለሁ ጥናቱ በደረጃ-1 ኮንትራክተሮች ላይ የሚያተኩር ነው እናም ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ የዚህ ቻናል ቤተሰብ ይህ ከታች ያለው ፎርም እንድትሞሉልኝ በአክብሮት እጠይቃለው ፤ በቅድሚያ ለምታደርጉልኝ ትብብር እጅግ በጣም አመሰግናለው።

ሊንኩ ከዚህ በታች የተቀመጠው ነው
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdX0KJCSqQ9vRCYTykDeO8D6mRt7-vnxun_JM5-VvwcVFoRgg/viewform?usp=sf_link
👍10❤1
🏗በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ  ኢንጅነርዎች ሊያውቃቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች...
.

1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ አንማር ይሆናል ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::
:
2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን። እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።
:
3)የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !
:
4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካምድራቸው የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ   ፀባያቸውአንፃርየሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ (Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።
፡
5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ። ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል
፡
6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል ማለት ነው።
ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው::
፡
7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው። (እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)
፡
8 )የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)
ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ
ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን አደጋ ለመከላከል።
፡
9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣
ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን ነው
:
10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ
እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ ሊኖረን ይገባል።
ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።
ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና
ወሳኝ ነገር ነው።
.
አንድ ጥሩ የሚባል CONSTRUCTION እንጅነር ማወቅ ስለሚገባው ነገሮች ትንሽም
ቢሆን እውቀት እንደሰጠናቹ ተስፋ እናረጋለን::

@ethioengineers1
👍67💯4🙏3❤2
የኮንስትራክሽን ውል አደጋዎች ‼️

🏗የኮንስትራክሽን ኮንትራትን መንደፍ ወይም ማርቀቅ በየደቂቃዎች ውስጥ
ከመፈራረም አንድ ሚሊየን ዕጥፍ አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከኮንትራት ውል ውስጥ በስህተት የገባ ሀረግ ወይም ሳይፃፍ የቀረ አንድ አንቀጽ ወደ ፍርድ ቤት የሚያመላልስ ከፍተኛ ጦስ ሊያስከትል ስለሚችል ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኮንትራትን መንደፍ ወይም ማርቀቅ፣ አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ባለመዘንጋት በተወሰነ ደረጃ ረቂቅ ከመዘጋጀቱ በፊት የሥራውን ሂደት በጀቱን እና ኘላኑን በተመለከተ ፕሮጀክቱን እንዲያካሂድ ከተመረጠው ኮንትራከተር ጋር መወያየት ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ አንድ አስገንቢ የኮንትራት ውል ሲያረቅ የሚከተሉትን አምሰት ዋና ነጥቦች ማስወገድ እንደሚኖርበት የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

🏗ለህግ አስቸጋሪ የሆኑ ቴክኒካል ዝርዝሮች በረቂቅ ውስጥ በህግ አግባብ ለመፍታት አስቸጋሪ የሆኑ፣ በመደበኛ የህግ አንቀጽ ውስጥ ያልተካተቱ ቴክኒካል ዝርዝሮችን በውሉ ላይ ማካተት በቀጣይ
ችግር ቢከሰት እንኳ ለመፍታት በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆኑ ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምከንያቱም አንዳንድ ቴክኒካል አሠራሮች እና ቃላቶች ለህግ ባለሞያዎች አስቸጋሪ በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ በኮንትራክተሮች በቀላሉ የሚታወቁ እና የዘርፉ ባለሙያዎች በህግ ፊት ቀርበው ሊመሰክሯቸው የሚችሏቸውን ቴክኒካዊ ቃላት በውሉ ማካተት አይገባም፡፡

🏗ረጃጅም አረፍተ ነገሮች ዋናውን ነጥብ በቀጥታ ከመጥቀስ ባለፈ፣ ዝርዝር ሀተታ ማስቀመጥ ረጃጅም
አረፍተ ነገር መፃፍ አላስፈላጊ አይደለም::

🏗ተደጋጋሚ ቃላትና አረፍተ ነገር መጠቀም ቀደም ብሎ የሠፈሩ ቃላት እና አረፈተ ነገሮችን ልዩ አንቀጽ እየደጋገሙ ማስፈር አያስፈልግም፡፡
አስፈላጊ ከሆነ የሠፈረበትን አንቀጽ መጥቀስ ብቻ በቂ ነው፡፡

🏗የዲዛይን ለውጥን በቃል መፈጸም

ማንኛውም የዲዛይን ወይም የአሠራር ለውጥ ሲደረግ በቃል ሥምምነት ብቻ እንዲፈጸም ማድረግ ችግር ቢፈጠር በህግ አግባብ ለመፍታት እንዳይቻል የሚያደርግ እንቅፋት ስለሚፈጥር ማንኛውንም የዲዛይን እና የለውጥ
ስምምነቶች በጽሑፍ መሥፈርት እና የእያንዳንዱ አባል ፊርማ፣ አሻራ ባረፈበት የህግ አግባብ መፈጸም ይገባል፡፡
🏗ሊለወጥ የማይችል ቋሚ ውል አለመፈራም በሥራ ሂደት በጊዜ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ቀደም ብሎ መረዳት አስቸጋሪ በሚሆንባቸው የሥራ ዘርፎች አንዱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው፡፡
ስለዚህ የኮንትራት ውል ሲረቀቅ እና ሲፈረም ውሉ እንደአስፈላጊነቱ የሚለወጥበት እና የሚታደስበትን የህግ አንቀፅ በውሉ ላይ ማስፈር ተገቢ ነው፡:

@ethioengineers1
👍18👌3😍1
ለ14ኛው ዙር የ20/80 እና ለ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞች በሙሉ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከጥር 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ የ14ኛ ዙር 20/80 እና የ3ኛ ዙር 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለ ዕድለኞችን እያዋዋለ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑም የመጨረሻ የውል ቀን ግንቦት 07/2015 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጣ ባለዕድለኛ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን እስከ አሁን ያልተዋዋላችሁ ባለዕድለኞች ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት እስከ ግንቦት 07/2015 ዓ.ም ድረስ በአካል ቀርባችሁ እንድትዋዋሉ እናሳስባለን፡፡

https://t.me/ethioengineers1
👏7❤1
🚧ይህ የከተማችን ውዱ መንገድ ነው። በወሎ ሰፈርና በሩዋንዳ መካከል ይገኛል። በአካባቢው ከሚካሄድ ግንባታ ጋር በተያያዘ መንገዱ በዚህ መልክ ጨቅይቶ ተበላሽቷል። እነዚህ ዝርክርክ ነገሮች የመንገድን ዕድሜ በማሳጠር ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው።

ቻይናዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያህል ግዙፍ ሕንፃ ሲገነቡ አካባቢውን በቆሻሻ እና አፈር ሲያውኩና ሲያወድሙ አልታዩም። የቻይና ተቋራጮች ፕሮጀክቶች አካባቢን ሳይበክሉና ሳያራቁቱ ግንባታን ማካሄድ እንደሚቻል ጉልህ ምስክሮች ናቸው።

ወደ እኛ አገር ስንመለስ ፕሮጀክቶች ሲካሄዱ መንገድን በሰፊው ካላዘጉ፣ የሰውን ጆሮ ካላደነቆሩ፣ የውኃና የኤሌክትሪክ መሥመር ቆራርጠው ካልጣሉ የሚካሄድ የማይመስላቸው ተቋራጮች ብዙ ናቸው።

አካባቢን ሳይበክሉ ግንባታን የሚያካሂዱ ተቋራጮች መመስገንና ዕውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባው ሁሉ፣ አካባቢን የሚበክሉ በአርማታና በአፈር መንገድን ከጥቅም ውጪ የሚያደርጉ ሊቀጡና ሃይ ሊባሉ ይገባል።


Via:- social media

https://t.me/ethioengineers1
👍23🤔7❤3
🏗Purpose of chicken mesh

👉To prevent crack in plastering work we use chicken mesh at junction of different material such as between wall and column  junction where coefficient of thermal expansion of different material is different and due to that chances of crack after plastering is bound to occur that’s why we use chicken mesh

https://t.me/ethioengineers1
👍15
#ማስታወቂያ

ለሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤቶች
via:- AddisCityCon
https://t.me/ethioengineers1
👍3🙏1
#ማስታወቂያ

ከላይ በደብዳቤው ላይ ለተጠቀሳችሁ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት

via:- AddisCityCon
https://t.me/ethioengineers1
👍8
👍7❤1