ለመጀመሪያ ጊዜ 26 የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን አውደርእይ ሊካሄድ ነው
ይሄ የተባለው በዛሬው እለት የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን አውደርእይ በተመለክተ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ።በመገለጫቸው የኮንስትራክሽን ዘርፉ 19 በመቶ ያህል በኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቅሰው ሆኖም የተለያዩ የግብአት ችግሮች በተለይ የሲሚንቶ እጥረት ለዘርፉ ማነቆ መሆኑን መግለፃቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል የተባለለት ቢግ 5 ኮንስትራክሽን ሲምፖዚየም እና የንግድ ትርኢትን መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል። ይህም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ DG ኢቨንትስ እና ከሀገር አቀፉ አጋር ኢትኤል ኢቨንት እንዲሁም የሲምፖሲየሙ ስትራቴጂክ አጋር ከሆነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 በሚሊኒዬም አዳራሽ በጋራ እንደሚያካሂዱት አንስተዋል።
ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ሲምፖዚየም 26 የአለም ሃገራት ብሎም 116 አለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን 6000 ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የግንባታው ዘርፍ ማነቆ የሆነውን ከአቅም ውስንነት ጋር የሚያያዙ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው ክፍተት የሚፈታበት ይሆናል ሲሉ አክለዋል።
ይህ ኮንስትራክሽን ዘርፉ ማነቆ የሆነበትን የግብአት እጥረት በተለይ የሲሚኒቶ እጥረት ዙሪያ
አለም የደረሰበትን የአመራረት ሂደት በዘርፉ ከተሰማሩት ልምድ እንዲወስዱ እድል ይሰጣል።
በመርሃ ግብሩ አምራች ተመራማሪዎች ፣ገዢና አቅራቢዎች ፣ከቱሪዝም ብሎም ከተማን ከማነቃቃት አኳያ እንዲሁም የኢትዮጲያን የገጽታ ግንባታ የምናሳይበት ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።

👍5🔥4
ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛዎች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
(ኢ ፕ ድ)
ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳዊት መሐሪ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ ተቋራጮች ጋር በጋራ እንዲሠሩ የሚያስገድደው ረቂቅ ሕግ ዝግጅት ተደርጎበታል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=99460
https://t.me/ethioengineers1

👍15❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏗There are several reasons why buildings can collapse,but one of the most significant causes of building collapses is column buckling.
👉Column buckling is a phenomenon where a structural column fails due to an applied load exceeding its load-bearing capacity.
It occurs when a column, typically made of steel or concrete, is too long and slender in relation to its cross-sectional area. When the column is subjected to compressive forces, it starts to deform, and the cross-sectional area of the column begins to bend out of shape.
As the deformation continues, the column loses its stability and collapses.

👍25
🚧የአፍሪካ ጥንታዊና ዘመናዊ ድንቅ ሥነ ሕንጻ ጥበብ ውጤቶች
የግብፅ ፒራሚዶች በመላው ዓለም በስፋት የሚታወቁ ቢሆንም በርካታ በጥበብ የተሞሉ ብዙ ያልተባለላቸው የአፍሪካ ሥነ ሕንጻዎች አሉ።
https://t.me/ethioengineers1
የግብፅ ፒራሚዶች በመላው ዓለም በስፋት የሚታወቁ ቢሆንም በርካታ በጥበብ የተሞሉ ብዙ ያልተባለላቸው የአፍሪካ ሥነ ሕንጻዎች አሉ።
የሥነ-ሕንጻ ጥበብ ባለሙያዎቹ አዲል ዳላባይ እና ሊቪንግስተን ሙካስ ድንቅ የአፍሪካ ሥነ ሕንጻ ውጤቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ተነስተዋል።
ሁለቱ የሥነ ሕንጻ ባለሙያዎች በቅርቡ ከሰሃራ በታች ስለሚገኙ ሥነ ሕንጻዎች የሚያወሳ መጽሐፍ ያሳተመ ቡድን አባላት ናቸው።
በዚህ መጽሐፍ ላይ ከጥንታዊ ሕንጻዎች እስከ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ ሕንጻዎችን ተቃኝተውበታል።
ከዚህ በታች ስምነቱን ታሪካዊ እና ተምሳሌታዊ ሕንጻዎች እናቀርባለን
https://t.me/ethioengineers1
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍8
ይህ ቤተ-መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ ፋሲል ግቢ ውስጥ ይገኛል።
በዚህ ስፍራ ወደ 20 የሚጠጉ ሕንጻዎች ይገኛሉ። እነዚህ ሕንጻዎች እንደ የንጉሣውያን መኖሪያ እና ማረፊያ፣ ቤተ-ክርስቲያናት፣ ገዳማት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎችን አካተዋል።
የዚህ ሕንጻ ቅርጽ ጽንሰ ሃሳብ ወደ አካባቢው ከመጡ ሚሲኦኖች ተጽእኖ የመጣ እንደሆነ ይታመናል።
https://t.me/ethioengineers1
በዚህ ስፍራ ወደ 20 የሚጠጉ ሕንጻዎች ይገኛሉ። እነዚህ ሕንጻዎች እንደ የንጉሣውያን መኖሪያ እና ማረፊያ፣ ቤተ-ክርስቲያናት፣ ገዳማት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ግንባታዎችን አካተዋል።
የዚህ ሕንጻ ቅርጽ ጽንሰ ሃሳብ ወደ አካባቢው ከመጡ ሚሲኦኖች ተጽእኖ የመጣ እንደሆነ ይታመናል።
https://t.me/ethioengineers1
❤14
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
As engineer, we have heard the terms "one way slab" and "two way slab". The major difference between them is the placement of steel and encountered bending forces.
In one way slab, main reinforcement is provided on one side only because bending moment occurs on one direction only i.e., shorter direction, whereas in two way slab main reinforcement is provided in both sides because moment is generated on both sides.
Apart from that, if Longer to shorter side value is greater than 2, it will be one way slab. If value is less than 2 it will be two way slab.
In two way slab, main bars are cranked which are also called as cranked bars. These bars are cranked at an angle of 45 degrees. And these are placed alternatively in the slab. Moreover, to counter the shear forces at corners or supports, extra bars are provided.

👍24❤3
🚧ዘመናዊ ገጽታ ያለው ይህ ሕንጻ የሚገኘው በመሃል አዲስ አበባ ልደታ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነው።
ሕንጻው ክፍተት እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራው ተፈጥሯዊ ብርሃን በቀላሉ ዘልቆ እንዲገባ እና አየር እንዲዘዋወር ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ነጸብራቃው ነጩ ሕንጻ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨርቅ ያመላክታል።
https://t.me/ethioengineers1
ሕንጻው ክፍተት እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራው ተፈጥሯዊ ብርሃን በቀላሉ ዘልቆ እንዲገባ እና አየር እንዲዘዋወር ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ነጸብራቃው ነጩ ሕንጻ የኢትዮጵያ ባህላዊ ጨርቅ ያመላክታል።
https://t.me/ethioengineers1
👍11
በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ የሚገኘው እና በርካታ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ካሱቢ የቡጋንዳ ሥርወ መንግሥት ነገሥታት መቀበሪያ ቦታ ነበር።
ሕንጻው የተገነባው አብዛኛው ከእንጨት ሲሆን የሕንጻው የውስጥ ክፍልን ልዩ ስፍራ ከሚሰጠው ደን ጋር ለማመሳሰል እና 52ቱን የቡጋንዳ ጎሳዎች ለመወከል በክብ ቀርጽ በ52 ምሶሶዎች ቆሟል።
ትውልዱ በኡጋንዳ የሆነው ሙካሳ ይህን የመቃብር ስፍራ የጎበኘው ገና የ10 ዓመት ልጅ ሳለ ነበር። "ዘመናዊ የግንባታ መሳሪያዎች በሌሉበት ባህላዊ የግንባታ ዘዴዎችን በመጠቀም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነበር የተገነባው አስደናቂ ነው"

👍10
🏗
በውስጡ ማሕበራዊ አገልግሎቶች ሊከወኑ የሚችሉበት ቦታ እና ቤተ-መጽሐፍት አለው።
የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ዳላባይ ይህን ሕንጻ አስደናቂ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ ሕንጻው ጥንታዊ እና ዘመናዊ እንከን የለሽ ጥምረት ነው።
"ይህን ዘመናዊ ሕንጻ በኒጀራያውያን ባህል ውስጥ ስር የሰደደ ስለመሆኑ ግልጽ ነው" ይላሉ ጀርመናዊው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ።
https://t.me/ethioengineers1
ይህን ሕንጻ የቀድሞ የሃውሳ መስጅድ ወደነበረበት ለመመለስ የተገነባ ሕንጻ ነው። በውስጡ ማሕበራዊ አገልግሎቶች ሊከወኑ የሚችሉበት ቦታ እና ቤተ-መጽሐፍት አለው።
የሥነ ሕንጻ ባለሙያው ዳላባይ ይህን ሕንጻ አስደናቂ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ ሕንጻው ጥንታዊ እና ዘመናዊ እንከን የለሽ ጥምረት ነው።
"ይህን ዘመናዊ ሕንጻ በኒጀራያውያን ባህል ውስጥ ስር የሰደደ ስለመሆኑ ግልጽ ነው" ይላሉ ጀርመናዊው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ።
https://t.me/ethioengineers1
👍3👏3
🚧
ይህ አስደናቂ ሕንጻ የተገነባው በደቡብ አፍሪካው ጂኤፒፒ የሥነ ሕንጻ ባለሙያዎች እና ኤምኤምኤ ስቱዲዮ ነው።
ግንባታው ከመሬት በላይ ከፍ ብሎ የተሰራ እና ከተፈጥሮ ጋር በትክክል የተዋህደ የመቃብር ቦታ ይመስላል።
https://t.me/ethioengineers1
የፎቶው ባለመብት,GAPP ARCHITECTS & URBAN DESIGNERS
የሰው ልጅ መገኛ የዓለም የቅርስ ቦታ ተብሎ የሚታወቀው ማሮፔንግ፤ ጎብኚዎች የሰው ልጅ እድገት ምን እንደሚመስል እንዲማሩ ይረዳል።ይህ አስደናቂ ሕንጻ የተገነባው በደቡብ አፍሪካው ጂኤፒፒ የሥነ ሕንጻ ባለሙያዎች እና ኤምኤምኤ ስቱዲዮ ነው።
ግንባታው ከመሬት በላይ ከፍ ብሎ የተሰራ እና ከተፈጥሮ ጋር በትክክል የተዋህደ የመቃብር ቦታ ይመስላል።
https://t.me/ethioengineers1
👍5👏5
👉
ይህ በተባበሩት መንግሥታት የየትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው ቦታ የጥንታዊ ኩሽ ስርወ መንግሥት መቀመጫ ነበር።
በአከባቢው ቁፋሮዎች ተካሂደው የቤተ-መንግሥት ፍርስራሶች ተገኝቷል።
የዚህ መቃብር ስፍራ ፒራሚዶች የተገነቡት ከአሸዋ እና ከድንጋይ በተሰሩ ብሎኬቶች ነው።
✍ይቀጥላል ..........
የፎቶው ባለመብት,VALERIAN GUILLOT
እነዚህ ጥንታዊ ግንባታዎች የሚገኙት ከሱዳን መዲና ካርቱም በ125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በናይል ሸለቆ ውስጥ ነው።ይህ በተባበሩት መንግሥታት የየትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው ቦታ የጥንታዊ ኩሽ ስርወ መንግሥት መቀመጫ ነበር።
በአከባቢው ቁፋሮዎች ተካሂደው የቤተ-መንግሥት ፍርስራሶች ተገኝቷል።
የዚህ መቃብር ስፍራ ፒራሚዶች የተገነቡት ከአሸዋ እና ከድንጋይ በተሰሩ ብሎኬቶች ነው።
✍ይቀጥላል ..........
❤7👍3🙏1
SMH General Construction
ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛዎች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ (ኢ ፕ ድ) ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳዊት መሐሪ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ትላልቅ ተቋራጮች ከአነስተኛ ተቋራጮች…
🚧
እድሉን ለመጠቀም ተዘጋጁ .......ethio construction ይህ ተግባራዊ ከሆነ ቡዙ ነገሮች እንደምቀየሩ ያምናል ‼️❤5👏2
💥ይህ ጥንታዊ ግንባታ በተለያዩ የአካባቢውን ባህል በሚገልጹ ቀለማት ያሸበረቀ ነው።
ቀይ ቀለም ውልደት እና መስዋትነትን፣ ነጭ ቀለም ንጽህናን እና ሰላምን፣ ጥቁር ቀለም የቀደመውን ትውልድ የሚወክል ሲሆን "ጥቁር ዝናባማ ደመና" በዝናብ ይመሰላል።
💦ሙካሳ የባሶቶ ቤቶች ሁልጊዜም ከመሬት አቀማመጡ ጋር በተያያዘ ያስደንቁኛል ይላል። የቀለም አጠቃቀም እና ቅርጻቸው አስደናቂ ነው በማለት ይናገራል።
https://t.me/ethioengineers1
ቀይ ቀለም ውልደት እና መስዋትነትን፣ ነጭ ቀለም ንጽህናን እና ሰላምን፣ ጥቁር ቀለም የቀደመውን ትውልድ የሚወክል ሲሆን "ጥቁር ዝናባማ ደመና" በዝናብ ይመሰላል።
💦ሙካሳ የባሶቶ ቤቶች ሁልጊዜም ከመሬት አቀማመጡ ጋር በተያያዘ ያስደንቁኛል ይላል። የቀለም አጠቃቀም እና ቅርጻቸው አስደናቂ ነው በማለት ይናገራል።
https://t.me/ethioengineers1
👍7
⚡️
ይህ በቤኒን መዲና ፖርት-ኖቮ የሚገኘው መስጅድ የአፍሮ-ብራዚል ሥነ ሕንጻ ማሳያ ጥሩ ምሳሌ ነው። በብራዚል በ17ኛው እና 18ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ከዚህ ሕንጻ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ አብያተክርስቲያናት ተገንብተዋል።
🌟ቢጫ፣ ቡኒ፣ አረንጓዴ እና ሰሚያዊ ደማቅ ቀለማት ከብራዚል ጥንታዊ የሥነ ሕንጻ ግንባታ ጥበብ ጋር ቁርኝት አላቸው።
https://t.me/ethioengineers1
ተፈጸመ 🙏

🌟ቢጫ፣ ቡኒ፣ አረንጓዴ እና ሰሚያዊ ደማቅ ቀለማት ከብራዚል ጥንታዊ የሥነ ሕንጻ ግንባታ ጥበብ ጋር ቁርኝት አላቸው።ይህ በቤኒን መዲና ፖርት-ኖቮ የሚገኘው መስጅድ የአፍሮ-ብራዚል ሥነ ሕንጻ ማሳያ ጥሩ ምሳሌ ነው። በብራዚል በ17ኛው እና 18ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ከዚህ ሕንጻ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ አብያተክርስቲያናት ተገንብተዋል።
🌟ቢጫ፣ ቡኒ፣ አረንጓዴ እና ሰሚያዊ ደማቅ ቀለማት ከብራዚል ጥንታዊ የሥነ ሕንጻ ግንባታ ጥበብ ጋር ቁርኝት አላቸው።
https://t.me/ethioengineers1
ተፈጸመ 🙏
👍6❤5
🪐ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) VS ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
1, ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB)
✨በኮንስትራክሽን ጉዳይ በአብዛኛው በሀገራችን የሚሰራበት የፕሮጀክት አይነት ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ መንገድ እንዲዘጋጅ ካደረገ በኃላ ግንባታውን በተቋራጭ እንዲከናወን የሚያደርግበት ነው።ይሄውም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(Design bid build)(DBB) በመባል ይታወቃል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን አሰሪው በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን/ በሌላ አርክቴክት ድርጅት/ እንዲከናወን ያደርጋል፡፡
በመቀጠልም በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ ወደመምረጥ ሂደት ይገባል፡፡የግንባታው ባለቤት የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነ እንደሆነ ግንባታውን የሚያከናውን ተቋራጭ የመምረጡ ስራ የሚከናወነው በግዥ ህግ መሰረት ይሆናል፡፡ይሄ አይነቱ ፕሮጀክት በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡
2, ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB)
🌟በሌላ በኩል ደግሞ ተቋራጩ ዲዛይኑን እና ግንባታውን በራሱ የሚያከናውንበት የፕሮጀክት አይነትም አለ።ይሄውም ዲዛይን ቢዩልድ(Design build)(DB) ይባላል፡፡በዚህ የፕሮጀክት አይነት ተቋራጩ የታቀደውን ግንባታ ዲዛይኑን በራሱ አርክቴክት ወይም በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት ያከናውናል፡፡የአርክቴክት ስራው የሚያስከትለው ሀላፊነት የተቋራጩ ይሆናል፡፡ከዲዛይን ስራው ጋር የተያያዘ ችግር የሚያስከትለው ሀላፊነት አሰሪውን/የግንባታውን ባለቤት አይነካውም፡፡ሆኖም ተቋራጩ ዲዛይኑን ያሰራው በሌላ የአርክቴክት ድርጅት አማካይነት የሆነ እንደሆነ ከአርክቴክቸር ስራው ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ለአሰሪው የሚኖርበት ሀላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አርክቴክቱም ለተቋራጩ በፍትሀብሄር ህጉ ስለእውቀት ስራ ውል በተደነገገው አግባብ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
በዚህ አይነት ፕሮጀክት የግንባታው ባለቤት/አሰሪው ሙሉ በሙሉ የኮንስትራክሽን ስጋቶችን/risks/ ወደ ተቋራጩ ያስተላልፋል፡፡ይህ ማለት አሰሪው ውጤቱን ማለትም ግንባታውን በመጀመሪያ በቀረበለት ዲዛይን አግባብ በጥራት ተከናውኖለት ከመረከብና በውሉ የተቀመጠውን የግንባታ ዋጋ ከመክፈል ባለፈ ማናቸውም አይነት ሀላፊነት አይኖርበትም ማለት ነው፡፡ለአብነት ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጽያ መንገዶች ባለስልጣን(ERA) ዲዛይን ቢዩልድ የመንገድ ፕሮጀክት ሲኖረው ተወዳዳሪ ተቋራጮች የሰርቨየይንግና ዲዛይን ስራዎችን በራሳቸው ከሰሩ በኋላ በዋጋ ይወዳደራሉ፡፡ተቋራጮቹ ዲዛይኑን ሲሰሩ አሮጌ ድልድዮች ካሉ እና ተጠግነው በአዲስ ድልድይ የጥራት ደረጃ መድረስ የሚችሉ ከሆነ ተቋራጮች እንደየፍላጐታቸውና ሙያዊ ምርመራቸው/ምክንያታቸው ተጠጋኝ ድልድይ እና በአዲስ የሚገነባ ድልድይ እያሉ በዝርዝር በዲዛይን አካተው የሚያቀርቡ ሲሆን ምንም ሆነ ምን በውጤት ደረጃ አሰሪው በሚፈልገው የጥራት ደረጃ/ስታንዳርድ መገንባቱ እና ይሄውም በአማካሪው መረጋገጡ ግን የግድ ነው፡፡ምናልባት ተጠግኖ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ይደርሳል የተባለው አሮጌ ድልድይ በጥገና ወቅት ቢፈርስ እንኳ አሰሪውን ክፍያ የመጨመር ሀላፊነት አያስከትልበትም፡፡ስለዚህ ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ለአሰሪዎች ሪስክ ፍሪ/ከስጋት ነጻ የሆነ የፕሮጀክት አይነት ነው፡፡
⚡️ሌላው ሁለቱም የፕሮጀክት አይነቶች ለኮንስትራክሽን ውላቸው የሚጠቀሙት ጀኔራል ኮንዲሽን የተለያየ ነው።FIDIC በዚህ ረገድ የግንባታ ውል ዝግጅትን በማቅለል ለአለማችን ትልቅ ስጦታ ነው። አለበለዚያ አሰሪና ተቋራጭ በየአንዳንዱ ውል ዝግጅት ወቅት በሁሉም የውል ሁኔታወች ላይ መደራደርን ይጠይቃቸው ነበር።ዛሬ ላይ ግን ለውሉ ጥቅም ላይ የሚውለውን ጀኔራል ኮንዲሽን አስመልክቶ FIDIC ቨርሽን መረጣ እና በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በሚካተቱ ነጥቦች ላይ ብቻ መወያየት በቂ ነው።
✨በተጨማሪም በዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት የኮንስትራክሽን ስጋት/ሪስክ ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋራጩ የሚተላለፍ በመሆኑ ልዩ የዋስትና ሽፋን ያስፈልገዋል፡፡ስለዚሁም ተቋራጩ በግንባታው ዋጋ ልክ All risk insurance እንዲገባ እና ለዲዛይን ስህተት፣ለስራው ብልሽትና በተቋራጩ ባለሙያወች የስራ ስህተት ለሚከሰት ጉዳትና ኪሳራ ደግሞ professional indemenity insurance እንዲገባ FIDIC ዲዛይን ቢዩልድ ፕሮጀክት ኮምፖቴብል የሆነው ተርንኪ ጀኔራል ኮንዲሽን ግዴታ ያስቀምጣል።
✨በሀገራችን ዲዛይን ቢዩልድ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ብዙም የተለመደ አይደለም።ሆኖም በመንገድ ግንባታ ውሎች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አልፎ አልፎ ይጠቀምበታል።
⚡️በአጠቃላይ በሀገራችን በኮንሰትራክሽን ዲዛይኒንግ እና የውል አስተዳደር ረገድ ሰፊ የእውቀት ክፍተት ያለ በመሆኑ እና ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ የማይጠናቀቁበት ሁኔታ በሰፊው የሚስተዋል እንደመሆኑ ሙሉ የኮንስትራክሽን ሪስክ/ስጋት ወደ ተቋራጩ በማስተላለፍ መንግስታዊ ግንባታዎችን በዲዛይን ቢዩልድ የፕሮጀክት አይነት እንዲከናወኑ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም እወዳለሁ።
@ethioengineers1

👍41🙏3👏1
✨መያዥያ ገንዘብ (Retention money)
⚡️ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።
⚡️ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።
⚡️ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።
⚡️በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።
⚡️ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በ
አርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

👍25❤1
💥የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
⚡️የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡
⚡️በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡
⚡️በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
⚡️የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡
⚡️በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡
⚡️ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
⚡️በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
https://t.me/ethioengineers1
⚡️የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡
⚡️በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡
⚡️በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
⚡️የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡
⚡️በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡
⚡️ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
⚡️በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
https://t.me/ethioengineers1
Telegram
SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍14❤1
💥 Roller Compacted Concrete (RCC) ከኖርማሉ ኮንክሪት በምን ይለያል??
✨Roller Compacted Concrete (RCC) ከኖርማሉ ኮንክሪት የሚለየው በ Mix ratio ነው፡፡ ይኸውም RCC ላይ የምንጠቀመው የውሀ መጠን በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ኮንክሪቱ Compact የሚደረገው በሩሎ ወይም በ Roller Compactor ነው፡፡ በሀገራችንም ታላቁ የህዳሴ ግድብ (GRD) እና ግልገል ጊቤ 3 በዚህ ነው የተገነቡት፡፡ RCC ከኖርማሉ ኮንክሪት በተሻለ እድሜና ጥንካሬ አለው።
⚡️ Bending moment ቢም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የሚኖረው በምን Axis ላይ ነው?
👉Z axis ላይ
⚡️Maximum እና Minimum Bending Moment ?
✨ Maximum Bending Moment = Shear Force Diagram(SFD) ከፖዘቲቭ ወደ ኔጌቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይ ነው Moment Maximum የሚሆነው
.
Minimum Bending Moment = SFD ከኔጌቲቭ ወደ ፖዘቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይ ይገኛል፡፡
⚡️elastic እና inelastic ማቴሪያሎች ልዩነታቸው ምንድነው? ductility ምንድነው?
✨Elastic material = load remove ሲደረግ ማቴሪያሉ ወደ ቀድሞ ቦታው የሚመለስ ከሆነ
.
Plastic / Inelastic Material = load remove ሲደረግ የተወሰነው የማቴሪያሉ አካል ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ ቀሪው አካሉ ደግሞ አይመለስም
.
Ductility = inelastic deformation ን የመቋቋም ብቃት
.
⚡️ Toughness ምንድነው?
✨Toughness = ክራክን የመቋቋም አቅም
.
⚡️ አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??
.
💥ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው - በ Fatigue ና Creep
.
Fatigue = ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡
.
Creep = አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡

👍38❤3