SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
🔶Training on Advanced Building & Solar Powered Water Supply System Structural Design For proffessional working in Misistry of water & energy, regional water bureau & PLAN International Ethiopia.

📲 +251995016195 / 0116686857

🔸New class will begin on June 19/2023.

@BeGetEngineering
❤6👍5😍2👏1🤔1
💥ስለ ብርሃን የሚያሳልፍ ኮንክሪት ያውቃሉ?

ብርሃንን የሚያሳልፍ ኮንክሪት ( Transparent concrete ) የኮንክሪት አይነት ሆኖ ከምናውቀው ከኮንክሪት የሚለየው በውስጡ ብርሃንን ማሳለፉ ነው።

ይህ የኮንክሪት አይነት ከተለመደው የኮንክሪት አይነት በተለየ የተለየ አግሪጌትን ይጠቀማል (Aggregate ~gravel+add mixtures) ማለትም ብርሃን አሳላፊ የአግሪጌት አይነቶችን ይጠቀማል።

⚡️በዚህ የኮንክሪት አይነት እንደዋና የአግሪጌት ግብአት ምንጠቀመው ፋይበር ኦፕቲክስ ነው (fiber optics) እና Glass fiber ነው

ብርሃን አሳላፊ ኮንክሪት ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቀው በ2001 G.C በኃንጋሪያዊው አርክቴክት Aronlosonzi ነው

⚡️ብርሃን አሳላፊ ኮንክሪት አሰራሩ ከ4-5% (by volume) የፋይበር ኦፕአቲክስን ከደቃቅ ኮንክሪት (ደቃቅ ኮንክሪት በጣም ከደቀቀ የአሸዋና የሲሚንቶ ውህድ ነው) ጋር በማቀላቀል ነው ይህ ኮንክሪት ከተለመደው የኮንክሪት አይነት የወረደ ጥንካሬ አለው።

⚡️የምንጠቀመው የግብአት አይነት

ሲሚንቶ - ኦርድናሪ ፖርትላንድ ሰመንት ተመራጭ ነው

አሸዋ - 1.18mm seive ያነሰ መጠን ያለው በጥራቱም ላቅ ያለ መሆን አለበት

ውሃ- ለመጠጥ አገልግሎት የምንጠቀመው ውሃ ተመራጭ ነው ምክንያቱ turbid የሆነ ውሃ የብርሃን የማስተላለፍ አቅሙን ይቀንስብናል

Optical fiber- ኮንተንቱ ከ4-5% በvolume መሆን አለበት ቅጥነቱ (thickness) ደግሞ እንደየብርሃን የማስተላለፍ ልኩ ከ 2 µm እስከ 2 mm ሊሆን ይችላል::

⚡️የዚህ ኮንክሪት compressive strength በትክክል ከተሰራ እስከ 70Mpa ሊደርስ ይችላል


https://t.me/ethioengineers1
👍29❤2👏2
🌟Different beam name at the different positions

https://t.me/ethioengineers1
👍5❤2👏2
💥This bamboo-inspired supertall skyscraper is coming to Singapore. Designed by SOM (the same design firm which designed Burj khalifa) , the 305-metre structure will become the city's new tallest building

💥በቀርቀሀ 305 ሜትር ከፍታ ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ንድፍ ተነደፈለት ይህን ንድፍ ያዘጋጀው አማካሪ ድርጅት በርጅ ካሊፋን የነደፈው (design ያረገው) አሁን ደግሞ በ አዲስ ሀሳብ ብቅ ብሏል

https://t.me/ethioengineers1
👍10
💥በሰው መሬት ላይ ለተሰራ ቤት ሕጉ ምን ይላል??

አንድ ሰው የራሱ ይዞታ ባልሆነ መሬት ላይ  ወይም በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት ከሰራ ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል ለሚለው የፍትሀ ብሔር ሕጉን ቁጥር 1170 ና 1179 እናያለን።

የአንድ የመሬት ይዞታ ባለቤት በይዞታው ላይ የመጠቀም መብቱ የራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው በዚያ መሬት ላይ ህንፃ ወይም ቤት ሊሰራ አይችልም ልስራ ካለም ባለይዞታውን በማስፈቀድ መስራት አለበት አለበለዚያ ባለይዞታው በመሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም ብሎ  መቃወም ይችላል።

ነገር ግን መሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም እየተባለና ባለይዞታው እየተቃወመ  በእምቢተኝነት በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሰራ ሰው በሰው መሬት ላይ በሰራው ቤቱ አንዳችም መብት የለውም። ባለይ ዞታው በመሬቱ ላይ  እየተቃወመው  ቤት የሰራው ሰው ሁለት አማራጭ የህገ መፍቴዎች አሉት

1. ለቤቱን መስሪያ ያወጣውን ወጪ ሳይመልስለት ቤቱን ለቆ እንዲሄድ ማድረግ ይችላል።

2. ቤቱን የሰራው ሰው በራሡ ወጪ ቤቱን አፍርሶ እንዲሄድ ለመፍቀድ ይችላል፡፡ ባለመሬቱ በይዞታው ላይ ባለመኖሩ ወይም በሌላ ምክንያት በመሬቱ ላይ ቤት የሚሰራውን ሰው በወቅቱ መቃወም ባይችልም ቤቱ መሰራቱን እንዳወቀ ቤቱን ማስለቀቅ ወይም ማስፈረስ ይችላል።

ስለዚህ የራስ ያልሆነ ይዞታ ላይ ቤት መስራት አይቻልም። ይቻላልም ከተባለ ባለመሬቱ ፍቃደኝነቱን መግለፅ አለበት።

በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ቢሰራ እንደማይቃወም በግልፅ ወይም በዝምታ መፍቀድ ይችላል።

በግልፅ ወይም በዝምታ በመፍቀድ (ተቃውሞ ሳያቀርብ) በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ሲሰራ ያልተቃወመ ወይም የተስማማ ባለይዞታ እንደ ፌደራል ሰበር.በመዝገብ.ቁጥር 30101.ቅፅ 6 እና በመዝገብ.ቁጥር.105125.ቅፅ 20 በተወሰነው ውሳኔ መሰረት  ቤቱን የሰራው ሰው ባለቤት ይሆናል የመሬቱ ባለይዞታም በእንዲ አይነት ሁኔታ ቤቱን ለሰራው ሰው የቤቱን ግምት ከፍዬ ላስለቅቅ ማለት አይችልም።

የፍ/ህ/ቁ.1179ን አስመልክቶ ሰበር በቅፅ 25 የመ/ቁ. 189608 የሰጠው ትርጉም
***
በፍ/ህ/ቁ. 1179 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት  የሚኖረዉ በባለይዞታዉ እና ይዞታዉን ይዞ ቤት በሰራ ሰዉ መካከል የታወቀ ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ብቻ በመሆኑ የባድ ቦታ ሽያጭ ዉል መፍረሰን ተከትሎ በቦታዉ ላይ የተሰራ ቤት ህጋዊ ዉጤትን አስመልክቶ ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለዉ በፍ/ህ/ቁ. 1818 ነዉ።

Via ሳሙኤል ግርማ
 
#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍5❤2🔥1
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እና የጅቡቲው ዳዋሌህ ኮንስትራክሽን ያላቸውን የጋራ ትብብር የሚያጠናክር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል ፡፡

የአጋርነት ስምምነቱ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሌሎች የመካከለኛው እና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ  ትብብር መፍጠር የሚያስችል ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ስምምነቱን  በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ  ዮናስ አያሌው(ኢ/ር) ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጅቡቲ በምትገነባው የሞሉድ ፣ደኺል፣ጋላሞ የ35 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጅክትን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል
::

https://t.me/ethioengineers1
👍4🤔4❤1
🔶Advanced Structural Design

ST CHECK LISTS
እነዚህን መመዘኛ መስፈርቶች አሟልተን ነዉ ዲዛይን አሰገብተን የምናስፈቅደው።
ለ 2 ወሩ Special Structural Design Package ስልጠና መጨረሻ ላይ እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።

These are the checklists we will finally discuess for our 2months  special structural package course.

🔹Concrete structure (Ordinary & High rise)
🔹Steel structure

🔸Software : Etabs, Sap, Safe


🔶 Class Starts on June 19/2023
● Registration is active
📲
0911890392 / 0920933016

📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614

https://t.me/BeGetEngineering
❤6👍3
🔶Bridge Design with Midas Civil Software
      
I) General introduction   ( 1 hr)   
II) Major Drainage Structures (Bridges)     
● Superstructure design    
      ● Slab Bridge Design   (10 hrs)
      ● T-Girder Bridge Design   (15 hrs)
      ● Box Girder Bridge Design   (10 hrs)
  ● Substructure Design    
        ● Abutment Design   (5 hrs)
        ● Pier Design   (10 hrs)
III)  Minor Drainage Structures (Culverts)     
       ● Box Culvert Design    (10 hrs)
       ● Slab Culvert Design    (5 hrs)
       ● Retaining Wall Design     
● Bridge and Culverts Drawing Preparation ,and Detailing     (5hrs)
IV) Bill of Quantity Preparation (BOQ)     (5hrs)
       ● Manuals:     
   - AASHTO LRFD BRIDGE DESIGN SPECIFICATIONS    
   - ERA MANUAL 2013    
        ● Softwares     
   - AutoCAD    
   - Microsoft Excel    
   - Midas Civil

🔶 Class Starts on June 19/2023
● Registration is active
📲
0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍14❤5🤔1
በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት ሥልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ ነው።

በኮንስትራክሽን ሥራ ለመሠማራት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ያጠናቀቁ የመጀመሪያውዙር ባለሙያዎች ወደ ጀርመን ሊሠማሩ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሲቭል ኢንጂነሪንግ፣ በኮንስትራክሽን ማናጅሜንት ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸር እና መሰል ሙያዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ነበር ተብሏል።

ሥልጠናው፥ ከዛሬ ሦሥት ዓመት በፊት በቀድሞው ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የጀርመን ኮንስትራክሽን ማኅበራት ፌዴሬሽን በጋራ እንደተጀመረ ነበር።

‘ጎኤቴ’ በመባል በሚታወቀው የጀርመን ባህል እና ቋንቋ ኢንስቲትዩት ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 11ዱ ሥልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የጀርመን ኮንስትራክሽን ፌዴሬሽን የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው የመጨረሻውን ፈተና በማለፍ ለጉዞ ዝግጁ ሲሆኑ 6ቱ ጀርመን ከሚገኙ አሠሪዎቻቸው ጋር የሥራ ውል ተፈራርመዋል።

ሥልጠናቸውን አጠናቀው፣ የመጨረሻው ምዘና አልፈው እና አስፈላጊውን የሥራ ትዕዛዝ ተቀብለው ወደ ጀርመን ሀገር ለመጓዝ ዝግጀታቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም በመሠልጠን ላይ የሚገኙትን ምሩቃንን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

      
https://t.me/ethioengineers1
👍13🤔10🔥1
💥ዋና ዋና የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች

1,የወደብ (የባህር ዳርቻ) ምህንድስና

የወደብ ምህንድስና የወደብ አካባቢን የማልማትና የማስተዳደር
ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ ወደብን ለመጓጓዣ ስራ ከማዋል
በተጨማሪ፣ በወደብ አካባቢ የሚከሰቱ የውሃ መጥለቅለቅ
አደጋዎችን፣ የአፈር መሸርሸርና እና የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን
የመከላከል ስራ የሚያከናውን የምህንድስና ዘርፍ ነው።


2,የግንባታ ምህንድስና

የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣
ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣
እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል
በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን
የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው
መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት
አጠቃቀምን የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው።
የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ
ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ
የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች
አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል
የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን
ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት
በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን
በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ።

3,የመሬት ርዕደት ምህንድስና

የመሬት ርዕደት ምህንድስና መሬት ርዕደት በሚያይልባቸው አካባቢዎች
የሚሰሩ የግንባታ አካላት፤ የመሬት ርዕደትን ተቋቁመው እንዲዘልቁ
ለማድረግ የግንባታ አካላቱን አወቃቀር በተለየ መልኩ ትኩረት
በመስጠት የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ
የምህንድስና ዘርፍ የአወቃቀር ምህንድስና ዘርፍ አካል ነው። የመሬት
ርዕደት ምህንድስና ዋነኛ አላማው በመሬትና በግንባታ አካሉ እንዲሁም
በግንባታ አካላቱ መካካል በመሬት ርዕደት ጊዜ የሚኖረውን
መስተጋብር መረዳትና የግንባታ አካሉ የመሬት ርዕደት ሂደቱን አልፎ
አገልግሎት እንዲሰጥ አወቃቀሩን፣ የግንባታ ቁስ አመራረጡን
እንዲሁም መሰል የግንባታ መፍትሄዎችን በየሀገራቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ
የግንባታ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ መተግበር ነው።


4,የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና

የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ከጤና ጥበቃ ምህንስና ጋር ተጓዳኝ የሆነ
የምህንድስና ዘርፍ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ምህንድስና በአመዛኙ የንጹህ
ውሃ መጠጥ አቅርቦትና የአካባቢ ቆሻሻ ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ሲያተኩር፤
የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ሰፋ ባለ መልኩ የአካባቢ ብክለት
የሚያስከትሉና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጎጂ ኬሚካሎችን እና ቆሻሻዎችን
መቆጣጠርና ማስወገድ ይጨምራል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና፤
የማህበረሰብ ጤና ምህንድስና እና የአካባቢ ጤና ምህንድስና በሚል
አጠራርም ይታወቃል።
የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና በኬሚካል ውህደቶች፣ በባዮሎጂካል
ሂደቶች እንዲሁም በሙቀት ለውጥ አማካኝነት የሚፈጠሩ ቆሻሻዎችን
የማጥራትና የማስወገድ፣ አየርንና ውሃን የማጣራት፣ እንዲሁም በአደጋ
ወይም በቆሻሻ ክምችት የተበከለን የመሬት አካል ወደ ተፈጥሮዋዊ
ይዘቱ የመመለስ ስራዎች የሚያከናወኑበት የምህንድስና ዘርፍ ነው።
በአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ትኩረት ከሚደረግባቸው ዋና ነጥቦች
ውስጥ የመርዝ ወይም የኬሚካል እንቅስቃሴ ወይም ጉዞ (ከመሬት
ላይና ከመሬት በታች)፣ የውሃ ማጣራት፣ የቆሻሻ ፍሳሽ ማጣራት፣
የአየር ብክለት፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና የአደገኛ ቆሻሻዎች አያያዝ
ይገኙበታል። የአካባቢ ጥበቃ መሃንዲሶች ብክለትን የመቀነስ፣
የአረንጓዴ ምህንድስና ዘርፍ ስራዎች (የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ
የግንባታ መንገዶችንና ቁሶችን የኢኮኖሚ አቅምን ባገናዘበ መልኩ
የማጥናት ስራ)፤ እንዲሁም የኢንዱስትሪዎችን የቁሳቁስና የሃይል
አጠቃቀም ፍሰት የማጥናት ስራዎችና (industrial ecology)
የመሳሰሉት ላይ ይሳተፋሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአካቢቢ ጥበቃ
መሃንዲሶች ድርጊቶች (ለምሳሌ የአንድ የግንባታ አካል ትግበራ)
በአካባቢው ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተጽእኖ በመገምገም መረጃ
ያዘጋጃሉ።

5,የምርመራ ምህንድስና

የምርመራ ምህንድስና የግንባታ አካላት የሚፈለግባቸውን ጥቅም
ሳይሰጡ ለአገልግሎት ከታቀደላቸው ጊዜ በፊት በመፍረስ አገልግሎት
መስጠት ሲያቆሙ፣ እንዲሁም የመፍረስ አደጋው በሰው ወይም
በንብረት ላይ አደጋ በሚያደርስበት ጊዜ የግንባታ አካሉን አወቃቀር ፣
የተሰራበትን ቁስ ፣ የግንባታውን ጥናት እንዲሁም መሰል ተዛማጅ
ጉዳዮችን በመመርመር ተጠያቂ የሚሆነውን አካል ለማወቅና የፍርድ
ሂደትን ለማገዝ የሚያገለግል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ከዚህም
በተጨማሪ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ከምርመራ ውጤቶች በመነሳት
የግንባታ ቁሶችን ወይም የግንባታ አካላት ጥራትን እንዲሁም የግንባታ
አካላት አወቃቀርን የማሻሻል ስራዎን ለመስራት የሚያስችል የሲቪል
ምህንድስና ዘርፍ ነው። ልዮ የሆነ የባለቤትነት ፍቃድ (patent)
ያላቸውን የግንባታ ቁሶች ፣ አካላት ፣ ወይም የግንባታ ዘዴዎች የፍቃድ
ባለቤቱን ይሁንታ ሳያገኙ በሚፈጸሙ ግንባታዎች ላይ የባለቤትነት
ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚደረጉ ህጋዊ ሂደቶች ላይ ይህ የምህንድስና
ዘርፍ ቁልፍ ቦታ አለው።

6,መሬት ነክ ምህንድስና (ጂኦቴክኒካል ምህንድስና)

መሬት ነክ ምህንድስና የግንባታ አካላትን የሚሸከሙ አለቶችና አፈሮችን
የምህንድስና ጠባይ የሚያጠና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ
ዘርፍ ከአፈር ሳይንስ፣ ከቁስ ሳይንስ ፣ ከሜካኒክስ እንዲሁም የፍሰት
ሳይንስ (hydraulics) እውቀቶችን በመጠቀም ደህንነታቸው
የተጠበቀና የገንዘብ አቅምን ያገናዘቡ የግንባታ መሰረቶችን፣
የመጠበቂያ ግድግዳዎችን፣ ግድቦችን፣ ዋሻዎችን የመሳሰሉ የግንባታ
አካላትን መንደፍና መገንባት ላይ ትኩረት ያደርጋል ።
የከርሰ ምድር ውሃን በተለያዮ ምክንያቶች ከመበከል የመጠበቅ
እንዲሁም የቆሻሻ ክምችትን በአግባቡ ለመቆለልና ክምችቱ የአፈርና
የከርሰ ምድር ውሃን እንዳይበክል የማድረግ ስራዎችም በዚሁ
የምህንድስና ዘርፍ የሚተገበሩ ናቸው።
የአፈርን የምህንድስና ጸባይ የማወቅ ተግባር ለመሬት ነክ መሃንዲሶች
ፈታኝ ነው። በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች የግንባታ ቁሶች
ጸባይ (ለምሳሌ እንደ ብረት እና ኮንክሪት) በሚገባ የሚታወቅ ሲሆን፤
በግንባታ አካባቢ የሚገኝን የአፈር ጸባይ ማወቅ ግን ከተለዋዋጭነቱና
በናሙና በሚደረጉ ሙከራዎች መፈተሽ የሚቻለው ከጠቅላላውን
የተወሰነውን ብቻ በመሆኑ በጣም አዳጋች ነው።
ከዚህም በተጨማሪ አፈር በጭነት ምክንያት የሚያደርገው የቅርጽ
ለውጥ ከጫናው ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ (nonlinear) ተዛምዶ ስላለው፤
ማለትም አነስተኛ እና ከፍተኛ ለሆኑ ጫናዎች የተለያየ ጥንካሬ
(strength)፤ ጠጣርነት(stiffness)፤ የቅርጽ ለውጥ ስለሚኖረው፤
የአፈርን የምህንድስና ጸባይ በተሟላ ሁኔታ ለማወቅ የዳግታል።
መሬት ነክ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜ ከከርሰ ምድር ባለሙያዎችና
የአፈር ሳይንቲስቶች ጋር በትብብር ይሰራሉ።

7,የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና

ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና በሲቪል ምህንድስና ውስጥ
ከፍተኛ የሆነ ሚና ይይዛል። የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና
የቁሶችየቁሶችን ተፈጥሮዋዊ ባህሪ የሚያጠና የሳይንስ ወይም የምህንድስና
ዘርፍ ነው።


ይቀጥላል....

https://t.me/ethioengineers1
👍25❤4🤔1😍1
ለግንባታ ከሚውሉ ቁሳቁሶች ውስጥ ኮንክሪት፣ የአስፋልት ኮንክሪት፣ እንደ ብረት እና አልሙኒየም ያሉ ጠንካራ ብረታ ብረቶች፣ የፕላስቲ ውጤቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

የቁሶች ጥናት የግንባታ አካላትን ከተለያየ ጥቃት ለመከላከል የሚውሉ ቅባቶችና የመከላከያ ንጣፎችን፣ እንዲሁም አንድን የብረት አይነት ከሌላ የብረት አይነት ጋር
በማደባለቅ ለግንባታ ተስማሚ የሆነ ሌላ አይነት የብረት አይነት ማምረት የመሳሰሉ ስራዎችንም ያጠቃልላል።

የቁሶች ጥናት የትግበራ ፊዚክስና (applied physics) የኬሚስትሪ
እውቀቶችን የያዘ የምህንድስና ዘርፍ ነው።

በቅርቡ እየተስፋፋ የመጣው የናኖ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂን (ናኖ ሳይንስ የአንድን ቁስ የአቶምና የሞሎኪዮል አወቃቀር በመቀየር በተፈጥሮ የማይገኙ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸውን ቁሶች ለመስራት የሚደረግ ጥረት ነው) ደረጃ
ተንተርሶ በአሁኑ ጊዜ የቁሶች ጥናት ከፍተኛ የሆነ የምርምር ድርሻን
ይዞ ይገኛል። የቁሶች ጥናት ምህንድስና በምርምር ምህንድስናና
የግንባታ አካላት ከጥቅም ውጪ የመሆን መንስኤን ለማጥናት
በሚደረጉ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

8,
የአወቃቀር ምህንድስና (ስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ)

የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን፣ የድልድዮችን፣ የማማዎችን፣
ማቋረጫ ድልድዮችን፣ የዋሻዎችን፣ በባህርና ላይ የሚገነቡ
ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን
እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመንገድየመሳሰሉ የግንባታ አካላትን
በተመለከተ የአወቃቀር ንድፍና (structural design) የአወቃቀር
ትንታኔ (structural analysis) ላይ  የሲቪል ምህንድስና
ዘርፍ ነው።
የአወቃቀር ትንታኔ (structural analysis) ጉልበቶች በግንባታ
አካላት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ የሚያተኩርመመዘን ላይ ትኩረት ያደርጋል።
የአወቃቀር ምህንድስና በግንባታ አካላት ላይ የሚያርፉ ጉልበቶችን
ለምሳሌ የራሱ የግንባታ አካሉ ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ የሚያርፉ
ሌሎች ቋሚና ተቀሳቃሽ ክብደቶች፣ የንፋስ ግፊት ፣ የሙቀት ለውጥ፣
የውሃ ግፊት፣ የመሬት ጫና፣ የመሬት ፣ በረዶ እና የመሳሰሉትን
የመለየትና፣ በእነኝህ ጉልበቶች አማካኝነት በግንባታ አካላቱ ውስጥ
የሚከሰቱ ውስጣዊ ጫናዎችንና ርእደትጉልበቶችን (internal stresses
and forces) የማስላትና የግንባታ አካላቱ እነኝህን ጉልበቶች
ተቋቁመው አገልግሎት እንዲሰጡ መጠናቸውንና የሚሰሩበትን ቁስ
ላይ ያተኩራል። የአወቃቀር ምህንድስና ባለሙያው የግንባታ
አካላቱ ተጠቃሚዎችን ደህንነትን መንደፍበሚጠብቅ መልኩ (llimit state of
carrying capacity) እንዲሁም ግንባታ አካላቱ ከተሰሩበት አላማ
አንጻር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጎ (limit state
of serviceablity) መንደፍ ይጠበቅበታል።
እንደ ንፋስ እና የመሬት ርእደት አይነት ጉልበቶች በቀላሉ ለመተንበይ
አስቸጋሪ በመሆናቸው በአወቃቀር ምህንድስና ስር እንደ ንፋስ
ምህንድስና እና የመሬት ርእደት ምህንድስናን የመሳሰሉ ንኡስ ዘርፎች
እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኖዋል።
በአወቃቀር ምህንድስና ውስጥ የንድፍና የትንታኔ ስራ የግንባታ አካሉ
ቋሚ ጉልበቶችን ፣ተለዋዋጭ ጉልበቶችን (እንደ ንፋስና የመሬት ርእደት
ያሉ) ወይም ጊዜያዊ ጉልበቶችን (ለምሳሌ በግንባታ ጊዜ ጥቅም ላይ
የግንባታ ማሽኖች ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ በተንቀሳቃሽ
ነገሮች አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶች እና የመሳሰሉት)
የሚውሉለመሸከም የሚያስፈልገውን ጥንካሬና ጠጣርነት መወሰን እንዲሁም
የግንባታ አካሉ ሚዛኑን ጠብቆ መቆም መቻሉን ማረጋገጥ ያካትታል።
ከዚህም በተጨማሪ የንድፍና ትንታኔ ስራ  ዋጋ መተመን፣
የግንባታውን ተግባራዊነት ማረጋገጥ፣ ግንባታው ውበት የተላበሰ
መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የሃብት የግንባታውንአጠቃቀምና የተፈጥሮ ሚዛንን
በጠበቀ መልኩ ግንባታው እንዲከናውን ማስቻልን ያካትታል።

9,ቅየሳ

ቅየሳ የአንድን የመሬት ገጽ ወይም የግንባታ አካል አቀማጥ ለማወቅ
የሚደረግ የልኬት ስራ ነው። የቅየሳ ስራ  ስራ የሚውሉ እንደ
ውሃ ልክ (level) ወይም ቴዎዶላይት (አግድምና ሽቅብ ማእዘንን
ለመለካት የሚችል አጉሊ መነጽር) ያሉ ለቅየሳመሳሪያዎች በመጠቀም
በሁለት የልኬት ቦታዎች መካከል ከልኬት ቦታው አንጻር የሚኖረውን
የቦታ ልዮነት ለማወቅ የማእዘን (angle) ፣ የአግድም ቁመትና
የሽቅብ ቁመት ልኬቶችን በመውሰድና የሂሳብ ስሌትን በመጠቀም
የመሬት ገጽን ወይም የግንባታ አካልን አቀማመጥ የመወሰን ተግባር
ነው። ከኮምፒውተር እውቀት ማደግ ጋር በተያያዘ አውቶማቲክ የሆኑ
እንደ የኤሌክትሪክ ርቀት መለኪያዎች በመፈልሰፋቸው እንደ ቶታል
ስቴሽን ፣ ጂፒኤስ፣ የጨረር ዳሰሳ (laser scanning) የመሳሰሉ
መሳሪያዎች ባህላዊ የሆኑ መሳሪያዎችን በመተካት ላይ ናቸው።
ትራንስፖርት ምህንድስና
የትራንስፖርት ምህንድስና ሰዎችንና ቁሳቁስን ከቦታ ወደ ቦታ በደህንነት
፣ በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ መንገድ ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
ይህንን አላማማ ለማሳካትም የመኪና፣ የባቡር፣ የውሃና የአየር ማረፊያ
መንገዶች እንዲሁም የወደቦች ንድፍ፣ ግንባታና ጥገና ስራዎች
በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ። የትራንስፖርት
ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ (transportaion
design) ፣ የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ (transportation
planning)፣ የትራፊክ ምህንድስና (traffic engineering)፣ የከተማ
ልማት ምህንድስና፣ የመንገድ ንጣፍ ምህንድስና የመሳሰሉ ንኡስ
የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍18❤2
🏗 የከተማ ባለብዙ ወለል ህንጻዎች

⚡️የከተማ ባለብዙ ወለል ህንጻዎች፣ አቀማመጣቸውና የውጭ ቅርጻቸው ከብርሀን እና ከንፋስ አንጻር እንዴት መሆን እንዳለበት አሳብ የሚሰጡ ምስሎች ተያይዘዋል፡፡

Via 07sketches


https://t.me/ethioengineers1
👍7❤2
⚡️ግድብ (Dam) ማለት ገዝፈ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።

ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀሊል ያደርገዋል ። ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
ግድም በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር - for flood control
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ - for water supply and irrigation
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት - for electric power generation
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - for regulation or balancing of a river flow

#Hydraulics
👍17❤2
💥ጥቁር ምንጣፍ ወይስ አስፋልት ያስባለው አነጋጋሪው የህንድ አስፋልት

⚡️በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ጃልና የተሰኘው ወረዳ ነዋሪዎች ለአመታት የመንገድ ይገንባልን ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ አግኝቷል።  ነገር ግን ደስታቸውን የቅጽበት ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ክስተት ገጥሟቸዋል ይላል የአልዐይን ዘገባ።

⚡️የጠጠር መንገዳቸው የለበሰው አስፋልት በቀላሉ እንደምንጣፍ ሊነሳ የሚችል በሌላ ቋንቋም ጥቁር ምንጣፍ ሆኖ አግኝተውታል።

⚡️በእጃቸው ሲያነሱትም ከስሩ ጨርቅ ነገር ለብሶ ከላዩ ላይ በስሱ አሽዋና ሬንጂ ተደርጎበት የተሰራ መሆኑንም ያረጋግጣሉ። መንገዱን የሰራውን ተቋራጭ ሲጠይቁት አዲስ የጀርመን ቴክኖሎጂ ተጠቅሜያለሁ ሲል ተሳልቋል።


https://t.me/ethioengineers1
👍11🔥11🤔5❤1🙏1👌1
የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply  reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ  ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።

#Hydraulics
👍18❤1👏1
💥Advance Security vs
Performance Security.

1. Advance security

⚡️ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው የቅድም ክፍያ ገንዘብ በሚከፈለው የገንዘብ መጠን ልክ የሚያሲዘው የባንክ ዋስትና ቦንድ ነው። እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርበታል።
ስራ ተቋራጩ የወሰደውን ቅድመ ክፍያ ከፍሎ እስኪጨርስ ያስያዘው ዋስትና ግዜው ማለቅ(Expire) አይችልም። ከአንድ ወር ቀደም ብሎ የዋስትና ቀነ ገደቡ ከማለፉ በፊት ከአማካሪ በሚፃፍለት ደብዳቤ መሰረት ሊታደስ ይገባል። ነገር ግን ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቀነ ገደቡ አልፎ ሳያሳድስ ቢቀር ቀሪ ያልተከፈለ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ከሚቀጥለው ክፍያ ቅፅ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ከፍሎ እንደጨረሰ ተመላሽ ይደረግለታል።
የተለየ የቅድመ ክፍያ እና የዋስትና አከፋፈል አካሔድ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/ ይችላል።

2. Performance Security

⚡️ስራ ተቋራጩ ውል ተቀብሎ ተፈፃሚ ማድረግ የሚችልበትን ለብቃት ማረጋገጫ የሚያሲዘው ዋስትና ነው። ውል በተፈራረመ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ (15) ውሉ የሚያዘውን መጠን ዋስትና ያቀርባል ።
ዋስትናው ስራ ተቋራጩ በተገቢው መንገድ ውሉን ተፈፃሚ ሳያደርግ ቢቀር ለውል ሰጪ (ባለቤት) እንደ ካሳ ክፍያ ይሆናል።
እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ውሉ ላይ በተቀመጠው ፎርማት መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል።
ይህ ዋስትና ሳይቀርብ ምንም አይነት ክፍይ ተፈፃሚ ሊደረግ አይገባም። ስራው ተጠናቆ እስኪያልቅ


https://t.me/ethioengineers1
👍21👏1
ምድር ውስጥ ብቻ የተገነባው የዓለማችን ጥልቁ ሆቴል

ምድር ውስጥ ብቻ የተገነባው የዓለማችን ጥልቁ ሆቴል የስዊድኑ ሳላ ሲልቨር የተሰኘው ሆቴል ከመሬት ወደ ውስጥ 154 ሜትር ርቀት ላይ ተገንብቶ ዓለምን ጉድ አስብሎ ነበር፡፡

አሁን ደግሞ በዌልስ ወደ ውስጥ 419 ሜትር ርቀት ላይ የተገነባ ሆቴል ከአንድ ወር በፊት ተመርቋል፡፡

ሆቴሉ በተለይም ቅዳሜ ምሽት ላይ የአዳር መኝታ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ለአንድ አዳርም 688 ዶላር እንደሚያስከፍል አስታውቋል፡፡

ሆቴሉ በብዛት የውጪ ወይም ቴክአዌይ አገለግሎት የሚሰጥ ሲሆን ቅዳሜን በተለየ መንገድ መዝናናት ለሚፈልጉ ደንበኞች ግን ልዩ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

ምንም ነገር በማይሰማበት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የተገነባው ይህ ሆቴል አራት ጥንድ አልጋዎች ያሉት ሲሆን ከመሬት ወደ ሆቴሉ ለመግባት በመሬት ውስጥ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በእግር መጓዝ የግድ ነው ተብሏል፡፡

ሆቴሉ ምድር ውስጥ መገንባቱን ተከትሎ ቅዝቃዜው ለደንበኞች አመቺ ሆኖ መገንባቱ የተገለጸ ሲሆን ትንሽ ለብ ያለ ነገር ብቻ መጠጣት እንደሚፈቀድ ተገልጿል፡፡

የ4ጂ ኢንተርኔት፣ ሙቅ ነገሮች እና ሌሎች የሆቴል አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ መስጠት የጀመረው ይህ ሆቴል በአጭር ጊዜ ውስጥ ደንበኞቹ ደርተውለታል ተብሏል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍14❤3👏1👌1
🌟ማስታወቂያ

📌ለ ነባር እና ለ አዲስ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራት በመሉ

✨የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በቀጣይ በጀት አመትም በያዘው መደበኛ እቅድ  በመንግስት እና በግል አጋርነት የቤት ልማት ፕሮግራሞች አዲስ ለሚያስገነባቸው 120ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተለያዩ ዘርፎች  በግንባታ ፣ በአገልግሎት እና በአምራች ዘርፍ በቀጣይ 5 ወራት ከ4500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አዲስ የስራ እድል ለመፍጠር በዝግጅት ላይ ሲሆን በዘርፉ የተሠማሩ ስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን አሳታፊ አድርጎ ለመስራት አስቧል።

✨በመሆኑም ተቋሙ በቤት ልማት መሳተፍ የሚፈልጉ አዳዳስ እና ነባር ከ2006 ዓ.ም ወዲህ በተቋሙ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው በተቋማችን ሲሰሩ የነበሩትን ባለድርሻ አካላት በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ዙር ለመመልመል እንዲሁም  አሰራሩን ለማዘመን እንዲያስችለው በተደራጀ እና በዘመናዊ በሆነ መልኩ  አዲስ እና ዘመናዊ የዌብ ሳይት ፕላትፎርም አዘጋጅቶ መረጃዎችን በማደራጀትና በማጥራት ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

✨ስለሆነም በቅርቡ በተቋሙ ድረ-ገጽ በሚለቀቀው አዲስ ፕላት ፎርም ለአግልግሎቱ ፈላጊ በሙሉ ምዝገባ ስለሚጀምር  ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ኮርፖሬሽኑ እያሳሰበ

📜ተመዝጋቢዎች ከታች ያሉትን መረጃዎች አደራጅታችሁ እንድትጠብቁ  ያሳውቃል

👉 የታደሰ ንግድ ፍቃድ 
👉 TIN NO
👉 የስም ስያሜ ምዝገባ ሰርተፊኬት
👉 የብቃት ማረጋገጫ
👉 የስራ ልምድ በአንድ በተጠቃለለ ገጽ
👉 የስራ ክብደት በገንዘብ ሲቀየር  የሚያሳዩ መረጃዎች ከ ገፅ 1 - 2
👉 እና ሌሎች ስራ ተቋራጩን እና ማህበራቱን የሚገልጽ ሰነዶችን ናቸው።

📍የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

https://t.me/ethioengineers1
👍20❤1