SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥Core structure (አንኳር የመዋቅር አይነት)

ረዣዥም እና ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ለመስራት በተለመደው እና በመደበኛው ፍሬም ስትራክቸር መስራት economicalም አይደለም adequateም አይደለም። ስለዚህ የ20ኛው ክፍለዘመን የምህንድስና ጠበብቶች Core structureን አስተዋወቁ።

⚡️Core structure ማለት shear wall ( በ አርማታ እና በ ፌሮ የሚሰራ ግንብ ሆኖ የጎንዮሽ ጫናን (lateral load) በበቂ ሁኔታ የሚከላከል ከ ሌሎች ፍሬም መዋቅሮች የተሻለ stability ያለው ነው።

ይህ የመዋቅር እይነት ሾጠጥ (slender) ያለ ነው። ብዙ ጊዜ የቦታውን ይዞታ ኮንክሪት ብቻ ከመከመር መዋቅራዊ ይዘቱም እንዳለ የ አሳንሰር አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል የከተማታችን ብንወስድ የ ህብረት ባንክ ዋና ፅህፈት ቤት ህንፃ (elevator 🛗 station) የ ኮር ስትራክቸር አንዱ ማሳያ ነው። ብዙ ጊዜ core structure at the centroid of the plan of the building እንዲሆን ይመከራል።

https://t.me/ethioengineers1
👍20❤3
ቅድሚያ ለደህንነት‼️

💥ለእለት እንጀራ ሲባል "50 ኪሎ ተሸክሞ በዚህ እንጨት ላይ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሲሮጥ ማየት ልብ ይነካል!! 🥺🥺"

#neba bcaa

https://t.me/ethioengineers1
👍20🤔5👏1🙏1
💥የ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ ሀይቅ ፕሮጀክት አሁናዊ ገፅታ -በፎቶ
https://t.me/ethioengineers1
❤15👍5
💥ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ የውል ተፈጻሚ ስላለመሆን /Privities of Contract/

⚡️የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1952 “በህግ ተለይቶ የተመለከተ ካልሆነ በቀር ውሎች ውጤት ያላቸው በተዋዋሏቸው ወገኖች መካከል ብቻ ነው”

⚡️ውል ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ ተፈጻሚነት እንደሌለው የታመነ ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ፍትሃብሄር ሕግም በአንቀጽ 1952 ላይ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

⚡️በዚህም መሰረት ውሎች ልዩ ሁኔታዎች (exceptions) እንደተጠበቁ ሆነው በሦስተኛ ወገኖች ላይ ተፈጻሚ አይሆኑም ማለት ነው፡፡

🌟ታዲያ! ከዚህ መርሆ ተቃርኖ በሚመስል መልኩ መሀንዲሱ እንዴት በአሰሪው እና በሥራ ተቋራጩ መካከል በተደረገ ውል ላይ ጣልቃ ሊገባ ይችላል ፣ ብሎም የተለያዩ ሚናዎች ሊኖሩት ቻሉ የሚሉ ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም ይስተጋባሉ፡፡

📌መልሱ:-መሀንዲስ የአሰሪው ወኪል መሆኑ በራሱ የተለያዩ በሕግ ፊት ሊጸኑ የሚችሉ ተግባራትን (juridical acts) ሊፈጽም ይችላል እንደ ማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በወጥ ውሎች ላይ እንደተመለከተው የፕሮጀክቱ ተሳታፊ በመሆኑ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ግልጽ ነው፡፡

❤️ለሚወዱት ያጋሩ🙏

https://t.me/ethioengineers1
👍14❤2👏1👌1
💥News

የሲሚንቶና የብረት ዋጋ ቅናሽ አሳየ

በከተማዋ የ1 ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ከ800 ብር እስከ 500 ብር ቅናሽ እንዲሁም 1 ቤርጋ ፌሮ በኪሎ የ15 ብር ቅናሽ ማሳየቱ ሰሞኑን ተመልክተናል

ከዚህ ቀደም ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 800 እስከ 2 ሺህ ሲሸጥ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ኢትዮ ሲሚንቶ ከ1 ሺህ 250 እስከ 1 ሺህ 270፣ ሀበሻ ሲሚንቶ በ1 ሺህ 300 ብር እና ሙገር ሲሚንቶ በ1 ሺህ 350 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ የብረት ገበያም ቅናሽ የታየበት ሲሆን ለአብነትም 10 ቤርጋ ብረት 1 ሺህ 332 ሲሸጥ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ 1 ሺህ 36 ብር፣ 14 ቤርጋ ፌሮ ብረት 3 ሺህ 412 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 2 ሺህ 654 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍35👏2🤔2❤1
💥News
የለቡ ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ 80 በመቶ ደረሰ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በተለምዶ ለቡ መብራት ኃይል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው  የለቡ ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ 80 በመቶ አፈፃፀም ላይ መድረሱ ተገለፀ።

ቀደም ሲል 270 ሜትር ርዝመት ያለው የማሳለጫ ድልድዩ ስትራክቸር ግንባታ ተከናውኖ ለትራፊክ ክፍት መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ የተሸጋጋሪ ድልድዩ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት የመቃረቢያ መንገዱን ጨምሮ አጠቃላይ 1.1 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ የፕሮጄክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ከመፍታቱም ባሻገር ለከተማዋ ገፅታ ተጨማሪ ውበት እንደሚያላብስ ይታመናል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍10
💥News

#ትግራይ

መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ይፋ አደረገ። 

ፋብሪካው በቴሌግራም ገፁ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላክተው ፤ በ PPC አይነት ስሚንቶ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ተመን ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት በአዲሱ የመሸጫ አሰራር ከፋብሪካ ሰሚንቶ ለመግዛት ፣ ለማከፋፈልና ለመቸርቸር ፍቃድ ተሰጥቶዋቸው ውል ያሰሩ አካላት ፣ በችርቻሮ የሚሸጡበት ዋጋ አውጥቷል።

ፋብሪካው ጨምሮ እንደገለፀው በትግራይ ንግድና ኤክስፓርት ኤጀንሲ የስሚንቶ ምርት ተደራሽነቱ ለማስተዳርና ለመቆጣጠር በወጣውና በፀደቀው አዲስ መመሪያ ቁጥር 02/2015 መሰረት ከፋብሪካው ገዝተው በመላ ትግራይ በችርቻሮ የሚሸጡበት  የዋጋ ተመን አውጥቷል።

አዲስ የመሸጫ ዋጋው PPC አይነት ስሚንቶ የሚመለከት ሆኖ የትራንስፓርት : የመጋዘንና አስተዳደራዊ ወጪዎች ግምት ያስገባ የችርቻሮ ዋጋ እንደተቀመጠለት የፋብሪካው የቴሌግራም ገፅ  ላይ ተጠቅሶል

(የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)


https://t.me/ethioengineers1
👍9❤2
BeGet Engineering PLC.

🔸ላለፉት 8 አመታት ዲዛይንና ስልጠና ላይ ያዳበርነውን ልምድ በመጠቀም ለ2016 ዓ.ም ስልጠናዎችንና የዲዛይን ስራዎችን በጥራትና በተደራጀና መልኩ  አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።እያንዳንዳቸው ለ2 ወር የሚቆዩ በፓኬጅ የተዘጋጁ ስልጠናዎች አሉን ።

Advanced Level Training Package 

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
8) Graphic Design


📲 0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍8❤2
💥News
አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው #አቃቂ_ስታዲየም አሁን ላይ የተመልካች ወንበር እየተገጠመለት ይገኛል

https://t.me/ethioengineers1
👍19