SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💥ገደል ላይ የተሰራ ቤት/ Building a house in a cliff

https://t.me/ethioengineers1
👍17❤2
💥ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት አምራች

የናተ ምቾት የኛ ትርፍ ነው ቡዙ
🇪🇹ፕሌት በሚፈልጉት መጠን ሳይዝ
🇪🇹ጄቦልት በፈለጉት ውፍረት እና ቁመት
🇪🇹ታዮር ዎድ የምን መከራየት በተረፈ ፌሮ ቢያስ ለሁለት ዙር አገልግሎት እንዲሰጥ አዘጋጅተን እናዘጋጃለን
🇪🇹ማንኛው ያጡት እቃ ሞደፊክ

🇪🇹ምን አለፋቹ በረት ነክ ይጠይቁን ለሁሉም መልስ አለ

🇪🇹🛠🔩🔩🔩ፀግሽ መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ 0912492727
0913061530
0923764834
👍7👏2
💥የኖህ ሪል ኢስቴት 10ኛ አመት መርሃ ግብር

https://t.me/ethioengineers1
❤4👍1
SMH General Construction
Photo
💥ኖህ ሪል እስቴት ያስገነባቸውን አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች አስረከበ

♦"የአስተዳደሩ ድጋፍ ይቀጥላል" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኖህ ሪል እስቴት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ያስገነባቸውን 754 የመኖሪያ ቤቶች ምርቃት ስነ-ስርአትና 10ኛ ዓመቱን የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት አክብሯል።

ኖህ ሪል እስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት 8 ሺ በላይ ለሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ቤቶችን በታማኝነት፣ በሰዓቱ እና በቃሉ መሰረት ያስረከበ ሲሆን ይህ ጉዞ ኩባንያውን በኢትዮጵያ የቤቶች ልማት ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ሆኖ እንዲቀጥል እንዳስቻለው ተገልጿል። ለአገራዊ የልማት ግቦች ስኬትም ትልቅ አስተዋዕዖ እያደረገ እንደሚገኝም ተነግሯል።

የኖህ ሪል ኢስቴት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ንፁህ አውግቸዉ “በዛሬው ዕለት በኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት አዲስ የተገነባውን የመኖሪያ መንደር በይፋ ሲያስመርቅ ባለፉት አስርት ዓመታት የስኬት ጉዞአችን የምናከብርበት፣ እንዲሁም ወደፊት በአብሮነት ለተሻለ ሥራ ቃልኪዳናችንን የምናድስበት ነው” ብለዋል።

“ኖህ ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በጊዜው እና በጥራት ገንብቶ በማጠናቀቅ በደንበኞቹ ዘንድ አመኔታን ያተረፈ ተቋም ነው ሲሉም አክለዋል።

ኩባንያው በ2020 ዓ.ም ፣ 30 ሺ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ትልቅ ራዕይ የሰነቀ ሲሆን ፣ የመኖሪያ ቦታዎችን ወደ ሚሊዮኖች ካሬ ሜትር ለማስፋፋት ማቀዱም ተነግሯል።

በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለማልማት ከታቀደው 3 ሚልየን ካሬ ሜትር በላይ የሚሆነው ለመኖሪያ ቤት መገንቢያ ሲሆን 1 ሚልየን ካሬ ሜትር ያህል ደግሞ የንግድ ማእከላት ለመገንባት ይውላል ተብሏል ።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ እየተካሄዱ ያሉ ፕሮጀከቶች የኖህ ሪል ስቴት ለላቀ ትጋት ቀጣይነት ማሳያ እንደሆኑ ተነግሯል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ እንደተገለፀው የኖህ ታላቅ ስኬት ዋነኛ ማሳያው 31 ፕሮጀክቶች በጥራት እና በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉ ነው። አሁን ላይ በርካታ በመካሄድ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉት ኩባንያው ከፕሮጀክቶች መካከል በጉርድ ሾላ፣ በሰሚት፣ በቦሌ ፣ በፍላሚንጎ፣ በቀበና እና በእንቁላል ፋብሪካ ያሉ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ይገኛሉ።

በመርሐግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስአበባ ከተማ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪዎች አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው የመኖሪያ ቤት አቅርቦት በመንግስት ብቻ የሚመለስ ሳይሆን ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር መስራትን እና የግሉን ዘርፍ ማበረታታትን ይጠይቃል ብለዋል።

አያይዘውም ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት የተገነቡ 5 ሺ ቤቶችን ጨምሮ እስከአሁን ከ8 ሺ 600 በላይ ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች ያስተላለፈ ሲሆን፣ ግንባታቸው በመጠናቅቅ ላይ ያሉ ቤቶች በጥራት መገንባታቸውን እና የበርካታ ነዋሪዎችን የቤት ችግር የሚቀርፉ መሆናቸውን በጉብኝታችን ወቅት መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።

በመኖሪያ ቤት ላይ ለተሰማሩ ኩባንያዎች የከተማ አስተዳደራችን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።


🏗እውነትም ያልገነባችሁትን አትሸጡም ምስጋና እና አድናቆት ይገባችኋል 🙏

https://t.me/ethioengineers1
👍14❤1
🏗ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቧንቧ እና መገጣጠሚያ ማምረቻ ፋብሪካ በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በ14.5 በሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተገንብቶ ስራ ጀመረ ‼️

✨ይህ ፋብሪካ ከኢዜድ ትሬዲንግ ኤንድ ኢንቨስትመንት የንግድ ኩባንያ ከRHFO(Rifeng Enterprise Foshan) ኃ.የተ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር የተቋቋመ የአቅርቦት አጥረትን ለመፍታትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ያለመ ነው።

✨ይህ የማምረቻ ፋብሪካ እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው
👉ፒፒአር
👉ኤችዲ ፒኢፒቪሲ ቧንቧዎች
እና ቱቦዎች አስፈላጊ የመገጣጠሚያ ዕቃዎች መለዋወጫዎች ጋር ለማምረት ስለሚያስችል በዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት ለማስመዝገብ ያስችላል።

✨ፋብሪካው እስከ 2000000 ሜትሪክ ቶን ፒፒአር ትቦዎች፣ 1900000 የፒፒአር የመገጣጠሚያዎች 1000000 ሚ.ቶ ቶን የፒቪሲ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች እና 900,000 የፒቪሲ መገጣጠሚያዎች እንዲሁም ከ3,500,000 ሜትር በላይ የፒቪሲ ኮንዲዩት ማስተላለፊያ ትቦዎችን የማምረት ዓመታዊ ዐቅም ያለው ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን የቧንቧ እና የትቦ ዝርጋታ ሥርዓት  አቅርቦትና ጥራት እጥረትን ለመፍታት የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ከውጭ ይመጣ የነበረውን በማስቀረት የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ያስችላል
ኢዜድ ኤም ንግድና ኢንቨስትመንት ከRIFO ጋር በመሆን በአሁኑ ወቅት ከ2000 ለሚበልጡ ሰራተኛች ቋሚ የስራ ዕድል የፈጠራ ሲሆን ለ400 የኢትዮጵያውያንም ኢ-መደበኛ የስራ እድል አመቻችቷል።

✨የኢዜድኤም ጥናት በግንባታው ዘርፍ ያሉ ደንበኞች የአዲስ ፋብሪካ ምርቶች ወደ ገበያ ሲቀላቀሉ በሚኖረው ከ20 እስከ 30 በመቶ በሚደርስ የገበያ ዋጋ ቅናሽ ጥራትን ከዘመናዊነት ያጣመረ እንደሚሆን ይተነበያል።

✨በአዳማ የኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የሚገኘው እና 3000 ሜትርካሬ ስፋት ላይ የተቀመጠው አዲሱ ፋብሪካ የኢትዮጵያዊ ኩባንያ ከአለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ሽርክና በመመስረት የከፈተውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲሁም በአይፒቪሲ ሰርተፍኬት ያለው ዘመናዊ የቧንቧ ኢንዱስትሪ በመሆኑ የመጀመሪያ ፋብሪካ ነው።
✨ኩባንያው የሀገር ውስጥና የአለም አቅፍ ጥራት እና የአካባቢ መስፈርቶችን ለማሟላት ቁርጠኛ ሲሆን እስካሁን ከ50 የዓለም አቀፍ የጥራት ሰርተፍኬቶችና ዕውቅና አግኝቷል
::

https://t.me/ethioengineers1
👍16❤1
በጣም በጥራት የተመረተ በፍጥነት ያሉበት ቦታ ድረስ በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን

በ 0912492727
0913061530 ይደውሉ
((መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ ))

ፀግሽ
👍7
💥የ ድምር ባዶ ከተማ ንድፍ አይነቶች።
(Net Zero urban development types)


⚡️ድምር ባዶ እድገት ማለት በእለት ተለት ኑሮአችን ወደ አካባቢው የምንለቀውን ያህል ካርቦን ከአካባቢ በማስወገድ የምንተገብረው አይነት እድገት ነው።

✨ሶስቱ የድምር ባዶ የከተማ አይነቶች።
1. ዘላቂ ከተሞች
2. ችግር ተቋቋሚ ከተሞች እና
3. ጠቢብ ከተሞች ናቸው።

ምስል ምንጭ። አንቶኒዮ አብዶ


https://t.me/ethioengineers1
👍8❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💥ሁሉንም እናውቃለን ካለኛ አዋቂ የለም የምትሉ ሰዎች (ጋዜጠኞች ) ግን ትንሽ እንኳን ባለሞያ ጠየቁ program ለህዝብ ከማቅረባቸው በፍት ‼️

አስፈላጊነቱን ማወቅ ከፈለግክ ጠይቅ 🤔

https://t.me/ethioengineers1
👏14👍10🤔4❤1
🌟ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ /Soil Compaction/ በጥቂቱ

☄Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።

✨እንዴት?

✨አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ/density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው።

💥ይህም በመሆኑ:

*የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን።

*በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን።

*ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/

⚡️የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/

⚡️የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው።

⚡️በሰው ሰራሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ
/Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል።

🤞ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው።

✨የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/

⚡️በዋናነት በሁለት ይመደባሉ።

-በሳይት ላይ የሚተገበሩ
/Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው።

-በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test... 

ለዛሬ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን።

⚡️Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/

ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው።

* *የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/

የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር

መቆፈሪያ፣ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/

ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/:

ንፁህ አሸዋ

ወንፊት

ሚዛን/Balance/

ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ

* *የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/

1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ።

2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት።

3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።

ማስታወሻ:- የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን።ምስል 5 ን ይመልከቱ

4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ።

5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

6ኛ. የተሰበሰበው ዳታ በመጠቀም. የሳይት ላይ እፍግታውን/Bulk density/ ማወቅ እንችላለን። በቀጣይ ጽሁፍ የሚወጣውን ምሳሌ መመልከት ይቻለል።

7ኛ. ከፍተኛው የደረቅ እፍግታ ልኩን/MDD/ በቤተ ሙከራ ለመስራት ከሰሃኑ ላይ ለናሙና 1/3ኛ ያህሉን በንፁህና ደረቅ ላስቲክ በማድረግ ማዘጋጀት።

ማስታወሻ:-የተወሰደው ናሙና ባእድ ነገር እንዳገባበትና ከሌላ ናሙና ጋር ለመለየት እንዲያስችለረ በጥንቃቄ መታሸግና እላዩ ላይ መለያ ኮድ መጻፍ ይገባል።

እንደስራው ደረጃና የሳይቱ ስፋት መጠን ከላይ የተጠቀሰውን አካሄድ ቢያን ሶስትና ከዚያ በላይ በመሃንዲሱ በተመረጡ ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል።

⚡️የአፈር ጥቅጠቃ ስራ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

የአፈሩ ዓይነት/soil type/

ለምሳሌ: ኮረታማ/ጠጠርማ/Gravel/Granular/ አፈር ለመጠቅጠቅ ምቹና በጣም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሲሆን፣በተቃራኒ ጥቁርና ብስባሽ ያለው አፈር ደግሞ ለመጠቅጠቅ የማይሆንና የማይች በመሆኑ ለማንኛውም ስትራክቸራል ሙሊት ስራ የማይመረጥ ነው ይሆናል ማለት ነው።ከታች በምስል 4 ላይ የተቀመጠውን ይመልከቱ።

⚡️የአፈሩ ውሃ ይዘት/soil water content/:

⚡️አፈሩ በጣም ውሃ ያዠ ወይም ከልክ በላይ የደረቀ መሆን የምንፈልገውን እፍግታ ማግኘት እንዳንችል ያደርጋል ማለት ነው።

⚡️የጥቅጠቃ ሃይል/Compaction Effort/


https://t.me/ethioengineers1
👍34❤2👏2🤔1
💥ዘመን አመጣሽ ፒራሚዶች

⚡️ኢንጂነሪንግ ጥንታዊውን ጊዜ ከወደፊቱ ዘመን ጋር ለማገናኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። ይህ እየሆነ ያለው ደግሞ በግብጽ ነው። በኢትዮጵያም መጀመር ያለበት ምርጥ የምህንድስና ሃሳብ ነው።

⚡️ይህ ማለት የላሊበላ አብያተ ክርስቲያን ውቅሮችን ወይም የፋሲል ግንብን አልያም የአክሱም ሃውልትን በተንቆጠቆጠ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች እየታገዙ አዲስ አበባ ውስጥ እንደ መገንባት ማለት ነው።

⚡️አሁን ግብፆች ጀምረውታል። አዲሱን ትውልድ ካለፉት ታሪኮቹ ጋር ሊያገናኙት ነው። ግብፆች የጥንት ዘመን ፒራሚዶቻቸውን በዘመን አመጣሽ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ እውን ለማድረግ ከጫፍ ደርሰዋል።

መሃንዲሶቹ "Where past meets future." በሚል አላማ የጀመሩት ፕሮጀክት በ2030 ለምርቃት ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል።


https://t.me/ethioengineers1
👍24👏3❤1🔥1
Plan Symbols part 1🚽🚪🛁 🪟 🚪

https://t.me/ethioengineers1
👍15👏1
Plan Symbols part 2

https://t.me/ethioengineers1
👍23❤3👏2
💥የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/

🌟የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

⚡️እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡

⚡️የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡

🌟ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡

⚡️የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡

⚡️የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡

🌟እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡

⚡️ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡

🌟ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍13❤2