SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
በጣም በጥራት የተመረተ በፍጥነት ያሉበት ቦታ ድረስ በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን

በ 0912492727
0913061530 ይደውሉ
((መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ ))

ፀግሽ
👍7
💥የ ድምር ባዶ ከተማ ንድፍ አይነቶች።
(Net Zero urban development types)


⚡️ድምር ባዶ እድገት ማለት በእለት ተለት ኑሮአችን ወደ አካባቢው የምንለቀውን ያህል ካርቦን ከአካባቢ በማስወገድ የምንተገብረው አይነት እድገት ነው።

✨ሶስቱ የድምር ባዶ የከተማ አይነቶች።
1. ዘላቂ ከተሞች
2. ችግር ተቋቋሚ ከተሞች እና
3. ጠቢብ ከተሞች ናቸው።

ምስል ምንጭ። አንቶኒዮ አብዶ


https://t.me/ethioengineers1
👍8❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💥ሁሉንም እናውቃለን ካለኛ አዋቂ የለም የምትሉ ሰዎች (ጋዜጠኞች ) ግን ትንሽ እንኳን ባለሞያ ጠየቁ program ለህዝብ ከማቅረባቸው በፍት ‼️

አስፈላጊነቱን ማወቅ ከፈለግክ ጠይቅ 🤔

https://t.me/ethioengineers1
👏14👍10🤔4❤1
🌟ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ /Soil Compaction/ በጥቂቱ

☄Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።

✨እንዴት?

✨አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ/density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው።

💥ይህም በመሆኑ:

*የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን።

*በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን።

*ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/

⚡️የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/

⚡️የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው።

⚡️በሰው ሰራሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ
/Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል።

🤞ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው።

✨የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/

⚡️በዋናነት በሁለት ይመደባሉ።

-በሳይት ላይ የሚተገበሩ
/Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው።

-በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test... 

ለዛሬ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን።

⚡️Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/

ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው።

* *የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/

የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር

መቆፈሪያ፣ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/

ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/:

ንፁህ አሸዋ

ወንፊት

ሚዛን/Balance/

ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ

* *የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/

1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ።

2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት።

3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።

ማስታወሻ:- የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን።ምስል 5 ን ይመልከቱ

4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ።

5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

6ኛ. የተሰበሰበው ዳታ በመጠቀም. የሳይት ላይ እፍግታውን/Bulk density/ ማወቅ እንችላለን። በቀጣይ ጽሁፍ የሚወጣውን ምሳሌ መመልከት ይቻለል።

7ኛ. ከፍተኛው የደረቅ እፍግታ ልኩን/MDD/ በቤተ ሙከራ ለመስራት ከሰሃኑ ላይ ለናሙና 1/3ኛ ያህሉን በንፁህና ደረቅ ላስቲክ በማድረግ ማዘጋጀት።

ማስታወሻ:-የተወሰደው ናሙና ባእድ ነገር እንዳገባበትና ከሌላ ናሙና ጋር ለመለየት እንዲያስችለረ በጥንቃቄ መታሸግና እላዩ ላይ መለያ ኮድ መጻፍ ይገባል።

እንደስራው ደረጃና የሳይቱ ስፋት መጠን ከላይ የተጠቀሰውን አካሄድ ቢያን ሶስትና ከዚያ በላይ በመሃንዲሱ በተመረጡ ቦታዎች ላይ መስራት ይገባል።

⚡️የአፈር ጥቅጠቃ ስራ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

የአፈሩ ዓይነት/soil type/

ለምሳሌ: ኮረታማ/ጠጠርማ/Gravel/Granular/ አፈር ለመጠቅጠቅ ምቹና በጣም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ሲሆን፣በተቃራኒ ጥቁርና ብስባሽ ያለው አፈር ደግሞ ለመጠቅጠቅ የማይሆንና የማይች በመሆኑ ለማንኛውም ስትራክቸራል ሙሊት ስራ የማይመረጥ ነው ይሆናል ማለት ነው።ከታች በምስል 4 ላይ የተቀመጠውን ይመልከቱ።

⚡️የአፈሩ ውሃ ይዘት/soil water content/:

⚡️አፈሩ በጣም ውሃ ያዠ ወይም ከልክ በላይ የደረቀ መሆን የምንፈልገውን እፍግታ ማግኘት እንዳንችል ያደርጋል ማለት ነው።

⚡️የጥቅጠቃ ሃይል/Compaction Effort/


https://t.me/ethioengineers1
👍34❤2👏2🤔1
💥ዘመን አመጣሽ ፒራሚዶች

⚡️ኢንጂነሪንግ ጥንታዊውን ጊዜ ከወደፊቱ ዘመን ጋር ለማገናኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። ይህ እየሆነ ያለው ደግሞ በግብጽ ነው። በኢትዮጵያም መጀመር ያለበት ምርጥ የምህንድስና ሃሳብ ነው።

⚡️ይህ ማለት የላሊበላ አብያተ ክርስቲያን ውቅሮችን ወይም የፋሲል ግንብን አልያም የአክሱም ሃውልትን በተንቆጠቆጠ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች እየታገዙ አዲስ አበባ ውስጥ እንደ መገንባት ማለት ነው።

⚡️አሁን ግብፆች ጀምረውታል። አዲሱን ትውልድ ካለፉት ታሪኮቹ ጋር ሊያገናኙት ነው። ግብፆች የጥንት ዘመን ፒራሚዶቻቸውን በዘመን አመጣሽ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ እውን ለማድረግ ከጫፍ ደርሰዋል።

መሃንዲሶቹ "Where past meets future." በሚል አላማ የጀመሩት ፕሮጀክት በ2030 ለምርቃት ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል።


https://t.me/ethioengineers1
👍24👏3❤1🔥1
Plan Symbols part 1🚽🚪🛁 🪟 🚪

https://t.me/ethioengineers1
👍15👏1
Plan Symbols part 2

https://t.me/ethioengineers1
👍23❤3👏2
💥የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/

🌟የኮንስትራክሽን ውል ስምምነት/contract agreement በአሰሪ/client እና በተቋራጭ/contractor መካከል የሚፈረምበት ቀን የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

⚡️እዚህ ላይ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020 ድንጋጌ እና አንድ ውል ተቋቋመ ሊባል የሚችለው መቸ ነው? የሚለው ማለትም የውል አቀራረብ/offer እና አቀባበል/acceptance በሚመለከት በፍትሀብሄር ህጉ 1681 እና ተከታዮቹ የተደነገገው እና የውል ፎርም ጉዳይ ከግምት ውስጥ መግባት ጭምር አለበት፡፡

⚡️የግል የኮንስትራክሽን ውል ጉዳዮችን በሚመለከተው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ አሰሪና ተቋራጭ ስለሚሰራው ስራ እና ስለዋጋው ካልተስማሙ በስተቀር የተቋራጭነት ውል አለ እንደማይባል ተደንግጓል፡፡

🌟ሌላው ከአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎችን በሚመለከት ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው ጭምር ተፈጸሚነት እንዳለው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3131(1) ይደነግጋል፡፡

⚡️የአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጽሁፍ መደረግ እንዳለባቸው በፍትሀብሄር ህግ ስለውሎች በጠቅላላው በሚደነግገው ክፍል በአንቀጽ 1724 ላይ ተደንግጓል፡፡

⚡️የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2005(1) ላይ እንደተደነገገው ደግሞ የጽሁፍ ሰነድ በላዩ ላይ የተጻፈውን ቀን በሚመለከት በተፈራራሚዎች መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ነው ይላል፡፡

🌟እንግዲህ ውል የተደረገበት ቀን በአሰሪና ተቋራጭ መካከል የውል ግንኙነት መቋቋሙን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡

⚡️ውል ደግሞ ከተቋቋመበት ቀን ጀምሮ በተዋዋዮች መካከል እንደህግ እንደሚቆጠር የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731(1) ይደነግጋል፡፡

🌟ሆኖም ግን ውሉ የተደረገበት ቀን የውሉ የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን ተደርጐ ሊወሰድ አይገባም፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍13❤2
💥BEDRU HAMZA IMPORTER

🏗we import different kinds of construction materials
*RHS
*CHS
*SHEET METAL
*WIRE MESH
*ANGLE IRON
*FLAT BARS
*ROUND BARS

and other construction related materials

phone no 0911085788, 0903343003
👍4❤1
💥ሒልተን ሆቴል

🌟ሒልተን ሆቴል አዲስ አበባ እኤአ  ህዳር 3 ቀን 1969 ዓ.ም የተመረቀ ሲሆን የተነደፈው አሜሪካ በሚገኘው በዋርነር በርንስ ቶአን እና ሉንዴ ኪነህንጻ ፅህፈት ቤት  ነበር።

🚧ጽ/ቤቱ በባህር ዳር፣ በጎንደር እና በየሃ አውዳዊ ሆቴሎችን ጨምሮ ነድፏል።

🌟ሒልተን ሆቴል በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢሲኤ እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቶች ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለመጣው የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች መገኘት ተስማሚ የሆነ ማረፊያ ለመስጠት የታቀደ ከንጉሰ ነገስቱ  ዋና ዋና ፕሮጀክቶች አንዱ ነበር።

🌟ሒልተን ሆቴል ውስጥ የምናያቸው ቀለሞች፣ ንድፎች፣ የቦታ መጠኖች፣ የብርሀን አገባቦች፣ ምጣኔዎች እና ሚዛኖች በሙሉ ታሪካዊውን እና ባህላዊውን የሰሜን ኢትዮዽያ ኪነህንጻ ያስታውሱናል።

Via ዳዊት በንቲ


https://t.me/ethioengineers1
👍15🤔1
💥Load calculation on column👆

✨Factors affecting the size of column

1. Number of story - when the number of story increase the size of the column increases for example we are not using the same size of column for G+1 building and G+9 building

2. Loading condition -  Loading is the most important factor to be considered in column design the loads are two types gravity loads and lateral loads. The loading condition is also directly proportional to dimensions of the column. If the total load on the building increases the dimensions of the column is also increases and if the less amount of the loading is taken by the building then the less dimensions of column are assumed in building design.

3. Center to center distance between columns

The dimensions of column is also affected by  the center to center distance between the columns. If the columns center to center distance  increases the column size increases.

https://t.me/ethioengineers1
👍10👏4❤3
💥Roof

🏗ጣራ(roof) በስነ ህንፃ ንድፋ ውስጥ ዋና የሆነውን ቦታ(space) በመፋጠር ሂደት ውስጥ የሰው ልጅ በስፍራው ውስጥ ያለውን የእንቅስቃሴና ተግባራት በማገናዘብ አማካይ የሆነውን የቁመት ልኬትን እንዲሁም የአየር ሁኔታን በዋናነት በማጥናት ይሰራል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም የምንገነባውን ግንባታ ቁመት የሚወስን ሲሆን በተለያየ ቅርፀና የግንባታ መሳሪዎች ይኖሩታል፤ ከነዚህም ውስጥ

1, አሞራ ክንፍ(gabled roof) የምንለው በሁለት በኩል ያጋደለ መዋቅር ያለው ሲሆን በላዩ ለሚከሰቱ እንደ ዝናብ እና የበረዶ ክምርን በቀላሉ ለማስወገድ ተመራጭ ነው።

2,sloped roof ሲሆን ከመጀመሪያው የሚለየው የሚያጋድለው ክፍሉ በአንድ በኩል በመሆኑ ነው ይህም የግንባታ ጊዜና እቃን የማቃለል አማራጭን ይወስዳል።

3,ሶስተኛውና ሌላኛው በተለይም በዘመናዊ የስነ ህንፃ ዘርፍ የሚታየው በአሰራሩም ከሌሎቹ የሚለየው flat roof የሚባለው የጣሪያ አይነት ሲሆን የሚሰራበት የግንባታ እቃም እንደ ሲሚንቶና  ብረት ያሉ ጠንካራ እቃዎችን በመጠቀም ነው። ዝርግ(flat) የሚለውን ስያሜ የግኝ እንጂ በአይናችን የማናየው የማጋደል ድርሻ በሁለቱም ወይም በአንዱ በኩል ይኖረዋል።
flat roof ተመራጭ የሆነባቸውን ምክንያቶችን ስናይ
👉በዝናብ ወቅት ድምፅን በመቀነሱ፣ 👉የሙቀት መከላከያ(insulation) በማቀናጀቱ፣
👉ጠንካራና ረጅም እድሜ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን በላዩ ማስቀመጥ በማስቻሉ ነው።
▶️ጣራዎች(roofs) ከሚሰጡን የመጀመያ ደረጃ አገልግሎት በተጨማሪ እንደ green roof ያሉ ተክሎችን በላያቸው ላይ በማብቀል እንዲሁም solar panels በመያዝ ታዳሽ ለሆነው የግንባታ ዘርፍ የራሳቸውን አስተዋጽኦ የበረክታሉ።

https://t.me/ethioengineers1
👍16❤4👏2
💥አንድ መሀንዲስ እፈልጋለሁ

በደንብ drawing አንብቦ ማሰራት የምችል እና ከዚህ በፍት ሳይት የሰራ በውስጥ መስመር contact ያርገኝ @Ethiocon143bot

ደሞዝ :-10,000ETB

ሥራ ያላችሁ ይህ ማስታወቂያ አይመለከታችሁም ‼️

https://t.me/ethioengineers1
❤24👍17👏1
💥Wall symbols...Part 3

https://t.me/ethioengineers1
👍15❤1
💥ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ

ግዙፉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡

ግንባታው በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓቱን የማብላላት ተግባር ያለውን የፋብሪካው ክፍል እና ወደ ቀጣዩ ሂደት ማስተላለፊያ ቱቦ መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ ከቻይና ባለሀብቶች ጋር በመሆን እየተገነባ ያለውን ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ቀንና ማታ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

#Ethiopia
https://t.me/ethioengineers1
👍24👏2