SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥ምርጥ ምርጥ የኮርኒስ ዲዛይን ሃሳቦችን ይዘን መጥተናል። በአሁኑ ወቅት የኮርኒስ አሠራር ከሚገባው በላይ እየዘመነ መጥቷል። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ የኮርኒስ ዲዛይኖች አሠራር ተመሳሳይ ከመሆኑ የተነሳ የመሰልቸት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

በተለይ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች በጂፕሰም ቦርድ እንደ ፋሽን በስፋት እየተሠሩ ያሉት ኮርኒሶች ተመሳሳይ በመሆናቸው ተወዳጅነታቸው በቶሎ ሊቀንስ ችሏል።  አሁንም ድረስ የዲዛይን እጥረት እንዳለ ይስተዋላል።

ይህን ክፍተት ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ ባይሆንም ከታች የተቀመጡት 9 ፎቶዎች ለአዳዲስ ገንቢዎችም ሆነ ቤታቸውን ለሚያድሱ ተጨማሪ አዳዲስ ሃሳቦችን ይሰጣሉ የሚል ዕምነት አለን።


https://t.me/ethioengineers1
👍12
💥BEDRU HAMZA IMPORTER

🏗we import different kinds of construction materials
*RHS
*CHS
*SHEET METAL
*WIRE MESH
*ANGLE IRON
*FLAT BARS
*ROUND BARS

and other construction related materials

phone no 0911085788, 0903343003
👍7
💥ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?

🌟ካዳስተር ማለት መሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡

⏺እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

▶️ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡-

🚧አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም ዬትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡

🚧ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

🚧ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

⏺የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡

⏺አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡ በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

⏺በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው:: ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍31❤1🤔1
💥ዲዛይን ስታረጉ ማስታወስ ያለባችሁ ህግ

1. መስኮት ስታበጁ ከ አጎራባች 2 ሜትር ገባ
  በሉ
2. ለ ሽንትቤት ከ 60 ሳንቲም በታች የሆነ መስኮት ስታበጁ 1.5 ሜትር ገባ በሉ

Here is some tips you need to remember designing in Addis Ababa

1. To provide a window you need to
   offset 2 meter from your boundary line
2. To provide bathroom window <60 cm you need to offset 1.5 meters


https://t.me/ethioengineers1
👍21👏3❤2
💥ግጭቶችን የመፍታት ሂደት ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተግባቦት (Arbitration)

🌟በኮንስትራክሽን ውሎች አፈጻጸም ላይ የሚከሰቱ ያለመግባባቶች ሊፈቱ ከሚችልባቸው ዘዴዎች አንዱ የሆነው የግልግል ሥርዐትም (Arbitration) አከራካሪነቱ የሰፋ ነው።

የፍትሐ ብሔር ስነስርዓት ሕጋችንና ሌሎች የግልግል ስርዓትን የሚገዙ ህጎቻችን የማይጣጣሙባቸው አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑ ይታወቃል።

⏺የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 315(2) (4) ሲታዩ የአስተዳደር ውሎች በግልግል የማይታዩ መሆናቸውን ሲያስገነዝቡ የፍትሐ ብሔር ህጉና ሌሎች በሥራ ላይ ያሉት የመንግሥት ተቋማት ማቋቋሚያ ደንቦች ግን በዚህ ረገድ ግልጽ ክልከላ አላደረጉም።

▶️እንዲሁም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር በሰ/መ/ቁ 16896 በቀን 16/02/1998 ዓ.ም (ቅጽ 2 ገጽ 75-78 ይመለከታል)።

⏺የአስተዳደር ውሎችን በግልግል ለመጨረስ ስምምነት ማድረግ የሚቻል መሆኑን የሚአይስገነዝብ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ደግሞ የቀደመውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በግልጽ ሳይሻር የአስተዳደር ውሎች የግልግል ሊታዩ የማይችሉ መሆኑን የሚያሳይ ትርጉም በሰ/መ/ቁጥር 127459 መስከረም 23/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሰጥቷል።

▶️የዚህ ውሳኔ ይዘቱ ሲታይም የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቂ 315 (2) የአስተዳደር ውልን አስመልክቶ የሚነሳ አለመግባባትን ለመዳኘት የማይችለው የግልግል ዳኝነት አካል ወይም (Arbitrator) ነው የሚል ነው።

⏺ይህ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 454/97 የታሰበውን የውሳኔዎች ተገማችነት ዓላማ የሚቃረን ውሳኔ መስጠቱን ከማሳየቱም በላይ በኮንስትራክሽን ውሎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሚፈቱባቸውን መንገዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋርም አብሮ የማይሄድ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ጉዳይ ነው (አልማው ወሌ, 2019)

#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍13❤2
💥የቤት ባለቤትነት ማረገገጫ/ካርታ/ ለምን ይመክናል?

▶️ካርታ ማምከን ማለት ፡- ከዚህ በፊት በተለያየ አግባብ ተሰጥቶ የነበረ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ በህግ ፊት የፀና እንዳይሆን ወይም ለማንኛውም ህጋዊ አገልግሎት እንዳይውል ማድረግ ማለት ነው።

⏺በማናቸውም ጊዜ የወጡ ካርታዎች ካርታውን ሊያመክን የሚችል ጉዳይ ሲገኝ በየትኛውም ጊዜ እንዲመክኑ ይደረጋል።

▶️ካርታ ሊመክን የሚችልባቸው ዋና ዋና ምክኒያቶች አራት ናቸው።

1ኛ. አንደኛው ምክኒያት ካርታው ወይም ይዞታው በተጭበረበረ ወይም ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን ባልተከተለ መንገድ የተገኘ መሆኑ ሲረጋገጥ

2ኛ. ሁለተኛው ምክኒያት ደግሞ በተለያየ ህጋዊ ምክኒያት የሊዝ ውሉ ሲቋረጥ ነው፡፡

3ኛ. ሶስተኛው በባለይዞታው ዕጅ መኖር ያለበት ካርታ መጥፋቱ ሲረጋገጥ በምትኩ ካርታ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካርታ ሊመክን ይችላል፡፡

4ኛ. አራተኛ በከተማው ካቢኔ ሲወሰን ቀደም ሲል የወጣው ካርታ እንዲመክን ይደረጋል።

🚧የአንድ ካርታ ይምከንልን ጥያቄ ጥቆማ ሲቀርብ ተገቢው ማጣራት ሳይደረግበት ጥቆማው ወይም በጥያወቄው መሰረት ብቻ ካርታ አይመክንም።

⏺ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ የምንመለከተው ጉዳይ ካርታን አግዶ ስለማቆየት ይሆናል።

⏺አንድ ካርታ ወሳኔ ሳያገኝ በዕግድ ሊቆይ የሚችለው ከሶስት ወር ላልበለጠ ጊዜ ብቻ ሲሆን አንድን ካርታ ለማምከን በቅድሚያ ጉዳዩ ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ካርታው ታግዶ እንዲቆይ ለባለይዞታው እና ለሚመለከታቸው አካላት በክ/ከተማው ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ አማካኝነት ምክንያቱ ተጠቅሶ በጽሁፍ እንዲያውቁት ማድረግ ይኖርበታል።

▶️በክፍለ ከተማ ደረጃ የተሰጠው የካርታ ይምከን ውሳኔ ላይ የሚነሳ ቅሬታ ለከተማው ፕሮጀክት ጽ/ቤትና ለቢሮው በቅደም ተከተል ቀርቦ ሊታይ ይችላል።

▶️ቅሬታው ተቀባይነት ካገኘ የመከነው ካርታ የዕግድ ደብዳቤ እንዲነሳ ወይም ወደ አገለግሎት እንዲመለስ ይደረጋል። {የይዞታ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁ 12/2004፣ አንቀፅ 16}

https://t.me/ethioengineers1
👍11🙏3❤2
💥በጋራ የኮንስትራክሽን ሥራ ንግድ ፍቃድ ስታወጡ ስለስያሜው
{ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት}


🚧በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ አክሲዮን ማኅበር፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሽርክና የሚባሉ ከአንድ በላይ የሆኑ አባላት በጋራ ሆነ ንግድ ፍቃድ የሚያወጡባቸው ዘርፎች አሉ እነዚህ ስያሜዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በዚህ ክፍል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር—ኃ.የተ.የግ.ማ (Private Limitted Company - PLC) እና የአክሲዮን ማህበር - አ.ማ (Social Company - SC) ያላቸውን አንድነትና ልዩነት እንመለከታለን። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

🌟ተመሳሳይነታቸዉ

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

🌟ልዩነታቸዉ

⏺አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል።

〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም።
〰️ አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም
〰️ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም  ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ
〰️ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
〰️ አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም።

🖱ምንጭ፦ ሳሙኤል ግርማ  — የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ


https://t.me/ethioengineers1
👍25❤1😍1
💥የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ ትዕዛዝ መሥጠት

🚧“አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ በግንባታ ሒደት ውስጥ ለተቋራጩ የስራ ትዕዛዞችን እየሰጠ፣ የስራዎቹን አካሄድ የመወሰንና ስራው በሚፈቅደው አይነት እንዲፈፀም የስራ ተቋራጩን የማዘዝ ሥልጣን ያለው ሲሆን፣ ተቋራጩ በበኩሉ በአሠሪው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተሰጡት ፕላኖች አይነቶችና የዋጋና የስራ ማስታወቂያ መሰረት ጠንቅቆ የግንባታ ሥራውን የመስራት ግዴታ እንዳለበት  በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3252 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ንዑስ አንቀጽ 2 በግልፅ ተደንግጓል።

🌟ነገር ግን የጨረታ ሰነዱ በሚወጣበት ጊዜ በግንባታ ዲዛይኑ ላይ ከተመለከተው ልኬት በታች ሆኖ በኋላ በዲዛይኑ መሰረት ለሚሰራ ግንባታ የሥራው ባለቤት በግንባታው ሥራ ውል ሰነዱ ላይ ከተመለከተው ክፍያ ውጪ በተጨማሪነት በባለቤቱ ፈቃድና ትዕዛዞች መሠረት ለተሠሩ ሥራዎች ክፍያ ለመክፈል የሚገደድ ሲሆን በህጉ አግባብ በባለቤቱ የተሰጡ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዞች የሥራ ውሉ አካል ተደረገው የሚወሰዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ.3244, 3225,(1)(2), 3152(1), 3266(1), 3263, 3265(3) በዝርዝር ተዳስሰዋል።

⏺በተለይ አሠሪው መሥሪያ ቤት በሚመለከተው ክፍል ማህተም ያለበት ደብዳቤ ተጠቅሞ አልያም በተመደበው ተቆጣጣሪ ፊርማ ሥራዎችን እያጸደቀና እያዘዘ እንዲሰሩ የተደረጉ ሥራዎች በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 3152 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3266(1) ድንጋጌዎች መሰረት የሰጣቸው ተጨማሪ የስራ ትዕዛዞች የግንባታ ሥራ ውሉ አካል ተደርገው የሚያዙ ናቸው።


https://t.me/ethioengineers1
👍21❤3
💥የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት አብሮ በጋራ ለመስራት የሶስትዮሽ የመግባቢያ የስምምነት ፊርማ ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሽራተን አዲስ ተፈራርመዋል።

የውል ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር ኢ/ር ግርማ ሀብተ ማርያም ፡ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኢ/ር መስፍን ነጋዎ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማናጅመንት ኢንስቲትዮት በኩል ደግሞ ዋና ዳይሬክተሩ ኢ/ር ታምራት ሙሉ ናቸው።


https://t.me/ethioengineers1
👍12❤3
💥የቁፋሮ ሥራ (Excavation works) ላይ መረጋገጥ ያለባቸው የቁጥጥር ነጥቦት

🌟የቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቁፋሮዎች፣ አጎራባች ቦታዎች እና የመሬት መንሸራተት መከላከያ ዘዴዎች በባለሙያ ጥናት ሊደረግባቸው ይገባል።

⏺ይመረመራሉ በመሆኑም በቁፋሮ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያው የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት አድርጎ ማረጋገጥ አለበት።

1. የአጎራባች ወሰንን ከመፍረስ መታደግ፦ በግንባታ ሥራ የመጀመሪያው ተግባር ቁፋሮ ሲሆን ማንኛውም ቦታ አጎራባች የሆነ የሕንጻ ቦታ ወይም መንገድ የሚኖረው ሲሆን ቁፋሮው ወደአጎራባች ወሰን ተጠግቶ የሚከናወን ከሆነ በቁፋሮው መጠጋት አልያም በንቅናቄ (Vibration) የተነሳ የአጎራባች መሬት በመውደቅ ወይም በመንከባለል ለሁለቱም ቦታዎች አደጋ እንዳይፈጥር የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጎረቤት ወሰን/አጥር/ ቢፈርስ ወይም ሕንጻ ቢወድቅ በመሐንዲሱ የክትትል ድክመት የተነሳ ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ ይችላሉ።

2. በሕግ የሚፈቀደውን የውጪ መስመር አለማለፉን ማረጋገጥ፦ ሕንጻው የሚሰራበት የካርታ ቦታ በአካባቢ ልማት (Local development plan) መሰረት ከፍተኛ የኢሌክትሪክ ኃይል (High Electric tension) የሚያልፍበት አልያም የመንገድ ማስፋፊያ ስፋት (Road Widening Area) የሚገባበት ሊሆን ስለሚችል በግንባታ ወቅት የተዘጋጀ አዲስ የፕላን ስምመትን በማመሳከር እንደዲዛይኑ በተፈቀደ ክልል ውስጥ ማረፉን እና በባለቤት ግፊት የተነሳ ያልተፈቀደ ቦታ ላይ አለማረፉን ማረጋገጥ አለበት።

3. በቁፋሮ ክልል ደህንነትን ማረጋገጥ፦ ከቁፋሮው በኋላ ከመሬት ውስጥ ያለው ሥራ (Sub Structure Works) ተጠናቆ የተቆፈረው ክፍል እስኪሞላ ድረስ የሰከረ፣ ወይም የአእምሮ እክል ያለበት፣ ወይም ሕጻናት፣ ወይም ሽማግሌዎች ወደጉድጓድ ገብተው አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከተፈቀደላቸው የግንባታ ሰራተኞች ውጪ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የታጠረ (Fenced) እና የውስጥ መሸጋገሪያ (Bridge Ladders) የተሰራላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

4. የመሬት ውስጥ ዝርጋታዎች (Underground installations)፦ በሰፋፊ ግቢዎች ውስጥ ለግቢው አግልግሎት የሚሰጡ አስቀድሞ የተዘረጉ የውኃ፣ የኢንተርኔት፣ የመረጃ እና የመብራት ዝርጋታዎች የሚኖሩ ከሆነ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በጥንቃቄ እንዲነሱ አልያም ግንባታው ጉዳት ሳያደርስባቸው እንዲከናወን ማድረግ ይኖርበታል።

5. የቁፋሮውን ልኬት ማረጋገጥ፦ በተለይ በአርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል እና ሳኒታሪ ንድፎች ላይ የተመለከተው ተጓዳኝ የቁፋሮ ሥራ የሚጠይቁትን ልኬቶች ማሟላቱን (ወርዱን፣ ስፋቱን፣ ርዝመቱን፣ ዲያሜትሩን፣ ጥልቀቱን) ጠብቆ ቁፋሮ መንዲከናወን የመቆጠጠርና መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።

6. ውኃ እንዳይቋጥር ማስደረግ፦ በዝናባማ እና የመሬት ውኃ በሚፈልቅባቸው አካባቢዎች ቁፋሮ እንደተከናወነ ዝናብ ቢዘንብ ቢያንስ የጎርፍ ውሃ እንዳይገባ የመከላከያ ሥራዎች፣ እንዲሁም የመሬት ውስጥ ምንጭ ውሃን የመከላከያ (like: Permeable hardcore layer, geotextile material, channelization...) መንገዶች ተግባራዊ የሚደረጉበት መሆኑን ማረጋገጥና መከታተል አለበት።

7. የቁፋሮ ግብአቶችና ማሽኖችን ደህንነት ማረጋገጥ፦ በቁፋሮ ሥራ መወጣጫ የሚሆኑ የብረት፣ የእንጨት እና የፕላስቲክ ግብአቶችን ብልሽት የሌለባቸው መሆኑ እና ለቁፋሮ ሥራ የቀረቡ የእጅ መሳሪያዎች እና ማሽኖች የደህንነት ችግር የሌለባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

8. በቂ አየርና ብርሃን የሚገኝበት መሆኑን፦ በጣም ልዩ ሁኔታ የሚባልና በብዙዎቹ ግንባታዎች ላይ የማይገጥም ቢሆንም በውኃ ውስጥ፣ በመሬት ውስጥ ለሚከናወኑ ቁፋሮዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች በቂ የሆነ የኦክስጅን አየር ማግኘት ስላለባቸው መሐንዲሱ የአየር ሁኔታውን የሚቆጠጠሩ ማሽኖች፣ አልባሳት እና ብርሃን መቅረባቸውን ማረጋገጥ ማድረግ አለበት።


https://t.me/ethioengineers1
👍19❤3🙏2
💥የአቅም ማረጋገጫ (Performance bond/guarantee)

🌟የአቅም ማረጋገጫ አንድ ተቋራጭ ለክፍት ጨረታ ተወዳድሮ ሲያሸንፍ ቅድመ ክፍያ ወይም ፐርፎርማንስ ጋራንቲ እንዲያስገባ ይጠየቃል።

📂ይህ ሰነድ ጨረታውን ያሸነፈው ተቋራጭ ፕሮጀክቱን በብቃትና በጥራት ማጠናቀቅ ለመቻሉ እንደማስያዣ ሆኖ በባንክ የሚቀመጥ ቅድመ ክፍያ ነው።

📍በሀገራችን የኮንስትራክሽን ውል ሰነድ (Public Procurement Agency – PPA) መሰረት አንድ የጨረታ ተወዳዳሪ የቅቡልነት (የጨረታ አሸናፊነት) ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ (Performance bond) ጨረታ ላወጣው አካል ማቅረብ እንዳለበት በክፍል አንድ (section 1)  “instruction to bidder (ITB) article 33 (33.1) ላይ ተቀምጧል።

🔗ይህ የብቃት ማረጋገጫ ገንዘብ መጠንና የገንዘብ አይነት (Amount and Currencies) በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት መሆን የሚገባው ሲሆን  በብዛት ጨረታውን ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያህል የባንክ ማረጋገጫ ማቅረብ የተለመደ ነው። 

📇የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) ክፍያ የሚከፈልበት ጭምር ሲሆን ስለ ቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) ምንነት በሚቀጥለው ክፍል እንመለከታለን።

https://t.me/ethioengineers1

በ ኢ/ር ዳንኤል ታጠቅ
👍9👏4❤1