SMH General Construction
22.5K subscribers
1.48K photos
45 videos
293 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥አርክቴክቸር ሰዎች መጠለያ መገንባት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ጥንታዊ የምህንድስና ጥበብ ነው። የሰው ልጅን ቁሳዊም ሆነ ሞራላዊ ፍላጎት ለማሟላት ህንጻዎችን መንደፍ፣ ማቀድ እና መገንባትን የሚያካትት ጥበብ እና ሳይንስ ነው። ከመኖሪያ ቤቶች እና ከቢሮዎች እስከ ሀውልቶች ድረስ አካላዊ መዋቅሮችን ለመግለጽ የሚያገለግል አጠቃላይ ቃል ነው።

አርክቴክቸር በውስጥም ሆነ በውጭ ለህንፃዎች ተግባራዊ እና ውበት ያለው ዲዛይን የመፍጠር ጥበብ ነው። ሕንፃውን የሚጠቀሙ ሰዎችን ፍላጎት፣ ለዓላማው ተስማሚ የሆኑትን ቁሳቁሶችና የግንባታ ዘዴዎችን መረዳትን ይጨምራል። በዚህ ጥበብ አማካኝነት አርክቴክቶች በዓለም ዙሪያ ባሉ ከተሞች ውስጥ ታዋቂ የሆኑ ውብ እና ዘላቂ መዋቅሮችን መፍጠር ችለዋል።

እንደሚታወቀው፣ በአለማችን ላይ ከተገነቡ አስደናቂ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው በዱባይ የሚገኘው "ቡርጅ ከሊፋ" ይጠቀሳል። የዚህ ግዙፍ ሰማይ ታካኪ ግንባታ  የሕንፃ ንድፍ ሥራ የተሠራው በአርክቴክት አድሪያን ስሚዝ ነው።

እንዲሁ በዱባይ፣ "ቡርጅ አል አረብ" ታዋቂ ቅንጡ ሕንፃ ንድፍ አውጪ ቶም ራይት ሲሆን፣ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ ውስጥ የምትገኘው "ኦፔራ ሃውስ" ንድፍ የተሠራው በአርክቴክት ጆርን ኡትዞን መሆኑ ይታወቃል። ሁሌም ሲዲኒን ስናስብ ይቺህ የኦፔራ ሃውስ ሕንፃ የማትረሳ ነች።

ታዋቂዋ ኢራናዊ የሕንፃ ንድፍ  አውጪ ዛሃ ሃዲድ የቢጂንግን ኤርፖርት ንድፍ በማውጣት አለም አቀፍ እውቅናን አግኝታለች።

እነዚህ በጥቂቱ የተጠቀሱ የአርክቴክቸር ውጤቶች ሲሆኑ፣ ከታች የቀረቡትን ዕውቅና ያላቸው የግንባታ ሥራዎችና ነዳፊዎቻቸውን መመልከትም ይቻላል።


https://t.me/ethioengineers1
👍28❤6
💥የወጪ እና ተጨማሪ ክፍያ ውል (Cost Plus Fee Contract)

🌟ይህ የውል አይነት ለግንባታው የወጣውን ዋጋ እና ለተቋራጩ የሚከፈለውን የጉልበት ዋጋ ወይም ትርፍ የሚከፈልበት ሲሆን በሦስት አይነት መንገድ ሊገለጽ የሚችል ነው።

(1). ወጪ እና ቁርጥ ክፍያ (Cost plus fixed fee):- አንድን ሕንጻ ለመገንባት የሚዋዋለው ተቋራጭ ለሕንጻው ግንባታ ያወጣው  የሚያስአጋ ምንምም ይሁን ምን ለሰራበት ለብቻው ተለይቶ የሚከፈለው ሲሆን ነው። ለምሳሌ አንድ ሕንጻን ከሚፈጀው ዋጋ የተለያየ (የሚቀያየር) ቢሆንም ተቋራጩ ግን ለገነባበት የተስማማው ገንዘብ 1,000,000 ብር ያ ብር ብቻ የሚከፈለው ሲሆን ነው።

(2). ወጪ እና አንጻራው ፐርሰንት ክፍያ (Cost Plus Percentage fee)፦ በዚህ አይነት ውል ላይ ተቋራጩ የሰራውን ሥራ ያህል በተቆረጠ ፐርሰንት የሚከፈለው ሲሆን ነው። ለምሳሌ፦ ተቋራጩ አንድን ፕሮጀክት በ100,000,000 ብር ቢያጠናቅቅ ግንባታውን ላከናወነበት ክፍያ 10% የተዋዋለ ቢሆን 10,000,000 ብር የሚቀበል ሲሆን ነው።

▶️ነገር ግን የግንባታ ዋጋው ቢጨምር ወይም ቢቀንስ ለተቋራጩ የሚከፈለውም በዚያው ልክ (በፐርሰንት ስለሚባዛ) ይለያያል ማለት ነው።

(3) ወጪ እና የተለያየ ክፍያ (Cost Plus Variable Fee)፦ በዚህ ውል አይነት ተቋራጩ በተለያዩ የሥራ አይነቶች የተለያየ ክፍያ የሚያገኝበት ሲሆን ነውል። ለምሳሌ፦ የመሬት ሥራዎችን ሲያጠናቅቅ 10% ክፍያ ለሰራበት የሚፈጸመበት፣ ከመሬት በላይ ላሉ ዋና ዋና ስትራክቸራ ሥራዎች ሲያጠናቅቅ 15% ክፍያ ለሰራበት የሚፈጸመበት፣ ፣ ማጠቃለያ ሥራዎች (Finishing works) ሲያጠናቅቅ 8% ክፍያ ለሰራበት የሚፈጸመበት ሲሆን ወይም በሌላ መንገድ በየደረጃው የተለያየ ክፍያ ከተዋዋለ ነው።

Via ኢ/ር ስዩም መሸሻ

https://t.me/ethioengineers1
👍17👏1💯1
🔶Bridge Design with Midas Civil Software Course Content
      
I) General introduction   ( 1 hr)   
II) Major Drainage Structures (Bridges)     
● Superstructure design    
      ● Slab Bridge Design   (10 hrs)
      ● T-Girder Bridge Design   (15 hrs)
      ● Box Girder Bridge Design   (10 hrs)
  ● Substructure Design    
        ● Abutment Design   (5 hrs)
III)  Minor Drainage Structures (Culverts)     
       ● Box Culvert Design    (10 hrs)

       ● Manuals:     
   - AASHTO LRFD BRIDGE DESIGN SPECIFICATIONS    
   - ERA MANUAL 2013    
        ● Softwares     
   - AutoCAD    
   - Microsoft Excel    
   - Midas Civil

🔸Registration is active!
🔸Class begins on January 10/2024
📲 0712273536 / 0948002510
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍11❤5
🌟ጥያቄ፦ አንድ ተቋራጭ 63,930,000 ብር ቅድመ ግምት የተሰራለትን ፕሮጀችት
ከባለቤቱ ጋር በወጪ የሚሸፈንበት (Cost-reimbursement)" ውል
አይነት ተዋውሎ ግንባታውን በቀጥተኛ ዋጋ ብር 59,322,550.60 እና
በተዘዋዋሪ ወጪዎች ብር 7,250,000 ትርፍና የአገልግሎት ወጪ) ቢያጠናቅቅ የዋጋ ልዩነት የመጣውን 2,642,550,60 ብር የመሸፈን ግዴታ የማን ነው
?

✨ወጪ የሚሸፈንበት ውል (Cost-reimbursement contract)

⏳አንድን ፕሮጀክት ለመገንባት ከተቀመጠው ግምታዊ ዋጋ በላይ
ከሆነ አሰሪው አካል ተጨማሪውን ወጪ የሚሸፍንበት ሁኔታ ደግሞ ከተገመተው ካነሰም ለአሰሪው አካል የሚመለስበት
በተለይ በአጫጭር የጊዜ hፍሎች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ መለዋወጥ የሚስተዋል ከሆነ ተመራጭ የውል ባለው የውል አይነት በግንባታ ሂደት የተመዘገበ ያለበት ሲሆን የሥራው ወጪ ውል ነው።

▶️ይህ የውል ሽግግር የግብአትና የሰው ኃይል ዋጋ

• አይነት ሲሆን በተለይ በፍትሐ ብሔር
ህግ አንቀጽ 3032 (1) ለእንደዚህ አይነት ውሎች እውቅና በመስጠት ተቋራጩ እንዲሰራ ከታዘዘው ሥራ ላይ የተወሰነው እንዲቀነስ) አሰሪው አካል ከጠየቀ የተቀነሰውን የሥራ መጠን ዋጋ ተይዞ ከነበረው ዋጋ ላይ እንዲቀነስለት አሰሪው የሥራ ተቋራጩን የመጠየቅ መብትንም ይሰጣል።

⏺በተመሳሳይ በሥራ መለዋወጥ ምክንያት የሥራ ተቋራጩን ዋጋ የሚጨምርበት ከሆነ የመጠየቅ መበት አለው ተቋራጩ የተጨማሪ ሥራውን ዋጋ ከነ አበሉ እንዲከፈለው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 47526 በዛፍኮ ..የተ.የግ.ማ እና በብሔራዊ መሐንዲሶች ሥራ ተቋራጭ ድርጅት
መካከል ለነበረው ኽርክር “የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የግንባታ ውሎች ውል ከተደረገበት ፎርም አግባብ አይሻሻሉም፣ በዚህ አግባብ የተደረጉ ውሎች በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 3O19-3040 መሰረት በልዩ ህግ የሚገ ከመሆናቸው ባሻገር ውሉም ተፈጸመ የሚባለው ተዋዋዮች ስለሚሰራው ሥራም ሆነ ስለ ክፍያ ከተስማሙ ጭምር እንደሆነ መገንዘብ ይችላል።

▶️አንድ የሥራ ተቋራጭም የሥራ ለውጥ/ጭማሪ (alteration) ከተደረገበት ተጨማሪ ክፍያ ይገባዋል።

⏺የፍትሐ ብሔር ሕጉ 1721 በዚህ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፣ ምከንያቱም ስለማይንቀሳቀስ ውል የፍትሐ ብኄር ሕጋችን ልዩ ሕግ አስቀምጧልና” የሚል ትርጉም ሰጥቷል::

📍በዚህ አግባብ በጥያቄው ላይ ለተመለከተው ምላሹ “ወጪውን አሰሪው አካል ይሸፍናል" ነው።

#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍30❤3🙏1
💥የግንባታ ፕላን ፍቃድ ስለማቅረብ

⏺Submission of Application and Plans

🌟የኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ  ፮፻፳፬/፪ሺ፩ ክፍል ሁለት መሰረት “የግንባታ ሥራ ለማካሄድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለከተማው አስተዳደር ወይም ለተሰየመው  አካል ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

▶️ሕንፃን ለመገንባት የሚቀርብ ማመልከቻ የከተማው አስተዳደር ወይም የተሰየመው አካል ለዚሁ ብሎ ባዘጋጀው ቅፅ መሠረት ሆኖ ይህም  እንደ ሕንፃው ምድብ አይነት ዲዛይንና ሪፖርት የያዘ መሆን አለበት።

▶️ከማመልከቻው ጋር በአዋሳኝ ባሉ ስፍራዎች የሚገኙ ዋና መንገዶችንና የታወቁ ቦታዎችን ስም የሚገልፁ መረጃዎች መቅረብ ይኖርባቸዋል። አመልካቹ ሕንፃ በሚገነባበት ቦታ ወይም በንብረቱ ላይ የይዞታ መብት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል

▶️የሚቀርቡት ሠነዶች በዚህ አዋጅና በሌሎች ሕጐች የተመለከቱት መሟላታቸውን ለማረጋገጥ በበቂ ሁኔታ የተሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል”

🖱According to Proclamation No. 624/2009 “Any person intending to carry out construction shall submit an application to the urban administration or designated organ. The application to carry out construction shall be made on an application form prepared by the urban administration or designated organ and shall consist of a design and report according to the category of building in question.

⏺The application shall be accompanied with a reference to main roads and names of prominent places. The applicant shall submit proof of possession rights to the land or property on which the construction will take place. The documents to be submitted shall be sufficiently complete to determine compliance with this Proclamation and other laws”

#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍18🙏2❤1
💥"ነገረኛ" ሃውልት

ይህ በመዳብ ተለብጦ የተሠራ ቁመታም የመታሰቢያ ሃውልት "African Renaissance Monument" ተብሎ ይጠራል። መገኛውም ከሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ወጣ ብላ በምትገኝና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ዳርቻ ባለች ከተማ ነው።

የዚህ "ነገረኛ" ሃውልት ግንባታ እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም ተጀምሮ በ2010 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የሃውልቱ ቁመትም 52 ሜትርም ይደርሳል።

የሃውልቱ ዲዛይነር ሴኔጋላዊው አርክቴክት ፒየር ጓዲያቢር ሲሆን፣ የሃሳቡ ጠንሳሽ የቀድሞው የሴኔጋል ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ዋዴ ነበሩ፤ ሃውልቱን ያቆመው ደግሞ "Mansudae Overseas Projects" የተባለ የሰሜን ኮሪያ ኩባንያ ነው።

እንደሚታወቀው ሴኔጋል የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ከአዲስ አበባ እንዲነሳ ከሚፈልጉት ጥቂት የአፍሪካ አገሮች ዋናዋ ነች። ብዙም ጥረት ስታደርግ ኖራለች። ከሌሎችም ጋር እየኖረች ነው!!!

#መቼም_ቅኔው_ገብቷችኋል?
👍19❤3
💥የግንባታ ተቋራጭ ስለመሆን

🌟በሀገራችን የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ምዝገባ ሂደት ውስጥ ሁለት አይነት ምድብ ይሰጣል።

A.የሀገር ውስጥ (ሀገር በቀል) ተቋራጮች እና
B. የውጪ ሀገር (ከውጪ ሀገራት የመጡ) የግንባታ ተቋራጮች ሲሆኑ በሀገሪቱ የግንባታ ሥራ ተቋራጭነት ለመሳተፍ የሚያስችላቸው የሚከተለው መስፈርት ነው።

🖱A. የሀገር ውስጥ ተቋራጮች – local contractors

⏺የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች በመስፈርቱ መሠረት ማሟላት በሚችሉት ደረጃ ለመመዝገብ፦ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ የአገልግሎት ንግድ ፈቃድ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር፤ ፎርም መሙላት /ፎርሙ በተቋራጩ ወይም በወኪሉ ሊሞላ ይችላል። ፎርሙ በወኪሉ ከተሞላ የውክልናውን ደብዳቤ አብሮ መያያዝ አለበት/፣ የአገልግሎት ክፍያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በድርጅታቸው ሠራተኛነት የሚቀጥሯቸው ባለሙያዎቻቸው ደግሞ፦ ከሥራና ከተማ ልማት የተሰጣቸውን የታደሰ የባለሙያ ሠርተፊኬት፣ ባለሙያው ቀድሞ ሲሠራበት ከነበረው ድርጅት የተሰጠው የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እና በማኀበራዊና ሲቪል ጉዳይ ፎርማት መሠረት የተዘጋጀ ባለሙያ የቅጥር ውል ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተሽከርካሪ እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን በተመለከተ፦ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እና ሚክሰርና የእጅ መጠቅጠቂያ መሣሪያዎች የተገዙበት ደረሰኝ ያስፈልጋቸዋል።


https://t.me/ethioengineers1
👍18❤3
🖱💥 የመንግሥት አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች አንድን ግንባታ ለተቋራጭ ለመስጠት ጨረታ የማውጣት ግዴታ አለባቸው❓

🌟
አንድን ውል ለመመስረት ተዋዋይ አካላት በሦስት አይነት መንገድ የውል ግቢ ጥሪ (Invitation to bid)
ሊቀርብላቸው ይችላል።

⏺እነዚህም መንገዶች ከአንድ ብቁ ተዋዋይ ጋር ድርድር (Negotiation)፣
የተመረጡ ጥቂቶችን የመጋበዝ (Short listed) እና ከፍት ጨረታ የማውጣት (Open Tendering)
መንገድ ናቸው።

▶️ድርድር (Negotiation የተባለው መንገድ ተግባራዊ የሚሆን አንድ ዮፕሮጀክት ባለቤት ግንባታውን ሊያከናውን ይችላል ተብሎ ከሚታመንበት አንድ ተቋራጭ ጋር የብቃት ድርድርን ተመርኩዞ የሚከናወን ውል አልያም ደግሞ ፕሮጀክቱን ተቋራጮች በአካባቢው የማይገኙ ከሆነ የሚመረጥ ነው ይህ መንገድ የሚስተዋል ሲሆን የግንባታው ባለቤት የሚያምንበትን አንድ ተቋራጭ
የተመረጡ ጥቂቶችን የመጋበዝ (Short listed) የሚባለው ደግሞ በተመረጡ ወይም በፕሮጀክቱ አይነት ላይ የቀደመ ልምድ ያላቸው ዝርጋታ፣ ግድብ እና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ግንባታ ላይ ተግባራዊ

📍(ለምሳሌ፦ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ጠቅላላ ተቋራጭ)፣ ወይም ላይ ልምድ ያላቸው፣ በባቡር ሐዲድ ሥራ ላይ ልምድ ተለይተው ሊጠሩ የሚችሉ ሲሆን ይህ የመለየት ሥራ የማውጣት (Open Tendering) የሚባለው የሚችል ጨረታ ነው።

✨የሚያደርገው የዋጋ እና ሊያከናውኑ የሚችል ብቁ ብዙ ጊዜ የግል ግንባታ ላይ
የሚደራደር ሲሆን ነው።

⏳አንድ ፕሮጀክት ሊከናወን የሚችለው
ሲሆን ነው። ብዙ ጊዜ የባቡር ሀዲድ
የሚደረግ ሲሆን ተቋራጮቹን በደረጃ
በፕሮጀክት አይነት (በትላላቅ ግድብ ግንባታ ያለው ...) አልያም እገሌ፣ እገሌ እና እገሌ በሚል Short listed መንገድ ይባላል።

⚡️ክፍት ጨረታ ማንኛውው የንግድ ፍቃድ ያለው አካል ሊሳተፍበት ደግሞ
Bount በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 3140 አካላት ውል እንዲዋዋሉ ፍቃድ የተሰጠ የሚገደዱ ናቸው ማለት ግን አይደለም።

✨መመስረት ያለባቸው በጨረታ 3141 ድንጋጌዎች መሰረት የመንግሥትም ይሁኑ የግል እና በጀት እንዲበጀት የተደነገገ ቢሆንም ወደውል እንዲገቡ ቢሆንም ግን የመንግሥት አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ውል መነሻነት ስለመሆኑ በአዋጅ ዉጥር 649 የተደነገገ ነው።

⏺ይህ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 ሥር በግልጽ ተመልክቷል ምክንያቱም አንድን
ፕሮጀክት ለማከናወን በቂ አቅም ያላቸው ሀገር በቀል እና ዓለማቀፍ ተቋራጮች
ባሉበት ሁኔታ የመንግሥትን ግንባታ ያለጨረታ መስጠት የማይቻል እና የመንግሥትን በጀት እንቅስቃሴ ኦዲት ለማድረግ ጨረታ ተመራጭ መንገድ ስለሆነ ነው።

▶️ጨረታው ብሔራዊ (National) ወይም ዓለምአቀፋዊ (international) ሊሆን ይችላል እንጂ ጨረታ ግድ ነው።
በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ብቁ ተቋርጮች እንደሌሉ ከተረጋገጠ እና ልዩ ፍላጎትና አቅም የሚጠይቅ ፕሮጀክት ከሆነ ግን እንደ ፕሮጀክቱ ጸባይ ሁሉም የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተወያይተው እና ወስነውበት መንግሥት ድርድር (Negotiation) መንገድን ተጠቅሞ በድርድር
ብቻ ውል ሊፈጽም የሚችልበት አግባብ ይኖራል።

📎በእርግጥ ጨረታ መውጣቱ የሂደቱን አግባብነት እንደማረጋገጫ አንድ መንገድ ይሆናል እንጂ በጨረታ ውድድር ተጫራች ስለተመረጠ እና አሸናፊነቱ ስለተገለጸ ብቻውን የግንባታ ውል እንደትፈጸመ አይቆጠርም።


#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍13❤3
💥የግንባታ ደረጃዎች

🌟Building Construction Classification"

▶️በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ የመጀመሪያ እና የማጠናቀቂያ ቀነ ገደብ እንደ ግንባታዎቹ ደረጃ ተለያይቶ ተቀምጧል (በሚቀጥለው ክፍል ይዳሰሳል)።

⏺ለዛሬው የግንባታ ደረጃዎ አከፋፈልን እንመልከት።

📍የሀገራችን የኮንስትራክሽን ሕግ ግንባታዎችን በሦስት (3) ዋና ዋና መደብ ይከፍላቸዋል።

✨እነሱም፦ አንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች፣ መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች፣ እና ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ናቸው።

📎Construction start and completion dates on leased land vary depending on the stage of construction (will be discussed in the next section). Let's take a look at the distribution for build level. Our country's construction law divides buildings into three (3) main categories. They are: small scaled constructs, intermediate-scale constructs, and high-level constructs.

☄A. አነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች (Small scale constructions)

⏺አነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት እስከ ሦስት ወለል ያላቸው የተናጠል መኖሪያ ቤቶች (private residential building) ወይም እስከ ሦስት ወለል ያላቸው የሕዝብ መጠቀሚያ ያልሆኑ ሌሎች ግንባታዎች ወይም የይዞታ ስፋቱ እስከ 250 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነቡ ግንባታዎች ናቸው። Small-scale buildings are private residential buildings with up to three floors or non-public buildings with up to three floors or buildings with a coverage area of up to 250 square meters.

☄B. መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች (Intermediate scale constructions)

⏺መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት 5 ወለል እና ከዚያ በታች የሆኑ የሕዝብ መጠቀሚያ ሕንጻዎች፣ ወይም የይዞታ ስፋቱ ከ251 ካሬ ሜትር እስከ 5000 ካሬሜትር ይዞታ ላይ የሚገነቡ ግንባታዎች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት ባለ 4 እና ባለ 5 ወለል የሆኑ ግንባታዎች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት በአንድ ጊዜ እስከ 80 ነጠላ ቤቶች የያዙ ግንባታዎች፣ ወይም የሕዝብ መጠቀሚያ ያልሆኑ ሌሎች ወለላቸው ባለ 4 እና ባለ 5 የሆኑ ግንባታዎች፣ ወይም ለትምርት ተቋማት እስከ 2ኛ ከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃልሉ ግንባታዎች፣ ወይም ለቤተ መጻሕፍትና ለሁለገብ አዳራሾች እስከ 500 ሰው የሚይዙ ግንባታዎች፣ ለጤና ማዕከል እስከ ከፍተኛ ክሊኒክ የሚያጠቃልሉ ግንባታዎች፣ ለስፖርት ሜዳዎች እና ለስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት እስከ 500 ሰው የሚይዙ ግንባታዎች፣ ወይም በአጠቃላይ የወጪ ግምታቸው እስከ ብር አምስት ሚሊዮን (5,000,000) ብር የሆኑ መካከለኛና አነስተኛ የማምረቻ እና ማከማቻ ተቋማትን ያጠቃልላል።

✨Mid-level buildings are public buildings with 5 floors and below, or buildings with an area of 251 square meters to 5000 square meters, or residential buildings with 4 or 5 floors, or residential buildings with up to 80 single houses at a time. Buildings, or other non-public buildings with 4 and 5 floors, or buildings for educational institutions up to 2nd high level, or buildings for libraries and multi-purpose halls that can hold up to 500 people, buildings for health centers up to senior clinics, sports fields and sports facilities Centers include buildings that hold up to 500 people, or medium and small manufacturing and storage facilities with a total cost estimate of up to five million (5,000,000) Birr.

☄C.  ከፍተኛ ግንባታዎች (High scale constructions)

⏺ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት ባለ ስድስት (6) ወለል እና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ግንባታ፣ ወይም የይዞታ ስፋቱ ከ5000 ካሬሜትር ቦታ በላይ የሆነ ይዞታ ላይ ለሚገነቡ ወይም በዓለም በሀገር እንዲሁም በከተማ አቀፍ ደረጃ ለሚገነቡ የትራንስፖርት የመናኸሪያ ተቋማቶች፣ ወይም ትላልቅ የዲፕሎማቲክ ተቋማት የሚገነቧቸው ግንባታዎች፣ ወይም ከላይ በአነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ከተጠቀሱት ውጪ ያሉ ግንባታዎችን ያጠቃልላል።

✨High-rise buildings are any building with six (6) floors or more, or buildings with an area of more than 5,000 square meters, or for transportation hub facilities that are built at the national and city levels, or large diplomatic facilities, or small buildings above. And the intermediate level includes constructions other than those mentioned.


https://t.me/ethioengineers1
👍25❤5
የብረት ዋጋ አወሳሰን

በዓለም አቀፍ ደረጃ የብረት ጥሬ ዕቃዎች እና የብረት ምርቶች ባላቸው ፈጣን የዋጋ መለዋወጥ ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የብረት ምርቶችን በገቡበት fcወቅት በተደራጀ ወቅታዊ ዋጋ ከማስተናገድ አንፃር የዋጋ አወሳስን ሂደት አሰራር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡  በዚሁ መሰረት፡-

1.  ማንኛውም አዲስ ዲክላራሲዮን መዝግቦ ለመስትንግዶ የሚቀርብ አስመጪ ሰነድ ለዕቃ አወጣጥ የስራ ክፍል ቀርቦ ተቀባይነት ባገኘበት ቀን (Risk selective Date) በአስመጪው የቀረበው የግብይት ዋጋ በጉምሩክ የዋጋ መረጃ ስርአት (ECVS-G2, IP MODULE) በአስራ አምስት ቀኑ ከተደራጀው የመነሻ ዋጋ አንሶ ከተገኘ የዕቃውን ዋጋ በዋጋ መረጃ ስርዓት ተደራጅቶ የሚገኘውን ዋጋ እየተወሰደ አግልግሎት ይሰጣል፤

2.  እቃው በአንድ ጭነት ተጠቃሎ የማይገባ ወይም በክፍልፋይ የሚገባ ሲሆን ቀድሞ የገባው ጭነት የተስተናገደበት የግብይት ዋጋ ወይም የመነሻ ዋጋ በቀጣይ የገባው የጭነት ትራንዚት ባጠናቀቀበት ቀን (Transit validation Date) በዋጋ መረጃ ስርዓት ከተደራጀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ በገባው የዕቃ መጠን ልክ በጉምሩክ የዋጋ መረጃስርዓት በየአስራ አምስት ቀኑ ከተደራጀው ዋጋ ተወስዶ የዲክላራሲዮን ማሻሻያ በማድረግ ይስተናገዳል፤

3.  በስሪት አገራቸው በቀጥታ ተደራጅተው የማይገኙ የብረት ምርቶች በሚመጡበት ወቅት በጉምሩክ የዋጋ መረጃ ስርዓት (ECVS-G2, IP MODULE) በተመሳሳይ ዕድገት ደረጃ ባሉ የስሪት አገሮች መሰረት እንዲስተናገዱ ይደረጋል፤

4.  የብረት የዋጋ መስተንግዶ በጉምሩክ የዋጋ መረጃ ስርዓት የሚደራጁ ዋጋዎችን መሰረት በማድረግ በጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ ማስከፈያ መመሪያ ቁጥር 158/2011 አንቀፅ 19(1) መሰረት በመነሻ ዋጋ መስተንግዶ እንዲሰጥ ይደረጋል፤

በመሆኑም ወደ ሀገር የሚገቡ ብረት እና ብረት ነክ ምርቶች መስተንግዶ በየአስራ አምስት ቀኑ በሚደራጁ የዋጋ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ይስተናገዳሉ፡፡

(ገቢዎች ሚኒስቴር)


https://t.me/ethioengineers1
👍12❤2
❤️DEAR ETHIO CONSTRUCTION FAMILIES
here is the link to boost our channel👇

https://t.me/ethioengineers1?boost
❤7🔥1🙏1
💥የግንባታ ፍቃድ አጠያየቅ እና የወሰንተኛ ጉዳይ

🚧የማሻሻያ፣ የመጠቀሚያ ፈቃድ፣ ጊዜያዊ ግንባታ ወይም የማፍረስ ሥራ ለማከናወን የሚቀርብ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ ሲኖር በተናጠል በተዘጋጀላቸው (ማለትም  ለአዲስ ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ግንባታ ቅፅ፣ ለግንባታ እድሳት ፈቃድ ቅፅ፣ ለግንባታ ማፍረስ ፈቃድ ቅጽ፣ ለአገልግልት ለውጥ ቅጽ፣ ለጊዜያዊ ግንባታ ቅጽ) በመሙላት የግለሰብ ከሆነ በአመልካቹ ተፈርሞ፣ በመንግስታዊ፣ በሕዝባዊ እና የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተያዘ ወይም የሚተዳደር ከሆነ በኃላፊው ተፊርሞ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት ጥያቄው መቅረብ ይኖርበታል።

🌟ማንኛውም የግንባታ ፈቃድ ጠያቂ ስለወሰንተኞቹ ትክክለኛ መረጃ በወሰንተኛ ግንባታ መግለጫ ቅጽ ላይ ወሰንተኛውን በማስሞላትና በማስፈረም ማቅረብ አለበት፣ ቅፁን ለመሙላት ፈቃደኛ በማይሆን ወሰንተኛ የከተማ አስተዳደሩ ቅፁን የማስሞላት ሃላፊነት አለበት።

▶️ወሰን ላይ የሚገነባ የምግብ ማብሰያና መሰል አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ግድግዳ የእሳት ቃጠሎን በተሻለ ሁኔታ መከላከል በሚችል ድፍን የግድግዳ ቁሳቁስ መገንባት አለበት። ጭስ እና እንፋልት ወደወሰነተኛ መውጣት የለበትም።

⏺በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ አንድ ዓይነት ስታንዳርድ ፕላኖች ያላቸው ግንባታዎች የየራሳቸው የግንባታ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።

▶️ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማካተት ይኖርበታል፣ ወለልና በላይ ያለው ማንኛውም ግንባታ (የምድር በታች ወለል ቢኖረውም ባይኖረውም) ከወሰን ሁለት ሜትርና ከዚያ በታች ተጠግቶ የሚሰራ ከሆነ በቅድሚያ የወሰን ላይ ግንባታ ቅጽ መሙላትና ስምምነት ማግኘት ይኖርበታል፣ ለፈቃድ የሚቀርበው ስትራክቸራል ዲዛይን የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መዋቅር ይዘት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፤ የሚቀርበው የዲዛይን ሠነድ የወሰንተኛውን ነባር ህንፃ መጠን ለምሳሌ የኃይል ሚዛን (Load) ከግምት ያስገባበት አግባብ ማመልከት አለበት፣ በወሰንተኛ ነባር ግንባታ ደህንነት ላይ ምንም አይነት መናጋት እንዳይፈጠር በቁፋሮና በግንባታ ሂደት መወሰድ የሚኖርበትን የሚያሳይ የጥንቃቄ ንድፍ ለፍቃድ ከሚቀርበው ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት።

▶️አየር ማስገቢያ ሳይኖረው ብርሃን ብቻ የሚያስገባ ግንባታ ወሰን ላይ ለመሥራት ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁና አሳልፈው በማያሳዩ ውፍረታቸው ከ5 ሳ.ሜ የማያንስ የመስታወት ግርግዳ መጠቀም ይቻላል።

▶️ይህም በሚቀርበው ዲዛይን ላይ በግልጽ መጠቀስ ሲኖርበት ወሰን ላይ የተሰራ ከሆነ ወሰንተኛው እንደማንኛውም ድፍን የግድግዳ አካል አስጠግቶ ሊሰራበት ስለማይከለከል የብርሃን ማስገቢያ መስፈርት ለሚጠየቅበት ተጨማሪ ወይም አማራጭ የብርሃን ምንጭ ማመልከት አለበት።

⏺ማንኛውም ሰው ግንባታውን እስከ ወሠን አስጠግቶ ማከናወን ይችላል ሆኖም ወሠን ላይ ለመገንባት ያቀደ ሰው በአዋሳኙ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርገውን የመከላከያ ዘዴዎች ለአጎራባቹ ማሳወቅ ይኖርበታል።

▶️ግንባታው ተጀምሮ እስኪጠናቀቀ ድረስ በአጎራባቹ አደጋና ችግር በማያስከትል ሁኔታ መከናወን አለበት። በማንኛውም ጊዜ ወሰንተኛው ግንባታውን እንዲከታተል መፍቀድ   አለበት።

▶️በማንኛውም የግንባታ ወቅት ለሚፈጠር ችግር ገንቢው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል።

▶️በአዋጁ፣ በደንቡ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባረቀቀው የሕንጻ መመሪያ (Building Directives) እና በሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነድች ላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ያላሟላ የግንባታ ፈቃድ ጥያቄ በግንባታ መጠየቂያ ቅጽ ላይ በተመለከተው ቦታ ያልተሟላበትን ምክንያት በመግለፅ ተመላሽ መደረግ ይኖርበታል።


https://t.me/ethioengineers1
👍21❤3
💥የህንፃ የራሱ ክብደት (self weight ) አገልግሎት ክብደት ( live load) መሬት ከደረሰ በሁዋላ በምስሉ እንደምትመለከቱት ሶስት ጎን ቅርፅ ተሰርቶ የፈር ጠንካራ አካል ይደረሳል።

🚧በጥንቃቄ ካልተሰራ የሚያመጣው አደጋ የከፍ ነዉ።

https://t.me/ethioengineers1
👍14❤1🤔1
💥ስለ “Specification” ሰነድ

☄በ'FIDIC multilateral Development Bank Harmonized edition 2010  ሕግ መሰረት “Specification” የተባለ ሰነድ በግንባታ ውል ውስጥ መካተት እንዳለበት ግልጽ ነው።

▶️ስለ ሰነዱ ምንንነት “Specification” means the document entitled specification, as included in the Contract, and any additions and modifications to the specification in accordance with the Contract. Such document specifies the Works ይላል።

⏺ነገር ግን በሀገራችን አብዛኞቹ የግንባታ ውሎች (contract documents) ውስጥ የሚገኝ አይደለም።

⏺ስለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር፣ ስለሚጠቀሙት የግንባታ ግብአት ዝርዝር ማብራሪያ (የምርት አይነት፣ ልኬት፣ መጠን፣ ጥራት)፣ ስለሚያስፈልገው የሰው እና የማሺነሪ ዝርዝር የሚያስረዳ የውል ሰነድ አካል ነው።

⏺ይህ ሰነድ በብዙዎቹ ውሎች ውስጥ የተለመደ አለመሆኑ የግብአት (Material) ጥራት ጥያቄ፣ የጊዜ መጓተት ቅሬታ እና የተጨማሪ ዋጋ ክርክር አያስነሳ ይገኛል።


https://t.me/ethioengineers1
👍23❤1
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

መልካም በዓል!


https://t.me/ethioengineers1
❤17👍1
👉የአሸዋ ደለል መጠን (Silt Content)

☄በአርማታ (concrete)፣ ልስን (plastering)፣ ወለል ጭረሳ (floor screed) እና የአሸዋ ግርፍ (rendering) ሥራዎች በብዛት የምንጠቀምባቸው ሦስት የግንባታ ግብአቶች ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር (Cement, Sand/Fine aggregate & Coarse Aggregate) ናቸው።

☄ሲሚንቶ ዋናው ዓላማው የግንባታ ግብአቶች እስር በእርሳቸው ያላቸውን የመጣበቅ/የመጣመር ሂደት ማጠናከር (As binding agent) ሲሆን የአሸዋ ድርሻ የውስጥ ለውስጥ (air voids) መሙላትና ማእከላዊ የሆነ ማጣበቅና ጥንካሬ መስጠትን ማገዝ ነው።

☄የጠጠር ዋናው ድርሻ ደግሞ የኮንክሬት ክፍሎችን ጥንካሬ መስጠት ነው። 

🖱አሸዋ (Fine aggregate) ማእከላዊ ወሳኝ ግብአት ተብሎም ይታወቃል። በትላልቅ አውሮፓውያን እና በሩቅ ምስራቅ ሀገራት በተለይ በህንድ እና በቻይና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው እና እንደሲሚንቶ የአሸዋ ማጣሪያ ፋብሪካ ጭምር የተገነባለት ግብአት (material) ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የአሽዋ መሰረታዊ የቤተሙከራ  ማረጋገጫ ምዘናዎች ውስጥ ቀላሉ ነገር ግን ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የደለል ይዘቱ (silt content) ነው። /ደለል ማለት በጣም የላመ ወይም የደቀቀ ዱቂታማ የአፈር አይነት ነው/። አሸዋ በተቻለ መጠን ምንም የደለል ይዘት አንዳይኖረው ይመከራል። ደለላማ የአፈር መጠን በአሸዋ ውስጥ በብዛት ካለበት አሸዋው ጥቅም ላይ ሲውል የአርማታ ባህርይን ወደ ጭቃማ ጸባይ ይቀይራል ማለት ነው። ደለላማ የአፈር ክፍል አሸዋው ማንኛውንም የቤተሙከራ መስፈርት (laboratory tests) በብቃት እንዳያልፍ ያደርገዋል። አርማታ ጥንካሬ እንዳይኖረው እና ልስን በቀላሉ እንዲፈራርስ የሚያደግ ነው።

✨ደቃቅ አፈር/ደለል (silt content) የሚባለው እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ልዩ ሀሳቦች የሚነሱበት ቢሆንም በ'ASTM, AASHTO, IS እና በሌሎች መመሪያዎች ላይ እንደተጠቆመው በብዛት ከ75 micro-millimeter sieve በታች የሚወርደውን ክፍል ነው።

✨በመሆኑም አሸዋ በውስጡ ከስድስት በመቶ (6%) በላይ ደለላማ አፈር (silt content) እንዲኖረው አይፈቀድም። በግንባታ ቤተሙከራዊ የግብአት መስፈርቶች (Experimental criterion) መሰረት አሸዋ ከ6% በላይ ደቃቅ አፈር አንዳለበት ከታወቀ ሁለት አይነት ርምጃ ይወሰዳል።

⏺አንደኛው:- አሸዋውን በአሸዋ ወንፊት መንፋት (sieving) ሲሆን (ሁለተኛው) አሸዋውን አስወግዶ (rejection) ሌላ መስፈርቱን የሚያሟላ አሸዋ መጠቀም ነው።

🌟በብዙ የሀገራችን የግንባታ ቦታዎች ላይ አሸዋ በቁም ወይም በአግዳሚ ወንፊት ሲነፋ የሚስተዋለው ይህንን የደለል መጠን ለመቀነስ እና ከአሸዋ ቅርጽ መጠን በላይ (Above determined sieve size of sand) የሆነ ጠጠራማ ክፍልን (aggregated particles) ለመለየት ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍25👏3❤1😍1