SMH General Construction
22.5K subscribers
1.48K photos
45 videos
293 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
👉የአሸዋ ደለል መጠን (Silt Content)

☄በአርማታ (concrete)፣ ልስን (plastering)፣ ወለል ጭረሳ (floor screed) እና የአሸዋ ግርፍ (rendering) ሥራዎች በብዛት የምንጠቀምባቸው ሦስት የግንባታ ግብአቶች ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር (Cement, Sand/Fine aggregate & Coarse Aggregate) ናቸው።

☄ሲሚንቶ ዋናው ዓላማው የግንባታ ግብአቶች እስር በእርሳቸው ያላቸውን የመጣበቅ/የመጣመር ሂደት ማጠናከር (As binding agent) ሲሆን የአሸዋ ድርሻ የውስጥ ለውስጥ (air voids) መሙላትና ማእከላዊ የሆነ ማጣበቅና ጥንካሬ መስጠትን ማገዝ ነው።

☄የጠጠር ዋናው ድርሻ ደግሞ የኮንክሬት ክፍሎችን ጥንካሬ መስጠት ነው። 

🖱አሸዋ (Fine aggregate) ማእከላዊ ወሳኝ ግብአት ተብሎም ይታወቃል። በትላልቅ አውሮፓውያን እና በሩቅ ምስራቅ ሀገራት በተለይ በህንድ እና በቻይና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው እና እንደሲሚንቶ የአሸዋ ማጣሪያ ፋብሪካ ጭምር የተገነባለት ግብአት (material) ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የአሽዋ መሰረታዊ የቤተሙከራ  ማረጋገጫ ምዘናዎች ውስጥ ቀላሉ ነገር ግን ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የደለል ይዘቱ (silt content) ነው። /ደለል ማለት በጣም የላመ ወይም የደቀቀ ዱቂታማ የአፈር አይነት ነው/። አሸዋ በተቻለ መጠን ምንም የደለል ይዘት አንዳይኖረው ይመከራል። ደለላማ የአፈር መጠን በአሸዋ ውስጥ በብዛት ካለበት አሸዋው ጥቅም ላይ ሲውል የአርማታ ባህርይን ወደ ጭቃማ ጸባይ ይቀይራል ማለት ነው። ደለላማ የአፈር ክፍል አሸዋው ማንኛውንም የቤተሙከራ መስፈርት (laboratory tests) በብቃት እንዳያልፍ ያደርገዋል። አርማታ ጥንካሬ እንዳይኖረው እና ልስን በቀላሉ እንዲፈራርስ የሚያደግ ነው።

✨ደቃቅ አፈር/ደለል (silt content) የሚባለው እንደ ፕሮጀክቱ አይነት ልዩ ሀሳቦች የሚነሱበት ቢሆንም በ'ASTM, AASHTO, IS እና በሌሎች መመሪያዎች ላይ እንደተጠቆመው በብዛት ከ75 micro-millimeter sieve በታች የሚወርደውን ክፍል ነው።

✨በመሆኑም አሸዋ በውስጡ ከስድስት በመቶ (6%) በላይ ደለላማ አፈር (silt content) እንዲኖረው አይፈቀድም። በግንባታ ቤተሙከራዊ የግብአት መስፈርቶች (Experimental criterion) መሰረት አሸዋ ከ6% በላይ ደቃቅ አፈር አንዳለበት ከታወቀ ሁለት አይነት ርምጃ ይወሰዳል።

⏺አንደኛው:- አሸዋውን በአሸዋ ወንፊት መንፋት (sieving) ሲሆን (ሁለተኛው) አሸዋውን አስወግዶ (rejection) ሌላ መስፈርቱን የሚያሟላ አሸዋ መጠቀም ነው።

🌟በብዙ የሀገራችን የግንባታ ቦታዎች ላይ አሸዋ በቁም ወይም በአግዳሚ ወንፊት ሲነፋ የሚስተዋለው ይህንን የደለል መጠን ለመቀነስ እና ከአሸዋ ቅርጽ መጠን በላይ (Above determined sieve size of sand) የሆነ ጠጠራማ ክፍልን (aggregated particles) ለመለየት ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍25👏3❤1😍1
💥በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የዐድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ውስጣዊና ውጫዊ ገፅታ በምስል

https://t.me/ethioengineers1
👍21❤4
ጋቢዮን - Gabion

የጋቢዩን ግንባታ አሠራር በኢትዮጵያ በአግባቡ ተጠቅመንበታል ለማለት አይቻልም። በእርግጥ በአንዳንድ ቦታዎች የአፈር ናዳን እና ጎርፍን ለመከላከል ጋቢዩን ጥቅም ላይ ሲውል ለመመልከት ችለናል።

ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ሰፊ የሠራተኛ ኃይል በሚገኝበት፣ የሲሚንቶ ምርት ውድ በሆነበት እና ለጋቢዩን ፕሮጀክት የሚሆን የወንዝ ዳርም ሆኑ የተለያዩ የድንጋይ አይነቶች እንደ አፈር በሚገኙበት አገር ጋቢዩን በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ አለመዋሉ ያስቆጫል።

የጋቢዩን ግንባታ አሠራር ዘዴ ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ ነው። ከተማን በቀላሉ ለማስዋብ ከጋቢዩን የቀረበ ሌላ የግንባታ አይነት ሊኖር አይችልም። ጋቢዩን አጥር ይሆናል። ጋቢዩን የመወጣጫ ደረጃ ለመሥራትና መቀመጫዎችን ለመገንባት ተመራጭ ነው።

በገጠሪቱ የአገራችን ክፍል ለተፋሰስ ሥራዎችና ለመንገድ እንዲሁም ለመስኖ ፕሮጀክቶች ጋቢዩን የልብ አድርስ ነው። ከኮብልስቶን በላይ ብዙ የሠራተኛ ኃይል ሊሠማራበት የሚችል የግንባታ ዘርፍ ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍29❤5👏2
2016 2ND QUARTER CONSTRUCTION WORKS (ONLY DIRECT COST).pdf
20.1 MB
🏷በ2016 ዓ.ም የ ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።


https://t.me/ethioengineers1
👍30❤7