SMH General Construction
22.5K subscribers
1.48K photos
45 videos
293 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥የፎርምወርክ ማፍረሻ ቀነ ገደብ

💫በቀድሞው የሀገራችን የሕንጻ እና መንገድ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ባለሥልጣን (Building and Transport Construction Design Aucthority – BaTCoDA Specification) ላይ በቁጥር 03244  ላይ እንደተመለከተው  ፎርምወርክ የሚነሳበት (የሚነቀልበት/የሚፈርስበት) ቀንን (Formwork Removal) በተመለተ እንደሚከተለው አስቀምጧል።

⏺አቀባዊ የአርማታ ግድግዳዎች ( shear wall)፣ አምዶች (columns) እና aግዳሚ ጋንዴላዎች ወይም ምሰሶዎች (beams) = ከ16 ሰዓታት በኋላ

⏺የወለል አርማታ ሙሌት የታችኛው አልጋ (slab soffit) = በ21 ቀናት ውስጥ

⏺የወለል አርማታ የጎንዮሽ ማፈኛ (props of slab) = በ14 ቀናት

⏺የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የታችኛው አልጋ (soffit of beam) = 21 ቀናት

⏺የአግዳሚ ጋንዴላ/ምሰሶ የጎንዮሽ ማፈኛ (Props of beam) = 14 ቀናት

🖱ማሳሰቢያ፦ ለተዘረዘሩት የአርማታ ስትራክቸር ክፍሎች (Concrete skeletons) የተጠቀሱት ቀናት "ቢያንስ ቢያንስ" ተብሎ የተቀመጠ ዝቅተኛው የጊዜ ገደብ ነው።


https://t.me/ethioengineers1
👍26❤2👏1
💥አነጋጋሪው የኮተቤ መንገድ ዲዛይን እና አደጋዎቹ!!

አነጋጋሪ የሆነው የኮተቤ መንገድ ዲዛይን በርካታ ተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ እያስከተለ ነው !!

Source driving in addis

https://t.me/ethioengineers1
👍19❤5🤔5
💥የቤቶች ገበያ እንዴትና ወዴት?

ቤትን ለትርፍ መግዛት በዚህ ወቅት ይመከራል ወይ? የሪል እስቴት ዋጋ በእውነት እየቀነሰ ነው ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ሰሞኑን እየተጠየቅን ካለናቸው ውስጥ ሚዛን የሚደፉት ናቸው።

መልሱን በውይይት እንጂ በጽሁፍ አሳጥሮ ለማስረዳት በእውነቱ ከባድ ነው ።ምክንያቱም ብዙ ታሳቢዎችን አይቶ ገምግሞ መወሰን የሚፈልግ ጥያቄ ስለሆነ ነው።
አሁን ያለውን የሪል እስቴት የገበያ ሁኔታ ለመረዳት የሃገራችንን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታን ከ ሪል እስቴት ቢዝነስ ተፈጥሯዊ ዑደት (Real Estate Cycle ) ጋር አገናዝቦ ማየት ለውሳኔ ይረዳል ብዬ አምናለሁ።

በተጨማሪም የሃገራችን የሪል እስቴት ገበያ ትኩረት ያደረገው የተወሰነውን የማህበረሰብ ክፍል መሆኑ ጠቅለል ያለ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ከባድ ስለሚያደርገው ግምገማውን ገበያው ታሳቢ አድርጎ ይሰራበት ከነበረው የህብረተሰብ ክፍል አንጻር ብቻ ለይቶ መመልከት ይቻላል።

ከታች የተያያዘው የ Real Estate cycle  እንደሚያሳየው በዚህ ወቅት ብዙ ቤቶች እየተገነቡ ያሉበት ፣ በርካታ አልሚዎች ገዢ የተቸገሩበት ፣ ብዙ ቤቶች ለገበያ የቀረቡበት፣  ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አልሚዎች ዘርፉን እየተቀላቀሉ መሆኑ፣ አዳዲስ የግብይት አማራጮች እየመጡበት ያለበት ወቅት ላይ በመሆኑ በሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዑደት ላይ ሶስተኛው ደረጃ ማለትም Hypersupply (phase 3) ላይ ይገኛል ብሎ መውሰድ ይቻላል ።

በዚህ ወቅት ገበያው ለተጠቃሚ ገዢዎች ምቹ የሚባል (Buyyers Market) የሚባል ሲሆን በቤት ግብይት ላይ ተሰማርተው እየገዙ ጥቂት አቆይተው በመሸጥ ብር ለሚያገላብጡ ለአትራፊ ነጋዴዎች ግን እንዲገዙ የሚመከርበት ወቅት አይደለም ምክንያቱም ዋጋው እየቀነሰ ይሄዳል ተብሎ ስለሚገመትና የገዙትን በቶሎ ሸጠው ተመልሰው ገንዘባቸውን ከነትርፉ ያገኙታል ተብሎ ስለማይጠበቅ።

የሪል እስቴት ዋጋ መቀነስም የተረጋገጠና በቀጣይም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችንና የኢኮኖሚውን ሁኔታ ታሳቢ ያደረጉ ዲዛይኖችን በማቅረብ፣ ወጪ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ በመንግስት እየተሞከሩ ያሉ 70/30 ዓይነት (PPP) ፕሮጀክቶች መተግበር መጀመር ሌሎችም የፖሊሲ አማራጮችን ጨምሮ ገበያው የሚያስገድዳቸው የተለያዩ አስቻይ የክፍያ አማራጮችን በመፍጠር የሚቀጥል እንደሚሆን ይገመታል አካሄዱም ይታያልም የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዑደቱም ይህንኑ ያሳያልንና መቀነስ ይቀጥላል።

በዚህ ወቅት ቤት ግብይት ውስጥ ለገዢዎች በርካታ አማራጮች በመኖራቸው ገዢዎች ወደግብይት በሚገቡበት ወቅት ውጤታማ ግብይትን ለማከናወን በዘርፉ ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችን በማማከር ይገበያዩ ዘንድ ይመከራል። አልሚዎችም ከተለመደው የተኮራረጀ አሰራር ተላቀው በሙያ የተደገፍ አዋጪነቱ የተረጋገጠለት ፈጠራ የታከለበት ኢንቨስትመንት ውስጥ ሊገቡ ይገባል። የሽያጭ ባለሙያዎችም ጊዜው የእነሱን ሙያ እጅግ የሚፈልግ መሆኑንና ለገዢዎች ያደላ መሆኑ አውቀው የግብይት ሂደታቸው ከገዢዎች ፍላጎት የሚነሳ ሊያደርጉት ይገባል።
Desalegn Kebede


https://t.me/ethioengineers1
👍30❤3😍2
💥ራሱን የሚጠግን ሕያው ኮንክሪት

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን የሚያሳድጉና የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየመጡ ነው፡፡ በዓለማችን ላይ ታዋቂው የሮማዊያን ፓንታዮን ግንባታ ከ2000 ዓመት በፊት ከተገነባበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ኮንክሪትን ለግንባታ ሂደት በስፋት እየተጠቀምነው እንገኛለን፡፡

ሁሌም ቢሆን አንድ የግንባታ ኮንክሪት ምንም ያህል በጥንቃቄ ቢሠራም በአንዳንድ ሁኔታዎች ሊሰነጣጠቅ ብሎም እነዚህ ስንጥቆች ወደ ፍርስራሽነት ሊቀየሩ ይችላሉ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ሳይንቲስቶች "ሕያው" ኮንክሪትን መፍጠር ችለዋል፡፡ ሳይንቲስቶቹ ይህን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር አሸዋ፣ ጄልና ባሲለስ ሱቲሊስ የተባሀ ባክቴሪያን በመጠቀም ነው "ሕያው" ኮንክሪትን ለመፍጠር ችለናል ብለዋል።

የግንባታ ቁሳቁሱም መዋቅራዊ ሸክምን በብቃት የመሸከም ተግባር አለው ያሉት ሳይንቲስቶቹ ኮንክሪቱ ለአካባቢ ተስማሚ ነው ብለዋል፡፡ የተፈጥሮ አደጋዎች እና ከባባድ የአየር ሁኔታዎች ለምሳሌ እንደ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም ከፍተኛ ንፋስ የመሳሰሉ አደጋዎች በሚከሰቱበት ሰዓት ይህ አዲሱ ኮንክሪት ችግሩን መቋቋም ይችላል። በተጨማሪም ውኃ አይገባውም ምክንያቱም ስንጥቆች በሚከሰቱበት ወቅት የኮንክሪት ውህድ አካላት ራሳቸውን መጠገን ስለሚችሉ ነው፤ በዚህ በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭ ያደርጋቸዋል።

ኮንክሪቱ በሥራ ላይ በሚውሉበት ጊዜ ጉዳት የደረሰበትን ጥቃቅን ስንጥቆችን በኬሚካላዊና ሜካኒካል ባህሪያቸውን ሳያበላሹ ራሳቸውን ወደነበሩበት በመመለስ ህይወቱን እንደሚያራዝመው  ታውቋል። የኮሎራዶ ቡልደር ዩኒቨርሲቲ ቡድን እንዳሉት ሥራቸው ወደፊት በሚሰሩ ህንጻዎች ሂደት ስራ የሚያቀል እና በህንጻ፣ በወለል ላይ ስንጥቆች በሚፈጠሩበት ጊዜ አደገኛ መርዞችን ከአየር ላይ ወይም ከብርሃን በመሳብ ወደ ነበሩበት ለመመለስ የሚያስችል አቅም አላቸው፡፡
👍31👏4❤3🔥1
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2016ዓ/ም የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳቹ።
👍11❤4
SMH General Construction
💥አነጋጋሪው የኮተቤ መንገድ ዲዛይን እና አደጋዎቹ!! አነጋጋሪ የሆነው የኮተቤ መንገድ ዲዛይን በርካታ ተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ እያስከተለ ነው !! Source driving in addis https://t.me/ethioengineers1
💥የኮተቤ የአስፓልት መንገድ ዲዛይን

💫BRT ምንድን ነው ? ...ለምን የአደጋ ምንጭ ሆነ ?

🌟BRT ማለት Bus Rapid Transit Mode of Transport ማለት ነው ።
ይህ የትራንስፖርት አይነት ተመራጭ የሚያደርገው ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው ከተሞች ውስጥ ከተለመደው የመንገድ ክፍል ዉስጥ ለባስ ብቻ !!! የተመደበ በማዘጋጀት ካለምንም የትራፊክ መጨናነቅ ባሶች የትራንስፖርት ተጠቃሚውን ህዝብ በጊዜ ፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በማመላለስ በትራንስፖርት እጦት የሚባክነውን ጠቃሚ ጊዜ ለመቆጠብ ያስችላል ። በመላው አለም ጥቅም ላይ ውሏል ።

ታዲያ ይህ BRT የትራንስፖርት ዘርፍ ህዝብ እንደማመላለሱ የተለያዩ ፌርማታዎች ይኖሩታል የተለያየ ቅርፅ ያላቸው እነኚ ፌርማታዎች በመሃል በሚሆኑበት ሰአት መንገዱ የLayout ለውጥ ያደርጋል እንግዲህ ይህ ነው ለኮተቤው መንገድ ያደጋ ምንጭ የሆነው !!!

💥አዲስ አበባ ውስጥ የተለመደው የመንገድ Layout ወጥ የሆነ ነው በዚህ ምክንያት
አዲስ የሆነ Layout ሲመጣ ያንን ከግምት ያስገባ የአሽከርካሪ ስነ ባህሪ ባለመላመድ የመጣ ልሆን ይችላል ።

በአለማችን ረዥም BRT ... ያላት የኢንዶኔዣዋ ጃካርታ


🦺የተሻለ ማብራሪያ ካላችሁ ፃፉልን እንማማርበታለን @Ethiocon143bot❗️

https://t.me/ethioengineers1
👍18👏9❤2
💥ኬንያ በአጼ ሀይለስላሴ ስም የሰየመችውን ፈጣን መንገድ አስመረቀች

🌟አዲሱ የመውጫ መንገድ በአምስት ወራት ውስጥ በቻይና እና ኬንያዊያን ተቋራጮች ተገንብቷል ኬንያ በአጼ ሀይለስላሴ ስም የሰየመችውን ፈጣን መንገድ አስመረቀች።

ጎረቤት ሀገር ኬንያ የፈጣን መንገዷን መውጫ ኢትዮጵያን ከ40 ዓመት በላይ ለመሩት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በመሰረቱት አጼ ሀይለስላሴ ስም ሰይማለች።

ካሳለፍነው ሀምሌ ጀምሮ የተገነባው ይህ የፈጣን መንገድ መውጫ በናይሮቢ ዋና የትራፊክ ፍሰትን ለማቀላጠፍ በሚል በቻይና እና የኬንያ ተቋራጮች ተገንብቷል።

መንገዱ ከዛሬ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ሁለት ሰዓት ይፈጅ የነበረውን መንገድ ወደ 20 ደቂቃ ዝቅ እንዲል እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ባለ አምስት መስመር ያለው ይህ የመውጫ መንገድ ከናይሮቢ በፍጥነት ለመውጣት እንደሚያስችል የኬንያ ትራንስፖርት ሚንስትር ኪፕቾምባ ሙርኮመን ተናግረዋል።

ሚንስትሩ አክለውም አዲሱ መንገድ ወደ ማዕከላዊ የቢዝነስ ቦታዎች እና መንግስታዊ ተቋማት አካባቢ ያሉ መጨናነቆችን ያስቀራልም ብለዋል።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በክፍያ ይጠቀማሉ የተባለ ሲሆን በቀን 65 ሺህ አሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

Via Alain


https://t.me/ethioengineers1
👍33❤6
💥በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ

ሀ) ግንባታ ማስጀመሪያ

▶️አንድ ግለሰብ/ድርጅጥ በከተማ ቦታ ላይ በሊዝ የተረከበው ቦታ ላይ የሊዝ ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ለቦታው በተቀመጠው ደረጃ መረሰት ግንባታ እንዳለበት የሚደነግግ የጊዜ ጣሪያ ተቀምጧል።

⏺በሊዝ ቦታ ላይ የግንባታ መጀመሪያ የጊዜ ጣሪያ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች = 9 ወር፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 18 ወር ነው። ሆኖም ግን እስንደአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች በተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች ግንባታ ሳይጀመር ቢቀር ለአንድ ዙር ብቻ የሚፈቀድ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 9 ወር፣ ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች አንድ ዓመት ተጨማሪ የግንባታ ማስጀመሪያ ጊዜ በግንባታ ፍቃድ ሰጪው አካል ከማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጋር ሊሰጣቸው ይችላል።

ለ) ግንባታ ማጠናቀቂያ

▶️በሊዝ ቦታ ላይ ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች 24 ወራት፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 36 ወራት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች  48 ወራት ነው።

⏺ነገር ግን የአካባቢው የግንባታ ፍቃድ ሰጪ አካል ካመነበት የግንባታውን ውስብስብነት እያየ ሊያራዝምለት ይችላል።

⏺ሆኖም ግን ለግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሰጠው ጊዜ በማንኛውም ምክንያት (ሁኔታ) ቢሆን ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  2 ዓመት 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 4 ዓምት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ከአምስት ዓመት መብለጥ የለበትም።


https://t.me/ethioengineers1
👍16❤3😍1
💥የቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee bond) እና የመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ (performance bond) ልዩነት ምንድን ነው❓

🌟ስራ ተቋራጩ ሁለት ዓይነት ዋስትና ማለትም የቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee bond) እና የመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ (performance bond) የሰጠ ሲሆን ተቋራጩ በግንባታ ውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ ውሉ በአሰሪው ተቋርጧል።

🚧የግንባታ ስራው በመጓተቱ ምክንያት የግንባታ ስራ ውሉ በስራ ተቋራጩ ጉድለትና ጥፋት የግንባታ ስራ ውሉን አሰሪው ያቋረጠው ቢሆንም የስራ ተቋራጩ በዋስትና የወሰደውን የቅድመ ክፍያ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለህንፃ ግንባታ ስራው ያዋለው መሆኑ ከተረጋገጠ አሰሪው የቅድመ ክፍያ ዋስትናው ሊከፈለው አይገባም።

🖱ሆኖም ከቅድመ ክፍያ ዋስትና በተጨማሪ የመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ (performance bond) ተሰጥቶ ከሆነ የግንባታ ውሉ በስራ ተቋራጩ ጉድለትና ጥፋት ሲቋረጥ አሰሪው ለመልካም ስራ አፈፃፀም የዋስትና ቦንድ በተሰጠው ዋስትና መሰረት ገንዘቡ ሊከፈለው ይገባል።

Via ሰ/መ/ቁጥር 116714

#ConstructionContract

https://t.me/ethioengineers1
👍14👏1
👍1
💥የአዲስ አበባ የቤቶች ዋጋ እና ሽያጭ

የመኖሪያ ቤት ዋጋን ጨምሮ የኑሮ ውድነትን በአለም ላይ መረጃ አጠናቅሮ የሚተነትነው Numbeo ድረ ገጽ አዲስ አበባ ከሰው ገቢ አንጻር የመኖርያ ቤት እጅግ ውድ ከሆነባቸው የአለማችን ከተሞች በሦስተኛ ደረጃ አስቀምጧታል።

የ African Investor ድረ ገጽ ደግሞ የአዲስ አበባ ቤቶችን የኪራይ እና የመግዣ ዋጋ ግምትን ያስቀመጠ ሲሆን፣ የየመኖሪያ ሰፈር ቤቶች ላይ  ጠቋሚ ቅኝቶችን አስቀምጧል።

💫በአሁኑ ጊዜ ኢንቨስተሮች በአዲስ አበባ ከተማ ታይቶ የማይታወቅ የሪል ስቴት ልማት ውስጥ የገቡ መሆኑን መገመት የሚቻል ሲሆን፣ በዚሁ በሪል ስቴት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ከምንጊዜውም በላይ መደበኛና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሽያጭ ለማድረግ ሲሞክሩ መታዘብ ይቻላል።

በተጨማሪም መካከለኛ ገቢ ያለው ሰው አዘውትሮ የሚገኙባቸው ቦታዎች ናቸው ተብሎ የሚታሰቡ የዘመናዊ ገበያ ቦታዎች፣ በሻጮቹ የሚዘወተር በመሆኑ ሪል ስቴቶቹ ከፍተኛ የሽያጭ ውድድር ውስጥ የገቡ መሆኑ ይገመታል።

ከዚህ ተያይዞ በሪል ስቴት ልማት ዙሪያ የሚከተሉት ጥያቄዎች በጥናት መልስ የሚፈልጉ ናቸው።

1. ለምን የአዲስ አበባ ቤቶች ገቢን ያላገናዘቡ ውድ ንብረቶች ሆኑ?

2. የመሬት ውድነት ለቤት መወደድ ያለው አስተዋጽዎ ምንድን ነው?

3. ቤት አልሚዎች ገዢ ብለው አላማ ያደረጉት ቤት ፈላጊውን ወይስ በውጭ ምንዛሪ የሚገዛን ግለሰብ ነው?

4. በግል ከለሙት የሪል ስቴት ቤቶች ውስጥ ስንቱ ነው የመጀመርያ ጊዜ ቤት ገዢ የሆነው?

5. አሁን ባለው ገበያ ስንቱ አልሚ የልማቱን ስንት በመቶ  ካፒታል ይዞ ነው የቤት ልማት ውስጥ የገባው?

6. አሁን ባለው ገበያ አልሚዎች የሊክዊዲቲ ችግር ውስጥ (አልምቶ መሸጥ ችግር ) ገብተዋል ወይ?

7. ገዢዎች የቤት ስፋት ሲነገራቸው ከሚኖሩበት ውጪ ያለው በቀጥታ የማይጠቀሙበት ስፋት ስንት ይደርሳል?

በተረፈ አብዛኞቹ ሻጮች የዕጩ ገዢዎችን  ስልክ ቁጥር ለመውሰድ ከመጓጓት ባለፈ ስለሚሸጡት የቤት ፕላን አማራጮች ንድፍ ላይ የተደገፈ መሠረታዊ ሙያዊ እውቀት ያልተላበሱ ናቸው።

በመሆኑም በዛው በሚሸጡበት ቦታ በንድፍ ተደግፎ  ከማስረዳት ይልቅ ባህላዊ በሆነ ሁኔታ ደንበኞች ቤቶቹ  ያሉበት ድረስ በአካል እንዲሄዱ የመገፋፋት ፍላጎት ይታይባቸዋል።

(Ethiopian Architecture & Urbanism)


https://t.me/ethioengineers1
👍26❤3
💥የግንባታ ዲዛይን ለተቋራጭ ይሰጣልን?

🌟አንድ ግንባታ ዲዛይን በአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ከተሰራ በኋላ ሙሉ የዲዛይን ሰነዱ በወረቀት ቅጅ (hard copy) እና በሶፍት ቅጅ (soft copy) ለባለቤቱ ይሰጣል።

🚧ነገር ግን በ’ ከተማ ልማት እና ሥራዎች ሚኒስቴር አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 (Ministry Of Works And Urban Development Standard Conditions Of Contract Clause 6

⏺(1) ‘Custody of Drawings’) መሰረት፣ የግንባታ ዲዛይኑ የግንባታ ክትትል ለሚያከናውነው ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (supervision engineer) በሶፍት ቅጅ (soft copy) ሊሰጥ የሚችል ቢሆንም ለግንባታ ተቋራጩ (contractor) መሰጠት ያለበት ሁለት

⏺(2) የወረቀት ቅጂዎችን ሲሆን  ያለምንም ክፍያ በባለቤቱ ወጪ መዘጋጀትና ለተቋራጩ መሰጠት አለባቸው።

▶️የግንባታ ተቋራጩ የሚፈልገው ተጨማሪ ቅጂዎች ካሉ በራሱ ወጪ እንዲባዙለትና እንዲሰጡት ማድረግ ይችላል፣ ነገር ግን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማባዛትና ለሦስተኛ (ሌላ) ወገን አሳልፎ መስጠት ተቋራጩን ያስጠይቀዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ ተቋራጩ በውሉ መሠረት በቅጂ የቀረቡትንና የተረከባቸውን ሁሉንም ዲዛይኖች ለመሐንዲሱ (Engineer) እንዲመልስ በሕግ ግዴታ አለበት።

#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍19❤2👏2👌2
💥የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor)

🚧የግንባታ ዋጋ በሚወጣበት ጊዜ የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor) የሚባል ጽንሰ ሀሳብ አለ።

🌟የጠቃሚነት ተሳትፎ (Utilization Factor) ማለት “አንድ ሰው ወይም ማሽን በተመሳሳይ ሰዓት ስንት ሥራዎች ላይ ሊሳተፍ ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ መሰረት አድርጎ የሚሰላ የዋጋ ማባዣ መረጃ ሲሆን ብዙ ጊዜ በሰው ኃይል ላይ የሚተገበር ነው።

🖱ለምሳሌ፦ አንድ ፎርማን በአንድ ፕሮጀክት ላይ የሚሰሩ የቁፋሮ፣ የድንጋይ ግንባታ፣ የአፈር ሙሌት፣ የፌሮ ሥራዎችን ሊቆጣጠር ይችላል።

⏺በዚያ ሰዓት ፎርማኑ አራት ሥራዎችን እየተቆጣጠረ ስለሆነ የጠቃሚነት ተሳትፎው (Utilization Factor) ለአራት ሥራዎች ነው ማለት ነው።

▶️ይህ ማለት ለቁፋሮ፣ ለአፈር ሙሌት፣ ለፌሮ ሥራ፣ ለድንጋይ ግንባታ ሥራዎች የፎርማን አስተዋጽኦ ለእያንዳንዳቸው ያላቸው 25%፣ 25%፣ 25%፣ 25% ነው ማለት ነው። በዚህ አግባብ ለአንዱ ሥራ ዋጋ በሚወጣበት ጊዜ የፎርማን አስተዋጽኦ በ25% ይባዛል ማለት ነው።

🖱ለምሳሌ፦ አንድ ፎርማን በሰዓት 75 ብር የሚከፈለው ቢሆን እና የቁፋሮ ሥራን ዋጋ እያሰላን ቢሆን በቁፋሮ ሥራ የዋጋ ስሌት ውስጥ የፎርማኑ በሰዐት ይከፈለው የነበረው 75ብር በ25% (0.25) ይባዛል ማለት ነው።

⏺ቀሪዎቹ 75% ክፍያዎች በሌሎቹ ሦስት ሥራዎች ሂሳብ ስሌት ውስጥ የሚካተቱ ይሆናል።

⏺በተመሳሳይ ሰዓት አንድ ሥራ ላይ ብቻ የመሳተፍ ዕድል የሚኖራቸው ሰራተኞች ላይ ግን የጠቃሚነት ተሳትፎው (Utilization factor) ሁልጊዜ አንድ (1) ነው።

🖱ለምሳሌ፦ የቁፋሮ ሰራተኛ በአንድ ጊዜ ቁፋሮ ብቻ እንጂ እየቆፈረ እያለ ሌላተጨማሪ ሥራ ሊሰራ አይችልም።


https://t.me/ethioengineers1
👍36👏3
💥ጀርመን አደባባይን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የትራፊክ መጨናነቅን ለማቃለል የጀርመን አደባባይን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመቀየር ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

ይህ አደባባይ ከኃይሌ ጋርመንት - መብራት፣ ከአየር ጤና፣ ከጎፋ እንዲሁም ሜክሲኮ ሳር ቤት የሚንቀሳቀሱ አሽከርከሪዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ የአደባባይ ማሻሻያ ስራ መከናወኑ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና ጫና ለማቃለል የሚያግዝ መሆኑን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

መስሪያ ቤቱ የማሻሻያ ስራውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማይበዛባቸው ክፍለ ጊዜያት በመስራት በአጭር ጊዜ አጠናቅቆ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ሲገልፅ ተጠቃሚዎች ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ አሳስቧል።


https://t.me/ethioengineers1
👍15🤔1🙏1
💥አርማታና ብረት ተደርምሶ በስራ ላይ የነበሩ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 4:35 ሰዓት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦርማ ጋራዥ ጀርባ እየተገነባ ባለ ህንጻ ላይ እየተሞላ ያለ አርማታና ብረት ተደርምሶ በስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ላይ የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት የሟቾቹ ዕድሜ 32 እና 35 መሆኑን ገልፀዋል።የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሟቾቹን አስከሬን ከተጫናቸዉ ፍርስራሽ ስር አንስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

የኮንትራክሽን ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ አስሪዎችም ሆነ ሙያተኞች አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎች ባለመከተል መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የጥንቃቄዉ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ያሻዋል ሲሉ አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።


https://t.me/ethioengineers1
👍7👏7🤔5