SMH General Construction
22.4K subscribers
1.48K photos
45 videos
294 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
Foundations_of_Engineering_Geology.pdf
6.4 MB
⬆️
📚 Book 👉 Foundations of Engineering Geology
👤 Author 👉 Tony Walthom 📚 Book tip @civil_Cotm_eng
➡Hydraulics and water supply Lecture @civil_Cotm_eng
.
👉ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል 👇
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት
ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ
ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን
አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው
እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3)
አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት
(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ
(በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።
፟
➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን✌
ም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
👍1
👉 SFD Vs BMD
.
Shear Force Diagram = የአንድን አካል ርዝመት ‘ X ’
ብንለው በፎርሶች የሚፈጠረውን ሺር ፎርስ ደግሞ ‘ Y ’ ብንለውና
ግራፍ ላይ ስለን እያንዳንዱ የርዝመቱ ነጥብ ላይ ያሉትን ሺር
ፎርሶች በመስመር ስናገንኛቸው (የተገናኙ ናቸው በዕርገጥ)
የምናገኘው ቅርፅ ነው SFD
.
Bending Moment Diagram = ከ SFD ጋር አንድ ሆኖ ነገር
ግን ለ Moment ሲሆን Bending Moment Diagram
(BMD) ይባላል
.
Concentrated Load ሲኖር SFD ቀጥ ብሎ ወደጎን ይሄዳል
ወይም በሌላ አገላለጽ Constant ይሆናል፡፡ BMD ደግሞ linearly ወይም right angle triangle በሚመስል መልኩ ይሄዳል::
.
Distributed Load ሲኖር SFD linear ይሆናል BMD ደግሞ
Parabolic ይሆናል
ሁልጊዜ BMD ከ SFD በ አንድ ዲግሪ ይበልጣል ( SFD
constant ሲሆን BMD = linear…….. SFD linear ሲሆን
ደግሞ BMD is parabolic )
.
Maximum Bending Moment = SFD ከፖዘቲቭ ወደ
ኔጌቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይ ነው Moment Maximum
የሚሆነው
.
Minimum Bending Moment = SFD ከኔጌቲቭ ወደ ፖዘቲቭ የሚቀየርበት ነጥብ ላይ ይገኛል፡፡
ም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
👉Load Combination
.
Load Combination - አንድ ፎቅ ላይ የሚመጡ ሎዶችን Analyze ስናደርግ ሁሉም ሎዶች (LL,DL,EQ,WL, etc)
በተመሳሳይ ሰዓት ይከሰታሉ ተብሎ አይታሰብም እንደዛ ቢሆን ኖሮ ለትንንሽ ፎቆች ትልልቅ size ያላቸው Beam, Column እና
Slab ባስፈለገንና Uneconomical በሆንን ነበር፡፡ እንትን ሎድና እንትን ሎድ አንድ ላይ ሲከሰት ወዘተ እያልን Load
Combination እናወጣለን፡፡ ሎዶቹንም በ Factor እናባዛቸዋለን:: Factor ያስፈለገበትም ምክንያት Load
occurrence probability እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ
Load Uncertainties ለማስወገድ ነው፡፡
.
ስንት Load Combination አለ??
.
.
ብዙ ምሁራን በ Load Combination ብዛት ሲወዛገቡ ይታያል፡፡
አንዳንዶች 2 ነው ይላሉ ፤ ሌሎች 7 ነው ይላሉ ፤ ሌሎሎሎች 5
፤ ሌሎሎሎሎሎች 11……..ለማንኛውም ሰባትና ዘጠኝ ናቸው!!!
.
.
ሰባት የሚሆነው Earth Quake እና Wind Loadን እኛ
ካልኩሌት አድርገን ከሁለቱ Govern የሚያደርገውን ከለየን በኋላ
Governing ሎዱን በቁጥር ለሴፍትዌሩ (SAP/Etabs)
ስንሰጠው ሰባት ነው፡፡
.
.
ዘጠኝ የሚሆነው የ Earth Quake ወይም Wind ሎዱን የተለያዩ ፋክተሮች ለሶፍትዌሩ እንሰጠውና እራሱ ሶፍትዌሩ ሎዱን ካልኩሌት አድርጎ አንዲጠቀም ከፈለግን ዘጠኝ Combo እንጠቀማለን፡፡
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
👉 የትኛው ኢኮኖሚካል ነው ?? => Flat Plate, Waffle, Flat @civil_Cotm_eng
with Drop or Solid Slab
.
.
በጠቅላላው በፍሎር ደረጃ ኢሄኛው የተሻለ ኢኮኖሚካል ነው
አይደለም ለማለት Quantity ካልሰራን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ….
በፓኔል ደረጃ ( ስለአንድ እስላብ ብቻ ) ካወራን ግን EBCS
ሪኮመንድ የሚያረጋቸው የስላብ አይነቶች አሉ ፡፡ ሪኮመንዴሽኑ
100 ፐርሰንት ትክክል ነው ማለት አይደለም - ኢኮኖሚካል ነው
ለማለት ጂኦሜትሪንና የፌሮ ብዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት
አለብን - ስለዚህ አሁንም 100 ፐርሰንት እርግጠኛ የምንሆነው
ኳንቲቲ በመስራት ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ኮዱ ባደረገው ጥናት
መሰረት ከኮለን እስከ ኮለን ያለውን ርቀት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚካል ነው ያለውን የስላብ አይነት አስቀምጡዋል፡፡
እነዚህም፡
.
.
1. Flat Plate - ሎዱ ቀላል ከሆነና ከኮለን ሴንተር እስከ ኮለን
ሴንተር ከ4.5 እስከ 6ሜ ለሆነ ስላብ ኢኮኖሚካል ነው
.
2. Flat Slab With Drop - ከባድ ሎድ ካለና ከሴንተር -
ሴንተር ከ6 እስከ 9ሜ. ለሆነ እስላብ ኢኮኖሚካል ነው፡፡
.
3. Waffle Slab - ለትልቅ እስፓን ከ7.5 – 12ሜ………
ለትልቅ እስፓን ከmoment ይልቅ vertical load ገቨርን
ስለሚያደርግ መሃል ስፓን ላይ ያለውን የስላብ ውፍረት መቀነስ
እንችላለን - ዋፍል ስላብ በመጠቀም ማለት ነው፡፡
.
4. Ribbed Slab -ትልቅ ስፓን ላላቸውና ከቀላል እስከ
መካከለኛ የሆነ ተንቀሳቃሽ ሎድ ላላቸው ፓኔሎች ኢኮኖሚካል
ነው፡፡
.
5. Solid Slab - የስፓኑ ርዝመት በጨመረ ቁጥር ኢኮኖሚካል
አይደለም፡፡ ፍላት ስላቦች ናቸው ኢኮኖሚካል የሚሆኑት
ምክንያቱም የፍላት ስላብ ብረት አቀማመጥ በ Strip ስለሆነ
የፌሮ ብዛት ይቀንሳል::
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚ከ 1ኛ አመት እሰከ 5ተኛ ይሉትን ሙሉ የ ምህንድስና መጽሐፍ በ ቅርብ ቀን የጠበቁን👇👇👇👇👇👇 @civil_Cotm_eng
👆👆👆👆👆👆👆👆
Share $joine
👉 PRE-STRESSED CONCRETE (PSC) @civil_Cotm_eng
.
ፕሪ እስትረስድ ኮንክሪት - ኮንክሪቱ ላይ ሎድ ከመጫኑ በፊት
Axial Compressive Stress አፕላይ ይደረግባቸዋል….
ለምሳሌ አንድን ቢም ከጎንና ከጎን Compressive ፎርስ
ስናደርግበት የ ‹‹ በ ›› ፊደል አይነት ቅርፅ ይኖረዋል (ሲጋነን)
….. ኢሄ የታጠፈው ቢም እላዩ ላይ ሎድ ሲጫንበት ቢሙ ወደ
ነበረበት ቦታው ይመለሳል…. እንደዛ ነው pre-stressed
ኮንክሪቶች act የሚያደርጉት
.
✔PSC Vs RC
1 RC beam ላይ ለዲዛይን assume ስናደርግ ኮንክሪቱ ምንም አይነት tensile stress አይሸከምም - tensile እስትረሱን
የሚሸከመው ፌሮው ነው ብለን ነው…… ሌላው assumption ፌሮው ቴንሽኑን ይሸከማል ብንልም
የፌሮውን አቅም fully utilize አናደርገውም ወይም ደሞ ሙሉ
ለሙሉ አንጠቀምበትም የዚህም ምክንያቱ ኮንክሪቱ ቴንሽን ዞን
ውስጥ የሚከሰተውን Crack width ለመገደብ ወይም limit
ለማድረግ ነው
.
ከላይ በተገለፁት ሁለት ምክንያቶች ማለትም የኮንክሪቱንም የፌሮውንም አቅም ሙሉ ለሙሉ ባለመጠቀማችን የተነሳ ለትልልቅ ሎዶች RC ከ PSC አንፃር ኢኮኖሚካል አይደለም ….. የዚህም ምክንያቱ የ RCን አቅም ሙሉ ለሙሉ ስለማንጠቀምበት ነው….. በተጨማሪም RC ላይ ትልልቅ Grade ያላቸው ኮንክሪትና ፌሮ መጠቀማችን ብዙም ዋጋ የለውም……. ከ RC ድክመት ለመዳን Pre-Stressed ኮንክሪቶች ተፈጠሩ…… ከRC
በተሻለ መልኩ የኮንክሪቱንና የብረቱን እስትሬንግዝ ይጠቀማሉና
.
✔ Methods of Prestressing
1) Pre- tensioning -> ቢሙን ካስት ማድረጊያ mold እናዘጋጃለን… ሞልድ ውስጥም psc ኬብሎች ወይም tendon
እናስቀምጣለን…እነዚህ ኬብሎችም ላይ Tensile ፎርስ apply እናደርጋለን….. አፕላይ እንደተደረገ ኮንክሪቱን ሞልድ ውስጥ አስገብተን ኮንክሪቱን ካስት እናደርጋለን - ኮንክሪቱ ሲደርቅ ፎርሶቹን remove እናደርጋለን … ቢሙም ዝግጁ ሆነ ማለት ነው::
2) Post –tensioning -> ኮንክሪቱ ከደረቀ በኋላ ነው
Compressive force አፕላይ የምናደርገው:: Apply የሚደረጉት ፎርሶች ኮንክሪቱ ላይ compressive stress
ሲፈጥሩ ብረቱ ላይ ደሞ tensile stress ይፈጥራሉ ማለት ነው:: ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት @civil_Cotm_eng
.
የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን የመስራት አቅም (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል
.
ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት
ስራውስጥ መተግበር አለበት ። ስላምፕ ቴስት በትንሽ ወጪ
ምንተገብረው የኮንክሪትን Workability ምንመዝንበት
ተመራጭ መፈተሻ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 G.c ጀምሮ
እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።
.
የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ነገሮች
(Factors which influence the concrete slump test)
.
1- ለ ኮንክሪቱ እንደግብአት የተጠቀምናቸው እቃዎች
ባህርይ...ለምሳሌ ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን
እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት
፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም.
.
2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠን አይነት መስተጋብር...
.
3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም
.
4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ
.
5- የኮንክሪቱ temperature
.
6- በኮንክሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውሃ መጠን
.
7- ኮንክሪቱ ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ
.
.
Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች
.
Slump ለመስራት የሚያገለግል መሃሉ ክፍት የሆነ ኮን
(cone) መሰል ቅርፅ ማውጫ ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm
ርዝመት 20 cm የታችኛው ዲያሜትር 10cm የላይኛው
ዲያሜትር ያለው ነው (mold)
መለኪያ ማስመሪያ
ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት
.
ስላምፕ ቴስትን የመከወኛ ቅደም ተከተል
.
step-1 መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ
መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት
.
step-2 ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር
ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን ላይ አቁመው
.
Step 3- የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer
በኮንክሪት ሙሉት
.
Step 4- እያንዳንዱን የኮንክሪት ላየር 25 ግዜ
በመጠቅጠቂያ ብረት ምቱት (ጠቅጥቁት) የአጠቃጠቅ
ጉልበታችሁ እኩል መሆን አለበት
.
Step 5- ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ዲያ ባለው
ጫፍ ላይ ያል ትርፍ ኮንክሪትን አስወግዱት ጫፉንም ለስኑት
.
Step 6- ቅስ በማለት የኮንክሪት ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ከኮንክሪቱ አለያዩት
.
Step 7- ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold)
ያለውን የርዝመት ልዩነት ለኩት
.
.
Note - እዚጋ ማሳሰብ ምፈልገው ነገር ይህን ቴስት
ስታደርጉ ቦታው ከእርግብግቢት (Vibration) የፀዳ መሆን
አለበት ያልተረጋጋ ቦታ ላይ ማድረግ የቴስቱን ውጤት
ያበላሸዋል...ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን
መከወን አለብን
.
.
ከኮንክሪት ስላምፕ ቴስት የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች
.
True Slump- ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ብቸኛው ልኬት
ነው ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ
ቁመት ከቅርፅ ማውጫው በንፃሬ የምናገኘው ልዩነት (ምስሉን
ይመልከቱ)
.
Zero Slump - ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃ-
ሲሚንቶ ratio ያለው መሆኑን ያሳያል ዜሮ ስላምፕ ያለው
ኮንክሪት ለመንገድ ግንባታ አገልግቶት ላይ ይውላል...
.
Collapsed Slump- ይህ ደግሞ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃ ሲሚንቶ ውህድ Ratio ትልቅ መሆን ያሳያል
ይህ ማለት የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠን ከፍተኛ መሆኑን እና
High workability mix ያሳየናል።
.
Shear Slump- ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤት ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።
ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
👍1
Construction 🏗 technologies:
👉የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/
.
⏩ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ
ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታ
ልኬት/Elevation/ እና በሁለቱ መካከል የሚገኘውን ማዕዘን/
Angle/ ለማውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው።
.
➡ሁለት አይነት የቅየሳ መሳሪያ ይገኛሉ
1. ቴዶላይት/Thedolite/
2. ቶታል ስቴሽን/Total Station/ @civil_Cotm_eng
➡ቶታል ስቴሽን ጂፒስ፣ጨረር እና የከፍታ መለኪያ ሴንሰር
በመጠቀም ትክክለኛ የከፍታ ልዪነት/Elevation difference እና ርቀትን ለመለካት ይጠቅመናል።
➡ቴዶላይት ደግሞ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ
ልዪነት ለመለካት ሲያገለግል በመካከላቸው ያለውን ርቀት ግን
መለካት አይችልም።
. ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
👉የ ዕለቱ የ ምክር...
.
➡ሶሪያ😢 ከአመታት በፊት ይህቺ ምድር ማንም እንዲህ ወደ ፍርስራሽነት ትቀየራለች ብሎ አልገመተም፤ግን ሆነ! ሶሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን አጣች፤ በሚሊዮኖች ተወልደው ካደጉበት ሀገር ተሰደዱ!! ጦርነቱ ዛሬም አላባራም ዛሬም ሰው ይሞታል!! ያሳዝናል! ሶሪያውያን ይህ ከመሆኑ በፊት ከስሜታዊነት ወጥተው፤ በሰከነ መንገድ ተረጋግተው ተነጋግረው ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ባልመጣ ነበር።
.
▶ማስተዋል የመሰለ ጥበብ ከየት ይመጣ ይሆን?

🚩መገንባት እንደማፍረስ ቀላል አይደለም!!
.
➡ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ኣብዝቶ ይባርክ::😍
Construction 🏗 technologies:
👉ስለ ብሎኬት @civil_Cotm_eng
.
⏩Hollow Concret Block (HCB) ወይም የግድግዳ ብሎኬት/Wall HCB/ በመባል ይታወቃል።
*የብሎኬት ምርት ሲደረግ ጠቀሜታው ለሁለት ጉዳይ ነው
1. ሸክም መቌቌም የሚችል/Load Bearing/
2. ሸክም መቌቌም የማይችል /Non-Load Bearing/
*ይሄንን መሰረት ያደረገም የደረጃ ክፍፍል/Class/ ይኖራቸዋል።
*ሸክም መቌቌም የሚችሉት ብሎኬቶች "ክላስ ኤ እና ቢ" /
Class A and B/ በመባል ሲመደቡ ሸክም መቌቌም
የማይችሉት የብሎኬቶች ደግሞ "ክላስ ሲ" /Class C/ በመባል
ይመደባሉ።
➡ብሎኬት በተለምዶ በመጠናቸው ባለ10፣ ባለ15 እና ባለ 20 በመባል ይለያሉ::
ርዝመት x ስፋት x ቁመት/ Length x width x depth/
ማለትም Standard Dimenssion
*40x20x20cm
*40x15x20cm
*40x10x20cm
➡እያንዳንዱ ብሎኬት ሸክም የመቌቌም አቅማቸው
በሜጋ ፓስካል(Mpa) ይለካል ከዚህ በላይ 👆 በምስል አስደግፈናል።
*Note:
1 kilogram per square centimetre = 0.0981 mega pascal

*Class A=3.8mpa
*Class B=3.2mpa
*Class C=1.8mpa
. ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
👍1
ውድ የ ቻናላችን ቤተሰቦች ለዛሬ Today Book Tip ምን ኣይነት የ ኮንስትራክሽን reference መፅሐፍ እንደምትፈልጉ በ @sintman Discussion ጉሩፓችን ወይም ፃፉልን። መልሰን እሁድ ቀን 6:00 ሰዓት ላይ የተመረጡ መፅሃፍቶች እንልክላቸዋለን።
.
ተሳተፉ እንወቅ እንማማር ለወደጅ ዘመዶ share ያርጉ @civil_Cotm_eng
👉ፎርምወርክ/Formwork/
➡በምን ያህል ቀን ማፍረስ ይቻላል?👇 @civil_Cotm_eng
.
⏩ ለቌሚ ፎርምወርክ 16ሰዓት
⏩ ለወለል እና ደረጃ /ሶሌታ/ ፎርምወረክ 21 ቀን
⏩ ተጨማሪ ለቢም/beam/ እና ወለል/slab/ ድጋፍ የሚገባ
14ቀን
⚡ የፎርም ወርክ ክፍያን በተመለከተ ባትኮዳ/Batcoda/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች ይጠቅሳል።
1. ከ 0.25ካ.ሜ በታች የሆነ ክፍት/opening/ ፎርሞርክ ክፍያ
ላይ ሊቀነስ አይገባም።
2. በተለየ ሁኔታ ካልተጠቀሰ በስተቀር በካ. ሜ ሊለካ ይገባል።
3. የወለል ጠርዝ፣ የደረጃ መወጣጫ እና የጎን ፎርምወረክ
ጥልቀቱን በመጥቀስ በሜትር ሊለኩ ይገባል። ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
@civil_Cotm_eng

👆👆👆👆👆
EBCS code