💥Hydraulics and water supply Lecture
🚧ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል
🌟⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት እንዳይገቡ ያግዳል ።
🌟⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
⏺ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3) አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
⏺እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
🌟⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት (coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
🌟⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ።
⏺ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
🌟⓹ ማጥራት (filtration)፦በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
🌟⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ (በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች) ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
⏺ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
☄በሃገራችን በዋነኛነት ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን።
➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ።
🏷ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን
https://t.me/ethioengineers1

👍27❤1💯1
🌟Online Class (With Certificate)
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA

Telegram
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍3👏1
💥በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ከተሰማሩ ተቋማት የመረጃ ማሰባሰብያ መጠይቅ
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ‘የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዳታ አስተዳደር ሥርዓት (Ethiopian Construction Data Management System (ECDMS))’ ለማዘጋጀት ያለመ ፕሮጀክት እያሰራ ይገኛል።
የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ የኮንስትራክሽን
ኢንደስትሪ መረጃዎችን በፌዴራል፣ በክልል፣ በከተማ/ወረዳ እንዲሁም ከግል ድርጅቶች በመሰብሰብ፣ በማደራጀት እና በመተንተን እንዲሁም በተቀናጀ ድረ-ገጽ ላይ የተመሰረተ አሰራርን በመጠቀም ለተጠቃሚዎች ለማዳረስ ያለመ ነው። የፕሮጀክቱ የመጨረሻ ውጤት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አፈፃፀም እና ተወዳዳሪነት ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።
ለዚህም የሚኒስቴር መ/ቤቱ (MUI) ፕሮጀክቱን ክአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንጻ ግንባታ እና
ከተማ ኢንስቲትዩት (EiABC – AAU) የፕሮጀክት ጥናትና የምክር አገልግሎት ስምምነት ፈጽሟል።
EiABC - AAU ከመንደር ኢንፎርሜሽን አርኪተክቸር ሶፍትዌር ዲዛይን (MinArc)፣ አልሚው ድርጅት ጋር በመተባበር ጥናቱን በማካሄድ እና
የመረጃ ሥርዓቱን በመንደፍ ላይ ናቸው።
ይህ መጠይቅ የተዘጋጀው በEiABC - AAU የፕሮጀክቱ ጥናትና ዲዛይን ቡድን ሲሆን አላማውም ከኮንስትራክሽን
ኢንዱስትሪ ተዋናዮች መረጃ ለመሰብሰብ ነው፡፡
ለሁሉም ጥያቄዎች ምላሽ እንድትሰጡ እና በተቋማችሁ ከግንባታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን
(ማለትም ከህንፃዎች፣ መሠረተ ልማት፣ የግንባታ እቃዎች እና የማሽነሪ ግብአቶች፣ የግንባታ ባለሙያዎች ጋር
የተያያዙ መረጃዎችን) ለመሰብሰብ የምትጠቀሙባቸውን ቅጾች፣ ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) እና ሰነዶች (ሶፍት ኮፒ እና/ወይም ሃርድ ኮፒ) እንድታቀርቡ በአክብሮት ለመጠየቅ ነው።
የምታቀርቧቸው የመረጃ ቅጾች እና የግንባታ ተዛማጅ መረጃዎች
ለዳታቤዝ ሲስተም ልማት ፕሮጀክት ጠቃሚ ግብአቶች ይሆናሉ።
ለምታደርጉልን ትብብር በቅድሚያ እናመሰግናለን።
የካቲት 2016
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት እና ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ የጥናት ቡድኑን የወከለውን ባለሙያ ማግኘት ይችላሉ።
(አቶ ባህሩ ሰለሞን
ስልክ
09 16 05 50 16)
https://forms.gle/tPkNzKmQ7JDqDUQZ8

Google Docs
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ከተሰማሩ ተቋማት የመረጃ ማሰባሰብያ መጠይቅ
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ‘የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዳታ አስተዳደር ሥርዓት (Ethiopian Construction Data Management System (ECDMS))’ ለማዘጋጀት ያለመ ፕሮጀክት እያሰራ ይገኛል። የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ መረጃዎችን በፌዴራል፣ በክልል፣ በከተማ/ወረዳ እንዲሁም ከግል ድርጅቶች በመሰብሰብ፣ በማደራጀት እና በመተንተን እንዲሁም በተቀናጀ ድረ…
👍17🙏1
🦺ውድ የኢትዮ ኮንስትራክሽን ቤተሰቦቻችን በዚህ ቻናል ላይ ፖስት ምናረጋቸውን በ ድምፅ ቨዲዮ ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ የቲክቶክ ገጻችንን ይቀላቀሉ እናመሰግናለን❗️
https://www.tiktok.com/@ethiocons
https://www.tiktok.com/@ethiocons
❤8👍1
💥የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
⚡️የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡
⚡️በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡
⚡️በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
⚡️የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡
⚡️በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡
⚡️ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
⚡️በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

SMH General Construction
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👷♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
👍13👏2
🌟Online Class (With Certificate)
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
Telegram
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍11
💥በሰው መሬት ላይ ለተሰራ ቤት ሕጉ ምን ይላል??
አንድ ሰው የራሱ ይዞታ ባልሆነ መሬት ላይ ወይም በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት ከሰራ ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል ለሚለው የፍትሀ ብሔር ሕጉን ቁጥር 1170 ና 1179 እናያለን።
የአንድ የመሬት ይዞታ ባለቤት በይዞታው ላይ የመጠቀም መብቱ የራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው በዚያ መሬት ላይ ህንፃ ወይም ቤት ሊሰራ አይችልም ልስራ ካለም ባለይዞታውን በማስፈቀድ መስራት አለበት አለበለዚያ ባለይዞታው በመሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም ብሎ መቃወም ይችላል።
ነገር ግን መሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም እየተባለና ባለይዞታው እየተቃወመ በእምቢተኝነት በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሰራ ሰው በሰው መሬት ላይ በሰራው ቤቱ አንዳችም መብት የለውም። ባለይ ዞታው በመሬቱ ላይ እየተቃወመው ቤት የሰራው ሰው ሁለት አማራጭ የህገ መፍቴዎች አሉት
1. ለቤቱን መስሪያ ያወጣውን ወጪ ሳይመልስለት ቤቱን ለቆ እንዲሄድ ማድረግ ይችላል።
2. ቤቱን የሰራው ሰው በራሡ ወጪ ቤቱን አፍርሶ እንዲሄድ ለመፍቀድ ይችላል፡፡ ባለመሬቱ በይዞታው ላይ ባለመኖሩ ወይም በሌላ ምክንያት በመሬቱ ላይ ቤት የሚሰራውን ሰው በወቅቱ መቃወም ባይችልም ቤቱ መሰራቱን እንዳወቀ ቤቱን ማስለቀቅ ወይም ማስፈረስ ይችላል።
ስለዚህ የራስ ያልሆነ ይዞታ ላይ ቤት መስራት አይቻልም። ይቻላልም ከተባለ ባለመሬቱ ፍቃደኝነቱን መግለፅ አለበት።
በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ቢሰራ እንደማይቃወም በግልፅ ወይም በዝምታ መፍቀድ ይችላል።
በግልፅ ወይም በዝምታ በመፍቀድ (ተቃውሞ ሳያቀርብ) በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ሲሰራ ያልተቃወመ ወይም የተስማማ ባለይዞታ እንደ ፌደራል ሰበር.በመዝገብ.ቁጥር 30101.ቅፅ 6 እና በመዝገብ.ቁጥር.105125.ቅፅ 20 በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ቤቱን የሰራው ሰው ባለቤት ይሆናል የመሬቱ ባለይዞታም በእንዲ አይነት ሁኔታ ቤቱን ለሰራው ሰው የቤቱን ግምት ከፍዬ ላስለቅቅ ማለት አይችልም።
የፍ/ህ/ቁ.1179ን አስመልክቶ ሰበር በቅፅ 25 የመ/ቁ. 189608 የሰጠው ትርጉም
***
በፍ/ህ/ቁ. 1179 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረዉ በባለይዞታዉ እና ይዞታዉን ይዞ ቤት በሰራ ሰዉ መካከል የታወቀ ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ብቻ በመሆኑ የባድ ቦታ ሽያጭ ዉል መፍረሰን ተከትሎ በቦታዉ ላይ የተሰራ ቤት ህጋዊ ዉጤትን አስመልክቶ ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለዉ በፍ/ህ/ቁ. 1818 ነዉ።
Via ሳሙኤል ግርማ
#ConstructionLaw

👍19
Smart City Approach in ADDIS
የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ሽፋንና ዘመናዊነት ለማሻሻል የሚረዳ ውሳኔ ተላለፈ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማዋን የመንገድ ሽፋንና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ሊያሳድግ የሚችል የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ላይ እና የአካባቢ ልማቶች ላይ ውሳኔ አሳለፈ።
ካቢኔው የከተማዋን አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን እና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድግ የሚችል የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ላይ እና የአካባቢ ልማቶች ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ መሠረት የሚለሙት የመንገድ ኮሪደሮች የሚከተሉት ናቸው:-
ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ድልድይ (7 ኪ.ሜትር)
ከቦሌ አየር መንገድ እስከ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ (4.9 ኪ.ሜትር)
ከመገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ በአራት ኪሎ በኩል የአድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ ድረስ (6.4 ኪ.ሜትር)
ከፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ፣ በለገሃር ሜክሲኮ፣ በሳርቤት በኩል እስከ ወሎሰፈር (10 ኪ.ሜትር) ናቸው።
እነዚህ የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ሁለንተናዊ የመንገድ ዘመናዊነት ያሟሉ ከመሆናቸውም በላይ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማዋን ገጽታ እንደሚያሻሽሉ ታውቋል።
የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቶቹ አዋሳኝ የወንዝ ተፋሰሶችን ያቀፉ፣ የሳይክልና ሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የከተማዋን ማስተር ፕላን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው።
በተጨማሪም አስፈላጊ በሆኑ የኮሪደሩ ቦታዎች ላይ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ተሸጋጋሪ ድልድዮች፣ ማሳለጫዎች እና ሰፋፊ መጋቢ መንገዶችን ያቀፈ ሲሆን የከተማ አረንጓዴ ልማትን ያካተተ እንደሚሆንም ታውቋል።

👍22❤2👏1🤔1😍1
🌟Online Class (With Certificate)
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
Telegram
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍5❤1
💥የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/
.
⏩ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታ
ልኬት/Elevation/ እና በሁለቱ መካከል የሚገኘውን ማዕዘን/ Angle/ ለማውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው።
.
➡ሁለት አይነት የቅየሳ መሳሪያ ይገኛሉ
1. ቴዶላይት/Thedolite/
2. ቶታል ስቴሽን/Total Station/
➡ቶታል ስቴሽን ጂፒስ፣ጨረር እና የከፍታ መለኪያ ሴንሰር በመጠቀም ትክክለኛ የከፍታ ልዪነት/Elevation difference እና ርቀትን ለመለካት ይጠቅመናል።
➡ቴዶላይት ደግሞ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ ልዪነት ለመለካት ሲያገለግል በመካከላቸው ያለውን ርቀት ግን
መለካት አይችልም።
.
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
@ethioengineers1

👍41👏2🤔2❤1
የኮንስራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ የ20 አመት ወጣት ህይወቱ አለፈ‼️
ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:09 ሰዓት ላይ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ ዕድሜዉ ሀያ ዓመት የሆነ የድርጅቱ ሰራተኛ ወዲያዉ ህይወቱ ማለፉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን ከፍርስራሽ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ በአንድ ወር ዉስጥ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

🤔10👍8👌1
🌟Online Class (With Certificate)
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software
🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken
🫵For Registration - 0948552002 Or @AbelMuluken
🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution
🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
Telegram
Engineering Solution
Youtube link - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍5
💥SHEAR_WALL
⚡️Shear wall is a structural member in a reinforced concrete framed structure to resist lateral forces such as wind forces.
✨ሺር ዎሎች በትክክል ዲዛይን ተደርገው ትክክለኛ ቦታቸው ላይ ካልተቀመጡ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ህንጻውን አፍራሽ ግብረ ሃይል ናቸው - ስለዚህ እንዴት ማስቀመጥ እንዳለብን ቀጥለን እንመልከት፡
1) አንድ ህንፃ ላይ የሚፈቀደው ትንሹ የሺር ዎል ብዛት ሶስት ነው፡፡ ቢያንስ-ሶስት
2) ሶስት ወይም ከዛ በላይ ሺር ዎሎች ካሉን የዎሎቹ አክሲሶች አንድ ነጥብ ላይ መገናኘት የለባቸውም
3) ትይዩ እንዲሆኑ የሚፈቀደው ቢበዛ ለሁለት ዎሎች ነው፡፡
ሺር ዎሎች ከኮለንና ቢም ይልቅ የህንፃውን ጥንካሬ ወይም Stiffness ወደ ራሳቸው የመጎተት ከፍተኛ አቅም አላቸው ፤ እንደሚታወቀው የመሬት መንቀጥቀጥ act የሚያደርገው Center of Mass ላይ ነው ፤ የመሬት መንቀጥቀጥን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ደግሞ የህንፃው ጥንካሬ ወይም Center of Stiffness የሚገኝበት ነጥብና የህንጻው Center of Mass የሚገኝበት ነጥብ በተቻለ መጠን መቀራረብ አለበት ፤ እናም ስናጠቃልለው - በትክክል ያልተቀመጡ ሺር ዎሎች የህንጻውን Center of Stiffness ወይም ጥንካሬ ወደራሳቸው ሲጎትቱት ከ Center of Mass እንዲርቅ ያደርጉታል - በመራራቃቸው የተነሳ እሽክርክሪት ፎርስ ወይም Torsion ይፈጠራል ፡፡ Torsion ህንፃው እንዲፈርስ ያደርገዋል፡፡ የኒውተን ሶስተኛ ህግ ምን ይላል “The forces of action and reaction between interacting bodies are equal in magnitude, opposite in direction and COLLINEAR” – ሁለት ፎርሶች Collinear force የሚባሉት ደግሞ በአንድ መስመር act ሲያደርጉ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ CM ላይ Act ሲያደርግ CS ደግሞ በሺር ዎሎቹ ስለተጎተተ ሌላ ቦታ React ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ Collinear force አይደሉም ማለት ነው፡፡
ስለዚህ Newton Third Law ውድቅ ሆነ ማለት ነው፡፡
Action እና Reaction በመጠንም ይሁን በአቅጣጫ እኩል ስለማይሆኑ ትርፍ balance ያልተደረገ force ይፈጠራል
Newton First Lawን ታሳቢ በማድረግ ህንፃው Equilibrium ላይ አይሆንም ማለት ነው፡፡
የኒውተን ሁለተኛ ህግስ ማን አለው የሚል ሰው ካለ - በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የሚፈጠረው ፎርስ ማለት የህንፃው ክብደት ሲባዛ በእንቅጥቃጤው የሚፈጠር Acceleration ነው - ይህም Newton Second Law ነው::
ስናጠቃልለው ከጥፋት ለመዳን ሺር ዎልን ስናስቀምጥ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡
@ethioengineers1
⚡️Shear wall is a structural member in a reinforced concrete framed structure to resist lateral forces such as wind forces.
SHEAR WALL የአግዳሚ ወይም horizontal load ተፅዕኖዎችን የሚቋቋሙልን ግድግዳዎች ናቸው፡፡ ሺር ዎል የተባሉበትም ምክንያት የመሬት መንቀጥቀጥ በጎን አቅጣጫ ስለሚመጣና ዎሎቹ ላይ የሺር ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው ( ሺር በ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል፡፡ Horizontal force የሆኑት Earth Quake እና Wind Load በዎሎቹ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ ነው የሚመጡት) ፡፡ ✨ሺር ዎሎች በትክክል ዲዛይን ተደርገው ትክክለኛ ቦታቸው ላይ ካልተቀመጡ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ህንጻውን አፍራሽ ግብረ ሃይል ናቸው - ስለዚህ እንዴት ማስቀመጥ እንዳለብን ቀጥለን እንመልከት፡
1) አንድ ህንፃ ላይ የሚፈቀደው ትንሹ የሺር ዎል ብዛት ሶስት ነው፡፡ ቢያንስ-ሶስት
2) ሶስት ወይም ከዛ በላይ ሺር ዎሎች ካሉን የዎሎቹ አክሲሶች አንድ ነጥብ ላይ መገናኘት የለባቸውም
3) ትይዩ እንዲሆኑ የሚፈቀደው ቢበዛ ለሁለት ዎሎች ነው፡፡
ሺር ዎሎች ከኮለንና ቢም ይልቅ የህንፃውን ጥንካሬ ወይም Stiffness ወደ ራሳቸው የመጎተት ከፍተኛ አቅም አላቸው ፤ እንደሚታወቀው የመሬት መንቀጥቀጥ act የሚያደርገው Center of Mass ላይ ነው ፤ የመሬት መንቀጥቀጥን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ደግሞ የህንፃው ጥንካሬ ወይም Center of Stiffness የሚገኝበት ነጥብና የህንጻው Center of Mass የሚገኝበት ነጥብ በተቻለ መጠን መቀራረብ አለበት ፤ እናም ስናጠቃልለው - በትክክል ያልተቀመጡ ሺር ዎሎች የህንጻውን Center of Stiffness ወይም ጥንካሬ ወደራሳቸው ሲጎትቱት ከ Center of Mass እንዲርቅ ያደርጉታል - በመራራቃቸው የተነሳ እሽክርክሪት ፎርስ ወይም Torsion ይፈጠራል ፡፡ Torsion ህንፃው እንዲፈርስ ያደርገዋል፡፡ የኒውተን ሶስተኛ ህግ ምን ይላል “The forces of action and reaction between interacting bodies are equal in magnitude, opposite in direction and COLLINEAR” – ሁለት ፎርሶች Collinear force የሚባሉት ደግሞ በአንድ መስመር act ሲያደርጉ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ CM ላይ Act ሲያደርግ CS ደግሞ በሺር ዎሎቹ ስለተጎተተ ሌላ ቦታ React ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ Collinear force አይደሉም ማለት ነው፡፡
ስለዚህ Newton Third Law ውድቅ ሆነ ማለት ነው፡፡
Action እና Reaction በመጠንም ይሁን በአቅጣጫ እኩል ስለማይሆኑ ትርፍ balance ያልተደረገ force ይፈጠራል
Newton First Lawን ታሳቢ በማድረግ ህንፃው Equilibrium ላይ አይሆንም ማለት ነው፡፡
የኒውተን ሁለተኛ ህግስ ማን አለው የሚል ሰው ካለ - በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የሚፈጠረው ፎርስ ማለት የህንፃው ክብደት ሲባዛ በእንቅጥቃጤው የሚፈጠር Acceleration ነው - ይህም Newton Second Law ነው::
ስናጠቃልለው ከጥፋት ለመዳን ሺር ዎልን ስናስቀምጥ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡
@ethioengineers1
👍42👏3❤2🤔1🙏1
ከኢትዮጵያ አልፎ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት አርማ ለሆነው 128ኛ ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ እንኳን አደረሳችሁ!!!!
ኢትዮ ኮንስትራክሽን
የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
https://t.me/ethioengineers1
ኢትዮ ኮንስትራክሽን
የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
https://t.me/ethioengineers1
❤29👍5🔥3
🚧ስለሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) እና የጥገና/የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
========== ===========
#የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ የሚባለው በኮንስትራክሽን ውል አስተዳደር ወቅት ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ፈጽሞ ክፍያ በሚጠይቅበት ወቅት የፕሮጀክቱ ባለቤት ከግንባታው አማካሪ መሀንዲስ ጋር በመሆን ስለሥራው ጥራት ደረጃ በሚል ሊይዘው የሚችለው ዋስትና ነው፡፡
የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ዓላማ የግንባታውን ጥራት ለማስጠበቅ ሲባል ሥራ ተቋራጮች ለአሰሪዎች የሚገቡት ዋስትና ነው፡፡የግዥ መመሪያውም በአንቀጽ 28.5(ለ) ላይ በግልጽ እንደሚደነግገው በእያንዳንዱ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ 5(አምስት) ፐርሰንት የክፍያው ገንዘብ የሚያዝ ይሆናል፡፡
በዋናነት ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት የሚሆነው ገንዘብ ሥራው እንደ ተጠናቀቀ እና ጊዚያዊ የርክክብ ምስክር ወረቀት (provisional acceptance certificate) ከተሰጠ በኋላ ለሥራ ተቋራጩ ይመለስለታል፡፡ የቀረው ገንዘብ ደግሞ እስከ አንድ አመት ድረስ ዋቢ ሆኖ ይቆያል፡፡ ነገር ግን የተቀረው የመያዣ ገንዘብን አስቀድሞ ሥራ ተቋራጩ ለአንድ አመት የሚጸና ዋስትና ማቅረብ ከቻለ የተያዘበትን ቀሪ ገንዘብ ማስለቀቅ ይችላል፡፡
በተመሳሳይ መልኩም የሲቪል ሥራዎችን በተመለከተም እኤአ በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውልም ስለ የዋና ገንዘብ መያዣ ዋስትና በአንቀጽ 59(5) እና 60 ላይ ተቀራራቢ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡
BUT,,,,የሪቴንሽን ገንዘብ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ እና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡ በዚህ ሳቢያም ሥራ ተቋራጮች ለሌላ ወጪ የሚዳረጉበት ሁኔታ አለ፡፡////The law stipulates that the retention bond shall be paid to contractor after provisional acceptance or final acceptance but its applicability is denied by government side most of the time. So, dear contractors, please ask before you bankrupt///
#የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡ በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡ በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡

👍26❤5👏1