SMH General Construction
22.5K subscribers
1.48K photos
45 videos
293 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
🏗 በአዲስ አበባ በሚያጋጥም የኮንስትራሽን የስራ ላይ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል ፡፡

🚧 በዚህ ረገድ አደጋውን ለመቀነስና ለመከላከል የሀገራችን የኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ ምን ይላል!

🏢 በህንፃ ግንባታ ስራ ላይ እያጋጠሙ አደጋዎችና ለመከላከል ስጋቶችን ለመቀነስ እንዲሁም ከህንፃ ግንባታ ጋር የተያያዙ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ የህንፃ ህግ በሀገራችን ይገኛል፡፡

🏗 የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 243/2003 ተጠቃሽ ናቸው፡፡

🚧 በህንፃ ግንባታ የሚሳተፉ አካላት የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቀው ባለመስራታቸውና ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው በአዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት ተጠያቂነት አለባቸው፡፡

በዚህ መሰረት:-
➡️ ለሚያከናውነው ግንባታ የሚያስፈልግን የዲዛይን ስራ፣ ወይም የተሰራውን ዲዛይን መሰረት የሚከናወነውን ግንባታ የሙያ ደረጃው በማይፈቅድለት ባለሞያ ያሰራ እንደሆነ፣ ወይም
➡️ ለሚያከናውነው ግንባታ ደረጃ ከሚጠይቀው የግንባታ ቁሳቁስ ያነሰ የጥራት ደረጃ ያላቸው ቁሳቁሶች በጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገ እንደሆነ፣ ወይም
➡️ ግንባታውን አግባብ ካለው አካል የመጠቀሚያ ፍቃድ ሳያገኝ ወይም ከተፈቀደው ውጪ ለሌላ አገልግሎት አውሎ የተገኘ እንደሆነ፣ ወይም
➡️ በማንኛውም ሌሎች ሁኔታዎች ግንባታው የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ እንደሆነ፣
ከአምስት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር ሃያ ሺህ እስከ ብር ሃምሳ ሺህ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።

➡️ ማንኛውም የተመዘገበ ባለሞያ ወይም የስራ ተቋራጭ፣ በዋና ወይም በንዑስ ስራ ተቋራጭነት ወይም ከፊል ውለታ በመውሰድ ያከናወነው ህንፃ ዲዛይን ወይም የግንባታ ስራ ለሚያስከትለው ጉዳት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው አሰሪው ለሆነው ሰው አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሄር ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

➡️ በተጨማሪ የስራ ተቋራጩ ሆን ብሎም ይሁን በቸልተኝነት በሚገነባው ህንፃ በሰው ላይ ለሚደረሰው ወይም በህንጻው አካል ላይ ለሚደርሰው የስራ ጥራት ጉድለት ተጠያቂነቱ ሳይቀር ጉድለቱን የማስተካከል ግዴታ አለበት፡፡

ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ወይም በ011-1-55-53-00 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
👍16❤2👏1
💥ቤዝ አይሶሌሽን/የመሠረት ማግለል/

🚧ሕንፃዎችን ከመሬት መንቀጥቀጥ ለመከላከል በግንባታ ላይ የሚውል ዘዴ ነው።

⏺ህንጻውን በተለዋዋጭ ማሰሪያዎች ወይም ማግለያዎች ላይ እንደ ጎማ ወይም ተንሸራታች ቁሶች በመዋቅሩ እና በመሠረቱ መካከል ማስቀመጥን ያካትታል።

▶️እነዚህ ገለልተኞች ህንጻው የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ኃይልን በመሳብ እና በማሰራ ከመሬት ተነጥሎ እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል።

🖱ይህ ዘዴ የህንፃውን የመሬት መንቀጥቀጥ የመቋቋም ችሎታን ያሻሽላል ፣ የነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና መዋቅራዊ ጉዳቶችን ለመቀነስ ፣ የመሠረት ማግለል በሴይስሚክ ክስተቶች ጊዜ ሕንፃዎችን በመጠበቅ ረገድ የተሳካ ነበር፣ ይህም ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ በሆኑ የከተማ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ ጠቃሚ ስትራቴጂ እንዲሆን አድርጎታል።

☄Base isolation is a method used in construction to protect buildings from earthquake damage.

⏺It involves placing the building on flexible bearings or isolators, like rubber or sliding materials, between the structure and its foundation.

▶️These isolators allow the building to move independently of the ground during an earthquake, absorbing and dissipating seismic energy.

🖱This technique improves a building's ability to withstand earthquakes, keeping occupants safe and reducing structural damage.

⏺Base isolation has been successful in safeguarding buildings during seismic events, making it a valuable strategy for enhancing earthquake resilience in earthquake-prone urban areas.


https://t.me/ethioengineers1
👍18❤4
💥መንግሥት የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ የቤት ባለቤት ማድረግ አይችልም ተባለ!
Via
#ethiopian_reporter
መንግስት ኮንዶሚኒየም መሥራት አቆመ
!

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቃለል አስተዳደሩ በአማራጭነት ባቀረባቸው የተለያዩ አማራጮች በመጠቀም የመኖሪያ ቤቶችን መገንባት እንደሚቻልና ኅብረተሰቡም በዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አስተላለፉ፡፡

ከንቲባዋ ይህንን የገለጹት ሰሞኑን ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የገነባቸውን አምስት ሺሕ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ባስተላለፈበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ እንደ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ገለጻ፣ መንግሥት የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ የቤት ባለቤት ማድረግ የማይችል በመሆኑ አስተዳደሩ አዲስ በቀረጻቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ መሆን የሚቻልበት ዕድል ማመቻቸቱን አመልክተዋል፡፡ በከተማዋ ነዋሪዎች በዋነኛነት የሚነሳው የመኖሪያ ቤት ችግር መሆኑን ያመለከቱት ከንቲባዋ አስተዳደሩም ይህንን ጉዳይ ከሁሉም በላይ በአንገብጋቢነት እንደሚመለከተው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የተለያዩ የአማራጮች እየተተገበሩ መሆኑን በማስታወስ የከተማው ነዋሪም እነዚህን አማራጮች መጠቀም እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

እንደ ከንቲባዋ ገለጻ የተቀየሱት አማራጮችን በመጠቀም የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ቢሆንም አሁንም የመኖሪያ ቤት አቅርባትና ፍላጎቱ ግን ሊጣጣም አልቻለም፡፡ በመሆኑም ይህንን ለማጣጣምና የመኖሪያ ቤት አቅርቦቱን ለመጨመር በርካታ የቤት አቅርቦት ፕሮግራሞች በመቅረጽና አስፈላጊው የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ወጥቶለት አብሮ የማልማት እንቅሰቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት የከተማ አስተዳደሩ አቅም ላላቸው የከተማው ነዋሪዎች፣ ለባለሀብቶች፣ ለግል አልሚዎችና ሌሎችም በዚህ ሥራ መሳተፍ የሚችሉትን ሁሉ በማበረታታት ላይ የሚገኙ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በእነዚህ የቤት ግንባታ አማራጮች ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሩ ክፍት ስለመሆኑ በመግለጽም አስተዳደሩ በአማራጭነት ባቀረባቸው የቤት ግንባታ አሠራሮች ኅብረተሰቡ ተሳታፊ ይሆን ዘንድም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አስተዳደሩ በአማራጭነት ካቀረባቸው የቤት ማልሚያ ፕሮግራም ውስጥ አንዱ በፓርትነርሺፕ ወይም በአጋርነት አብሮ መሥራት በቀዳሚነት ጠቅሰዋል፡፡ ሁለተኛ በሪልስቴት መሬት ሳይሸጥ ዓላማው ሳይቀር በዕለቱ አምስት ሺሕ ቤቶችን እንዳስተላለፈው ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የተሰጠውን መሬት አልምቶ ለተፈለገው ዓላማ ማዋል መቻል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የተረከቡት መሬት ዓላማው ሳይቀር ለተፈለገው ዓላማ መዋል የሚችል ከሆነ አስተዳደሩ የሚያበረታታ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡ ኅብረተሰቡ በአማራጭነት ሊጠቀምበት ይችላል ብለው ሦስተኛ አማራጭ ብለው የገለጹት በማኅበር ተደራጅቶ ቤት መሥራትን ነው፡፡ አራተኛው አማራጭ ደግሞ ከሦስቱ አማራጮች ለየት ባለ መንገድ የሚተገበር ነው፡፡ ይህም ቤት የሚፈልጉ መሬት ያላቸው ገንዘብ ግን የሌላቸው ነዋሪዎች ገንዘብ ካለው አልሚ ጋር በአጋርነት አብረው ማልማት የሚችሉበት ዕድል የተመቻቸ መሆኑ ነው፡፡ አምስተኛ አማራጭ ደግሞ መንግሥት ራሱ እንዲገነባ የሚያቀርበው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ አማራጮች የከተማዋን ዲዛይን በጠበቀ መልኩ የሚገነቡ እስከሆነ ድረስ አስተዳደሩ ድጋፍ የሚያደርግባቸው አዳዲስ አሠራር ስለመሆናቸው ከገለጻቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹በየትም አገር የቤት አቅርባት እየጨመረ እንዲሄድ ይደረጋል እንጂ መንግሥት እየገነባ ሁሉንም ነዋሪ የቤት ባለቤት ማድረግ አይችልም፣ በየትኛውም ዓለም አልተደረገም፤›› ያሉት ከንቲባዋ ነገር ግን አዲስ አበባ የቤት አቅርባትን የሚያስችሉ አቅሞቻችንን ማቀናጀት በጋራ ማልማት የሚቻል ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡

አሁንም አስተዳዳሩ ይህንን ሥራ ለማጠናከር እየሠራ ሲሆን በዕለቱ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን አምስት ሺሕ ቤቶች ሠርቶ በማስረከቡ በከተማችን በዚህን ያህል ቁጥር የቤት አቅርቦት መጨመር ያስቻለ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ሰንሻይን ይህንን ያህል ገንብቶ ቤቶቹን ማስተላለፍ የቻለው መሬቱ ስላልተለወጠ ለተፈለው ዓላማ ስለዋለ መሆኑና ይህም 3.8 ሔክታር መሬት በነፃ አስተዳደሩ የቀረበ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ እንዲህ በትብብር ከተሠራ ውጤታማ መሆን ይቻላልም ማለትም አሁንም ወደፊትትም ቤት ለማልማት አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸው በትክክል ማቅረብና መተግበር ለሚችሉ አስተዳደሩ በነፃ መሬት ባያቀርብም በበርካታ ማበረታቻዎችን የሚሰጡና የሚደግፉ መሆናቸውም አስታውቀዋል፡፡ ከንቲባዋ እነዚህ አማራጮች ሌላ ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው ቤት መገንባት የሚችሉ ከሆነ ይህንን ለማበረታታት ቦታ የሚያቀርቡ እንደሆነም በሰሞኑ ንግግራቸው አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ አምስት ሺሕ ቤቶችን ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ወ/ሮ አዳነች ኩባንያዎች ለሠራተኞች ቤት መገንባት የሚፈልጉ ከሆነ ይበረታታሉ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የወሰደውን ዕርምጃ በምሳሌነት በመጥቀስ በከተማ ውስጥ በርካታ ትልልቅ ኩባንያዎች ስላሉ ለሠራተኞቻቸው ቤት በመገንባት የቤት አቅርባትን ችግር ለማቃለል ለሚያደርጉት ጥረት አስተዳደሩ መሬት የሚያቀርብ በመሆኑ ኩባንያዎች ይህንንም የቤት ማልሚያ መንገድ በመጠቀም መገንባት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ በአማራጭነት ካቀረባቸው አሠራሮች ውስጥ በተለይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ ለማልማት በተቀረጸው ፕሮግራም 70 የሚሆኑ አልሚዎች ከአስተዳደሩ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲህ ላሉ የቤት ልማቶች አስተዳደሩ 1,500 ሔክታር መሬት መዘጋጀቱም መገለጹ ይታወሳል፡፡

አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች ቁጥር ከ600 ሺሕ በላይ ደርሰዋል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ደግሞ በመንግሥት የተገነቡ ቤቶች 316 ሺሕ ሲሆኑ በዚህ የግንባታ ሒደት የቤት ፍላጎትን መሙላት እንደማይችልም በመታሰቡ አስተዳደሩ በአማራጭነት በቀረቡ የቤት ማልሚያ ፕሮግራሞች እየተሳተፉ ያሉ አልሚዎች የቤት ችግርን ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎም ታምኖበታል፡፡

ከዚሁ አንፃር በከተማዋ እየተካሄደ ያለውን የቤቶች ልማት በተመለከተ በ2016 በሙሉ በጀት ዓመቱ ግንባታቸውን ለማስጀመር ከታቀዱት 120 ሺሕ ቤቶች በግማሽ ዓመቱ ውስጥ 99113 ቤቶች ማልማት መቻሉን ከንቲባዋ በቅርቡ የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት መጥቀሳቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህም ሌላ በበጀት ዓመቱ 111 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የአጋርነት ውልና የመሬት ዝግጅት እየተከናወኑ ስለመሆናቸውም ጠቅሰዋል፡፡ እንዲህ ባሉ በአጋርነት ቤት በማልማት ሥራዎች በሪል ስቴት ኩባንያዎችና በግለሰብ አልሚዎች በግማሽ ዓመቱ ውስጥ አሥር ሺሕ ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በግለሰብና በሪል ስቴት ኩባንያዎች ከተገነቡት አሥር ሺሕ ቤቶች ሌላ በመንግሥት በጀት 4,200 በበጎ አድራጊ ግለሰቦችና ኩባንያዎች በኩል ደግሞ 5023 ቤቶች በአጠቃላይ 19,223 ቤቶች ስለመገንባታቸውም ጠቅሰዋል፡፡
#ሪልስቴት #ኮንዶሚኒየም #ኢትዮጵያ
👍21❤5🤔1
          🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002  Or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍9👏1
💥የሳይት መሐንዲስ ሚና

🌟የሳይት መሐንዲስ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት ደረጃ
መጠናቀቁን በማረጋገጥ በግንባታው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

🚧በግንባታ ላይ የሳይት መሐንዲስ ዋና ዋና ኃላፊነቶች መካከል፡-

🌟1. የግንባታ ሥራዎችን የመቆጣጠር፡ የሳይት መሐንዲስ በየእለቱ የሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን የመቆጣጠር፣ በፕሮጀክት መሥፈርቶችና በፕሮጀክት መሥፈርቶች መሠረት መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የጊዜ መስመር.

🌟2. የጥራት ቁጥጥር፡- የሳይት
መሐንዲሱ ሥራ በፕሮጀክት ዝርዝር መግለጫዎች እና በኢንዱስትሪ
ደንቦች የተቀመጡ የጥራት ደረጃዎችን የማሟላቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት
አለበት።

🖱የፕሮጀክቱን ጥራት ለማረጋገጥ ሥራን መፈተሽ፣ ፈተናዎችን ማካሄድ እና ማንኛውንም ችግር መፍታት ይችላሉ።

🌟3. ጤና እና ደህንነት፡-

⏺የሳይት መሐንዲሱ የጤና እና የደህንነት ደንቦች በቦታው ላይ መከበራቸውን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

⏺ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የመለየት እና የመፍታት፣ የደህንነት እርምጃዎችን የመተግበር እና የደህንነት ፍተሻዎችን የማካሄድ ሃላፊነት አለባቸው።

🌟4. ግብዓቶችን ማስተዳደር፡- የሳይት መሐንዲሱ ፕሮጀክቱ በተያዘለት መርሃ ግብር እና በበጀት ውስጥ እንዲቆይ ለማድረግ እንደ ቁሳቁስ፣ መሳሪያ እና ጉልበት ያሉ ሀብቶችን በብቃት የመምራት ሃላፊነት አለበት።

🌟5. ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት፡ የሳይት መሐንዲሱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ማለትም ደንበኞችን፣ ተቋራጮችን፣ አቅራቢዎችን እና የቁጥጥር አካላትን ጨምሮ እንደ መገናኛ ነጥብ ሆኖ ያገለግላል።

⏺የፕሮጀክት ሂደትን የማሳወቅ፣
ጉዳዮችን የመፍታት እና የሚነሱ ችግሮችን የመፍታት ሃላፊነት አለባቸው።

🫵በአጠቃላይ የሳይት መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎችን በመከታተል፣የጥራትና
የደኅንነት ደረጃዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ፣ሀብትን በመምራትና
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገናኘት የግንባታ ፕሮጀክቱ በተሳካ ሁኔታ
እንዲጠናቀቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።


https://t.me/ethioengineers1
👍27❤8😍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💥በአሜሪካ የሚገኝ ረጅም ድልድይ በመርከብ ተገጭቶ ተደረመሰ‼️

በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት የሚገኘው ፍራንሲስ ስኮት ኪይ ድልድይ በመርከብ ተገጭቶ መደርመሱ ተሰምቷል፡፡

ከ2 ነጥብ 5 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለው የባልቲሞሩ ፍራንሲስ ስኮት ኪይ ድልድይ ዛሬ ማለዳውን ነው ተገጭቶ የተደረመሰው፡፡

አደጋውን ተከትሎ የመሸጋገሪያው መንገድ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡንም ሲኤን ኤን ዘግቧል።
ድልድዩ እ.ኤ.አ በ1977 ላይ የተገነባ ሲሆን ጆርጅ ታውንን ከ ቨርጅኒያ የሚያገናኝ ነበር፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍9🤔7😍1
🔶Advanced Structural Design

🔸Every Sunday Morning 3:00-8:00 LT.

ST CHECK LISTS
እነዚህን መመዘኛ መስፈርቶች አሟልተን ነዉ ዲዛይን አሰገብተን  የምናስፈቅደው።
ለ 2 ወሩ Special Structural Design Package ስልጠና መጨረሻ ላይ እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።

These are the checklists we will finally discuess for our 2months  special structural package course.
🔹Concrete Stru(Ordinary & High rise)
🔹Steel structure
🔸4 Software : Etabs, Sap, Safe
, Idea statica
● Registration is active
● Class starts on March 31/2024

📲
0911890392 / 0920933016
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://t.me/BeGetEngineering
👍18❤3👏1💯1
💥ኮንስትራክሽን ውል እና ኣይነቶቹ

🌟1. Lump Sum Contract፡ በአንድ ጊዜ ድምር ውል ውስጥ ኮንትራክተሩ ሙሉውን ፕሮጀክት በተወሰነ ዋጋ ለማጠናቀቅ ይስማማል።

⏺ይህ ዓይነቱ ውል ከትንሽ እስከ መካከለኛ የግንባታ ፕሮጀክቶች የሥራው ወሰን በደንብ የተገለጸ ነው.

🌟2. ኮስት ፕላስ ውል፡- በዋጋ እና በኮንትራት ኮንትራክተሩ ለፕሮጀክቱ ትክክለኛ ወጪ የሚከፈለው ክፍያ ወይም በመቶኛ ነው።

▶️ይህ ዓይነቱ ውል ብዙ ጊዜ ለዋጋ አወጣጥ የበለጠ ተለዋዋጭነትን ስለሚያስችል እርግጠኛ ባልሆኑ ወይም በዝግመተ ለውጥ ላይ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ያገለግላል።

🌟3. የጊዜ እና የቁሳቁስ ውል፡- በጊዜ እና የቁሳቁስ ውል ውስጥ ኮንትራክተሩ የሚከፈለው በፕሮጀክቱ ላይ ባጠፋው ጊዜ እና ጥቅም ላይ በሚውልበት ቁሳቁስ መሰረት ነው።

▶️ይህ ዓይነቱ ውል ብዙውን ጊዜ ለትናንሽ ፕሮጀክቶች ወይም ፕሮጀክቶች ቋሚ ዋጋ ለመወሰን አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ ግልጽ ያልሆኑ የሥራ ወሰን ላላቸው ፕሮጀክቶች ያገለግላል.

🌟4. የአሃድ ዋጋ ውል፡ በአንድ የዋጋ ውል ውስጥ ኮንትራክተሩ የሚከፈለው በተጠናቀቁት የስራ ክፍሎች ብዛት ነው። 

▶️ይህ ዓይነቱ ውል የሥራው ስፋት በቀላሉ ሊለካባቸው ለሚችሉ ፕሮጀክቶች ለምሳሌ የመንገድ ግንባታ ወይም የመገልገያ ሥራ የተለመደ ነው።

🌟5. የንድፍ ግንባታ ውል፡- በንድፍ ግንባታ ውል ውስጥ ተቋራጩ ፕሮጀክቱን የመንደፍ እና የመገንባት ሃላፊነት አለበት። 

▶️የዚህ ዓይነቱ ውል ብዙውን ጊዜ ባለቤቱ የንድፍ እና የግንባታ ሂደቱን ለማቀላጠፍ ለሚፈልጉ ፕሮጀክቶች ወይም ፕሮጀክቶች በፍጥነት ያገለግላል::

🌟6. የተረጋገጠ ከፍተኛ ዋጋ (ጂኤምፒ) ውል፡ በጂኤምፒ ውል ውስጥ ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን በተወሰነ ከፍተኛ ዋጋ ለማጠናቀቅ ተስማምቷል። 

▶️ትክክለኛው ወጪዎች ከከፍተኛው ዋጋ በላይ ከሆነ, ተጨማሪ ወጪዎችን የመሸፈን ሃላፊነት ያለው ኮንትራክተሩ ነው።

▶️ይህ ዓይነቱ ውል ለባለቤቱ የወጪ እርግጠኝነት ይሰጣል እንዲሁም ኮንትራክተሩ ወጪዎችን እንዲቆጣጠር ያበረታታል።

🌟 7. የተቀናጀ የፕሮጀክት አቅርቦት (IPD) ውል፡ በአይፒዲ ውል ውስጥ ባለቤቱ፣ ስራ ተቋራጩ እና ዲዛይነር በቡድን ሆነው በጠቅላላው ፕሮጀክት ይተባበራሉ።

▶️ይህ ዓይነቱ ውል በሁሉም የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ግልጽነትን፣ ትብብርን እና ተጠያቂነትን ያበረታታል።

🌟8. የመንግስት-የግል ሽርክና (PPP) ውል፡- በፒፒፒ ውል ውስጥ አንድ የግል ተቋም የግንባታ ፕሮጀክት ለማዳበር እና ለማስኬድ ከህዝብ አካል ጋር ይተባበራል።  ይህ ዓይነቱ ውል ለትላልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጄክቶች እንደ የትራንስፖርት ሥርዓቶች ወይም የጤና እንክብካቤ ተቋማት የተለመደ ነው።

#ConstructionLaw

source :- dereje tariku law offical

https://t.me/ethioengineers1
👍22❤2🙏2🔥1👏1
💥SHEAR_WALL

⚡️Shear wall is a structural member in a reinforced concrete framed structure to resist lateral forces such as wind forces.

SHEAR WALL የአግዳሚ ወይም horizontal load ተፅዕኖዎችን የሚቋቋሙልን ግድግዳዎች ናቸው፡፡ ሺር ዎል የተባሉበትም ምክንያት የመሬት መንቀጥቀጥ በጎን አቅጣጫ ስለሚመጣና ዎሎቹ ላይ የሺር ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው ( ሺር በ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል፡፡ Horizontal force የሆኑት Earth Quake እና Wind Load  በዎሎቹ Thickness ትይዩ በሆነ አቅጣጫ ነው የሚመጡት) ፡፡

✨ሺር ዎሎች በትክክል ዲዛይን ተደርገው ትክክለኛ ቦታቸው ላይ ካልተቀመጡ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ህንጻውን አፍራሽ ግብረ ሃይል ናቸው - ስለዚህ እንዴት ማስቀመጥ እንዳለብን ቀጥለን እንመልከት፡

1) አንድ ህንፃ ላይ የሚፈቀደው ትንሹ  የሺር ዎል ብዛት ሶስት ነው፡፡ ቢያንስ-ሶስት

2) ሶስት ወይም ከዛ በላይ ሺር ዎሎች ካሉን የዎሎቹ አክሲሶች አንድ ነጥብ ላይ መገናኘት የለባቸውም

3) ትይዩ እንዲሆኑ የሚፈቀደው ቢበዛ ለሁለት ዎሎች ነው፡፡


ሺር ዎሎች ከኮለንና ቢም ይልቅ የህንፃውን ጥንካሬ ወይም Stiffness ወደ ራሳቸው የመጎተት ከፍተኛ አቅም አላቸው ፤ እንደሚታወቀው የመሬት መንቀጥቀጥ act የሚያደርገው Center of Mass ላይ ነው ፤ የመሬት መንቀጥቀጥን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ደግሞ የህንፃው ጥንካሬ ወይም Center of Stiffness የሚገኝበት ነጥብና የህንጻው Center of Mass የሚገኝበት ነጥብ በተቻለ መጠን መቀራረብ አለበት ፤ እናም ስናጠቃልለው - በትክክል ያልተቀመጡ ሺር ዎሎች የህንጻውን Center of Stiffness ወይም ጥንካሬ ወደራሳቸው ሲጎትቱት ከ Center of Mass እንዲርቅ ያደርጉታል - በመራራቃቸው የተነሳ እሽክርክሪት ፎርስ ወይም  Torsion ይፈጠራል ፡፡ Torsion ህንፃው እንዲፈርስ ያደርገዋል፡፡ የኒውተን ሶስተኛ ህግ ምን ይላል “The forces of action and reaction between interacting bodies are equal in magnitude, opposite in direction and COLLINEAR” – ሁለት ፎርሶች Collinear force የሚባሉት ደግሞ በአንድ መስመር act ሲያደርጉ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ CM ላይ Act ሲያደርግ CS ደግሞ በሺር ዎሎቹ ስለተጎተተ ሌላ ቦታ React ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ Collinear force አይደሉም ማለት ነው፡፡

ስለዚህ Newton Third Law ውድቅ ሆነ ማለት ነው፡፡
Action እና Reaction በመጠንም ይሁን በአቅጣጫ እኩል ስለማይሆኑ ትርፍ balance ያልተደረገ force ይፈጠራል

Newton First Lawን ታሳቢ በማድረግ ህንፃው Equilibrium ላይ አይሆንም ማለት ነው፡፡

የኒውተን ሁለተኛ ህግስ ማን አለው የሚል ሰው ካለ - በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የሚፈጠረው ፎርስ ማለት የህንፃው ክብደት ሲባዛ በእንቅጥቃጤው የሚፈጠር Acceleration ነው - ይህም Newton Second Law ነው::

ስናጠቃልለው ከጥፋት ለመዳን ሺር ዎልን ስናስቀምጥ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡

@ethioengineers1
👍22❤9👏4
አራዳ የከተማ የስህበት ማዕከል እንድትሆን ታላቅ አስተዋፅኦ ያለውና ቀድሞ አራዳ ገበያ በመባል ከሚጠራው የከተማው ነባር የገበያ ማዕከል አቅራቢያ የሚገኘው የመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ-ክርስቲያን ምስረታው ከአዲስ አበባ እድሜ ያልተናነሰና (ካልበለጠ) የግነቱ ታሪክም በእጅጉ ከአድዋ ድል ጋር ተያይዞ የሚነገርለት በአዲስ አበባ ከሚገኙ ቤተ-ክርስቲያኖች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው።

ቤተ-ክርስቲያኑ በመጀመሪያ ክብ የጎጆ ቅርፅ የነበረዉ ሲሆን አሁን የሚታየው የቤተ-ክርስቲያኑ ገፅታ በግሪካዊው ህንጻ ነዳፊ ኦርፋኒደስ ተነድፎ ከጣልያን በምርኮ በተገኘውና የመጀመሪያውና ታሪካዊዉ የአቢሲኒያ ባንክን በገነባው ህንጻ ገንቢ (Engineer) ሰባስቲያኖ ሙሴ ካስታኛ (Sebastiano Monsieur Kastagna- ሙሴ ቀስተኛ) መሪነት ፤ በግሪክና አርመን የግንባታ ሠራተኞች ተሳታፊነት በ1900 ዓ.ም ዳግም ታንጿል።

የህንጻ ግንባታው በባለሙያዎች ስምንት ክባዊ ቅርጽ (Octagon plan) የንድፍ መሰረትነት ተዋቅሮ ከአዲስ አበባ በተለይም ከቀበናና ከኮተቤ አካባቢዎች ተመርጠዉ በመጡና በመልክ በመልክ ተጠርበዉ በታነጹ ውብ ድንጋዮች ተገንብቶ በፈረንሳይ በተሠራ ያማረ የጣሪያ ጉልላት (dome) የተከደነ ታሪካዊ ቤተ-ክርስቲያን (Cathedral) ነው።

አራዳን ከጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ነጥሎ ማሠብ በማይቻልበት ደረጃ ቤተ-ክርስቲያኑ አሁንም በማዕከለ አራዳነት እያገለገለ ይገኛል።

ምስል ምንጭ: በሰርጌ ደውል ፣ በፋሲል ጊዮርጊስና ዴኒስ ጄራርድ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፃፉ የከተማ ታሪክ መፅሀፍት እና ናትናኤል ፍሬው

NArcHomeArchitecture

https://t.me/ethioengineers1
👍35❤13