🇪thio ቴክ
3.64K subscribers
405 photos
74 videos
647 files
589 links
🔍 ስለቴክኖሎጂ አዳዲስ ና ትምህርት አዘል መረጃዎችን የሚያገኙበት ቻናል..
ውድ የኢትዮ ቴክ ቤተሰቦች እና የቻናላችን ተከታታዮች በሙሉ
⚠️ሃሳብ ና አስተያየት => @endu12endu @yoni709 @baydis
Download Telegram
✳️ዛሬ ስለ ሳይበር ወንጀለኞች አጠር ያለች ማብራሪያ ይዤላቹ መጥቻለው።

🔻የሳይበር ወንጀለኞች በተለያዩ መንገዶች የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን ይፈፅማሉ። በሀገራችን የሳይበር ጥቃት ከተፈፀመባቸው ድርጅቶች አንዱ Ethio Telecom ነው።

🔻በ2020 በተደረገው ጥናት መሰረት የሳይበር ጥቃት የሚፈፀምበት አንዱ መንገድ የተለያዩ የ Mobile እና የ Computer Virus በማዘጋጀት የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
ምን አይነት ቫይረሶች ናቸው ለሚለው...

1️⃣. Clop Ransomware

🔻ይህ ቫይረስ በጣም አደገኛ ቫይረስ ሲሆን በኮምፒውተራችን ከገባ ቡሀላ የተለያዩ መረጃዎችን በመዝጋት እንዳንጠቀም የሚያደርግ ነው። የተዘጉትን መረጃዎች ማገኘት የምንችለው የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎቹ የሚጠይቁንን ክፍያ ከፈፀምን ቡሀላ ነው። ለምሳሌ በዚህ ቫይረሰ የተጠቁ ድርጅቶች Ethio Telecom ልንጠቅስ እንችላለን።

2️⃣ Hidden Ransomware

🔻ይህ ቫይረስ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር በEmail የሚላክና በየትኛውም Antivirus ሊታይ የማይችል ቫይረስ ነው። ይህም የተለያዩ መረጃዎችን በመዝጋት እንዳንጠቀም የሚያደርግ ነው። የተዘጉትን መረጃዎች ማገኘት የምንችለው የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎቹ የሚጠይቁንን ክፍያ ከከፈልን ቡሀላ ነው።

3️⃣. Zeus Gameover

🔻ይህ ቫይረስ በኮምፕዩተራችን ከገባ ቡሀላ የተለያዩ ሚስጥራዊ መረጃዎችን (Email, Bank account detail Info bla bla) በመስረቅ ለተፈለገው ሰው መረጃዎችን Email የሚያደርግ አደገኛ ቫይረስ ነው።

4️⃣. News Malware Attacks

🔻 ይህን ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችሁ እንዲገባ ለማድረግ የሚጠቀሙበት መንገድ አደገኛ ያደርገዋል።

‼️ማሳሰቢያ ‼️

⚠️በ Email የሚላኩ መልዕክቶችን ከማን እንደተላኩ ካላወቁ መልዕክቱን ይጠንቀቁት።
©Tech Amo
➜ Join Us ፦ @Ethiotec
✳️ ሰላም ውድ የ E Ethio Tech ቤተሰቦች ዛሬ ጥቁር መርብ (Dark Web) ምንድን ነው? የሚለውን እናያለን።

🔻Dark Web ማለት ኢንክሪፕትድ (ድብቅ) የሆነ የ Online አካል ሲሆን በማንኛውም የሰርች መሳሪያ (search engine) ኢንዴክስ ሊደረግ የማይችል የዌብ አይነት ነው። ዳርክ ዌብ አንዳንዴ ዳርክ ኔት (Dark net) እየተባለም ይጠራል። ዳርክ ዌብን ብዙወን ጊዜ ሰዎች የሚጠቀሙበት ሚስጥራዊ ፋይሎችን ወይም ፕራይቬሲን ለመጠበቅ ነው። በማንኛውም አይነት ብሮውዘር (Browser) ወደ ዳርክ ዌብ መግባት አንችልም።የተወሰኑ እንደ Tor Browser አይነት ብሮውዘሮች ያስፈልጉናል።

📌የ Dark Web ጥቅሞች

🔻Dark Web የብዙ ሰዎችን ሚስጥር እና የግል ጉዳያቸውን ለመጠበቅ ያረዳል። ሌላ አካል እንዳያይባቸው የሚፈልጓቸውን መረጃዎች በ Dark Web ያዘዋውራሉ። ከወንጀል የነጹ ሰዎች በወንጀለኦች እንዳትጠቁ እንደ የፖለቲካ እና የጤና መረጃቸውን በ Dark Web ያስቀምጣሉ። ፖሊሶች በድምብቅ ወንጀለኞችን ለመከታተል ይረዳ ማክንያቱን መደበኛ የፖሊስ ኢንተርኔት አካውንቶች Hack ሊደረጉ ስለሚችሉ።

📌የ Dark Web ጉዳቶች

🔻 አንዳንዴ Dark Web በጣም አደገኛ የሚባሉ ወንጀሎችን ለመፈጽም ሰዎች ይጠቀሙበታል። ለምሳሌ ፦ ዳርክ ዌብ እና ክሪፕቶከረንሲን (የኦንላየን ገንዘብ ክፍያ) አንድላይ በመጠቀም ሰዎችን ለመግደል ቅጥረ ነፍሰ ገዳዮች ይቀጠሩበታል። አንዳንድ አካላት የሌሎች ሰዎችን ግላዊ ሚስጥር ፋይሎች ፣ ፎቶዋች እና ቪዲዮዎች ይፋ አውጥተው Dark Web ላይ ይበትኑባቸዋል። ሌላው የመሳሪያ እና የ አደንዛዥ እፅ ንግድም ይካሄድበታል።

🔻እኛም ለትምርታዊ አላማዎች እና ለጠቃሚ ነገሮች ብቻ እንድትጠቀሙባቸው የሚከተሉትን የ ሰርች መሳሪያዎች (Search Engine) ከነ ሊንካቸው በቀጣይ የምንለቅላቹ ይሆናል።

‼️ ነገር ግን Dark Web ላይ ለመግባት ከባድ እና አደገኛም ነው። ከመግባታቹ በፊት ጥንቃቄ ማድርግ አለባቹ እንዲሁም ቆም ብላቹ ልታስቡ ይገባል።

© Mame Tech

➜ Join Us ፦ @Ethiotec
🍭 #10 ጠቃሚ የሆኑ አፕልኬሽኖች ልጠቁማችሁ!🙏

1.➡️ #ትሩኮለር/True Caller/ ይህ አፕ ማንኛውም ሰዉ ወደ ሞባይላችን ሲደውል በሶሻል ሚድያ የተመዘገበው ስሙ ያሳየናል: ማለትም ስልኩ በሞባይላችን ባንመዘግበዉም የደዋዪ ስልክ ስም ለማወቅ ይጠቅመናል!

2➡️ #ሴክሪቲ 360 /360 Security/
ይህ ጸረ ቫይረስ ስልካችንን ከቫይረስ፣ ማል ዌር እና ትሮጃኖች በመከላከል ረገድ የተዋጣለት አፕ ነው። በዚህም ከስልካችን ቀርፋፋነት እስከ ሙሉ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ብልሽት የሚያደርሱ የአንድሮይድ ቫይረሶችን አስቀድሞ በመከላከል ስልካችንን ከችግር ይጠብቅልናል።

3➡️ #ዋይፋይማፕ/WiFi Map/
በሆቴሎች ወይም በሌሎች ስፍራዎች የምናገኛቸው አብዛኞቹ ዋይ ፋይ ኔትወርኮች በይለፍ ቃል (password) የተዘጉ ናቸው። ይህም ማለት የዋይ ፋዩ ፓስወርድ ከሌለን ዋይ ፋዩን ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው። ይህ አፕሊኬሽን በአለማችን የሚገኙትን በሆ ፋዮች ሁሉንም በሚባል መልኩ ፓስወርዳቸውን በቀላሉ ይነግረናል። ከእኛ የሚጠበው አፑን ከጫንን በኋላ ከሚመጣልን የአለም ከርታ ላይ ኢትዮጵያን፤ ከዚያም የምንፈልገውን ከተማ መምረጥ ሲሆን በከተማው ውስጥ ያሉትን ዋይ ፋይ ኔትወርኮችና ፓስወርዳቸውን ያመጣልናል። ዋይ ፋይ ኔትወርክ በአቅራቢያችሁ ኖሮ ፓስወርድ ለገደባችሁ ሁሉ ቀላል መፍትሄ ነው።

4➡️ #ዊስትል ፎን ፋይንደር/Whistle Phone Finder/
ለመሆኑ ቤት ውስጥ ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ ጠፍቶዎት ያውቃል? የሚያውቅ ከሆነ ፍለጋውንና ከሌሎች ስልክ ተውሶ ወደራስ ስልክ ለመደወል የሚደረገውን ድካም በደንብ ያውቁታል። ይሄንን አፕሊኬሽን ስልክዎት ላይ አስቀድመው ከጫኑ, ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ ሲጠፋዎት ከእርስዎ የሚጠበቀው ማፏጨት ብቻ ነው። የፉጨትዎ ድምጽ አፕሊኬሽኑን በማንቃት ስልክዎ የመጥሪያ ደወል እንዲያሰማ በማድረግ ስልኩን በቀላሉ በድምጹ ተመርተው እንዲያገኙት ይረዳዎታል።

5.➡️ #ኔክስትዶር/NextDoor/ ይህ ሞባይል አፕሊኬሽን ከጎረቤቶቻቸን ለማዉራት የሚጠቅመን አፕ ነው ይህንን አፕ ተጠቅመን ከጎረበቶቻቸን ጋር መረጃ ለመለዋወጥ እርዳታ ለመፈለግና ተመሳሳይ ስራዎች ለማደረግ ይጠቅማል! ይህንን ስራ ለመስራት ኢንተርኔት አያስፈልገዎም::

6.➡️ #ኢንስታፔፐር/Instapaper/ ይህ ገራሚ አፕ በሞባይላችን የምናገኛቸው መረጃዎች ሴቭ ለማድረግና በፈለግነው ጊዜ ለማንበብ ወይም ለመመለከት ይጠቅመናል

7.➡️ #ዪቱዪብኪድስ/YoutubeKids/ ይህ አፕ የዪቱብ አፕ በጎግል በራሱ የተሰራ ሲሆነ ለልጆች ተብሎ የተሰራ አፕ ነው:: በዚህ አፕ ለልጆች የሚሆኑ ሙዚቃ የትምህርት መረጃዎች ቪድዮዎች ወዘተ ይገኛሉ! ከ18 አመት ለሆኑ ይህንን አፕ ብጨንላቸው ተመራጭነው::

8.➡️ #ለርንሲፕላስፕላስ/Learn C++/ ይህ አፕ ሲፕላስፕላስ ለመማር ለሚፈልጉ በጣም ምርጥ አፕ ነው! በሞባይልዎ ሁነው ሲፕላስፕላስ በመማር የተሻለ ፕሮግራመር ይሁኑ::

9.➡️ #IDM download manager
በኮምፒውተራችን ፋይሎችን በፍጥነት ዳውንሎድ ለማድረግ የምንጠቀምበት IDM, በቅርቡ ደግሞ ለአንድሮይድ ስልኮች የሚያገለግል አፕ ለቋል። IDM የስልካችን ብሮውዘር ዳውንሎድ ለማድረግ የሚወስድበትን ጊዜ በእጅጉ በመቀነስ የምንፈልገውን ፍይል በአጭር ጊዜ ያወርድልናል።


10.➡️ #ዲስክዲገር/DiskDigger/
ዲስክዲገር ከስልካችን በስህተት ያጠፋናቸውን ፎቶዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮዎችና ሌሎች ፋይሎቻችንን የስልኩን ጥልቅ ዳታ ስቶሬጅ በማሰስ ይመልስልናል። በጣም አስፈላጊ ፍይሎቻችንን በስህተት ወይም በሌላ ሰው delete ከተደረጉብን ዲስክዲገር አፕ መፍትሄያችን ይሆናል ማለት ነው። ➜ Join Us ፦ @Ethiotec
Yesterday Samsung has announced a range of new devices at its Galaxy Unpacked event, including the Galaxy S21, S21+, and S21 Ultra, as well as Galaxy Buds Pro earphones and Galaxy SmartTag item trackers.

Samsung's latest Galaxy S21 series of smartphones feature a new design, edge-to-edge Dynamic AMOLED 2X Infinity-O display with adaptive 120Hz refresh rate, and 8K video recording. The Galaxy S21 has a lightweight design and a compact 6.2-inch display, while the Galaxy S21+ has a 6.7-inch display and a larger battery.

S21 Ultra, which delivers an "intelligent pro-grade camera system," improved display, Wi-Fi 6E9, ultra-wideband capabilities, and better performance. The S21 Ultra also brings the popular S Pen experience to the Galaxy S series for the first time.

Pricing
S21 starting from $799.99 or 31,161 ETB
S21 + starting from $999.99 or 38,961 ETB
S21 Ultra starting from $1,199.99 or 46,761 ETB

We will provide the details specifications later on

@Ethiotec
#አሪፍ_አፕሊኬሽን_ላስተዋውቃቸሁ

ይህ አፕሊኬሽን Signal ይባላል፡፡

Signal አፕሊኬሽን እንደ WhatsApp፤ Facebook Messenger፤ Skype፤ Telegram…ወዘተ ፈጣን መልእክት(ቴክስት) መላላኪያ አፕሊኬሽን ነው፡፡

Signal አፕሊኬሽን ከሌሎቹ (WhatsApp፤ Facebook Messenger፤ Skype፤ Telegram) የሚለየው ሰዎች በ Signal የሚለዋወጡዋቸው ሚስጥራዊ መልእክቶች ከሰዎቹ በስተቀር ሌላ ሶስተኛ ወገን መልእክቶችን ማየትም ይሁን ማግኘት አይችሉም፡፡ በSignal የምንለዋወጠው መልእክት ሙሉ ለሙሉ አንድ መቶ ፐርሰንት ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፡፡(End-to-end encrypted)

ለምሳሌ እስካሁን ድረስ የምናውቀው በWhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች ሙሉ ለሙሉ ሚስጥራዊ እንደሆኑ ነበረ፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ በ በWhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች በሙሉ ፌስቡክ ኩባንያ ማወቅ ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ Edward Snowden እና Elen Musk የመሳሰሉ ተዋቂ ሰዎች ከWhatsApp፤ Facebook Messenger፤ Skype፤ Telegram ይልቅ Signal አፕሊኬሽንን እንድንጠቀም ይመክራሉ፡፡

Signal አፕሊኬሽን ለAndroid፤ iPhoneና iPad እና ለኮምፒውተር እነዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም የሚያስፈልገው ሞባይል ስልክ ቁጥር ብቻ ነው፡፡

በSignal አፕሊኬሽን አጭር መልእክቶችን ከመላላክ ባለፈ ግሩፕ መፍጠር ያስችላል፤ቪዲዮ ኮል አለው፤የተለያዩ ስቲከሮች አሉት፤ፋይል ማስተላለፍ ችላል..ወዘተ፡፡

የSignal አፕሊኬሽን የሚሰጣቸው ለየት ያሉ ሶስት ጥቅሞቸን ልንገራችሁ፡-

1ኛ፡- Block Screenshot

ለምሳሌ ከአንድ ሰው ጋር በFacebook Messenger የተፃፃፋችሁትን መልእክት ያ ሰው መልእክቱን በስልኩ ስክሪን ሻት በማድረግ መረጃ ሊዝባችሁ ይችላል፡፡ Signal ላይ ግን ማንም ሰው የተፃፃፋችሁትን መልእክት ስክሪን ሻት እንዳያደርግ ብሎክ ማድረግ ይቻላል፡፡

2ኛ፡- Blur Faces

በSignal ማንነታችሁን የሚገልፅ ፎቶዎች ልትላላኩ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ፎቶዋችሁን የላካችሁለት ሰው ቢያስፈራራችሁ-ለምሳሌ ሼር አረገዋለሁ ወይም ለቤተሰባችሁ አሳያለሁ…እያለ ቢያስፈራራችሁ Signal ሴቲንግ ውስጥ ገብታችሁ የላካችሁትን ፎቶ ወይም ፎቶዎች ምስላችሁ እንዳይታይ (Blur )ማድረግ ይቻላል፡፡

3ኛ፡-Disappearing Messages

በSignal አፕሊኬሽን የምንለዋወጣቸው መልእክቶች የላክንለት ሰው ካነበበው በሁዋላ መልእክቶቹ ከሰውዬው ስልክ ላይ እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡

Signal አፕሊኬሽንን ተጠቀሙት፡፡ትወዱታላችሁ፡፡
Signal አፕሊኬሽንን ፕሌይስቶር፤አፕስቶር ላይ በነፃ ታገኙታላችሁ፡፡
Credit Dotcomtvshow
#ሼር_ይደረግ
👍1
ከInstagram ላይ ፎቶ እና ቪድዮ እንዲሁም ፕሮፋይል በቴሌግራም እንዴት እንደምናወርድ ?? እንዲሁም በpython በመጠቀም እንዴት ማውረድ ይቻላል። የሚለውን በቅርቡ ከእነ ኮዱ post እናደርጋለን።

Like & share ያድርጉ።


@ethiotec
መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ

@ethiotec
Sundar Pichai ማን ነው ?


@Ethiotec
ሕይወት እና ትምህርት

Pichai የተወለደው በሕንድ የሚገኘው ማዱራይ ውስጥ ነበር፡፡ Pichai ያደገው ባለ ሁለት ክፍል አፓርታማ ውስጥ ነበር፡፡ ዲግሪውን ከአይቲ ካራግራጉር በብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ያገኘ ሲሆን ከዚያ ተቋምም የማእረግ ተመራቂ ነበር፡፡ በማቴሪያል ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ከስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ M.S እንዲሁም ከፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ከዋርተን ትምህርት ቤት MBA

ስራ

Pichai Applied Materials እና McKinsey ይሠራ ነበር. Pichai Google የተቀላቀለው እ.ኤ.አ. በ 2004 ሲሆን Google Chrome እና Chrome OSን ጨምሮ Google የደንበኛ Software ምርቶችን የምርት አያያዝ እና የፈጠራ ስራ ጥረቶችን የመራቸው እንዲሁም Google Drive በአብዛኛው ተጠያቂ ነው ፡፡ እንደ Gmail እና Google Map ያሉ የሌሎች መተግበሪያዎች ስራ በበላይነት ሲቆጣጠር ነበር ፡፡ እ.ኤ.አ. March 13 2013 Pichai በተቆጣጠራቸው የጉግል ምርቶች ዝርዝር ውስጥ Androidን ጨምሯል ፡፡ Pichai, 2015 August 10 ላይ የ Google ቀጣዩ ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ተመርጧል ፡፡ Pichai ዓመታዊ ደመወዝ ከተቆጣጠሪዎችና proxy statement መግለጫ መሠረት, 2019 በ $ 650.000 ነበር. Google ዘንድሮ ወደ 2 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ይደረግለታል ብሏል ፡፡ አሁን Pichai 48 አመቱ ነው ፡፡


@Ethiotec
👍1
You wrote an amazing Python application and showed it to your friend. He is impressed and wants to use it on his system. He neither has Python installed on his system and nor he has ever worked on it. You are stuck!!!

Convert Your Python Code into a Windows Application (.exe file)


To convert the Python code into an executable file, we will be using Pyinstaller package. Use the standard ‘pip install’ command to install this package.

#### Install Command

pip install pyinstaller

The Actual Task
Let’s go step by step to convert the Python file to a Windows executable:

Open the command prompt


Change folder location to the location of your Python code

#### Change Folder Location

cd folder_location

Use the following command to convert the Python file into a Windows executable

#### Command for conversion

pyinstaller --onefile filename.py


Replace " filename.py " to your python file name

The above code will create a single executable file with the same functionality as your python code. The executable file will be available in a new folder, dist, which will be available at the same location as your Python script.

#Python #Tip

@Ethiotec
WHAT WILL BE THE OUTPUT OF THE FOLLOWING PYTHON CODE?

x = [12, 34] print(len(list(map(int, x))))
Anonymous Quiz
48%
Error
22%
0
13%
1
17%
2
Tech Camp Ethiopia: Launching Program
📅 January 22, 2021 at 2pm
📍 Virtual

A tech boot camp is exactly what it sounds like – an encompassing program where we learn to either cultivate new tech skills or improve our current strengths. The Tech Camp Ethiopia 2020 will be a series of 6 programs that encourage all of the youths – makers, engineers, students, computer scientists, inventors, innovators – are making things that are not just nice to have, but that people need. The main goal of this program is to Create Job opportunities for youths through cultivating and capacity building in cutting-edge technologies within a short period of time.

https://gdg.community.dev/events/details/google-gdg-addis-presents-tech-camp-ethiopia-launching-program/
.

From #EventsEthiopia

@Ethiotec
STUXNET የአለማችን የመጀመሪያው የCyber መሳሪያ

እንደ ጎርጎሮስያኑ ዘመን አቆጣጠር 2010 ዓ.ም፣ በኢራን የናታንዝ ኒዩክሌር ማብለያ ጣቢያ ዩራኒየምን ለማብላላት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ እጅግ በጣም ውድ የሆኑ ሴንትሪፊዩጆች ባልታወቀ ምክንያት ከልክ በላይ እየተሽከረከሩ ተሰነጣጥቀው ከጥቅም ውጭ መውጣት ጀመሩ።

ይህ ግራ ያጋባቸው የ Iran ሳይንቲስቶች ስለጉዳዩ ማድረግ የቻሉት ነገር አልነበረም፤ በመጨረሻም አብዛኛዎቹ ሴንትሪፊውጆች በመውደማቸው የናታንዝ ኒውክሌር ማብለያ ጣቢያ ላልተወሰነ ጊዜ ስራ እንዲያቆም ተደረገ።

አንድ ቀን ረፋድ ላይ VirusBlokAda የተባለ ትንሽ የanti virus አቅራቢ ካምፓኒ ውስጥ የሚሰራ ሰው ኢራን ከሚገኝ ደምበኛቸው የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል፣ ደምበኛው ኮምፒተሩን በትክክል አብርቶ መጠቀም እንዳልቻለና ባበራው ቁጥር መልሶ እየጠፋ መቸገሩን ይነግረዋል።

...
@ethiotec
👍1
[የቀጠለ]

ይሄን የሰማው ሰራተኛ የሰውየውን ኮምፒዩተር በደምብ ከመረመረ በኋላ ኮምፒውተሩ በሆነ ቫይረስ መጠቃቱን ይገነዘባል፣ ከዛም ተጨማሪ ምርመራ ካደረገ በኋላ ኮምፒዩተሩን እንደዛ ያደረገውን ቫይረስ ለማግኘት ቻለ።

በቀጣይ ቀናትም በኢራን ኒውክሊየር ማብለያዎች ውስጥ የነበሩ ኮምፒዩተሮች ላይ በተደረገ ምርመራ ይህ ቫይረስ በአብዛኛዎቹ ላይ እንደሚገኝ ተረጋገጠ፣ ወራትን በፈጀ ተጨማሪ ምርመራም፥ የናታንዝ ኒውክሌር ማብለያን ሴንትሪፊውጆች እንዳልነበር ያደረጋቸው ይህ የኮምፒዩተር ቫይረስ መሆኑ ተረጋገጠ። ያ ቫይረስ በኮምፒዩተር ተመራማሪዎች Stuxnet የሚል ስያሜ ተሰጠው።

ነገር ግን ለኮምፒዩተርም ሆነ ለኒውክሊየር ተመራማሪዎቹ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች ነበሩ ነበሩ፣

1. አንድ የኮምፒዩተር ቫይረስ እንዴት የኒውክሌር ማብለያን ያህል ነገር ከጥቅም ውጭ ሊያስወጣ ይችላል?

2. እንደዚህ አይነት አደገኛ እና እጅጉኑ የረቀቀ ቫይረስ የትኛው ግለሰብ ወይም ቡድን ነው ሊሰራ የሚችለው?

ክፍል ሁለት ይቀጥላል

@ethiotec
🇪thio ቴክ via @like
ከInstagram ላይ ፎቶ እና ቪድዮ እንዲሁም ፕሮፋይል በቴሌግራም እንዴት እንደምናወርድ ?? እንዲሁም በpython በመጠቀም እንዴት ማውረድ ይቻላል። የሚለውን በቅርቡ ከእነ ኮዱ post እናደርጋለን። Like & share ያድርጉ። @ethiotec
ከinstagram ላይ እንዴት profile pic , stories , ፖስት የተደረጉ video እና photo ማውረድ እንችላለን ???

🔅pro pic እና stories

1. @Instasave_bot ላይ ሄዳቹ start ብላቹ bot ታስጀምሩታላቹ
2. ቀጥሎ browser ከፍታቹ www.instagram.com
3. login አድርጋቹ
4. ከዛ ለማውረድ የምትፈልጉትን የሰውዬውን ወይም የራሳቹ ላይ account ትገባላቹ
5. ከዛም ቀጥሎ የገባቹበት account ላይ ከላይ ያላውን copy ታደርጉታላቹ ......
6. @Instasave_bot ላይ link paste ታደርጉታላቹ
7. ከዛም pro pic ያመጣላቹዋል ሰውየው story post አድርጎ ከሆነ ከpro pic በተጨማሪ story ላይ ያሉትን በሙሉ ያመጣላችዋል።

🔅Video እና photo

1. @Instasave_bot ላይ ሄዳቹ start ብላቹ bot ታስጀምሩታላቹ
2. ቀጥሎ browser ከፍታቹ www.instagram.com
3. login አድርጋቹ
4. ከዛ ለማውረድ የምትፈልጉትን ፎቶ ወይም ቪድዮ ላይ 3 ነጥብ ላይ ትነኩት ና copy link የሚለውን ትመርጡለታላችሁ
5. @Instasave_bot ላይ link paste ታደርጉታላቹ
6. ከዛም ፎቶ ወይም ቪድዮን ፋይሉን ይልክላችዋል።

⚠️ ቦቱ አንዳንድ ጊዜ story ላይልክ ይችላል።

🙏መልካም ሰንበት 🙏

@ethiotec
👍1