“የሕዝብ መናቅ፣ የሕዝብ አለመከበር፣ የሕዝቡ ፍትሕ ማጣት፣ ባመናቸው ሰዎች መካዱ በጣም ያሳስበኛል” ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል
በራሱ የዩቲዩብ ቻና የኮሜዲ ሥራዎችን እያቀረበ የሚገኘው ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ጉዳዮች እንደሚያሳስቡት ገልጿል።
"ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማንሳት የአንድ ኪነጥበብ ውስጥ ያለ ሰው ኃላፊነት ነው ብዬ አምናለሁ የሚለው ምናለ፣ በሥራዎቹ ያሳስቡኛል የሚላቸውን ጉዳዮች እንደሚያነሳ፣ በሳቅ የተዋዛ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ተናግሯል።
ሳተየር ዘውግ ያለው የኮሜዲ ሥራው በሀገሪቱ የሚከናወኑ ጉዳዮችን እያነሳ ሳቅ እንደሚፈጥር ገልጿል።
ኮሜዲያን ምናለ በነበረው ቃለ መጠይቅ "እንደ ዜጋም ሆነ እንደ አንድ ኪነጥበብ ውስጥ እንዳለ ሰው ፖለቲካው ውስጥ ባሉ ሰዎች የሕዝብ መናቅ በጣም ያሳስበኛል፤ የሕዝብ አለመከበር፣ የሕዝቡ ፍትሕ ማጣት ያሳስበኛል ብሏል። አክሎም
ሕዝቡ “ባመናቸው ሰዎች መካዱ በጣም ያሳስበኛል፤ ማንነት ተኮር ጥቃቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መቆሚያ ያጡ ጦርነቶች እነዚህ ሁሉ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ በጣም ያሳስበኛል" በማለት ስሜቱን አጋርቷል።
"እንደ አንድ ግለሰብ [ለሚያሳስቡኝ ጉዳዮች] መፍትሔ ብሰጠው ደስ ይለኛል። ብችል እነዚህን ነገሮች ማቆም መከልከል ብችል ደስ ይለኛል። ያንን ነገር ለማድረግ ግን አቅሙ የለኝም። አቅሜ ምንድን ነው? በጉዳዩ ላይ ማውራት ወይ ማፌዝ ነው።
እንደ ሳታየር ኮሜዲ ፊት ላይ ሳቅ መፍጠር አእምሮ ላይ ደግሞ መልዕክት ማስቀመጥ ነው ሃሳቤ” ሲል የኮሜዲ ሥራውን ዓላማ አስረድቷል።
ለተመልካች በሚያቀርባቸው የኮሜዲ ሥራዎች ሳቢያ "የሆኑ ነገሮች ሊመጡ እንደሚችሉ እረዳለሁ ወደፊት የሆኑ ችግር ሊያመጡብኝ እንደሚችሉ ይገባኛል" ሲል ስጋቱን አጋርቷል
#Ethiopia #MinaleYaregal

የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና እየወሰዱ ነው
ሚኒስትሮች፣ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ወታደራዊ ሥልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያስታወቁት ኢትዮጵያ ከሩሲያ አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች እና አራት የኤስ-400 የአየር መከላከያ ስርዓት ባትሪዎችን መረከቧን ከተናገሩ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።
ዐቢይ ሥልጠናውን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ባለሥልጥናቱ ሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው ብለዋል።
“ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን” ሲሉ ጽፈዋል።
#Ethiopia #AbiyAhmed #PMAbiy

የማንችስተር ዩናይትድ የቁልቁለት ጉዞ እንደቀጠለ ነው - 9 ጨዋታ ያለ ድል
ቸልሲ 2-0 ማንችስተር ዩናይትድ
የዚህ ክለብ ችግር ምን ይሆን?
#PremierLeague #ManchesterUnited #Chelsea

አንጋፋው ሪፖርተር ጋዜጣ ታገደ
ሪፖርተር ጋዜጣ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታወቀ።
በ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሴንተር ኃ.የተ.የግል ማህበር ስር በሚታተሙ ሪፖርተር አማርኛ፣ ዘ ሪፖርተር እግሊዝኛ እንዲሁም ኢትዮጵያን ሪፖርተር የዲጂታል ፕላትፎርም ላይ የሚሰራጩ ይዘቶች ላይ ከአንድ ዓመት በላይ በተደረገው የይዘት ክትትል ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ስነ ምግባር ጥሰቶች በሚዲያው መፈጸሙ ተረጋግጧል ሲል ባለሥልጣኑ አስታውቋል።
በሀገር ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውድ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸውን ርዕሰ ጉዳዮች በማንሳት ከሚሰጣቸው አርዕስት/Headline/ ጀምሮ ማጮህ /Sensationalize/፣
በተለያዩ መድረኮችና ሪፖርቶች ላይ የሚገኙ ሀገራዊ መረጃዎችን አጠቃላይ አውዱን ተገንዝቦ መረጃን ከማድረስ ይልቅ በቁንጽል እይታ ላይ በመዘገብ በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬና ብዥታን መፍጠር፣ የውጭ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት፣
የሀገር ገጽታን የሚያጠለሹ፣ የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትን የሚጎዱ፣ የህዝቦችን አብሮነትና እሴት የሚሸረሽሩ መረጃዎች ማሰራጨት፣ ሚዛናዊነት የጎደለው አድሏዊ ዘገባዎችን ማሰራጨት፣ ከራስ ጥቅምና የግል ፍላጎት በመነሳት ባልተረጋገጠ መረጃ የተቋማትን ስምና ገጽታ ማጠልሸት የሚሉ ክሶች በጋዜጣው ላይ ቀርበዋል።
በዚህ ምክንያት የህግና የሙያ ስነ ምግባር ግዴታዎችን ተሟልተዉ ተግባራዊ እስኪደረጉ ድረስ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱ ከሰኞ ጥቅምት 23/2019 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከህትመትና ከስርጭት ሙሉ በሙሉ ታግዶ እንዲቆይ ተወስኗል ሲል በመግለጫው አስፍሯል።
#Ethiopia #EthiopianReporter #EthiopianPress #PressFreedom

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አሸነፈች
ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቷ ሜላት ኪሮስ በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አሸነፈች። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት የኮሎራዶ ዲስትሪክት ተወካይ ሆና ለመመረጥ በቅታለች።
ሜላት ከዚህ ቀደም ኮሎራዶ ግዛት በተደረገ የአካባቢ ቅድመ ምርጫ ማሸነፏ ይታወሳል።በህጻንነቷ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የ29 ዓመቷ ሜላት ምርጫው በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሆናለች።
በጥር ወር ቃለ መሃላ በመፈጸም ስራዋን እንደምትጀምር ይጠበቃል። ሕክምና ለሁሉም፤ ቅድሚያ ለቤት፣ የህጻናት እና አረጋዊያን እንክብካቤ፤ የስደተኞች የሚያሳድደው መሥሪያ ቤት መዝጋትን እና የጦር መሣሪያ ሽያጭ ዕገዳን ቅድሚያ እንደምትሰጥ በምርጫ ቅስቀሳዋ ወቅት ደጋግማ ገልጻለች።
#Ethiopia #EthiopianAmerican #MelatKiros #USMidterms

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካን ጥብቅ መረጃዎች ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አመነ
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አብርሃም ተክሉ ለማ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የአሜሪካን ምስጢራዊ መረጃ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማስተላለፍ በማሴር ወንጀል በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ መሆኑን አመነ።
የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሜሪላንድ የሚኖረው የ53 ዓመቱ አብርሃም ተክሉ ለማ፣ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2021 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ከፍተኛ ሚስጥራዊነት ያላቸውን የአሜሪካ መረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለማስተላለፍ በተደረገ ሴራ ውስጥ መሳተፉን አምኗል።
አብርሃም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳዳሪነት የነበረውን የይለፍ ፈቃድ በመጠቀም፣ ደህንነቱ ከተጠበቀ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ምስጢራዊ መረጃን ጨምሮ የብሔራዊ መከላከያ መረጃን በሕገወጥ መንገድ በማውጣት ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች አስተላልፏል" ሲሉ አቅቤ ሕጉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም አብርሃም ላይ ስለቀረበው ክስ ምንም ያለው ነገር የለም።የፍትህ መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ በቀረቡ የግንኙነት ሰነዶች ውስጥ አብርሃም ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በጦርነት ላይ በነበሩ ታጣቂ ቡድኖች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ሲያበረታታ እንደነበር ያመለክታሉ።
አብርሃም ታህሳስ 9/2014 ዓ.ም. ለአንድ ተባባሪው ባስተላለፈው መልዕክት "እነዚህን ሰዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት አለብን። አለበለዚያ በኢትዮጵያ መቼም ሰላም አይኖርም" ሲል መጻፉ በፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ተካትቷል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
#Ethiopia #EthiopianAmerican #AbrahamTekluLemma

ማንችስተር ዩናይትድ ማይክል ካሪክን አሰናበተ። በ3 አመት ውስጥ 3ኛው ተባራሪ አሰልጣኝ መሆናቸው ነው። ቀጣዩ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዩናይትድ ደጋፊዮች ምን ታስባላችሁ?
#ManchesterUnited #MichaelCarrick #PremierLeague

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አርሲ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነቱን ወሰደ
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) በኦሮሚያ ክልል ሽርካ ዞን ከ40 በላይ ሰዎች በተገደሉበት የጥቅምት ወር ጥቃት ወቅት "እርምጃ" መውሰዱን አረጋገጠ።
ይሁንና፣ በታጣቂው ቡድኑ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት ሲቪሎች ሳይሆኑ በጸጥታ አካላት "የተመለመሉ" እና "መደበኛ ነዋሪ የሆኑ የትርፍ ጊዜ ተዋጊዎች" ናቸው ብሏል።
በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ይህንን ያለው በጥቅምት አጋማሽ በቀድሞው አርሲ ዞን ውስጥ በሚገኘው ሽርካ ወረዳ ቦርቢና ጮሌ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ ትናንት ሰኞ ኅዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው።
በወቅቱ ሕፃናትን ጨምሮ ከ 40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋኀዶ ቤተክርስቲያን ጥቃቱ በምዕመኖቿ ላይ የተፈጸመ መሆኑን መግለጿ አይዘነጋም።
#Ethiopia #Oromia #Arsi #OLA

ድምፃዊ ሚኪያስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ድምፃዊ ሚኪያስ የሙዚቃ ሥራ ለማቅረብ በሔደበት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
አርቲስቱ ዘቢዳር ቢራ ባዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ወልቂጤ ከተማ ከደረሰ በኋላ ድንገተኛ ሕመም እንዳጋጠመው ተገልጿል።
የሙያ አጋሮቹ አርቲስቱን ለሕክምና ወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታል ቢወስዱትም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
ድምፃዊው “ግርማ ሞገሴ”፣ “የኔ ደሃ”፣ “የፍቅር ስጦታ” እና “አሁን አሁን” በተሰኙ የሙዚቃ ሥራዎቹ በሰፊው ይታወቃል።
“ሰላም አላት” እና “10 ከ10” የተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችንም አበርክቷል።
#Ethiopia #EthiopianMusic #MikiyasCherinet

በጋምቤላ ክልል 190 ጠርሙስ የጂን አልኮል መጠጥ ተወገደ
በጋምቤላ ክልል በአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ 190 ጠርሙስ የጂን አልኮል መጠጥ መወገዱ ተገለጸ።
እርምጃው የተወሰደው የወረዳው ፖሊስ “የተከለከለ የአልኮል መጠጥ” ይዘው የሚዘዋወሩ ግለሰቦች ላይ ክትትል አድርጎ ባገኘው የመጠጥ ምርቶች ላይ ነው።
የአልኮል መጠጦችን በሚያዘዋዉሩ ግለሰቦች ላይ ወረዳው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ አሮፖ ኡበንግ ተናግረዋል።
“አልኮል ለጤና ጠንቅ ነው መሆኑን” የገለጸው የወረዳው ፖሊስ ኅብረተሰቡ አልኮል የሚያዘዋውሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
#Gambella #Ethiopia