EthioTube
✔
7.86K subscribers
10.4K photos
57 videos
7 files
3.3K links
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
Download Telegram
የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች እንዴት ናችሁ? 🙂

#ChampionsLeague #ManchesterUnited #Roma #Football
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አሸነፈች

ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቷ ሜላት ኪሮስ በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አሸነፈች። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት የኮሎራዶ ዲስትሪክት ተወካይ ሆና ለመመረጥ በቅታለች።

ሜላት ከዚህ ቀደም ኮሎራዶ ግዛት በተደረገ የአካባቢ ቅድመ ምርጫ ማሸነፏ ይታወሳል።በህጻንነቷ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የ29 ዓመቷ ሜላት ምርጫው በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሆናለች።

በጥር ወር ቃለ መሃላ በመፈጸም ስራዋን እንደምትጀምር ይጠበቃል። ሕክምና ለሁሉም፤ ቅድሚያ ለቤት፣ የህጻናት እና አረጋዊያን እንክብካቤ፤ የስደተኞች የሚያሳድደው መሥሪያ ቤት መዝጋትን እና የጦር መሣሪያ ሽያጭ ዕገዳን ቅድሚያ እንደምትሰጥ በምርጫ ቅስቀሳዋ ወቅት ደጋግማ ገልጻለች።

#Ethiopia #EthiopianAmerican #MelatKiros #USMidterms
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካን ጥብቅ መረጃዎች ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አመነ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው አብርሃም ተክሉ ለማ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የአሜሪካን ምስጢራዊ መረጃ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማስተላለፍ በማሴር ወንጀል በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ መሆኑን አመነ።

የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሜሪላንድ የሚኖረው የ53 ዓመቱ አብርሃም ተክሉ ለማ፣ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2021 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ከፍተኛ ሚስጥራዊነት ያላቸውን የአሜሪካ መረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለማስተላለፍ በተደረገ ሴራ ውስጥ መሳተፉን አምኗል።

አብርሃም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳዳሪነት የነበረውን የይለፍ ፈቃድ በመጠቀም፣ ደህንነቱ ከተጠበቀ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ምስጢራዊ መረጃን ጨምሮ የብሔራዊ መከላከያ መረጃን በሕገወጥ መንገድ በማውጣት ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች አስተላልፏል" ሲሉ አቅቤ ሕጉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም አብርሃም ላይ ስለቀረበው ክስ ምንም ያለው ነገር የለም።የፍትህ መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ በቀረቡ የግንኙነት ሰነዶች ውስጥ አብርሃም ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በጦርነት ላይ በነበሩ ታጣቂ ቡድኖች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ሲያበረታታ እንደነበር ያመለክታሉ።

አብርሃም ታህሳስ 9/2014 ዓ.ም. ለአንድ ተባባሪው ባስተላለፈው መልዕክት "እነዚህን ሰዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት አለብን። አለበለዚያ በኢትዮጵያ መቼም ሰላም አይኖርም" ሲል መጻፉ በፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ተካትቷል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

#Ethiopia #EthiopianAmerican #AbrahamTekluLemma
ማንችስተር ዩናይትድ ማይክል ካሪክን አሰናበተ። በ3 አመት ውስጥ 3ኛው ተባራሪ አሰልጣኝ መሆናቸው ነው። ቀጣዩ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዩናይትድ ደጋፊዮች ምን ታስባላችሁ?

#ManchesterUnited #MichaelCarrick #PremierLeague
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አርሲ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነቱን ወሰደ

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) በኦሮሚያ ክልል ሽርካ ዞን ከ40 በላይ ሰዎች በተገደሉበት የጥቅምት ወር ጥቃት ወቅት "እርምጃ" መውሰዱን አረጋገጠ።

ይሁንና፣ በታጣቂው ቡድኑ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት ሲቪሎች ሳይሆኑ በጸጥታ አካላት "የተመለመሉ" እና "መደበኛ ነዋሪ የሆኑ የትርፍ ጊዜ ተዋጊዎች" ናቸው ብሏል።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ይህንን ያለው በጥቅምት አጋማሽ በቀድሞው አርሲ ዞን ውስጥ በሚገኘው ሽርካ ወረዳ ቦርቢና ጮሌ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ ትናንት ሰኞ ኅዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው።

በወቅቱ ሕፃናትን ጨምሮ ከ 40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋኀዶ ቤተክርስቲያን ጥቃቱ በምዕመኖቿ ላይ የተፈጸመ መሆኑን መግለጿ አይዘነጋም።

#Ethiopia #Oromia #Arsi #OLA
ድምፃዊ ሚኪያስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ድምፃዊ ሚኪያስ የሙዚቃ ሥራ ለማቅረብ በሔደበት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

አርቲስቱ ዘቢዳር ቢራ ባዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ወልቂጤ ከተማ ከደረሰ በኋላ ድንገተኛ ሕመም እንዳጋጠመው ተገልጿል።

የሙያ አጋሮቹ አርቲስቱን ለሕክምና ወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታል ቢወስዱትም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

ድምፃዊው “ግርማ ሞገሴ”፣ “የኔ ደሃ”፣ “የፍቅር ስጦታ” እና “አሁን አሁን” በተሰኙ የሙዚቃ ሥራዎቹ በሰፊው ይታወቃል።

“ሰላም አላት” እና “10 ከ10” የተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችንም አበርክቷል።

#Ethiopia #EthiopianMusic #MikiyasCherinet
በጋምቤላ ክልል 190 ጠርሙስ የጂን አልኮል መጠጥ ተወገደ

በጋምቤላ ክልል በአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ 190 ጠርሙስ የጂን አልኮል መጠጥ መወገዱ ተገለጸ።
እርምጃው የተወሰደው የወረዳው ፖሊስ “የተከለከለ የአልኮል መጠጥ” ይዘው የሚዘዋወሩ ግለሰቦች ላይ ክትትል አድርጎ ባገኘው የመጠጥ ምርቶች ላይ ነው።

የአልኮል መጠጦችን በሚያዘዋዉሩ ግለሰቦች ላይ ወረዳው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ አሮፖ ኡበንግ ተናግረዋል።

“አልኮል ለጤና ጠንቅ ነው መሆኑን” የገለጸው የወረዳው ፖሊስ ኅብረተሰቡ አልኮል የሚያዘዋውሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

#Gambella #Ethiopia
“ሠራተኞች አጥተን እስረኞችን እያሠራን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሚገነቡ ፕሮጀክቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች “አጥተን እስረኞችን አውጥተን” እያሠራን ነው ብለዋል።

ዐቢይ ዛሬ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ የለም የሚል ትችት ቢነሳም በአሁኑ ወቅት በሚገነቡ ፕሮጀክቶች ላይ ግን ሠራተኛ እየተገኘ አይደለም ብለዋል።

አጋጥሟል ያሉትን የሠራተኛ እጥረት ለማካካስ ሲባልም በእስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ሰዎች በቀን እስከ ሰባት መቶ ብር እየከፈላቸው ለቀን ሥራ እየተቀጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

“አንዳንድ ቦታ ላይ እስረኞች ራሳቸው ደከመን አንሠራም ወደሚል ደረጃ ደርሰዋል” ሲሉም አክለዋል። ዐቢይ፣ “ሹፌር ችግር ነው፤ ቀለም ቀቢ ችግር ነው፤ ጽዳት ችግር ነው፤ ወለል አንጣፊ ችግር ነው።

ትናንሽ የሚባሉ ሥራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በቀላሉ ሰው አግኝቶ ማሠራት ያስቸግራል” በማለት ወቅሰዋል።

#Ethiopia #AbiyAhmed #PMAbiy
ኮሜዲያን ያሲኖ የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር በመሆን 20 ሚሊዮን ብር አፓርትመንት አሸነፈ

4ኛው የጂ-ፓወር የቲክቶክ የፈጠራ ሽልማት፣ ኮሜዲያን ያሲኖ የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር በመሆን የ20 ሚሊዮን ብር አፓርትመንት አሸነፈ።

ኮሜዲያን ያሲኖ ከዋናው ሽልማት በተጨማሪ፣ ‹ምርጥ የጥበብ ባለሙያዎች፣ ሠዓሊና ገጣሚ፣ እንዲሁም ምርጥ የዕድሜ ዘመን ሽልማት በተሰኙት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ተጨማሪ ሽልማት ተቀብሏል።

#Ethiopia #Tiktok #Yasino #TiktokAward
ማን ያሸንፋል?

#PremierLeague #Arsenal #ManCity
የአርሰናል ደጋፊዎች ውጤት እንዴት ነው?

#PremierLeague #Arsenal #ManCity