የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከትግራይ ክልል 161 ሰዎችን ማውጣቱን አስታወቀ
የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰባት ትግራይ ክልል 161 ሰዎችን ማውጣቱን አስታወቀ። ተቋሙ ከክልሉ “ወደ ሌላ ስፍራ ካዘዋወራቸው” ሰዎች ውስጥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ የሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ሰራተኞች፣ የአፍሪካ ኀብረት ታዛቢዎች እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አባላት ይገኙበታል።
ከትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ወደ አፋር ክልል ሰመራ የተደረገው ጉዞ የቀይ መስቀል አርማ ምልክት በተደረገባቸው አውቶቡሶች እና በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ሰራተኞች እጀባ መካሔዱንም ገልጿል።
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በግጭቱ ውስጥ ካሉ ወገኖች ጋር ውይይት ማድረጉን በመቀጠል ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ በሚሆንበት ጊዜ እና ሁሉም ወገኖች ለእንደዚህ ዓይነት ስራዎች በሚስማሙበት ጊዜ ሁሉ ኃላፊነቱን እንደሚወጣም ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
#Ethiopia

በአዲስ አበባ እና አከባቢው ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ
በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
ይህ የተገለጸው የፌደራል መንግሥቱ የሚቆጣጠራቸው “ተቋማት የድሮን ትቃት ሰለባ ሆነዋል” የሚል መረጃ እየተዘዋወረ ባለበት ወቅት ነው
አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፤ በአዲስ አበባና አካባቢው የሚንቀሳቀሱ ድሮኖችንና ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ አካላትን የሚቆጣጠር የተቀናጀ የጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡
የተሰጠውን ማሳሰቢያ በመጣስ የሚነሱ እንዲሁም በየትኛውም አካባቢና ከፍታ የሚበሩ ድሮኖችን በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የአብራሪዎቹን ትክክለኛ መገኛ ቦታ በመለየትና በቁጥጥር ስር በማዋል ሕጋዊ እርምጃ እንድሚወስድ አስታውቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ የመጡ ድሮኖች እና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን የብሔራዊ ደኅንነት ስጋቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን መታጠቁንና ብቁ የሰው ኃይል ማፍራቱን ገልጿል።
#Ethiopia #AddisAbaba #Drones

የመከላከያ ሰራዊት የመቀለ ከተማን መቆጣጠሩ ተሰማ
የህወሓት ኃይሎች መቀለን ለቅቀው መውጣታቸውን የፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) ዘግቧል። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላ የመከላከያ ኃይሎች ከተማዋን እንደተቆጣጠሩ ተሰምቷል።
የስምረት ፓርቲ አመራር እና የትምሕርት ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት “ኋላ ቀሩ ቡድን” ሲሉ የገለጹት የህወሓት አመራር ከከተማዋ መሸሹን ተናግረዋል።
አልጀዚራ በዛሬው ዕለት በሰራው ዘገባ የትግራይ ሰላም ኃይል እና የመከላከያ ሰራዊት የመቀሌ አሉላ አባነጋ ኤርፖርትን መቆጣጠራቸውን አስታውቋል።
ዳግም ውጊያ ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መግለጫ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል አንዳንድ አካባቢዎች በመከላከያ ኃይል ሊያዝ እንደሚችል ተናግረው ነበር። ሆኖም ይህ እርምጃ "ሆነ ተብሎ የተደረገ ስትራቴጂካዊ እርምጃ" ነው በማለት ነበር የገለጹት
#Ethiopia #Tigray #Mekelle

ሁለት ሚኒስትሮች አፈጉባዔ ሆነው ተሾሙ
የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ሲመረጡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ በመሆን ተሹመዋል።
አቶ አሕመድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ታገሰ ጫፎን ተክተው ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚሠሩ ይሆናል።
ሙፈሪያት ደግሞ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ይተካሉ። የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ የወ/ሮ ሙፈሪያት ምክትል ሆነዋል።

የኑሮ ውድነትና የብድር ጫና በዜጎች ላይ የደቀኑት ጭንቀት
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በሰፊው እየታየ ያለው የኑሮ ውድነትና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የብድር ጫና፤ በዜጎች ዕለታዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ጭንቀት (Financial Stress) እየፈጠረ እንደሚገኝ ሪፖርተር በዘገባው አመላክቷል።
የዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ መናር፤ የቤት ኪራይ ጭማሪና የተበደሩትን ገንዘብ በተወሰነለት ጊዜ መመለስ አለመቻል፤ በዜጎች የአዕምሮ ሰላም፣ በማኀበራዊ ሕይወትና በሥራ ምርታማነት ላይ አሉታዊ ጫናን የሚያሳርፍ መሆኑን በመጥቀስ በቤተሰብ አስተዳደርና በወደፊት ተስፋ ላይም ትልቅ ሥጋት የሚፈጥር መሆኑን የምጣኔ ሐብት እና የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን ሃሳብ አንጸባርቋል።
የሥነ ልቦና ባለሙያና የቤተሰብ አማካሪ ነቢያት ነቢሳ እንደገለጹት፤ የኑሮ ውድነትና የብድር ጫና ዜጎችን ለከፍተኛ ጭንቀት በመዳረግ በሕይወት የመቆየት ተስፋንም የሚያሳጣ ነው።
ለችግሩ መፍትሔ መኖሩን በመገንዘብ ዜጎች የተሻለ አምራች መሆን እንዲችሉ ማድረግ እንደሚቻልም ተናግረዋል።
የኑሮ ውድነትና የብድር ጫናን መቋቋም አለመቻል የሰዎችን ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅምን የሚያመናምን በአጠቃላይም ሕይወትን የሚያቃውስ በመሆኑ በቀላሉ ቸል መባል የለበትም ብለዋል።
የሥነ ልቦና ባለሙያው አክለውም የኑሮ ውድነት በየትኛውም ዓለም ላይ ባሉ ዜጎች ሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥርና ሰዎች የተሻለ አቅም አውጥተው እንዳይሠሩ ትልቅ ፈተና እንደሚሆንባቸው አስረድተዋል።
ብድርን መልሶ አለመክፈል ዜጎችን ለከፍተኛ ወለድና ንብረት በሐራጅ መሸጥን የሚያስከትሉ ፈተናዎችን ያስከትላል። ይኸም ለከፍተኛ የሥነልቦና ጭንቀት በመዳረግ ጤናን እንደሚያቃውስና ተስፋን እንደሚያሳጣ ገልጸዋል።

ኤርትራ የኢትዮጵያን ድንበር ጣሰች - የኢትዮጵያ መንግሥት
የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በተለያዩ የትግራይ ከተማዎች መግባታቸውን የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር እናታለም መለሰ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ለ ብሉምበርግ በሰጡት መረጃ የኤርትራ " ወታደሮች ሉዓላዊ ግዛታችንን ጥሰው ገብተዋል። በአፋጣኝ መውጣት አለባቸው" ብለዋል።
ዛሬ መስከረም 27/2019 ዓ.ም በርካታ የዓለም አቀፍ መእናኛ ብዙኃን ትኩረት በዚህ ጉዳይ ላይ ሆኗል።
የፈረንሳይ ዜና ወኪል AFP ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት ከተማ በኩል በስተደቡብ ወደ ማዕከላዊው የትግራይ ክፍል መሰማራታቸውን ገልጿል።
የጀርመን ድምጽ ራዲዮ “የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ድንበርን አቋርጦ ዘልቋል” ሲል ዘግቧል።
ወታደሮቹ የዓዲግራት ከተማንጥሰው በማለፍ ወደ ዕዳጋ ሓሙስ መግባታቸውን ነዋሪዎችን ጠቅሶ አስነብቧል።
ዘገባው አክሎ “ስማቸው እንዳይጠቀስየገለጹት የትግራይ የሰላም አዛዥ እንደሚሉት ዕዳጋ ሓሙስ ከገቡትየኤርትራ ወታደሮች ወደ አፅቢ ወንበርታ አቅጣጫ በ2 የጭነት መኪኖችተጭነው በሚጓዙበት ወቅት በድሮን ተመተዋል” ማለታቸውን ጠቅሷል።
ቢቢሲ በበኩሉ 40 የጭነት ተሽከርካሪ የኤርትራ ወታደሮችን ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን ከነዋሪዎች መሰማቱን ገልጿል።
#Ethiopia #Eritrea

“ሁሉም ሚኒስትሮች ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መስከረም 28 አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። በዚህ ካቢኔያቸው 22 ሚኒስትሮች የተካተቱ ሲሆን። አዳዲስ ሰዎች ወደ ሥልጣን መጥተዋል።
ሹመቱን በተመለከተ ዐቢይ ሲናገሩ፤ “ሁሉም ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ላለፈው አንድ ዓመት ከፍተኛ ሚስጢራዊ ክትትል ሲደረግባቸው ነበር” ብለዋል።
ክትትሉ “በኢንተለጀንስ የተደገፈ” ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያላቸው እንቅስቃሴ፣ ፣በልጆቻቸው፣በሚስቶቻቸው፣በአጎቶቻችው ከሚገናኟቸው ሃብታሞች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል ይደረግ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።
የዛሬው ሹም ሽር የተደረገው በዚህ ግምገማ መሆኑን አስታውቀዋል። በዚህ ግምገማ ጥፋት የተገኘባቸው ሚኒስትሮች የካቢኔ አባላት አለመደረጋቸውን አስረድተዋል።
በዛሬው ሹመት ከሚኒስትርነት የተነሱ ባለሥልጣናት
👉የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ
👉 የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ
👉 የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል
👉የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
👉 የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)
👉የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ
👉 የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል
👉 የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
👉 የሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
👉የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ
👉የማዕድን ሚኒስትር አቶ ሃብታሙ ተገኝ ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እሁድ ይጀምራል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ጥቅምት 1/ 2019 ዓ.ም. እንደሚጀምር አስታወቀ።
አየር መንገዱ በፌስቡክ ገጹ ዛሬ ዓርብ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ ከቀጣዩ እሁድ ጀምሮ የመቀለ በረራውን እንደሚጀምር ገልጿል።
የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች መስከረም 13/ 2019 ዓ.ም. በክልሉ የሚገኙትን ሦስት አውሮፕላን ማረፊያዎች መቆጣጠራቸውን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎችን ለጊዜው አቋርጦ ቆይቷል።
ከሁለት ሳምንት በላይ የተቋረጠው በረራ ከነገ በስቲያ እሁድ ይጀምሯል ተብሏል። ይሁን እንጂ በሌሎች የትግራይ ከተማዎች የተቋረጠው በረራ መቼ ይጀመራል የሚለውን አስመልክቶ አየር መንገዱ የገለጸው መረጃ የለም።
#Ethiopia #Tigray #Mekelle #EthiopianAirlines

ጌታቸው ረዳ ከ 19 ወራት ቆይታ በኋላ መቀሌ ገብተዋል
የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከ 19 ወራት በኋላ ወደ መቀሌ ገብተዋል። አቶ ጌታቸው ከ ዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር በመሆን ነው ወደ ከተማዋ መግባታቸው የተገለጸው።
ከህወሓት አመራሮች ጋር በነበራቸው አለመግባባት እና የሃሳብ ልዩነት ምክንያት ከመቀሌ ወጥተው ወደ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ጌታቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
በአሁን ወቅት ስምረት የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ በማቋቋም በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ነው።
#Ethiopia #Tigray #Mekelle #GetachewReda